ተፈታኞች ከዛሬ ጀምሮ ይገባሉ።
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከዛሬ ሐምሌ 16 ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ይገባሉ።
ተፈታኝ ተማሪዎች ከሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች ወደ ተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲያችን የምትጓጓዙት በተዘጋጁላችሁ ተሽከርካሪዎች ነው።
ተፈታኞች ዩኒፎርማችሁን መልበስ ፤ ብርድልብስና አንሶላ ይዛችሁ መገኝት ይጠበቅባቸኋል።
ወደ መፈተኛ ተቋማት ቆሎ፣ ጭኮ፣ በሶ የመሳሰሉ ደረቅ ምግቦችን ይዞ መግባት የሚፈቀድ ሲሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ ሞባይል፣ አይፓድ፣ ላፕቶፕ የመሳሰሉ እንዲሁም ማንኛውም ጌጣጌጥ ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።
ተማሪዎች ከቤታችሁ ስትወጡ፦
- መታወቂያ ፣
- አድሚሽን ካርድ
- የት/ቤት ዩኒፎርም መያዛቸሁን እንዳትረሱ ፤ ወላጆችም ይህንን እንድታስታውሷቸው ጥሪ እናቀርባለን።