ISLAMIC SCHOOL


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


✏️ #የነብዩን_ቃል_ፈፅሜ_እዛዉ_እሞታለሁ
            ✍አሚር ሰይድ


ለእምነቱ ጥልቅ ፍቅር የነበረው ጀግና ወህብ ቢን ከብሻህ (ረ.ዐ) የነብዩ ﷺ  ክቡር ሱሀባ መቃብር የሚገኘው በቻይና ነው፡፡ ነብዩﷺ ወህብን ወደ ቻይና ሄዶ ኢስላምን እንዲሰብክ ታላቅ የሆነ ተልዕኮን አሸክመው ላኩት፡፡ ይሁን እንጂ በዚያ ዘመን አንድ ሰው ከመዲና ተነስቶ ቻይና ለመድረስ አንድ ዓመት ያህል ይፈጅበት ነበር፡፡ ወህብ ኢብን ከብሻህ (ረ.ዐ) ቻይና ከደረሰ በኋላ ኢስላምን እያሥፋፋ ለረዥም ዘመን ቆይቶ የሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ናፍቆት በጣም ስለበረታበት ዓይናቸውን ለማየት ወደ መዲና ተመለሰ፡፡ አንድ ዓመት ከፈጀ የመከራ ጉዞ በኋላም መዲና ደረስ፡፡ ሆኖም ግን ምን ያደርጋል! ናፍቆት እንዳንገበገበውና ዓይናቸውን ለማየት እንደጓጓ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ሳያያቸው ቀረ። ሞተው ነበር የደረሰው😔

  አለቀሰ አዘነ ተከዘ ከዱንያ ያጣዉ ነገር ትልቅ ሆኖ ተሰማዉ....ምንም እንኳ ናፍቆቱና ሰቀቀኑ ቢበረታበትም እንደገና ወደ ቻይና መመለስ ነበረበትና ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ምክንያቱም ይህንን የተቀደሰ ዓላማ እንዲያራምድ ኃላፊነት የሰጡት የአላህ መልዕክተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንደመሆናቸው ትዕዛዛቸው መከበር ነበረበት፡፡ ወሀብ ኢብን ከብሻህ(ረ.ዐ) ቻይና ደርሶ እምነቱን እያስፋፋ እያለ እዚያው አረፈ፡፡ በዚህም ተግባሩ በቻይና የመጀመሪያው የአላህ
መልዕክተኛ ﷺ አምባሳደር የመሆንን ደረጃ ተጎናፀፈ።

ፈራሽ የሆነው አካሉ በቻይና ቢቀበርም የማትሞተው ነፍሱ ግን ከአላህ መልዕክተኛ ትዕዛዝ ስር ነበር...ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ቢሞቱም ግን ፍቅራቸዉን ሁባቸውን ይገለፀዉ ከአላህ የመጣዉን ኢስላምን ሀይማኖት ነብዩ ﷺ ባዘዙት መሰረት ኢስላምን እያስፋፋ እዛዉ ቻይና ተቀበረ

ፍቅር ማለት ይህ ነዉ ....የወጣት ነሺዳ የሴት ማጥመጃ ነሺዳ እያዳመጡ ነቢይን እወዳለሁ ማለት እራስን ማሞኘት ነዉ፡፡ ሱሀቦቹ ሀቢቡና ሙሀመድን ከራሳቸዉ በላይ አስበልጠዉ ይወዱ ነበር ﷺ💚💛❤️


እኛም እንደሱሀቦቹ ያለ ወኔ ልብ ባይኖረንም በምንችለዉ ዉዴታችንን እንግለፅ በተመቸን አጋጣሚ ሶሉ አለነቢይ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ💚💛❤️💞💞💚💛❤️


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


⚡️⚡️⚡️ #የሶፍያ_ረዐ_ሶብር⚡️⚡️⚡️
          ✍  አሚር ሰይድ

 
የኡሁድ ጦርነት እንዳበቃ ሶፊያ (ረ.ዐ) በዚያ ውጊያ ሰማእት የሆኑትንና አካላቸውም እጅግ ዘግናኝ በሆነ አኳኋን የተቆራረጠውን የወንድሟን ሀምዛ አስክሬን ለማግኘት ጓጉታለች፡፡ ይህን እያሰበችም ሰማዕታቱ የወደቁባቸውን ቦታዎች ለማሰስ ፊቷን መለሰች። በዚያው ሰዓት ልጇ ዙቤይር (ረ.ዐ) አገኛትና እንዲህ አላት፡-

......የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ወደ ኋላ እንድትመለሺ አዘዋል፡፡”አላት

"ለምን? እንደዚያ ከሆነ ወንድሜን ላየው አልችልም ማለት ነው? አለች። ቀጠል አድርጋም:- "እርግጥ ነው ሰውነቱን በምን ዓይነት አሰቃቂ ሁኔታ እንደሚቦጫጭቁት አውቃለሁ፡፡ ይህን የመሰለ መከራ የወደቀበትም ለአላህ ብሎ ነው፡፡ ይህን ከማሰብና ከመፅናናት ውጭ ሀዘናችንን ልንረሳበት የሚያስችለን ሌላ መንገድ የለም፡፡ አላህ ከሻ እኔም ሀዘኔን ዋጥ በማድረግ ምንዳየን ከእርሱወ እጠብቃለሁ" አለች፡፡

ዙበይር (ረ.ዐ) ወደ አላህ መልዕክተኛ ﷺ ከተመለሰ በኋላ እናቱ ያለችበትን ሁኔታ፣ የተናገረቻቸውንም ነገሮች ዘርዝሮ አስረዳቸው፡፡ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ አሉ፡-

“እንደዚያ ከሆነ ተዋት፣ ትሄድና የወንድሟን አስክሬን ትመልከት::

ሶፊያ (ረ.ዐ) ከዚያ በኋላ በጀግንነት ተሰውተው የወደቁትን ወንድሟን አካል እያየችና የሰማዕታት ሁሉ አለቃ በመሆናቸው እየተፅናናች ከልቧ ዱዓ አደረገችላቸው.....


ሶብሩም ጀግንነቱም ወኔም ያኔ የነበሩ ሱሀቦች ምን ያህል ተራራ የሆነ ኢማን ቢኖራቸዉ ነዉ??


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


📌የአሊ ረዐ ለነብዩ ﷺ የነበራቸዉ ፍቅር 📌
                ✍አሚር ሰይድ

   የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የተወለዱባትንና የሚወዷትን መካን ለቅቀው ለመሰደድ በተዘጋጁበት ሌሊት ዓሊን (ረ.ዐ) ጠርተው ወደ መዲና እንዲሰደዱ መለኮታዊ መመሪያ የወረደላቸው መሆኑን ገለፁላቸው፡፡ ከዚያም በመቀጠል እርሳቸው ወደ ኋላ እንዲቀሩና መካውያን ከእርሳቸው ዘንድ በአደራ ያስቀመጧቸውን ገንዘብና ንብረት ለየባለቤቶቻቸው ከመለሱላቸው በኋላ እንዲከተሏቸው አሳሰቧቸው፡፡ ምክንያቱም መካ ውስጥ ውድና ዋጋ የሚያወጣ ሀብት ኖሮት ከአላህ
መልዕክተኛ ﷺ ዘንድ ያላስቀመጠ ብዙ አይገኝም ነበርና፡፡ ጠላቶቻቸው እንደዚያ ግድያና ታላቅ አደጋ ሊያደርሱባቸው እየፈለጉ ውድ ንብረቶቻቸውን ከእርሳቸው ዘንድ ማስቀመጣቸው እውነተኛና ታማኝ በመሆናቸው እንጂ በሌላ አልነበረም ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ

የከሀድያኑን እቅድ አስመልክተው የአላህ
መልዕክተኛ ﷺዓሊን (ረ.ዐ) ሲያስጠነቅቋቸው እንዲህ አሉ፡- “ዓሊ ሆይ! ሌሊቱን በመኝታዬ ጋደም በል፡፡ በዚህ መጎናፀፊያዬም ራስህን ሽፍን፡፡ የማትወደው ነገር ይደርስብኛል ብለህ ምንም ፍርሀት እንዳይዝህ፡፡''

ታላቅ በሆነ የእምነት ወኔ የደነደኑት ዓሊ (ረ.ዐ) በአካላቸው ላይ ሊሸቀሸቁ በተዘጋጁ ብዙ ጦሮችና ጐራዴዎች ጥላ ታጅበው እነሆ በነብዩ ﷺ መኝታ ላይ ተኝተዋል፡፡
.....አስፈሪ በሆነ ቁጣና እልህ እየተደናፉ የመጡት አጋሪዎች የአላህን መልዕክተኛ ﷺ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገድለው ለመገላገል ወስነው ይጠባበቃሉ። ሌሊቱ ሊገባደድ አቅራቢያ በሩን በኃይል በርግደው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ የነብዩን ﷺ መጎናፀፊያ ለብሰው የተኙት ዓሊ (ረ.ዐ) መሆናቸውን ተመለከቱ፡፡ በንዴት እሳት ለብሰውም እንዲህ በማለት ጮሁ

"ዓሊ ሆይ! የአጎትህ ልጅ የት ነው ያለው?"

