#LWEQESH-Ethiopia


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Travel


ልወቅሽ የተለያዩ በሀገራችን ውስጥ ያሉ ነገርግን ያልታዩ እና ያልተዳሰሱ ታሪኮችን፣ ተፈጥሮአዊ መልክኣ ምድረዎችን እናማህበረሰቦችን አጠር በለ መልኩ የሚዳስስ ሲሆን በተጨማሪም ጉዞዎችን እንዲሁም ልዩ ዝግጅቶችን ያዘጋጃል ።"የለንን በማሳወቅ ሀገራዊ እሴትን እንገንባ !!!!!"ዕሮብ እና ቅዳሜ ፪ሰአት ይጠብቁን ለበለጠ መረጃ
@Bersihailu@fikirhailu@LWEQESH_Events

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Travel
Statistics
Posts filter


🙏💚💛❤️


ያልተዘመረለት የሰማይ ላይ እንቁ✈️🎖🎖🎖👍😳
ለኢትዮጵያችን ዘመን አይሽሬ አበርክቶት ካላቸው የሙያ ዘርፎች መካከል ውትድርና ግንባር ቀደምትነትን ይይዛል።ከዚህም ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ብዙ ለነፃነት የተደረጉ ጦርነቶች አካሂዳለች።ከነዚህም መካከል ካራማራ የቅርብ ቀን ትዝታችን ነው።በካራማራ ጦርነት ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበረው እና የሰማይ ላይ ዕንቁ የሆነው ብ/ጄ ተፈራ ለገሰ ከብዙዎቹ የካራማራ ፈርጦች አንዱ አድርገን የፈፀመውን ጀብዱ በጥቂቱ እንዘክረው።ጀግናው በጦርነቱ ላይበጀቱ እየከነፈ ፭(5) ጀቶችን በግሉ ፬(4) ጀቶችን በቡድን ሰማይ ላይ አመድ አድርጓል።በተጨማሪም ያለ አዛዦቹ ጠላት ድንበር በመግባት አስጊ የነበሩ ቦንብ ጣይ ጀቶችን አውድሟል።ይህ ተግባሩ ቢያስጠይቀውም ከሰራው ስራ አንፃር ታይቶ በወቅቱ የነበረውን ከፍተኛ ሽልማት ተበርክቶለታል።በመጨረሻም የሚያበረው ጀት ተመቶ ወድቆ ከተማረከ በኋላ ለ፲፩(11)አመታት በሶማሊያ እስር ቤት ሲንገላታ ቆይቶ በነበረው የእስረኛ ልውውጥ ለሀገሩ በቅቷል።ሆኖም ባደረበት የጤና መታወክ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ፳፻፱(2009)ዓ.ም አረፏል።
"ይህ ነው ምኞቴ ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ!!!!!"መዝሙር ተጋበዙልን።
ልወቅሽ ኢትዮጵያ💚💛❤️




👇አሻ የመኢኒት ማህበረሰብ ባህላዊ የእርቅ ስርአት😱

ሰዎች እንደየልማዳቸው እና ባህላቸው ነገር እና ፀብ የሚያበርዱበት እርቅ የሚያወርዱበት የይቅርታ እና እርቅ ስርአት አላቸው።በዚህ መሠረት በመኢኒት ማህበረሰብ የሚደረገው የእርቅ ስነስርአት አሻ ይባላል።ይህ ስርአት ህግ ከተጣሰ የማይፈቀድ ተግባራት ሲፈፀም በተጨማሪም የተለያየ ለበቀል የሚያነሳሱ ነገሮች ተፈጥረው የበሰ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያደርግ ነው።በግጭት ምክንያት ለሚፈጠር የሰው ህይወት መጥፋት የሚደረግ የእርቅ ስርአት በገለልተኛ ሽማግሌዎች የሚደረግ ሲሆን የገዳይ ቤተሰብ ለተገዳይ ቤተሰብ የሚሆን ከብት እስካልሰጠ ድረስ ሟች አይቀበርም።በእርቅ ስርአቱም ላይ የማሽላ ገንፎ ብቻ ሲመገቡ የገዳይ ቤተሰቦች አንድ ልጃገረድ በካሳነት የመስጠት ግዴታ አለባቸው።ልጃገረዲቱንም የሟች ወንድም እንዲያገባት ይደረጋል።ይህም ስርአት አሻ ይባላል።
ልወቅሽ ኢትዮጵያ💚💛❤️
https://t.me/LWEQESH_Events


