🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ።
.
.
.
ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱


'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ

📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>✝                      ይቀላቀሉን                    ✝


የንጉስ ጭካኔ ፥ ክንዱ ቢበረታ፤
ለጣዖት ሳንሰግድ፥ እኛ ሳንረታ፡፡
የምናምነው አምላክ፥ ሊያድነን ወደደ፤
ገብርኤል መጣና፥ እሳቱ በረደ፡፡
፤
ፍላፃና ሠይፉን፥ አጠፈው መላኩ፤
ሰላም ይዞ መጣ፥ ባለም ለታወኩ፡፡
አትጠራጠሩ፥ ምልጃው ያስምረናል፤
የሚነደው እሳት፥ ሳይነካን ወተናል፡፡
፤
የሰልስቱ ደቂቅ፥ የእጠሉጣ ብርታት፤
የድንግል አብሳሪ፥ የቂርቆስ ረዳት፡፡
በሚመጣው አለም፥ እንዳይበላኝ እሳት፤
አማልደኝ ከጌታ፥ ነፍሴን እንዲምራት፡፡
፤
የነገርኩህ ሁሉ፥ በቀኑ ደረሰ ፤
በዘብር ገብርኤል፥ እንባዬ ታበሰ፡፡
ና ልጄ ስትለኝ፥ አልልህም እንቢ፤
ስለቴን ተቀበል፥ አባቴ ቁልቢ፡፡
፤
የልቤን ነግሬህ፥ የቁልቢው ገብርኤል፤
ሳትረሳ ፈፀምከው፥ ስለቴን ተቀበል፡፡
ለንግስ እንመጣለን፥ አንተ አትረሳምና፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ አድርሰን በደህና፡፡
+++++++

እንኳን ለሃያሉ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!

🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔
@MENFESAWItsufoche
🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔


🌿"#ሰማዕቷ #ቅድስት #አርሴማ"