"እኔ አላውቅም፡፡ ይህን ጉዳይ በተመለከተም ምንም መረጃ የለኝም፡፡ እኔ እርሳቸውን ስከታተል አልቆየሁም፡፡ እንደሚመስለኝ ግን ከመካ ውጣልን ያላችኋቸው በመሆኑ መካን ሳይለቁ አይቀሩም፡፡”አሉ አሊ ረዐ

....ይህን እንደሰሙ አሊን እየተራገሙና እያመናጨቁ ወስደው በመስጂደል ሀረም ውስጥ አሰሯቸው፡ ሆኖም ብዙም ሳይቆዩ ፈታቷቸው፡፡

አሊ ረዐ ዉዴታቸዉ በነብዩ ﷺ መተኛ ላይ ሁነዉ በነብዩ ﷺ ላይ የመጣዉ ሞትን ለመቀበል ተዘጋጅተዉ ነበር ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ አሊ ረዐ ከሚወዷቸዉ ዉዴታ ይቼ የዱቄት ያህል ትንሿ ነች ከዚህ በላይ አሊ ረዐ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ይወዷቸዉ ነበር...,

በቀንም በማታም ሶሉ አላሀቢቡና ሰይዱና
ሙሀመድ ﷺ ﷺ💚💚💚💚


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


👉ስለዚህ የመተት አጋንንት ውስጣችን ከገባ እራሱን እየቀያየረ የተለያየ በሽታ ይሆናል፡፡
በሚበላና በሚጠጣ ወደ ሆዳችን የገባው፣በቁሳቁስ ወደ እኛ የሰረጸው መተት
❌ሆዳችንን ሊያሳምመን
❌ለአእምሮ ሕመም ሊዳርገን
❌እጅ እግራችንን ሽባ ሊያደርገን
❌ለወገብ ለልብ ሕመም
❌ለጨጓራ ሕመም
❌ለደም ግፊት ለስኳር ሕመም
❌ለአስም ሊዳርገን ይችላል፡፡
መተትን አደገኛ የሚያደርገው ይህ ነው፡፡

⏩#ዓይነ ጥላ ሕይወታችንን የማጎሳቆል ሥራ
የሚሠራው በስውር ነው፡፡ ድግምት ግን በግልፅ ነው፡፡
⏩#ዓይነ ጥላ በውስጣችን አሸምቆ ተደብቆ ከእኛው ጠባይ ጋር ተስማምቶ አድብቶ ነው የሚኖረው፡፡ ድግምት ግን ጥቃቱ የሚታይና ግልጥ ነው፡፡
⏩#የዓይነ ጥላ አጋንንት የሚጎዳን በጊዜ ሂደት ነው፡፡ ድግምት ግን በድንገት ነው፡፡


#መፍትሄዉ ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ጠበቅ ማድረግ...ከሀራም ነገሮች መራቅ
ሩቃ ማድረግ..ሰደቃ መሰደቅ  ናቸዉ፡፡

ስለሲህር ድግምት ዙሪያ የተፓሰተ ተከታታይ  ፁሁፍ ስላለ ወደሆላ ፈልገዉ አንብባችሁ ራሳችሁን ፈትሹ




         join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


🔰 #የድግሞትና_የዓይነ_ጥላ_አንድነትና_ልዩነት🔰🔰

➪ድግምት(መተት) ከዓይነ ጥላ ጋር አንድ የሚያደርገው ሁለቱም የሰውን ልጅ ውድ ሕይወት ማበላሸት፣ ውጥኑን፣ እቅዱን ማኮላሸት ላይ ስለሚያተኩሩ ነው፡፡

➪ድግምትም ዓይነ ጥላም በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ጣልቃ በመግባት ሕይወትን ከማበላሸት እስከ ማጥፋት ይደርሳሉ፡፡
ሁለቱም አለን፣እጄ ገባ፣እርግጠኛ ነኝ በምንላቸው ነገሮቻችን ላይ የሚያደርሱብን ስውር ጥቃት አንድ ነው፡፡

➪ድግምት እና ዓይነ ጥላ በዕድላችን፣ በእውቀታችን ፣በትምህርታችን፣በእጮኛችን እና በትዳር ሕይወታችን እንዳንጠቀም ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ ድግሱ ድረስ
የመደንቀር፣የማበላሸት ሥራን ይሠራሉ፡፡

👉 ሁለቱም አሉኝ በምንላቸው ነገሮች እንዳንጠቀም የመጠርቀም ሥራን ይሠራሉ፡፡
👉ሁለቱም ተስፋ በጣልንባቸው ከመቶ ፐርሰንት በላይ እርግጠኛ በሆንባቸው ነገሮቻችን ላይ አጋንንታዊ የበላይ በመሆን በግልጽና በስውር የማይታይ ምስማር በመሆን ጠስቀው ይይዙብናል፡፡

⏩ድግምትና ዓይነ ጥላ ሲላቸው በራሳቸው ሲላቸው በሰው እያደሩ፣የእኛን ነገር ገና ከጅምሩ እየገረገሩ ያበላሹብናል፡፡

➪#ዓይነ ጥላና ድግምት የሰው ልጅ ዳግም የማያገኝውን፣ ተመልሶ የማይኖረውን ውድ ሕይወቱን በማባከን ፣የያዘውን በማስጣል ብሎም በመንጠቅ አንድ ናቸው፡፡

➪#ድግምትና የዓይነ ጥላ አጋንንት የሚለያቸው ወይም አንድ የማያደርጋቸው እንይ

▶#ድግሞት በደጋሚዎች ወይም በጠንቋዮች በመጎተት ሰውን የሚቆራኝ አጋንንት ነው፡፡

▶#ድግምት በሰው እድል የሚቀና፣በሰው መልካም ሕይወት በብግነት የሚኖር ሰው በሚበላ በሚጠጣ፣በቁስ ወዘተ በማስደገም የሚያቆራኘው አጋንንት ነው፡፡

⏩ #ዓይነ ጥላ በደጋሚዎች የሚጎተት አጋንንት አይደለም፡፡ እራሱን ችሎ፣ክፋቱን ተንኮሉን ጠቅልሎ ወደ ሰው ሕይወት የሚገባ አጋንንት ነው እንጂ በደጋሚዎች የሚቆራኝ አይደለም

#ድግምት ግን ድንገት ወደ እኛ ሕይወት በሰው ክፋት የሚመጣ አጋንንት ነው፡፡

⏩#ዓይነ ጥላ የማንም አጋንንታዊ ድግምት የማያዘው በራሱ የክፋት መንገድ የሚራመድ ክፉ መንፈስ ነው

👉ዓይነ ጥላ ግን ዕድላችን ላይ በመቅናት ሰተት ብሎ የሚገባ ነው፡፡

ልብ ይበሉ‼
✅#ድግምት በሰው ቅናት የሚገባ አጋንንት ሲሆን
✅#ዓይነ ጥላ እራሱ መንፈሱ በእኛ በመቅናት የሚገባ ነው፡፡
✅#ዓይነ ጥላ በውስጣችን ከገባ በኃላ እራሱን እየቀያየረ በሕመም እየተመሰለ ይቀመጣል፡፡
✅#ድግሞትም ውስጣችን ከገባ ደዌ ሆኖ ይቀመጣል፡፡

                   👉#ልዩነታቸው
☑ዓይነ ጥላ አንዴ ውስጣችን ከገባ እንደ ግል ይዞታው ተደላድሎ ይቀመጣል፡፡
☑#ድግምት ግን ውስጣችን ከገባ በኃላ እድሳት የሚባል አጋንንታዊ ሥርዓት አለው፡፡
እድሳት ማለት አንድ ሰው ላይ በመልካም ነገሩ መተት ሲመተትበት፣የሚያስመትተው ሰው በደጋሚው ወይም በመታቹ በኩል ለአጋንንቱ ግብር ያቀርብለታል፡፡ ለምሳሌ
ገንዘብ፣በግ፣ደም ወዘተ ያቀርባል፡፡ ይህንን ያስደገመ ቀን ያቀረበውን ግብር በየ ዓመቱ ሲያቀርብ አጋንንታዊ ውል ይገባል፡፡
ይህንን የሚያደርገው የሰውን እድል ስለወሰደ በዛም ስለሚጠቀምበት ከሰው የወሰደው ዕድል፣ እውቀት፣ የትዳር፣የሥራ እድል ወዘተ በአጋንንት ተጠብቆ እንዲቆይለት እንዲጠቀምበት የሚያደርገው ነው፡፡

⏩ብዙ ጊዜ ድግምት የተመተተባቸው ሰዎች ከአጋንንቱ በቀላሉ መላቀቅ የሚያቅታቸው በአጋንንቱና በሚደገምበት ሰው መሃል ያለው አስደጋሚው ሰው በየዓመቱ ወይም በየወራቶቹ በተደገመበት ሰው ስም ለአጋንንቱ ስለሚገበር የተመተተበት ሰው ሲታደስበት አጋንንቱ እንደ አዲስ ወደ ውስጡ ይገባል፣ ጤና ያጣል፣ የጀመራቸው ነገሮች በአስገራሚና ለማመን በማያስችል ሁኔታ ይበላሻል፡፡