👇ሄቦ የየም ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ😱

⭐️በሀገራችን ብዙ የብሔረሰቦች እንዳሉ የየራሳቸው ባህል እና አኗኗር እንዳላቸው ግልፅ ነው።ከነዚህም አንዱ ሄቦ የተሰኘው የዘመን መለወጫ በየም ማህበረሰብ ይጠቀሳል።

⭐️ሄቦ በማህበረሰብ በጉጉት የሚጠበቅ እና በትልቅ ዝግጅት የሚከበር አመታዊ ክብረ በአል ነው።ይህም ማህበረሰቡ ነጭ በቀይ በሆነ ባህላዊ ልብስ ደምቆ የተለያየ ባህላዊ ምግብ እና መጠጥ ተዘጋጅቶ እና በባህላዊ ዘፈን ደምቆ ይከበራል።

⭐️የበአሉ የመጀምሪያ ቀን ካማ ኬሳ ሲባል በእለቱ እርቅ የሚወርድበትና ቁርሾ ቅራኔ እንዲሁም ቂም በሽማግሌዎች አማካኝነት ሰላም የሚወርድበት ነው።
@LWEQESH_Events💚💛❤️


👇ሸዋንዳኝ ወለደየስ😱

ትውልዱ በሰሜን ሸዋ በቡልጋ በ1930ቹ ነበር። አባቱ በልጅነቱ ስለሞተበት ለአጎቱ ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ከአጎቱ ሚስት ጋር ባለመስማማቱ አጎቶ ለአሳዳጊው ወልደየስ በጉዲፈቻ ሰቶታል።ሸዋንዳኝ በላም ማርባት ስራ ተሰማርቶ የሰራ ሲሆን በክብር ዘበኛ ለመቀጠር ካመለከቱ ሰማንያ አምልካቾች ከ3 አንዱ ሆነው ተቀጥረ።ከሁለት አመት በኋላም በቃኘኛው ሻለቃ ጦር ወደኮርያ ዘመተ።ወደጃፓን ለእረፍት በሄዱ ወቅትም ሸዋንዳኝ በአንዲት ጃፓናዊት ሴት በፍቅር ይወድቅና ጓደኞቹ ከእረፍት ጨርሰው ሲመለሱ እዛው ይቀራል።ይህ ከወታደራዊ ስነምግባር ውጪ በመሆኑ አለቆቹ ሪፖርት በማድረጋቸው ከስድስት ሰአታት ፍለጋ በኋላ ተገኝቶ ወደካምፕ ተመለሰ።ለ15 ቀናት ወታደራዊ ቅጣት ነቀጥቶ ከጨረሰ በኋላም ከፍቅረኛው ጋር ሊገናኝ አለመቻሉ እንዲሁም ፍቅረኛው ወደኢትዮጵያ ለመምጣት ፍቃደኛ ብትሆንም ሊፈቀድ ባለመቻሉ ሳይገናኙ ወደሀገሩ እንዲመለስ ግድ ሆነ።ይህን ናፍቆቱን አላስችል ቢለው በግጥም እንዲህ ስል ከተበው።
   እሩቅ ምስራቅ ሳለሁ ጃፓኗን ወድጄ፣
  ትዝ ትለኛለች በፍቅሯ ነድጄ።
  የወይን ዘለላ አበባ የመሰለች፣
  ውበቷ ግሩም ነው ሲያዩአት ታፈዛለች ።
  ከሷ የሚወዳደር ከየት ይመጣል ልኳ?
  የትህትና ምንጭ ኢቺባን ነው መልኳ።
ልወቅሽ ኢትዮጵያ💚💛❤️
https://t.me/LWEQESH_Events