ቅድስት አርሴማ እናታችን ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡ ቤተሰቦቿ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን እንደነበሩ የገድሏ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡
ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከቤተሰቦቿ በሚገባ የተማረች፤ የተማረችውንም በተግባር የተረጎመች፤ በጸሎት ሕይወት የምትተጋ ከቅዱሳት አንስት አንዷ ናት፡፡ ይቺ ታላቅ ሰማዕት በነበረችበት ዘመን በአርመን የነገሠው አረማዊ ንጉሥ ድርጣድስ ይባላል፡፡ ይህ ንጉሥ እግዚአብሔር አምላክ በሙሴ ላይ አድሮ “ቀልጠው የተሠሩትን የአማልክት ምስሎች ለአንተ አታድርግ” ብሎ የተናገረውን በመቃወም ለጣዖት የሚሰግድ ፀሐይንም ያመልክ ነበር /ዘጸ.34፥17/፡፡ በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖችን
“እኔ ለማመልከው “አምላክ” ወይም ጣዖት መስገድ አለባችሁ፤ ይህን የማታደርጉ ከሆነ ትእዛዜን ጥሳችኋልና መከራ ይጸናባችኋል”
የሚል ዐዋጅ በማውጣት መከራ ያደርስባቸዋል፡፡
ጨካኙ ንጉሥ ድርጣድስ ይህን ትእዛዙን ባለማክበራቸው መከራና ስቃይ ያደረሰባቸው ክርስቲያኖች ቁጥራቸው 27 ናቸው፡፡ “እኔን የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ ይከተለኝ” ያለውን የእግዚአብሔርን ሕግ የፈጸሙ ክርስቲያኖች እሱ ለሚያመልከው ለጣዖት አንሰግድም በማለታቸው ይደበድባቸውና ግፍና መከራ ያጸናባቸው ጀመር፡፡ ይህን ግፍና መከራ የተመለከተች እናታችን ቅድስት አርሴማ የተጋድሎ ሕይወትን እነሱን አብነት አድርጋ እንደ ጀመረች የሕይወት ታሪኳን የያዘው መጽሐፏ ይነግረናል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ‘‘ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሳጧችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፏችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ! ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን ስለ እኔ ወደ ገዢዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ… አትጨነቁ! በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ የምትናገሩት እናንተ አይደላችሁም” /ማቴ.10፥16-20/፡፡ ብሎ የተናገረውን በማሰብ ቅድስት አርሴማ በሃያ ዓመቷ የንጉሡን እኩይ ግብሩን በመንቀፍ ስለ ክርስቶስ ከሚሰቃዩ ሰማዕታት ወገኖቿ ጋር በመሆን ስለ እግዚአብሔር አምላክነት ትመሰክር ነበር፡፡
የንጉሡም አገልጋይ በደም ግባቷና በንግግሯ ማማር ተደንቆ በዚች በፈቃዷ ሰማዕትነትን ልትቀበል በወደደች ሴት ምንም ሊያደርግባት ስላልወደደ ወደ ንጉሡ ወደ ድርጣድስ ከሃያ ሰባቱ ክርስቲያኖች ጋር ወሰዳት፡፡ ንጉሡም ብዙ የተነገረላትን ወጣት ሲያይ በውበቷና በንግግሯ ተማርኮ ለዓለማዊ ደስታውና ፍላጎቱ ተመኛት፡፡ ሚስት ትሆነው ዘንድ አብዝቶ ተማጸናት፡፡ እጅ መንሻና ማታለየ የዚህን ዓለም ወርቅና ብር አቀረበላት፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን መልክ ረጋፊ፤ የዚህ ዓለም ሀብትም ከንቱ እንደሆነ ስለምታውቅ በዓላማዋ ጸናች! ንጉሡንም ‘‘እኔ የንጉሥ የክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የዚህን ዓለም አላፊ ጠፊ የሆነውን ገንዘብና ደስታ የምሻ አይደለሁም፡፡’’ በማለት መለሰችለት፡፡
ንጉሡም ይህንን ከእርሷ በመስማቱ እጅግ ተቆጣ፤ እግዚአብሔር አምላኳን በማመኗ ተበሳጨ፤ አሽከሮቹንም ጠርቶ በቤተ መንግሥቱ የታሠሩትን አንበሶች እንዲለቀቅባቸው አዘዘ፡፡ አንበሶቹ ግን ይደሰቱ ነበር፡፡ በኋላም ፊታቸውን ወደ ንጉሡና አገልጋዮቹ በማዞር ሩጠው እስኪደበቁ ድረስ አሳደዷቸው፡፡