♦♦አንድ ሰው በተለይ ድግምት የተመተተበት ሰው መተቱ ሲታደስበት የሚያሳየው ጠባይ አለ፡፡
☞ በድንገት ጭው የሚል ስሜት መሰማት
☞ ያለ ምክንያት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ መግባት
☞ መረበሽ
☞ መጨናነቅ
☞ ፍርሃት መሰማት
☞ የሆነ የማናውቀው ነገር ውስጣችን ሲገባ መሰማት
☞ እራስን ስቶ መውደቅ/ይህ መንፈሱ ውስጣችን ሲገባ ነው/
☞ በጠራራ ፀሐይ ብርድ ብርድ ማለት
☞ ውልብ ብሎ ሰውነታችንን የሚከብድ ስሜት መሰማት
☞ በድንገት የልብ ምት መጨመርና ዝብርቅረቅ የሚል ስሜት መሰማት
☞ ከፍተኛ ድንገተኛ የሰውነት ድካምና የመክበድ ስሜት መሰማት
☞ ሰላም ማጣት
☞ ድንገተኛ የባሕርይ ለውጥ ማሳየት
☞ ያለ ምክንያት ብስጭት ብስጭት ማለት
☞ ማዞር መቅለሽለሽ፣ጭንቅላት
☞ ልብ ላይ ጭንቅ የሚል ስሜት መሰማት
☞ ጩኽ ጩኽ የሚል ስሜት ከውስጥ መግፋት
☞እጮኛሞች እና ባለ ትዳሮች ከሆኑ ድንገት የማስጠላት እና የመጥላት ስሜት ውስጥ መግባት
☞ መሳደብ
☞ ከፍቅር አጋር ጋር እንለያይ ማለት
☞ የትዳር አጋርንና ልጆችን መጥላት
☞ ያለ ጥፋት መምታት ወዘተ ሊከሰቱብን ይችላል፡፡

ስለዚህ የተደገመበት ሰው መተቱ ሲታደስበት እንኳን ለሰው ለራሱም የማያውቃቸው የሚይጨበጡ የባሕርይ ለውጦችን ያሳያል፡፡
ለምሳሌ ፦

👉 በእጮኛውና በትዳሩ ላይ በመቅናት የተመተተበት ሰው ከሆነ የታደሰበት ቀን ከእጮኛውና ከትዳር አጋሩ እና ከልጆቹ ጋር ያለ ምክንያት ከፍተኛ ጠብ ውስጥ ይገባል፡፡

👉 በእውቀቱ የተደገመበት ሰው ከሆነ የታደሰበት ቀን በዛን ሰሞን ደንዝዞ ፈዞ ይከርማል፡፡

👉 በገንዘቡ የተደገመበት ሰው ገንዘቡ ከኪሱ ለመውጣት የሚያጨበጭቡ ይመስል ያለ ምክንያት ይወጣል፡፡ ግን በምን እንዳወጣው ፣ገንዘቡን የት እንዳደረሰው፣ምን ቁም ነገር ላይ እንዳዋለው አይውቅም፡፡ ሌላም ሌላ ….

በአጠቃላይ እድሳት ማለት ከአጋንንቱ ጋር በሰው ሕይወት እና እድል ላይ ውል ማራዘም ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በሰው ሕይወት ላይ በአጋንንት ስውር ምስጢር መቆመር ማለት ነው፡፡

✅#ድግምት ከዓይነ ጥላ አንዱ የሚለይበት፦
#መተት በምንበላው ምግብ፣ በምንጠጣው መጠጥ፣በምንለብሰው የውስጥ እና ውጭ ልብስ/በላብ በወዝ/ በምንይዘው ቁስ ወዘተ ስለሚደገም በቀላሉ ሕይወታችን ሊያመሰቃቅል ፣ጤናችን ሊቃወስ ይችላል፡፡

✅ #ድግምት ከዓይነ ጥላ የሚለይበት ምክንያት፦
ድግምት አደገኛና ገዳይ መሆኑ ነው፡፡ ምንክያቱም መተት በመርዝ መልክ ሊሠራ ስለሚችል የተመተተበትን ምግብ የበላ ወይም መጠጥ የጠጣ ሰው በድንገት ሊሞት ይችላል፡፡ #በተለይ ወደ ሆድ በሚገቡ ነገሮች አጋንንቱ በሰውነታችን ሕዋሶች በመሰራጨት፣ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስብን ይችላል፡፡

⏩ #ድግሞት እና የዓይነ ጥላ መንፈስ በልዩነታቸው መተት የሚከብድበት አንዱ መተት አጋንንት እራሱን መቀየር መቻሉ ነው፡፡ መተት በሆድ ውስጥ አውሬ ሆኖ ይቀመጣል፡፡
#ለምሳሌ አንድ ሰው በሻይ፣በሚሪንዳ መተት ተመትቶ ቢሰጠው ያንንም ቢጠጣ ወደ ሆዱ ከገባበት ቀን ጀምሮ ጤና ማጣት፣ ህመም መሰማት ይጀምረዋል

ይህ በሚጠጣ ነገር ወደ ሆዱ የገባው ድግምት ሰውዬው ሳያውቀው ከቆየ፣ሥጋዊ በሽታም ከመሰለው በጊዜ ሂደት ሆዱ ውስጥ የገባው መተት እራሱን በመቀየር ሥጋውን በመብላት ደሙን በመጠጣት ለከፍተኛ ጤና መታወክና ጉዳት ይዳርገዋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ሊገድለውም ይችላል፡፡

👉 ዛሬ ሆዳችንን እያመመን፣የሆድ ህመማችን ትልቅ ጭንቀት ፈጥሮብን በየ ሆስፒታሉ ሄደን መፍትሔ የምናጣው መተት ቢሆንስ?
ምክንያቱም በመተት ወደ ሆድ ገብቶ ደዌ ሆኖ የተቀመጠው ነገር በሕክምና ምርመራ አይታወቅም👇👇👇


#ልጄ_ሞተ_ማለት_ሐያዕ_አጣሁ_ማለት_አይደለም
              ✍አሚር ሰይድ

ኡሙ ኸልላድ (ረ.ዐ) ከመዲና ሶሃቢያት አንዷ ነበረች። ልጇን ኸልላድን ሙስሊሞች ከበኒ ቀይኑቃዕ አይሁዳውያን ጋር ባደረጉት ውጊያ እንዲሳተፍ ልካው ነበር፡፡ ከጦርነቱ የተመለሱ የተወሰኑ ተዋጊዎች ኸልላድ ሰማእት (ሸሂድ) ሆኖ መውደቁን ሊነግሯት ወደ ቤቷ ገሰገሱ፡፡ እርሷም የልጇን እጣ ፈንታ ከአላህ
መልዕክተኛ ﷺ አፍ ለመስማት የምትለብሰውን መከናነቢያ(ሒጃብ) ስትፈልግ ያስተዋላት አንድ ስው እንዲህ አላት፡-

“ልጅሽ ኸልላድ ሞቷል እየተባልሽ ስለምለብሽዉ ሒጃብ ይህን ያክል ትጨነቂያለሽን?”አላት
ኡሙ ኸልላድ (ረ.ዐ) ግን ለዚህ እምነቱ የሳሳበት ሰው ማለፊያና ሁልጊዜም የማይረሳ መልሷን እንዲህ በማለት ሰጠችው፡-
ኸልላድን አጥቻለሁ ማለት ያለኝን ሐያዕ (ዓይን አፋርነት) አጥቻለሁ ማለት አይደለም፡፡"አለችም

ይህ የኡሙ ኸልላድ (ረ.ዐ) አነጋገር ለነብዩ ﷺ
ሲነገራቸው እንዲህ አሉ፡- "የኸልላድ ሰማእትነት ሁለት እጥፍ ምንዳ አለው፡፡"

"ለምን የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ?" ተባሉ፡፡

“ምክንያቱም እርሱ የተገደለው የመጽሐፉ ሰዎች በሆኑት አይሁዳውያን በመሆኑ ነው፡፡” (ኢብን ሰዓድ፣ ኢብኑ አል-አሲር)

⚠️ዛሬ ላይ ሀያአቸዉን ያጡ ወንድ ጋር እንደፈለገች የምትገላፈጥ ...እቤት ቤተሰቧን የማትታዘዝ..ለዉጭ አልጋ ለቤት ቀጋ የሆኑ እንስቶች እና የለባሽ እርቃን ሙስሊሞች በየመንገዱ በዝተዋል ነገ ኡሙ ኸላድ ጎን ሁነን አሏህ ሲጠይቀን መልስ ይኖረን ይሆን??


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


🔥#የጀሀነም_ቅጣትን_ሲያስታዉስ_የሞተዉ_ወጣት
             ✍  አሚር ሰይድ

መንሱር ኢብን አማር እንዲህ በማለት ተናግሯል፦ “አንድ ሌሊት የነጋ መስሎኝ ከቤቴ ወጥቼ ስሄድ ንጋቱ አለመቀረቡን ተገነዘብኩ፡፡ ከዚያም በአንድ ሰው ቤት አጠገብ ሳልፍ አንድ ወጣት ምርር ብሎ እያለቀሰ ጌታውን እንዲህ በማለት ሲማፀን ሰማሁት፡-