🌼እንኳን ለኢሬቻ በአል አደረሳችሁ!!!🌼
❤️🙏ምስጋና🙏
🌎በአለማችን ከተለመዱ ክንዋኔዎች ውስጥ🙏 "Thanks Giving Day,Turkey Day" ወይም የምስጋና ቀን በመባል የሚከበረው በአል በአብዛኛው ሰው ዘንድ  ተቀባይነት ያለው እንዲሁም ጥቅምት በገባ ሁለተኛው ሰኞ አንድንዶቹ ደግሞ ህዳር በገባ በአራተኛው ሀሙስ የሚያከብሩት በአል ነው።
⭐️ለምሳሌ
👉 ሩዋንዳ፣አሜሪካ፣ጃፓን፣ላይቤሪያ፣ካናዳ፣
ጀርመን፣ ወዘተ..
  ሀገራት በቀኑ ፈጣሪያቸውን እንዲሁም መልካም የሰሩላቸውን ሰዎች የሚያመሰግኑበት በአል ነው።በአሉ ምንም እንኳን ሃይማኖታዊና ባህላዊ አመጣጥ እንዳለው ቢነገርለትም ማንኛውም ሰው እንደ ብሔራዊ በአል የሚያከብረው ነው።

🇪🇹🌼🌳በተመሳሳይ በሀገራችን ኢትዮጵያ በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ በደማቅ ሁኔታ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ከምዕራብያኑ የምስጋና በዓል ጋር ተመሳሳይነትና ቀረቤታ ያለው ሲሆን ሁለቱም ምስጋናን ከማቅረብ ጋር የተያያዙ ናቸው።
🌼🌿🏞የኢሬቻ በአል የመስቀል በዓል በተከበረ የመጀመሪያው እሁድ የሚከበር በአል ሲሆን በእለቱ የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ እንዲሁም በማንኛውም ማህበረሰብ ተወላጅ የሆነ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት ክብረበአል ነው።በዋነኝነት ታዳሚው በባህላዊ ልብስ እና ጌጣጌጥ በመዋብ እርጥብ ሳርና አደይ አበባ በመያዝ "ፈጣሪን እናምናለን፣በምድር ላይ በፈጠራቸው ነገሮች በሙሉ እንደነቃለን፣እናደንቃለን.... ሆ.…ያ.…መሬዎ….መሬዎ" የሚሉበት ምድርን በዝናብ አጥግቦ ምርትን ለሰጠን ፈጣሪ ወደ ወንዝ በመውረድ ምስጋና የሚያቀርቡበት እርቅና ሰላም የሚያወርዱበት በዓል ነው።
እኛም ለዚህ ቀን ላደረሰን ፈጣሪያችን እንዲሁም ለቻናላችን ቤተሰቦች ምስጋናን ልናቀርብ ወደድን።🙏🙏🙏 ኢሬቻ🇪🇹

ልወቅሽ ኢትዮጵያ💚💛❤️
https://t.me/LWEQESH_Events


🔥ውድ የክርስትና እምነት ተከታዮች ቤተሰቦቻችን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!!በአሉ የሰለም የጤና እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛል።☺️😊🤩
መልካም በአል!!!🔥


👇ያሆዴ የሀዲያ ዘመን መለወጫ በአል😱

⭐️ያሆዴ የሀድያ ማህበረሰብ ዘመን መለወጫ አዲስ አመት ማብሰሪያ ክረምቱ ወጥቶ በፀደይ መባቻ የሚከበር በአል ነው።በአሉ ከመድረሱ በፊት ሁሉም ሰው የራሱን ድርሻ በመወጣት በጋራ የሚከበር ሲሆን ልዩ በሆኑ የባህል ጭፈራዎች ይከወናል።በበአሉ ለጋብቻ የደረሱ ወጣቶች ተውበው የሚታዩበት እና የሚተጫጩበት እንዲሁም አዲሱን አመት በእርቅ ስነስርአት ሰላም የሚያወርዱበት ነው።
⭐️በተጨማሪም ከበአሉ 15 ቀናት በፊት የሚደረገው የመቻእል ሜራ ሲሆን የቃሉ አቻ ትርጉም የእብድ ገበያ እንደማለት ነው።በገበያው ተፈልጎ የሚታጣ ነገር ካለመኖሩም በተጨማሪም ገበያው በ12:00 ይደራና ከቀኑ እኩሌታ ገብያው ይበተናል።ከዚህ ባለፈ በገብያው የተለያየ ነገር ስለሚከወንበት የእብድ ገብያ ተሰኝቷል።
🌼@LWEQESH_Events💚💛❤️🌼


🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
👇ሸክሸካ ዋሻና ፏፏቴ😱
⭐️ይህ በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ በወሎ እና በቄጃ ቀበሌ መካከል የሚገኝ ደንቅ ተፈጥሮአዊ በደን የተከበበ እንዲሁም ታሪካዊ ዳራዎች ያሉት መስህብ ሸክሸካ ዋሻና ፏፏቴ ይሰኛል።
⭐️ይህን ስፍራ ለየት የሚያደርገው ነገረ አይንን ከሚማርከው ፏፏቴ ስር በግምት እስከ 5000 ሰዎች መያዝ የሚይዝ ተፈጥሮ ጠርቦ የሰራው ዋሻ መኖሩ ነው።
⭐️በታሪካዊ ዳራው ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ የአካባቢው ህዝብ ቤተሰቦቻቸውን እና ከብቶቻቸውን እዛውስጥ በመሸሸግ ራሳቸውን ከጠላት ይጠብቁ እንደነበር የአካባቢው ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ።
🌼@LWEQESH_Events💚💛❤️


🌼🌼🌼እንቁጣጣሽ🌼🌼🌼

🌼እንኳን ለ2015ዓ.ም እንቁጣጣሽ አደረሳችሁ እያልን አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታ፣ የጤና እንዲሁም በለመለመ ተስፋ ወደ ብሩህ አዲስ ዘመን የምንሻገርበት እንዲሆን ከልብ እንመኛለን!!!🌼

🌼በየአመቱ በታላቅ ሁኔታ ከሚከበሩ በአላት መካከል የዘመን መለወጫ በአል እንቁጣጣሽ ዋነኛው ነው።🌼
🌼እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል መንፈሳዊ ትዉፊታዊ እንዲሁም ታሪካዊ ትርጓሜዎች ሲኖሩት ሁሉም ከዘመን መለወጫ በአል ጋር የሚያያዙ ናቸው።በከሣቴ ብርሃን ተሰማ አማረኛ መዝገበ ቃላት መሰረት ፍቺው በክረምት ወቅት በወፈረ መሬት የሚበቅልና ስሩ መልካም መአዛ ያለው በአውዳመት ወቅት ህፃናት ከአበባ ጋር እያሰሩ የሚሰጡት እንገጫ(የሳር አይነት) ነው።ሲሰጡም እንቁጣጣሽ ሲሉ በየአመቱ ያምጣሽ ተብሎ ይመለሳል።🌼
🌼ይህንንም ተከተሎ በጷግሜ ወር ውስጥ ልዩ የሆነ ቱፊታዊ ስነስርአት የሚካሄድ ሲሆን የአዲስ አመት ብስራትን መሰረት ያደረገ የአደይ አበባ የወይራ እና የእንገጫ መልቀም ይደረጋል።(ይህ በደብረ ማርቆስ እና ምስራቅ ጎጃም ይዘወተራል)
🌻🌻@LWEQESH_Events💚💛❤️🌼🌼


👇አእምሮ😱
⭐️በሀገራቸን ለመጀመሪያጊዜ በአማርኛ የታታም የነበረ ጋዜጣ አእምሮ ጋዜጣ ነው።በ1902 እኢአ በግሪካዊ አንድሪያ ካቫዲያ ነበር የተመሰረተው። ⭐️ከዚህ በፊት ግን በአፄ ምኒሊክ ቤተ መንግስት በብላታ ገ/እግዚአብሔር በእየለቱ በእጅ እየተፃፈ የሚሰራጭ ወረቀት እንደነበር ይነገራል።
ወደ ህትመት ታሪኩ ስንመለስ የአእምሮ ጋዜጣ ብዙ ውጣውረዶችን አልፏል።ከነዚህም የማተሚያ ማሽን በጊዜው ወደሀገር አለመግባት አንዱ ነው።
⭐️በቅድሚያ የሚታተመው ጋዜጣ ባለአራት ገፅ ሲሆን ሶስቱ ዜና ነክ ሲሆኑ አንዱ ደግሞ የማስታወቂያ ነው።
⭐️በተጨማሪም በመጀመሪያ 24 እትሞች ብቻ የነበሩ ሲሆን ከዛ ግን እየጨመረ እስከ 200 ደርሷል።
@LWEQESH_Events💚💛❤️