በቅድስት አርሴማ የገድል መጽሐፍ ላይ የሰፈረው ታሪክ በተመሳሳይ መልኩ በትንቢተ ዳንኤል ላይ ሲፈጸም እናያለን፡፡ ነቢዩ ዳንኤል ያለ በደሉ በክፉ ሰዎች ምክር የተራቡ አንበሶች ወዳሉበት ጉድጓድ በተጣለ ጊዜ አንበሶቹ ፈጽሞ ጉዳት አላደረሱበትም፣ እንኳን ሊበሉት የእግሩን ጥፍር እየላሱ ተገዝተውለታል፡፡ “በነጋውም ንጉሡ ማልዶ ተነሣ ፈጥኖም ወደ አንበሶቹ ጉድጓድም ወደ ዳንኤል በቀረበ ጊዜ በኃዘን ቃል ጠራው፤ ንጉሡም ተናገረ ዳንኤልንም፡- የሕያው አምላክ ባሪያ ዳንኤል ሆይ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶች ያድንህ ዘንድ ችሎአልን? አለው፡፡ ዳንኤልም ንጉሡን ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ንገሥ በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና በአንተም ፊት ደግሞ ንጉሥ ሆይ አልበደልሁምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልጎዱኝም አለው” የዳንኤል ከሳሾች ግን “በአንበሶች ጉድጓድ ጣሏቸው፤ ወደ ጉድጓዱም መጨረሻ ሳይደርሱ አንበሶች ያዟቸው ዐጥንታቸውንም ሁሉ ሰባበሩ” /ዳን. 6፥19-25/፡፡
ንጉሡ የክርስቲያኖቹ በሰማዕትነት መጽናት ስለነደደው በረሃብ እንዲያልቁ እንዲታሠሩ አዘዘ፡፡ እግዚአብሔርም በአምስተኛው ቀን በብርሃን ቤቱን ሞልቶት የሚበሉትን በመሶብ የሚጠጡትን በጽዋ ከሰማይ አወረደላቸው፡፡ንጉሡም ይህንን በማየቱ ከዚያ አውጥቶ በእሳት ውስጥም አስገባቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ ከእሳት ያወጣቸው እግዚአብሔር አምላክ እነርሱንም አዳናቸው፡፡ የክርስቲያኖቹ የእምነት ጽናት የሚደንቅ ስለነበር ንጉሡ አማካሪዎቹ ጠርቶ
“ምን ብናደርግ ይሻላል?” የሚል ምክር ጠይቆ ሁሉንም በሰይፍ ተሰይፈው እንዲሞቱ ስምምነት ላይ ይደርሳል፡፡
እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ሲሰይፋቸው ቅድስት አርሴማ ለሚሰየፉት ሁሉ የድል አክሊል ከሰማይ ሲወርድላቸው ትመለከት ስለነበር የእርሷን ተራ በጉጉት ትጠብቀው ነበር፡፡ በሰማዕትነት አምላኳ እንዲያጸናት እየጸለየች “አይዟችሁ ጽኑ! የዚህ ዓለም መከራ አያሰቅቃችሁ! አትፍሩ” እያለች ታጽናናቸው ነበር፡፡
ንጉሡም ሌሎቹን አሰይፎ ሲያበቃ ወደሷ ዞሮ በቁጣ እየጮኸ “አንቺን እንደ ባልንጀሮችሽ በቀላሉ አልገልሽም! ስቃይ አጸናብሻለሁ” ብሎ ለአገልጋዮቹ ትእዛዝ በመስጠት ዓይኗን አስወጥቶ በእጇ እንድትይዝ አደረጋት፤ ጡቷን ቆረጣል፤ በኋላም አንገቷን በሰይፍ በመቅላት መስከረም 29 ቀን በሰማዕትነት እንድታልፍ አድረጋት፡፡
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ
‘‘ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ’’ እንዲል /መዝ. 8፥3/፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‘‘በእኔ ስም አምነሽ የዚህ ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል፤ የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ፤ በዓልሽን ያከበረ፤ ዝክርሽን ያዘከረ፤ ገድልሽን የጻፈና ያጻፈ፤ የሰማና ያሰማም እስከ 12 ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ’’ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡
የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ጸሎትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይኑር፡፡ አሜን! ! !