    ጌታዬ ሆይ! እኔ ብዙ ሀጢያቶችን ፈፅሜያለሁ፡፡ በዚህም ድርጊቴ ራሴን መቀመቅ አውርጃለሁ። ዓላማዬ ያንተን ትዕዛዝ መጣስ አልነበረም። ሆኖም ግን ነፍሴ አሸነፈችኝ፡፡ ምንም እንኳን እኔ እራሴን ብበድልና መጥፎ ድርጊቶችን ብፈፅምም አንተ ግን ለዚህ ድርጊቱ የወሰድክብኝ ብቀላ የለም፡፡ በዚህ ቻይነትህና ይቅር ባይነትህም ተዘናግቼ ተወሰድኩ። ሀጢያቶቼንም የሠራኋቸው ባለማወቅ ነው፡፡ አሁን ግን መሳሳቴን ተገነዘብኩ። የምትቀጣኝ ከሆነ ምን ይውጠኛል? ወዮልኝ ለራሴ! ጌታዬ ሆይ! ባሮችህን ሁሉ በሲራጥ ድልድይ ላይ እንዲያልፉ በምታደርግበት ቀን የተወሰኑት ወድቀው ጀሀነም ሲገቡ የቀሩት ደግሞ ጀነት ይገባሉ፡፡ እኔ የአንተ ባሪያህ ከየትኛው ወገን ይሆን የምሆነው?' ይህን ካለ በኋላ ስለ ጀሀነም የሚናገር የቁርአን አንቀፅ ሲያነብ ሰማሁት፡፡ ከዚያም ረዥም ትንፋሽ ሲያወጣ ከሰማሁት በኋላ ፀጥታ ሰፈነ። ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ጓጓሁ፡፡ ለራሴም:- 'ይህ ወጣት ያለበትን ቤት በሚገባ እስካላየሁት ድረስ የተፈጠረውን ነገር ሲነጋ መስማቴ አይቀርም:: አሁን ወደ ቤቴ ልግባ' በማለት ወደዚያው አመራሁ፡፡


ነግቶ ወደዚያ ስፍራ ስሄድ ከቤቱ በር ላይ የሰው አስከሬን ተመለከትኩ፡፡ ምን እንደተፈጠረ ስጠይቅም እናቱ እንዲህ አለችኝ፡-

የሞተው የእኔ ልጅ ነው፡፡ ከነብዩ ﷺ ጋር የሚያያዝ የዘር ሀረግ አለው፡፡ ጨለማው ያዝ ካደረገ ጀምሮ እስኪነጋ ድረስ ሲሰግድና ሲያለቅስ ያነጋል፡፡ ያለውን ነገር ደግሞ ቀኑን ሙሉ ለድሆች ሲመፀውት ይውላል፡፡ ስለ ጀሀነም የሚናገር የቁርዓን አንቀፅ ከሰማ ፈፅሞ መቋቋም ስለማይችል ያለቅሳል፡፡ በዚህ ዓይነት ሲያለቅስ ሌሊት ላይ ወድቆ ሞተ፡፡አለችኝ
.... እኔም እንዲህ አልኳ ት፡-
እንቺ የተከበርሽ ሴት ሆይ! ልጅሽ በቀጥታ ያመራው ወደ ጀነት ነው ምክንያቱም አላህን ፈርቶ ይህን ያክል የሚያነባ ሰው ጀሀነብ ሊገባ አይችልም: በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነፍሱን ስቶ የሞተ ሰው እንዴት ጀሀነም ይገባል? አላህን አመስግኚው።'አልኳት

አሏህ ጀሀነምን ፈርተዉ ከሚያለቅሱ ..ጀነትን ከሚለምኑ አቢድ ዛሂድ ያረገን ዘንድ አላህን እንማፀነዋለን....


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


❤️ #ሱሀቦች_ለነብዩ_ﷺ_የነበራቸዉ_ፍቅር
            ✍ አሚር ሰይድ


በሀቢቡና ሙሀመድ  ﷺ ጊዜ በተፏፏመዉ በኡሁድ ዉጊያ ጊዜ ነብዩ ﷺ ተገድለዋል የሚል የዉሸት ዜና መዲናን እየናጣት ነበር ..የመዲና ሰማይ በዚህ አሳዛኝ ወሬ በሀዘን አጥልሏል..መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ኡሁድ አቅጣጫ እየተመመ ነዉ

    ከአንሶሮች መካከል የሆነችዉ ሱመይራ(ረ.ዐ) ሁለት ልጆቿ አባቷ ባለቤቷና ወንድሟ ሰማዕት መሆናቸዉን ተረዳች ..ሱመይራ እነዚህ ሁሉ ወገኖቿ ቢሞቱባትም በዚህ ሁሉ የሀዘን ዉርጅብኝ አልተናወጠችም ..እልቁንስ እሷን ያስጨነቃት በእዉነት የታወቀዉ የጓጓችለት አንድ ዜና አለ ይህም የነብዩ ﷺ በሒወት መኖር ነዉ
..በእርሳቸዉ ላይ የደረሰ አንዳች ክፉ ነገር አለ??በማለት ጠየቀች
...የነብዩ ባልደረባዎችም ለአላህ ምስጋና ይገባዉ እርሳቸዉ በሒወት ይገኛሉ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ አሏት
ሱመይራ እንዲህ አለች ፡-እሳቸዉን እስከማይ ድረስ እረፍት አላገኝም የአላህ መልዕክተኛን ﷺአሳዩኝ አለች
....እሳቸዉን እንዳሳዩዋትም በቀጥታ ወደ እርሳቸዉ በመሄድ የካባቸዉን ጫፍ ከያዘቼ ቡሀላ እንዲህ አለች
"""""እናቴና አባቴ መስዋት ይሁንለልዎ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!እርስዎ በሂወት እስካሉ ድረስ የቤተሰቦቼም ሞት ቀላል ነዉ ...አለቻቸዉ

.ያ በነብዩ ዙሪያ የነበሩ የተባረከ ትዉልድ ለእርሳቸዉ ይህን የመሰለ ድካ የሌለዉ ፍቅር ይለግሳቸዉ ነበር ...ሱመይራ አባቷ ልጇ ባለቤቷ ወንድሟ ሙተዉ እሷ ያሳሰባት ነብዩ ﷺ💚 በህይወት እንዲተርፉላት ነበር....

⚠️...እኛስ ነብዩን መዉደዳችንን የምንገልፀዉ በነሺዳ የተቀናበረ የራሳችንን ፎቶ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመልቀቅ ነዉ እንዴ??
እስልምና ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል ...ነብዩን መዉደድ ነሺዳ በማዳመጥ የሚመስስላቸዉ ብዙ ሚስኪን ሙስሊሞች ሞልተዋልና ሙተን አላህ ፊት ስንቀርብ ከነሱመይራ ረዐ ጎን ሁነን ስንጠየቅ የሰራነዉን ኸይር ስራ ፈትሸነዋልን???

ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


       #የምላስ_ወለምታ

ሶስት ሰዎች የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ውሳኔው ተግባራዊ ሊሆን ህዝብ በተሰበሰበበት ሜዳ ከፍ ካለው ቦታ ላይ ተደረደሩ። አሊም፣ የህግ ጠበቃና የፊዚክስ ሊቅ ናቸው።
     ገመዱ ተዘጋጅቶ አሊሙን ወደ ፊት አስጠጉት። አንገቱን ከገመዱ በታቸ አጠለቁት። ለመናገር ለምትፈልገው የመጨረሻ ቃል ካለ ተናገር ተባለ።


አላህ አላህ....የሚያድነኝ እርሱ ብቻ ነው" ሲል ተናገረ። ገመዱ አንገቱ ላይ እንደጠበቀ አልሸመቀቅ አለ። ሕዝቡ ተገረመ። የአላህን ስም ጠርቷልና ገመዱን ፍቱለት ተብሎ ተለቀቀ። ነፍሱንም በአላህ ስም ታደገ። ‎

የሕግ ባለሙያው ተራ ደረሰ። አንገቱ ላይ ገመድ ጠለቀ። ለእርሱም የምትናገረው የመጨረሻ ቃል ካለ ተናገር ተባለ። እንዲህም አለ አንደ ኡስታዙ ከአላህ ጋር አልተዋወቅም ግን ፍትሕ እንደሚያድነኝ በሚገባ አውቃለሁ። ፍትሕ ፍትሕ ሲል ጮኸ። ገመዱ በአንገቱ ውስጥ እንደጠለቀ አልሸመቀቅ አለ። ጠበቃውን ፍቱት ስሰ ፍትሕ ተሟግቷልና መሰቀያ ገመዱ እንኳ ነፍሱን ለመንጠቅ አልደፈረችም ተባለ። ጠበቃውም በፍትሕ ስም ነፍሱን አዳነ።

የፊዚክስ ሊቁ ተራ ደረሰ። እርሱም ተጠየቀ መናገር የምትፈልገው የመጨረሻ ቃል አለን? ተባለ።

"እኔ አላህን አንደ ኡስታዙ አላውቀውም። እንደ ጠበቃውም ስለ ፍትሕ አልለፈልፍም። ግን መስቀያ ገመዱ እስካሁን አንገታቸው ላይ ጠልቆ ያልተሸመቀቀው አናቱ ላይ ያለዉ ቋጠሮ ስለጠበቀ ነው" አለ። ገመዱን ሲመለከቱት በትክክል ቋጠሮው በመጥበቁ ምክንያት ነው ያልተሸመቀቀው። ቋጠሮውን አስተካክለው የፊዚክስ ሊቁ አንገት ላይ ገመዱን ሸምቅቀው ገደሉት።

   አንዳንዴ እውነታውን እንኳ እያወቅከ ምላስህን መያዝ ይኖርብሀል። ሞኝ መሆን ብልጠት የሚሆንባቸው በርካታ ቦታዎች አሉና አፍህን በመዳፍህ ላይ አድርገህ ዝም በል።


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


#በስነምግባር_ባልሽን_አክሚ “
✍ አሚር ሰይድ

85 ዓመቱ ሸይኽ ዐብደላህ በሳተላይት ቻናል ላይ የፈትዋ ፕሮግራም እየሰጡ አንዲት ትውልደ አልጄሪያዊት ሴት ደወለችና እንዲህ አለች፦

"ሙስሊም ነኝ ለጌታዬ ታዛዥ። ትውልዴም በሀገረ አልጄሪያ ነው። የአላህን ትዕዛዝ የባሌን ሐቅ እየተወጣሁ ለብዙ በደሎቹ ትዕግስትን ተላብሼ እኖራለሁ። ባሌ ዘወትር መጠጥ ሲጠጣ አምሽቶ እየተንገዳገደ ወደቤት ይገባል። ትላንት በዛ ሁኔታ ላይ ሆኖ ሲመጣ ቁርአን እየቀራሁ ነበር። እየተሳደበ ከእጄ ላይ ነጠቀኝና ሽንት ቤት ወረወረው። በንዴት ተቃጠልኩ ድንበር ማለፉ ከኔ አልፎ በክቡር የአላህ ቃል ቁርአን ላይም ደረሰ። እኔም ከዚህ በላይ መታገስ ከበደኝ ፍች መጠየቅ እችላለሁን?"