🌴☘🌳ጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ 😱

⭐️የተፈጥሮን ሚዛንን ከሚጠብቁ ተፈጥሮአዊ ፀጋዎች መካከል እፅዋት ዋነኞቹ ናቸው።በሀገራችን ከሰሃራ በረሃ የሚመጣውን ሞቃታማ አየር ከሚገቱ ና በደን የተሸፈኑ አካባቢዎች በሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል የሚገኘው የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ አንዱ ነው።
⭐️ፓርኩ 18987 ሄክታር የሚሸፍን ሲሆን ውብ ከሆነ የመልካምድር አቀማመጡና እንደ ዘብ ከቆሙ ተራራዎች ልዩ ውበት ተችሮታል።
⭐️በውስጡ ከ27 በላይ የዱር እንስሳት ከ57 በላይ የወፍ ዝርያዎች እንዲሁም እየተመናመነ የመጣውን የእጣን ዛፍ ለቅርፃ ቅርፅ መስሪያ አስተዋፅኦ ያለውን የቆላ ቀርከሃ ና ከ81 በላይ እፅዋትን የያዘ ነው።
@LWEQESH_Events💚💛❤️


👇ውበት እንደተመልካቹ!!!😱

ውበት እንደተመልካቹ ሲልቅም ማህበረሰብ እንደዳበረበትና የባህል እይታ የተወሰነ ይሆናል።
⭐️በመካከለኛው አፍሪካ በምስራቅ ኮንጎ በማንግቤቱ ማህበረሰብ ዘንድ ውበትን ለማጉላትና ደምቆ ለመታየት የሚጠቀሙት መንገድ ከተለምዶ ለየት ያለ ነው።

⭐️ይህም በማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ እና ሾጣጣ ጭንቅላት የውበት የእውቀት እንዲሁም የክብር መገለጫ መሆኑ ሲሆን ቅርፁን ለማምጣት አንድ ህፃን ከአራስነት ጀምሮ አናቱን በጨርቅ በመጠምጠም ሾጣጣ ያደርጉታል።ሂደቱም ልፖምቦ በመባል ይታወቃል።
@LWEQESH_Events💚💛❤️


👌🙏ከሴ(ከስየ) አጨዳ በአል👌👌🌿🌿🌿🌿🌿
ቀዝቃዛ ክረምት ነሀሴ ሲጋመስ ሁሌም የልጃገረዶች ባህላዊ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።እነዚህ ቱፊታዊ በአሎች በሀገራችን በድምቀት ከሚከበሩ በአሎች መካከልም ይካተታሉ።በአሎቹ ልጃገረዶች በተለየ መልኩ በጌጣጌጦች አምረው እና ተውበው ከማንኛውም ተፅእኖ ነፃ በመሆን ያለምንም ክልከላ ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋራ ነፃነታቸውን የሚያውጁበት ሲሆን በሀገራችንም የተለያየ ስያሜ ይሰጣቸው እንጂ ሁሉም አላማቸው ሴቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው።ከነዚህም ሻደይ፣አሸንዳ፣አሸንድየ፣ሶለን፣ከሴ(ከስየ) አጨዳ በአል ይካተታሉ።ዛሬ ከሴ(ከስየ) አጨዳ በአል ልናስቃኛቹ ወደድን።በአሉ በየአመቱ ነሀሴ 16(፲፮) ቀን ሴቶች ልጃገረዶች በባህላዊ ልብስ እና ጌጣጌጥ ተውበው ከሴ የተሰኘውን የተክል አይነት ከሜዳ ቆርጠው ያመጣሉ።ከዛም ለበአሉ ተብሎ የሚዜም ዜማ እያዜሙ ለጎረቤቶቻቸው የከሴ ተክልን እንደ ስጦታ እያደሉ እንኳን አደ
ረሳቹ ይላሉ። ከሴ ደግሞ ጥሩ መአዛ ያለው ተክል ስለሆነ ሰዎቹ እየተቀበሉ ተክሉን ለተለያየ አላማ ይጠቀሙታል። እንዲህ በማድረግ በአሉን ያሳልፋሉ።ነገር ግን ይህ በአል እየደበዘዘ የመጥፋት አደጋ ስለተጋረጠበት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
ልወቅሽ ኢትዮጵያ💚💛❤️https://t.me/LWEQESH_Events

15 last posts shown.