Law students Union ️️️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


LSU is created mainly to inform you updated laws; access teaching materials, references, exit exam files, short notes available;and to support law students.
🎓|=|🎓🌟LSU 🌟GBS ⭐የሕ.ተ.ህ🌟
📩if any✍️ @LSU2012_bot

For More Accessibility of Laws!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter






Let us do together for more accessibility of laws

@lawstudentsunion
@lawstudentsunion
@lawstudentsunion




የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ባንክ ገብተው “አንድም ሰው እንዳይንቀሳቀስ! ገንዘቡ የመንግሥት ነው፤
ህይወታችሁ ግን የእናንተ ነው” ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፡፡

ሁሉም ሰው ወለሉ ላይ በደረቱ ተኛ፡፡
ይኼ “Mind Changing Concept” ይባላል፤ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ የሰዎችን አስተሳሰብ መቀየር ነውና፡፡ ጠረጴዛ ላይ ተደፍታ የነበረች አንዲት ሴት የማጉረምረም ድምጽ ስታሰማ፣ ከዘራፊዎች አንዱ ቆጣ ብሎ፣ “እመቤት እንደሰለጠነ ሰው አስቢ እንጂ፡፡

ይህ እኮ ዘረፋ እንጂ አስገድዶ መድፈር አይደለም ” አላት፡፡ ፀጥ አለች፡፡ ይኼ “Being Professional” ነው፤ በሰለጠንክበት ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት ታደርጋለህና፡፡

ዘራፊዎቹ ያለምንም ችግር ቤታቸው ገቡ፡፡ ከዘራፊዎቹ መካከል ልጅ እግሩ እና የMaster of Business Administration ተመራቂው የተዘረፈው ገንዘቡ እንዲቆጠር ሃሳብ አቀረበ፡፡ ነገር ግን በዕድሜ ታላቅ የሆነውና እስከስድስተኛ ክፍል ብቻ የተማረው ዘራፊ፣ በቁጣ “አንተ የማትረባ ደደብ! ይህን ሁሉ ገንዘብ ማን ይቆጥራል? ዛሬ ማታ በቴሌቪዥን ዜና ላይ ስንት እንደዘረፍን ይነግሩናል፡፡” ይኼ “Experience” ይባላል፡፡

ዛሬ ዛሬ በትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት ይልቅ ‘ልምድ' የበለጠ ዋጋ
አለው፡፡ ዘረፋው ከተፈፀመ በኋላ፣ የባንኩ ማናጀር የባንኩን ሱፐርቫይዘር ጠርቶ በአስቸኳይ ፖሊስ እንዲጠራ ነገረው፡፡ ሱፐርቫይዘሩ ግን፣ “ቆይ ተረጋጋ! እየውልህ፣

መጀመሪያ ከካዘና 10 ሚሊየን አንስተን ለራሳችን እንውሰድ፡፡

ከዚያም ባለፉት ወራት የወሰድነውን 70 ሚሊየን እንጨምርበት፡፡ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ያለብን ይህን ገንዘብ ዛሬ ከተዘረፈው ጋር ደምረን ነው” አለው፡፡ ይኼ “Swim with the tide” ይባላል፡፡

የተፈጠረን አስቸጋሪ ሁኔታ ለራስ ጥቅም ማዋል እንደማለት፡፡
ሱፐርቫይዘሩም አለ፣ “በየወሩ ዘረፋ ቢካሄድብን እንዴት
መልካም ነበር!” በሚቀጥለው ቀን፡፡ ከባንኩ የተዘረፈው ገንዘብ 100 ሚሊየን እንደሆነ በቴሌቪዥን ዜና ተነገረ፡፡

ዘራፊዎች ደነገጡ፤ የዘረፉትንም መቁጠር ጀመሩ፤ ማመን አቃታቸው፤ ደግመው ቆጠሩ፤ ያው ነው፡፡ ትንሽ ቆይተው እንደገና መቁጠር ጀመሩ፤ ተመሳሳይ መጠን - 20 ሚሊየን ብቻ! በጣም ተናደዱ፣ “እኛ ህይወታችንን ለአደጋ አጋልጠን 20 ሚሊየን ብቻ ስናገኝ፣ የባንክ ማናጀሩ ቁጭ ብሎ 80 ሚሊየን እንዴት ያገኛል?” ከንፈራቸውን ነከሱ፣ ጠረጴዛውን በቡጢ ነረቱ፡፡ ሌባ ከመሆን መማር ይሻላል ማለት ይህ አይደል?i
(Africa’s elites are lords of poverty! ያለው ማን ነበር?)

የማናጀሩ ፊት በፈገግታ እንደ ማለዳ ፀሐይ አብረቅርቋል፤
የደስታ ግምጃ አድምቆታል፡፡ በሽርክና ገበያው የተፈጠረበት ጉድለት ተሞልቶለታልና፡፡ ይኼንን “Seizing the opportunity” ይሉታል።

@LawStudentsUnion
@LawStudentsUnion
@LawStudentsUnion


Federal_Courts_Costs_and_Damages_Determination_Directive_No_2_2017.pdf
6.1Mb
መመሪያ ቁጥር 2/2017
ፌዴራል ጠቅላይ ፋ/ቤት ወጭ እና ኪሳራ አወሳሰን መመሪያ


🛑🛑ጭብጥ(issue of fact)🛑🛑

ተከራካሪ ወገኖች የተለያዩበት የህግ ወይም የፍሬ ነገር ጉዳይ

ማንኛውም ፍርድ ቤት ባለጉዳዮችን ማከራከር የሚገባው የተለያዩበት የሕግ ወይም የፍሬ ነገር አግባብ ምን እንደሆነ አረጋግጦ ለጉዳዩ ትክክለኛ ጭብጥ በመያዝ ስለመሆኑ፣ የነገር ጭብጥ የሚመሰረተው አንደኛው ተከራካሪ ወገን ያመነውን የሕግ ወይም የነገር አግባብ ሌላኛው ተከራካሪ ወገን በማስተባበል የካደ በሆነ ጊዜ ስለመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ጭብጥን ለመመስረት የሚችለውም ከግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር እና ማስረጃ እንዲሁም በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 241 መሰረት በሚደረግ ምርመራ በተከራካካሪ ወገኖች የሚሰጠውን መልስ መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ የጭብጥ አመሰራረትን በሚደነግጉት ከቁጥር 246 እስከ 248 በተመለከቱት የስነ ስርዓት ሕጉ ድንገጌዎች እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ በክርክሩ የተያዘው ጭብጥ ምን እንደሆነ እና ጭብጡ በአንድ ወይም በሌላ አግባብ የተወሰነበትን ምክንያት በውሳኔው ላይ መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ የፍርድ አጻጻፍን በሚመለከተው በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 182(1) ስር በአስገዳጅነት ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 105869 ቅጽ 18፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 182(1)፣ 241፣ 246-248




Dear our families,
Keep striving for justice, for the law is your sword and shield.Your dedication shapes a brighter future, stay strong, stay bold.
Together, we can 💪🤝







12 last posts shown.