በማለት ጥያቄዋን ሰነዘረች።

“ስንት ልጆች አሉሽ” ሲሉ ጠየቋት

“አምስት ወንዶች ልጆች አሉኝ ገና ልጆች ናቸው" አለች።

ለትንሽ ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ። ጥንቃቄን የተሞሉ ቃላቶች ከአፋቸው እየሰነዘሩ ንግግራቸውን ቀጠሉ“ፍቺ አትጠይቂ ስሞታም ሳታቀርቢ ታግሰሽ ኑሪ የሚመጣብሽን ችግር ተቋቁመሽ በስነምግባርሽ ባልሽን አክሚ

በመሀል ጣልቃ ገብታ ንግግራቸውን አቋረጠች “ግን እንዴት ከዚህ በላይ መታገስ ይቻለኛል??" እያለች ተንሰቅስቃ አነባች።

"ልጆችሽ የእሱን ባህሪ ከሚላበሱ በጀሀነም እሳት ከሚማገዱ ታግሰሽ እሱን መመለስ አይሻልምን?!

ደሞስ በወንጀል ላይ ላለው ባለቤትሽ ችግሩን የሚረዳ ካንቺ በላይ ማን አለው?! ካንቺ በቀር ይህን ተግባሩን ታግሶና ወንጀሉን ደብቆ ከሰጠመበት ማዕበል ሊያወጣው የሚጥር ማንም የለም። ብትፈቸው እየሰከሩ ቁርአንን  ሽንት ቤት የሚጥሉ ልጆችን ያፈራልና እባክሽ ታገሺ እዘኚለት ፍቺ ጠይቀሽ ማምለጥ መፍትሄ አይደለም። ነገ ለልጆችሽ ድልድይ መሆኑን አውቀሽ ለሊት ተነስተሽ አምርረሽ ዱዓ አድርጊለት አሏት


ቀናቶች ወራቶችን ወልደው ድፍን አንድ ዓመት ተቆጠሩ። ሸይኹ በሕንድ የሳተላይት ጣቢያ ላይ ተጥደው ፈትዋ እየሰጡ ስልኩ አቃጨለ።

"አሰላሙ ዓለይኩም ያ ሸይኽ አልኮል እየጠጣ ቁርአንን ስለሚቀዳድደው ባሌ ከአንድ ዓመት በፊት የደወልኩህ አልጀሪያዊቷ ሴት ነኝ"

“ወላሂ አስታወስኩሽ ልጄ እንዴት ነሽ?? የባልሽስ ሁኔታ ምን ላይ ነው? "ብለዉ ጠየቋት

"በአላህ ይሁንብኝ መስጂድ ቀድሞ ገብቶ አዛን የሚል፣ ሶለተ ተሀጁድ ቆሞ የሚያነጋ፣ ቁርአንንም በአግባቡ የሚቀራ ሰው ሆናል። ግዴታ የተደረጉበትን ሶላቶች ከነሱናቸው የሚሰግድ የአላህ ባርያ ሆናል። እኔ እንድፀና እርስዎን ሰበብ አርጎ አላህ እሱን ወደ ቀጥተኛ መንገድ መራው” አለችና የደስታ እንባ ከዓይኗ እየዘረገፈች ተንሰቀሰቀች። ለጌታዋ የቀረበች አማኝ ሴት በመሆኗ ንፅህናዋንና የልቧን ቅንነት አይቶ በዱዓዋ መልስ ሰጣት።

#አንድ ሰው ከወንጀል አዘቅጥ ይወጣ ዘንድ ትዕግስትን ከዕዝነት ጋር ተላብሳችሁ በጥበብ አስተምሩ!

ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


📚📚 #የአንድ_ሺህ_ዲናሩ_ገጠመኝ
           ✍ አሚር ሰይድ

መነሻቸውን ከበስራ አድርገው መድረሻው ወዳልታወቀ ስፍራ ተቅጣጭተዋል። ሐዲስን የሚያውቅ ሰው አለ ተብለው ከምንጩ ሊቀስሙ ፈልገዋል። ጉዞው አድካሚ ነው። መንገዱም ሲበዛ የረዘመ። በረሀውን አቋርጠው ሲጨርሱ ገደል ገደሉን ሲያልፉ ጋራ ይጠብቃቸዋል። ዕድሜ ያቸው የገፋ አንድ አዛውንት አብረው በፍጥነት ይራመዳሉ። በዕውቀት የመጠቁ ዓሊም ናቸው። ኢማሙል ቡኻሪ ይሰኛሉ። ከእልህ አስጨራሽ ጉዞ በኋላ ከተማውን ለቀው በመውጣት በጀልባ ተሳፍረው ባህሩን ያቋርጡት ይዘዋል። አንድ ሺህ ዲናር በከረጢታቸው ቋጥረው ከቦርሳቸው አኑረዋል። ከጎናቸው ለተቀመጠው ሰው ስለያዙት ገንዘብ ነግረውታል።

   ገንዘብ የመያዛቸውን ወሬ የሰማው ሰው ቀይሉላ ሰዓት ወገቡን ከመጋደሚያው አሳርፎ ከእንቅልፉ እንደነቃ ስቅስቅ ብሎ አያለቀሰ እሪታውንና ኡኡታውን ያሰማ ጀመር። ልብሱን እየቀዳደደ ፊቱን እየቧጨረ ጭንቅላቱን እየመታ መሬት ላይ ይንከባለል ጀመር። ሰዎች ሁኔታውን ሲያዩ ግራ ተጋብተው ምን እንደሆነ ጠየቁት።

አንድ ሺህ ዲናር ከነቦርሳዬ ጠፋ አላቸው። ለካስ የኢማሙን ብር ከጀሎ ኖሯል።

.....በመርከቡ ውስጥ ያሉት ተሳፋሪዎች አንድ በአንድ እየተፈተሹ ገንዘቡን ያፈላልጉት ጀመር። ኢማም አል-ቡኻሪ በከረጢቱ ያስቀመጡትን ገንዘባቸውን አውጥተው ሰው ሳያያቸው ወደ ባህሩ ወረወሩት። መርከቡ ላይ የተሳፈሩት ፈልገው አፈላልገው አንድ ሺህ ዲርሀሙን ሲያጡ ተወሰደብኝ ብሎ የሚጮኸውን ሰው ወቅሰውና ሰድበው ከአጠገባቸው አገለሉት።

ከመርከቡ እንደወረዱ ሽማግሌው ሰው ወደ አማም አል-ቡኻሪ ተጠጋና ከበስራ ይዘውት የመጡትን አንድ ሺህ ዲናር የት አንዳደረጉት ጠየቃቸው።

“ወደ ባህር ወረወርኩት” አሉት።

"ይህን ታላቅ ገንዘብ በከንቱ ሲጠፋ ማየት አንዴት አስቻለህ?" አላቸው።

ኢማሙም እንዲህ አሉ "የአላህ መልአክተኛ ﷺ
ሐዲስ በመሰብሰብ ዕድሜዬን ሙሉ እንደፈጀሁ ታውቃለህ። ዓለምም ታማኙ የሐዲስ ሰው እያለ ይጠራኛል። ታዲያ በገዛ ሀቄም ቢሆን በስርቆት ተወንጅዬ አማናዬን አጥቼ የደከምኩበት የረሱል ﷺ ሀዲስ ተቀባይነት እንዳይኖረው ላደርግ አይገባም። በሕይወቴ ያገኘሁትን ውድ ዕንቁ ታማኝነትንና ፍትሀዊነትን ለጥቂት ዲርሃም ብዬ አንዴት አጠፋዋለሁ? "
ብለዉ መለሱለት

ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


⚡️⚡️...... #ቁርአንን_ስንኖርበት .....⚡️⚡️
                  ✍አሚር ሰይድ

      በሀገረ አሜሪካ በሚገኝ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ጫጫታ ነግሷል። ሁለት እናቶች በተመሳሳይ ሰዓት በሰላም ተገላግለው “ሴቷ የአንቺ ናት እኔ የወለድኩት ወንድ ነው" እየተባባሉ ሲጨቃጨቁ ሆስፒታሉ በጩኸታቸው ተናውጧል። ሐኪሞቹ ልጆቹ ተምታቶባቸው ግራ ተጋብተዋል። ማንኛዋ ሴት የትኛዋስ ወንድ እንደወለደች ማወቅ ተስኗቸው መፍትሄ ሊያበጁ ከመሀል ገብተዋል።

በዲ ኤን ኤ ምርመራ ለማረጋገጥ ውጤት መጠባበቅ ጀመሩ። አሁንም ግራ አጋቢ ነገር ተፈጠረ። ተቀራራቢ ውጤት በመታየቱ ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ሆኗል በማለት ለሆስፒታሉ ሀላፊዎች አሳወቁ። ኃላፊዎቹም ረጅም ሰዓት ከተወያዩ በኋላ ይህንን ችግር መፍታት የሚችሉት ሙስሊም አሊሞች ናቸው በሚል ከመግባባት ላይ ደረሱ።

   ወደ አንድ ሙስሊም ለቃውንትም አቀኑ። የተፈጠረውን ሁሉ በዝርዝር አስረዱ። ምናልባት በሀይማኖታችሁ መፍትሄ ካለው ብለን እዚህ መጣን አሉ።

እሱም ክስተቱን አዳምጦ እንዳበቃ “መፍትሄው በጣም ቀላል ነው” አለ።
.....ዶክተሮቹ እርስ በእርስ ተያዩ ፡ ንግግሩን ቀጠለ “አላህ በልጆቻችሁ ያዛችሆል፡፡ ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ብጤ አለው" የሚለውን የቁርአን አንቀፅ ከነትርጉሙ አነበበላቸው

"ከሁለቱም እናቶች የወተት ጠብታዎችን ውሰዱና መርምሩ። በጣም የበለፀገና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘችው የወተት ጡት ወንድ ልጅን የወለደችው እርሷ ናት” አለ።

ንግግሩን ሰምተው እንዳበቁ አመስግነው ወደ ሐኪም ቤት አመሩ። ከሁለቱም እንስቶች የወተት ናሙና ወስደው ላብራቶሪ አስገብተው መረመሩ። በመካከላቸው ያለውን ልዩነትም ተመለከቱ። ወንድና ሴት ልጅ የወለደው ማን እንደሆነ በዚህ መንገድ አወቁ።

“ (ይኽም) ከአላህ የተደነገገ ነው፤ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና” [ሱረቱ ኒሳእ]


#ቁርአንን_ስንኖርበት_ብሎም_ስንዳኝበት_እንዲህ_ነው። ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ተገባ!

ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


🎖 #ምስጢሮችህን_ራስህ_ጋር_ማቆየት_ቻል🎖
                 ✍አሚር ሰይድ

      ከጀርመን እስር ቤቶች በአንዱ ጠባቂዎቹ የጭካኔና የበደል ዱላቸውን ዘወትር በታሳሪዎች ላይ ያሳርፋሉ። “ሽሚት” የተባለ ረጅም የእስራት ጊዜ የተፈረደበት አንድ ሰው በፍርግርጉ ውስጥ አለ። ይህ እስረኛ በጥበቃዎች አክብሮት የተሞላበት መልካም አያያዝ ሲደረግለት ቀሪዎቹ የእስርቤቱ እስረኞች እነሱን ሊሰልል የመጣ ሰው አድርገው ይገምቱታል።
....በአንድ ወቅት በዚህ ግምታቸው ምላሽ ይሆን ዘንድ ከፖሊሶች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው እየማለ ነገራቸው። ማንም አላመነውም “የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ለምን ከእኛ የተለየ እንክብካቤና አያያዝ እንደሚያደርጉልህ ማወቅ አንፈጋለን" አሉት።

ሸሚትም “እስኪ ንገሩኝ ለዘመዶቻችሁ የምትፅፉትን ሳምንታዊ ደብዳቤ ምን ብላችሁ ነው የምትጀምሩት??"

“ስለ እነዚህ የተረገሙ ጠባቂዎች የእስርና የግፍ ጭካኔያቸው በደብዳቤዎቻችን ላይ አንነግራቸዋለን" አሉት።

“እኔ ግን በየሳምንቱ ለባለቤቴ ደብዳቤ እፅፋለሁ። በመጨረሻው መስመር ላይ የእስር ቤቱንና የጠባቂዎቹን መልካም አያያዝ እጠቅሳለሁ። አንዳንዴም ስማቸውን እየዘረዘርኩ አወድሳቸዋለሁ"

"አያያዛቸው ጭካኔ የተሞላበትና ከባድ መሆኑን እያወቅክ እንዴት ታወድሳቸዋለህ?" ብለው

ጠየቁት።

“ምክንያቱም ደብዳቤዎቻችን በጥበቃዎች ሳይነበቡ ከእስር ቤት አይወጡምና በፁሁፋችን ውስጥ የሰፈረውን እያንዳንዷን ነገር ጠንቅቀው ያውቃሉ የደብዳቤያችሁን የአፃፃፍ ዘይቤ ለውጡ" በማለት መከራቸው።

በሚቀጥለው ሳምንት ሁሉም እስረኞች የአፃፃፍ ስልታቸውን ቀይረው ወደ ቤተሰቦቻቸው ደብዳቤን ላኩ። ከቀናት በኋላ የእስር ቤቱ ጠባቂዎች አያያዛቸው በከፋ መልኩ ተቀየረ። ሁሉንም እስረኞች ማሰቃየት ጀመሩ። አሁን ሽሚትም አልቀረለትም አብሯቸው ይደበደብ ጀመር።


ሁኔታው ግራ የገባው ሸሚት ከጥቂት ቀናት በኋላ እስረኞቹን “በደብዳቤያችሁ ላይ የፃፋችሁት ምንድን ነው? " ሲል ጠየቃቸው።

እንዲህ አሉት "የተረገሙትን ጠባቂዎች አታለን ጥሩ አያያዝ የምናገኝበት ዘዴ እንዳስተማርከን ፅፈናል" አሉት።

ሸሚዝ ጉንጮቹን እየደበደበና ፀጉሩን እንደ እብድ እየነጨ አቀርቅሮ ተቀመጠ።



⚠️⚠️ #እናም_ወዳጄ

    ሌሎችን መርዳት መልካም ተግባር ቢሆንም ከማን ጋር ማውራት እንዳለብህ ልታውቅ ይገባሀል። ሁሉም አድማጭ ሚስጢር ጠባቂ አይደለም። ልብህን ለሁሉም ሰው ክፍት አታድርግ። የመኖርህ ጌጥ የሆኑትን ምስጢሮችህን ራስህ ጋር ማቆየት ካልቻልክ እመነኝ ሌሎች ሰዎች ምስጢርህን ለመጠበቅ የሚችል ልብ አይኖራቸውም።

#ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


🔰#ለሌሎች_ያጋራሉ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


>>>>>>>🎖#እንደዚህ_ሰው_አትሁን🎖


⚡️⚡️ #ሰላዩ_የመስጂደል_አቅሷው_ኢማም⚡️⚡️
              ✍   አሚር ሰይድ

ፋዲል የሁዛ ይባላል። ቅዱስ ቁርአን ከነተፍሲሩ ተምሯል። በቃሉም ሸምድዷል፡፡ የአል-አቅሳ መስጂድ ኢማም ነው፡፡

አብዛኛው ጊዜውን የሚያሳልፈው ቁርአንን በማንበብ፣ በዒባዳና፣ ስለ ኢስላም በማስተማር ነው፡፡ የከተማው ሰዎች ሁሉ ይወዱታል። ከየአቅጣጫውም በዙሪያው ተሰብስበው ያዳምጡታል። በፍልስጤም ውስጥ ለሚገኙት ሙጃሂዶች ጠንካራ ድጋፍ አድርጓል። አላህ ድልን እንዲያጎናፅፋቸውም ዘወትር አላህን ይለምናል። በመልካም ስብዕናና በኢማን ራሱን ገንብቷል።

   የፅዮናዊያን ጦርነት ግንቦት 1948 ሲጀመር በየቀኑ እኩለ ለሊት ላይ ወደ ፅዮናዊያን ካምፕ አየሄደ የሙስሊሞችን ወታደራዊ መረጃ ያቀብላል።

ለብዙ ሰዓታት ከዓይን የሚሰወረው ፋዲል በሙስሊሞች ላይ ጥርጣሬን ፈጥሯል። እኩለ ለሊት ከግብፅ የሽምቅ ተዋጊ ካምፖች ወደ ፅዮናዊው የሽምቅ ተዋጊ ካምፖች ሲገባ በተደጋጋሚ ተስተዉሏል፡፡

በፅዮናውያን እና በሙስሊሞች መካከል ድርድር ተካሂዶ ሰላም ከሰፈነ ቀናት አልፈዋል፤ የፅዮናውያን መኮንን አንገቱ ውስጥ ዘልቆ የገባውን ከባድ ጉዳት ማከም አቅቷቸው አስፈላጊውን የህክምና መሳርያዎችንና ሐኪም እንዲልኩላቸውም ሙስሊሞችን ጠየቁ።

የመስሊሞች ሐኪም ፅዮናዊውን መኮንን ለማከም የሚያስፈልገውን መድኃኒት ተሸክሞ ወደ ካምፑ ዘለቀ። ሐኪሙ ሌላ ስራም ተሰጥቶታል በጠላት ካምፕ ውስጥ መረጃን መሰብሰብ እንዳለበት ተነግሮታል።

አለመታደል ሆኖ ፋዳል በለሊት የሙስሊሞችን መረጃ ለፅዮናዊያን በማድረስ ሥራው ላይ ሳለ ነበር ከሙስለሞቹ ሀኪም ጋር ዓይን ለዓይን የተገጣጠመው። ሐኪሙም አይቶት እንዳላየ ሆነ።

ሐኪሙ ወደ ካምፕ ሲመለስ ፋዲል በፅዮናውያን ካምፕ ውስጥ እንደነበረ ለሙስሊሞች መሪ ተናገረ። ፋዲል ብልህ ሰላይ ስለነበር እንደተባነነበት ስላወቀ የሙስሊሞችን ካንፕ ለቆ ተሰወረ።

3 ሙስሊሞች ለዚህ ኦፕሬሽን ተላኩ፡፡ ለሊትን ተገን  አድርገው ገደሉት። አስከሬኑን ተሸክመው ፅዮናዊያን ሰፈር ዘልቀው በመግባት የፋዲልን አስክሬን አስቀመጡ።


ስለ እስልምና ያስተምር የነበረ፣ ቁርአንን በአግባቡና ማራኪ በሆነ አንደበቱ የሚፈስር፣ ሙስሊሞችን በአል-አቅሳ መስጂድ ኢማም ሆኖ የሚያሰግድ ሰላይ፡

   ዛሬም ከመካከላችን ስንት የካፊሮች ቅጥረኛ በየሀገሩ አለ ቁርአንን የሚያነብ ሙስሊሞችንም የሚያሰግድ... የሙስሊሞች መሪና አሊም የሚመስል መልኩን የቀየረ ፋዲል ስንት አለ።

ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ

ሼር ማድረግ ቅንነት ነዉ ለሌሎች ሼር በማድረግ ያካፍሉ


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


✨#ሰሐቦቹ_ለምን_ቀደሙ_እኛስ_ለምን_ዘገየን?!
          ✍ አሚር ሰይድ

   በወርሀ ረጀብ በ13ኛው ዓመተ ሒጅራ ስፍራው በሻም ምድር በዛሬዋ ሶሪያ የርሙክ ወንዝ ስር ሁለት በመጠንና በአደረጃጀት ፍፁም የተለያዩ ሀይሎች ለወሳኝ ፍልሚያ ተፋጠዋል። አርባ ሺህ ሙስሊም ወታደሮች ሁለት መቶ ሺህ የሮም ሠራዊትን ሊገጥሙ በተጠንቀቅ ቁመዋል።

   ኻለድ አብኑል ወለድ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ሱረቱል አንፋል አንዲቀራ አዘዘ። አቡ ሁረይራ ተነስቶ ዳዕዋ አደረገ አቡ ሡፍያንም ቀጠለ። የሱሀቦች የውጊያ ወኔ ተቀሰቀሰ። በቁጥር አናሳዎቹ ግዙፉን የሮም ጦር አንበርክከው በሙስሊሞች ድል አድራጊነት ጦርነቱ ተደመደመ።

   የሮሞች መሪ ሂረቅል ወደ አንጣኪያ አቅጣጫ አመለጠ። ያ ሁሉ ሰራዊት በአናሳ ጦር እንደዚህ መበታተኑ ንድድ አድርጎታል። አንጣኪያ ከተማ ላይ ሆኖ ከውጊያ ግንባር ሸሽተው የመጡትን ወታደሮች አነጋገረ :-

“አነዚያ የሚጋደሏችሁ እንደናንተው ሰዎች አይደሉምን? " ሲል ጠየቃቸው።

" አዎ ናቸው" አሉት።

"በሁሉም ግንባር ከእነሱ በእጥፍ ትበዛላችሁ ታዲያ ለምን ትሸነፋላችሁ?" አለ በብስጭት።

ከጦር አለቆቹ መሐል የተሰየመ አዛውንት ተነሳና : -

“እነሱ” አለ ንግገሩን ሲጀምር።
.... “እነሱ ለሊቱን ለጌታቸው ቆመውና ሱጁድ ተደፍተው ያነጋሉ። ቀኑን በሐሩር ይፆማሉ። ቃላቸውን ሁሌም ይሞላሉ። በመልካም የሚያዙ ከመጥፎም የሚከለከሉ ትውልዶች ናቸው። እርስ በርስ የሚተዛዘኑ የሚተባበሩ የሚረዳዱ ናቸዉ....

አኛ ግን በተቃራኒው አስካሪ መጠጥ አየጠጣን ሰዎችን የምንበድል.... ቃላችንን የምናፈርስ ነን። ሙስሊሞች እንደኛ በእኩይ ተግባር ካልተሳተፉና ከጌታቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ካልሻከረ እርስ በርሳቸው ያላቸው ውዴታና መተናነስ ተንዶ ወደ ጥላቻ ካልተለወጠ በፍፁም እነሱን ማሸነፍ አንችልም" አለ።

ሂረቅል የጦር አለቃዉን ንግግር ሰምቶ ሲያበቃ “አንተ እውነቱን ነገርከኝ" ሲል ተደመጠ።


‼️ ይሄዉ ዛሬ ዘመን ላይ የጦር አለቃዉ እንዳለዉ ሀራም ላይ ሙስሊሙ እየተሳተፈ..ሰዎችን እየበደልን የሰዉ ሀቅ
መፍራት ትተን በእኩይ ነገር በማንኛዉም ሶሻል ሚዲያ ላይ ሀያዕ አጥተን እየታየን ....ከጌታችን ጋር ያለን ግንኙነት ከአንገት በላይ ስለሆነ ...በትንሹም በትልቁም እርስ በራሳችን ቁርአንና ሀዲስ እያለ ለስሜታችን የሚመቸን እንዲሆን ክርክር የኔ ትክክል ነዉ የአንተ ጥመት ነዉ እያልን ጊዜያችንን እንጨርሳለን የሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች እንደፈለጉ ያሸከረክሩን ይዘዋል...በሂጃብ ጉዳይ የተናቅነዉ አንድ ተራ ሰዉ ተነስቶ ሂጃብን ከልክሎ ተማሪዎችን የሚያሰቃየዉ የኛን ልብ አይቶ እንደሆነ ሁላችንም ልናቅ ይገባል፡፡


-----------------------------
ታላቁ ዓለም አብኑ ቁተይባ ዑዩኑል አክባር በተባለ ከታባቸው ላይ ቀጣዩን ታሪክ አስፍረዋል።

✅✅ ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይርና ዐብዱልመሊክ ኢብኑ መርዋን እርስ በርስ መዋጋት በጀመሩበት ሰዓት የሮማዋያን መኳንንቶችና የጦር አበጋዞች ተሰባስበው ንጉሳቸው ዘንድ አመሩ። “ንጉሥ ሆይ! አሁን ሙስሊሞች እርስ በርስ መጣላት ጀምረዋል። ይህ ዕድል ሳያመልጠን እንፋለማቸው" አሉት።
.... ንጉሡ ግን "በፍፁም እንዳታደርጉት!" በማለት ግርምትን የሚያጭር መልስ ሰጣቸው።

መኳንንቶቹ በመልሱ በመደነቅ ምክኒያቱን ጠየቁ። ንጉሡም ሁለት ውሻዎችን አስመጣና እንዳያናክሳቸው አስደረገ። ውሻዎቹ እርስ በርስ እየተናከሱ ጠባቸው ሲፋፋም ንጉሡ ቀበሮ አስመጣና ወደ ውሾቹ ላከ። በዚህ ጊዜ ውሻዎቹ ጠባቸውን ትተው በመተባበር ቀበሮውን አሳደው ገደሉት። በዚህ ጊዜ ንጉሱ

“የኛና የሙስሊሞች ምሳሌ ይህ ነው! ካጠቃናቸው አንድ ሆነው ይጨርሱናል  ከተውናቸው ግን እርስ በርስ ይጨራረሳሉ" አላቸው።...ይኸው ነው ምሳሴያችን ዛሬ ዘመን ላይ በሚዲያዉ በየመስጊዱ እርስ በራሳችን በቃላት እንነካከሳለን....እነ ፉላን ግን ሂጃብ የለበሱ ሙስሊም እህቶቻንን ትምህርት አትማሩም አትፈተኑም ምን ታመጣላችሁ.... ዩኒቨርስቲ አትገቡም ተብለዉም እዉጭ ያሳድሯቸዋል የዚህ የኛ በቃላት የመነካከስ ዉጤት ነዉ፡፡

ወንድሜ! እህቴ ! ታሪኩ እርስ በርስ መናከሳችን ትርፉ
ለጠላት መሆኑን ነው የሚነግረን!

ግን መቼ ይሆን ከተኛንበት  የምንነቃዉ !!!???🤔


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


     🎖🎖 #ለእርሷ_እንባ_ሲል🎖🎖
            ✍    አሚር ሰይድ

   ውዷ እህቴ! በታሪክ ውስጥ ለሚመከርበት ሰው ታላቅ ተግሳፅ አለና ከዚህ ታሪክ ትማሪ ዘንድ ታሪኩን እነሆ ጀባ አልንሽ።

    በአልጀርስ አውሮፕላን ማረፊያ አንዲት ሴት ተንበርክካ ታለቅሳለች። የአላህን ቤት ለመጎብኘት ረዥም ዓመት ጓጉታ ስትናፍቅና ልቧ ሲዋልል ከርማ እሷን ትቶ የሐጅ ተጓዦችን ጭኖ አውሮፕላኑ ጥሏት በመሄዱ አምርራ ታነባ ይዛለች።

    በሰማይና በምድር መሐል የሚበረው ፕሌን በድንገት እንግዳ ጩኸትን ያሰማ ጀመር። ከምድር ሀያ አራት ጫማ ከፍታ ላይ ሆኖ መርገፍገፉን ተያያዘው። በዚህ ጊዜ ነበር ፓይለቱ መሪውን በመጠምዘዝ አቅጣጫውን ወደ አልጄሪያ አውሮፕላን ማረፊያ ያደረገው።   
    ተሳፋሪዎቹን አውርዶ የጥገና ሠራተኞቹ ሥራቸውን ጀመሩ። የጥገና መሐንዲሶቹ ብልሽቱን ለማወቅ ጣሩ። ግን አውሮፕላኑ ሙሉ በሙሉ ሰላም ነበር። ምንም ችግር የለበትም ሲሉ ተናገሩ።

   ስለሷ ዕንባ ሲል አላህ ከ200 በላይ ተሳፋሪዎችን የጫነውን አውሮፕላን ከመሐል መንገድ መለሰላት።


     በፍርሐት እየተንቀጠቀጠች አምርራ ያለቀሰችው እንስት ወደ ጌታዋ የዘረጋቻቸው መዳፎች ምላሽን በፍጥነት ተችረው ዳግም እንደ አዲስ ፕሌኑ ሴትዮዋን ጭኖ ጉዞውን ወደ መካ ጀመረ።

👌ሁሉም በሮች ቢዘጉብህ ደጃፎች ሁሉ ቢጠረቀሙብህ አጅህን ዘርግተህ ወደ አላህ ዱዓ ከማድረግ አትዘንጋ።‼️‼️


ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


#በሕይወቱ_አንድ_ጊዜ_የሱብሒን_ሶላት   
    #ባሰመስገዱ_ተንሰቅስቆ_ሲያነባ
          ✍አሚር ሰይድ


አነስ አብኑ ማሊክ አነባ

   አለቀሰ ያውም ስቅስቅ ብሎ የእንባ ዘለላዎች በጉንጮቹ ላይ እየፈሰሱ ለረዥም ሰዓት ቆየ። ሙስሊሞች ቱስቱር ከተማን ድል አድርገው የከፈቱበት ዘመቻ በተወሳ ቁጥር አንገቱን ሰበር አድርጎ ያነባል።

ስለቱስቱር ምን አሳወቃችሁ እሷ የፋርስ ከተማ አልነበረችምን? ሙስሊሞች ለአንድ ዓመት ያህል የከበቧት። ከእልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ከተማይቱ በሙስሊሞች እጅ ወደቀች። ግልፅ የሆነ ድልን ተጎናፅፈው ከፈቷት፡፡

ታዲያ አነስ ኢብኑ ማለክ የቱስቱርን ዘመቻ ሲያስታውስ ለምን ያለቅሳል??

    ገና ጎህ ሳይቀድ ነበር የኢስላም ሰራዊት ወደ ቱስቱር ምሽግ የዘለቀው። ሰላሳ ሺህ ሙጃሂዶች ከአንድ መቶ ሀምሳ ሺህ የመስቀል ሠራዊቶች ጋር ገጠሙ። መራር ውጊያ ተካሄደ። ከባድ ጦርነት ተከናወነ። ሙስሊሞች ደማቸውን እያንጠባጠቡ ሰውነታቸውን በጨርቅ እያሰሩ እልህ አስጨራሽ ውጊያ አደረጉ። እጅግ በጣም አስቸጋሪ እጀግ ከበዛ እልቂት በኋላ ለአላህ ምስጋና ይግባውና ሙስሊሞች ድል ተጎናፅፈው በጠላታቸው ላይ ድልን ተቀናጁ ይህ ድል ፀሀይ ከወጣች ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሙጃሂዶቹ በእጃቸው የያዙትን ሠይፍ ወደሰገባው ሲመልሱ የሰብሒ ሶላት እንዳመለጣቸው አወቁ። ጎህ ከመቅደዱ በፊት ሰዓቱን ጠብቀው የሱብሐን ሰላት መስገድ አልተቻላቸውም ነበር። እጅግ አዘኑ ምክንያታዊ ሆነው ዑዝር ኖሯቸው እንኳ አቅልለው አላለፏትም።

   አነስ ኢብኑ ማለክ በሕይወቱ አንድ ጊዜ የሱብሒን ሰላት ባለመስገዱ ተንሰቅስቆ አነባ። አቀርቅሮ አለቀሰ። የሙስሊሙ ጦር በእስልምና ሻኛ በአላህ መንገድ በጂሃድ ተጠምዶ አላህ ዑዝር ሰጥተቸው አነሱ ግን አነቡ።

አነስ እንዲህ ይላል፦ “ቱስቱር ምንድነው?! የሰብሂ ሶላት አምልጣኛለች ዓለም ሁሉ በዚህ ሶላት ልዋጭ ትሁንህ ብባል እንኳ አልቀበልም ብሏል፡፡


አሁንስ ለምን አላህ ድል አንደተጎናፀፋቸው ገባህ? እነዚህ ሰዎች ሕይወታቸውን ሙሉ ለአላህ ሰዉ። እኛስ ስለኢማናችን እንቅልፋችንን መስዋዕት ማድረግ ችለናልን?

ካልቻልን...የምን ድል የምን ከፍታን እንመኛለን?

በልባችንና በሕይወታችን ውስጥ የሶላት ዋጋ ተገፎ ኃያልነታችንንና  ክብራችንን አጥተናል። ዱንያ ጠባ አጣብቃናለች። ጠላቶቻችን ወረው ከዚህም ከዚያም ይቦጫጭቁናል።

   የእውነት ኢስላምን እንኑር “ምእመናን አንደሆናችሁ የበላይ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ" ተብሎ በአላህ ቃል ተገብቶልን ሳለ ለምን የበታች የሆንን ይመስላችኋል?? ራሳችሁ መልሱት
#ጣትህን_ወደሌላው_ከመቀሰርህ_በፊት_ወደራስህ_አቅጣጫት



ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላለዉ መፅሀፍ

ሚዲያ ላይ አፍጠን ሱብሂን የምናሳልፍ ሰንቶቻችን ነን?? አነስ አንድ ቀን አልፎት ሲያለቅስ የኖረዉ እኛ
ብዙ ቀን አልፎናል ቢለቀስ እምባ ይበቃን ይሆን❓❓


ሙተን ጀነት እንገባለን ብለን እየታገልን ሱብሂ ሶላት እያለፈን የጀነት መግቢያችንን እርዚቃችንን እያጣበብን መሆኑን አንዘንጋ⚠️⚠️


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
⚠️የሲህር የድግምት ምንነት
☞ሲህር የተደረገበት ሰዉ ምልክት
☞ሲህር የተደረገበት ሰዉ ህክምና
☞የጠንቋዮች ምልክቶች

የተለያዩ ድግምት ጋር የተያያዙ ብዥታዎችን የሚመልስ ምርጥ ሙሀደራ ነዉ እስከ መጨረሻዉ በማዳመጥ ራሳችንን እንፈትሽ

#ኡስታዝ_ሱለይማን አብደሏህ የቀረበ ትምህርት

🕞 የትምህርቱ ቆይታ 1ሰአት ከ19 ደቂቃ ያህል እርዝመት አለዉ፡፡
ያዳምጡት ጠቃሚ ትምህርት ነዉ፡፡



join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


በኳታር አደራዳሪነት ሲደረግ የነበረው የሀማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት 464 የግፍ ቀናቶች ቡሀላ ተፈፀመ።

በዚህም መሰረት በሀማስ እጅ ያሉ እስራኤላውያን የሚለቀቁ ሲሆን በእስራኤል እጅ ያሉ ፍልስጤማዊያንም ይለቀቃሉ። የተኩስ ድምፅ የማይሰማ ሲሆን የእስራኤል ጦር ከጋዛ ለቆ ይወጣል።
በመደመሪያዎቹ ቀናትም አስቸኳይ እርዳታን የያዙ 600 መኪኖች ወደ ጋዛ ይገባሉ።
በጋዛ ላይ የሚደረጉ የጦር በረራዎች የሚቆሙ ሲሆን ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ይደረጋል።

ከዚያም ጋዛን እንደገና የመገንባት ስራ በአለምአቀፍ ዘመቻ ይጀመራል።

የሞቱትን ከሸሂዶች ጋር አላህ ይቀስቅሳቸዉ፡፡ ግን እስኪ እስራኤልና አሜሪካን የሚታመኑ አይደሉምና ፈረጃዉ ከአሏህ ያድርግላቸዉ፡፡ የሁዶችና አሜሪካን በቃላቸዉ ይገኙ ይሆን??

እስኪ እናያለን ብቻ የጋዛን ሰላም ነዉ የምንፈልገዉ፡፡



ፍልስጤማዊያንን በጅምላ ሐገር አስጥሎ ወደ ሲና በረሐ እንዲሰደዱ የተደረገው ሙከራ ሁሉ አልተሳካም።
የጄኔራሎቹ እቅድና ውጥን ከሽፏል።
ከኔትዛሪም አንወጣም።
ፊላደልፊያን አንለቅም ሲሉ የፎከሩበት ሁሉ ውድቅ ሆኖ ሰራዊታቸውን ማጋዝ ጀምረዋል።
ሃማስን እናጠፋለን እስረኞቻችንን እናስለቅቃለን ብለው የደነፉበት ሁሉ ገደል ገብቷል።

ጋዛ ከነ ውድመቷ ራሷን ቀና አድርጋ ኃያላንን ሁሉ ሰባብራለች ምስጋና ለአላህ ክብርም ለቀሳሞች ይሁን
➖➖➖➖➖➖
 

ዛሬ ለሰማነዉ ኸበር አልሃምዱሊላህ አላ ኩሊ ሀል!!


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

20 last posts shown.