"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም ፡ ወከዓዉ ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ፡ ወተዐገሱ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት።"🌹🌹🌹

በዳ/ን በሃይሉ ተፈራ
🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹
@MENFESAWItsufoche
🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹


፨ልዩ ነው ህይወቱ፨

በማህፀን ሳለ
ለአምላኩ የሰገደ
በናዝራዊነቱ
ምድር በዳ ያደገ
የብሉይ መደምደሚያ
የሃዲስ ኪዳን መግቢያ
የእውነት ምስክር
ነብይ ሐዋርያ
ደሃውን ሳይንቀው
ንጉሱን ሳይፈራ
ለሕገ እግዚአብሔር ቀንቶ
እውነቱን የዘራ
ልዩ ነው ሕይወቱ
እፁብ እፁብ ድንቅ
የዘካርያስ ልጅ
ዩሐንስ መጥመቅ።

* / / *

➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴
@MENFESAWItsufoche
➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴


✝✝ የገነት መደብር ✝✝

ከእለታት በአንድ ቀን በሕይወት ጎዳና ስጓዝ #የገነት መደብር# የሚል ጽሑፍ የተለጠፈበት አንድ መሸጫ አይቼ ወደ እርሱ አቀናሁ ታዲያ ይኸውላችሁ ወደ በሩ ስጠጋ ድንገት በሮቹ በስፋት መደብሩ ውስጥ ገበያተኛውን ለመርዳት የቆሙ መላእክት ነበሩ። ከእነሱ መካከል አንድ እቃ የምይዝበት ቅርጫት ሰጡኝ ።
ልጄ ሆይ በጥንቃቄ ሸምት አሉኝመሔድ በዚህ መደብር ውስጥ ሰው የሚፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ ነበሩ። ሌላው ደግሞ በአንድ ጊዜ ገዝቶ ጭኖ የማይቻለውን ዳግመኛ ተመልሶ ሰብስቦ ይዞ መሔድ የሚቻልበት መደብር ነበር።
በመጀመሪያ ትዕግስትን አንስቼ ቅርጫቴ ውስጥ ከተትኩ ፍቅርም በዚያውም መደርደርያ ላይ ነበር ከእርሱ ዝቅ ብሎ የትም ብንሄድ የሚያስፈልገን ማስተዋል ተቀምጧል ከዚያምያህል 2እሽግ የሚሆን ጥበብ የሞላበት ካርቶንና ሌላ እምነት የሞላበት ካርቶን አግኝቼ የሚያስፈልገኝን ከወሰድኩ በኋላ ልግስና የሞላበትን ካርቶን እዚያው ስለነበር እንደሚጠቅመኝ አውቄ የምሻውን ያህል አነሳሁለት።
በመደብሩ ውስጥ የሞላው እቃ እጅግ ከማስደሰቱ የተነሳ ለመምረጥ ቢያስቸግርም ከሁሉም ግን በየመደርደርያውና በየቦታው ያለውን መንፈስቅዱስን ያለበትን ነገር ሁሉ አልተውኩትም በዚህ ዓለም የኑሮ ትግል ውስጥ እንዲረዳኝ ከጥንካሬና ከብርታትም ጥቂት ወሰድሁ።
ቅርጫቱ እየሞላ ቢመጣም ፀጋ እንደሚያስፈልገኝ አስትልወስኩና ከእርሱም አነሳሁ ከዚያ በኋላ ድኅነትአንስቼ የማይከፈልበት ነጻ ስለነበር ለእኔም ለእናንተም የሚሆን የምችለውን ያህል ቅርጫቱን ሞላሁ።
ልከፍል ወደ ባንኮኒው ሳመራ በዚህ ዓለም የጌታን ፍቃድ ለመፈጸም የሚያስፈልገኝን ሁሉ እያሰላሰልኩ ነበር በመተላለፊያው በኩል ወደ መክፈያው እያመራሁ ሳለ ጸሎትን አንድ ጥግ አየሁና አንስቼ ያዝኩት ምንም እንኳይህን ያህል ብሸምትም ከዚህ ወጣ እንዳልኩ ወደ ኃጥያት እንደምሮጥ ማሰቤ አልቀረም።ከእነርሱ
አለፍ ስል ሰላምና ደስታ በብዛት ተደርድረው አየሁ አጠገብ ደግሞ ዝማሬና ምስጋና ተንጠልጥለዋል ቅርጫቴ ቢሞላም እንደምንም ብሎ ለመጫን ከርሱ ወሰድኩ።
በመጨረሻም ወደ ገንዘብ ተቀባዩ ሄጄ ስንት ነው አልኩት መልአኩም ፈገግ ብሎ "ውሰደው ነጻ ነው" አለኝ እውነቴን ነው ስንት ነው የምከፍለው አልኩት .......የለም ልክፈል ብትይ እንኳን ዋጋውን አትችይውም ውሰደው አልኩሽ እኮ የኔ ልጅ ወሰደው እግዚአብሔር ከብዙ ዓመታት በፊት አስቀድሞ ሁሉንም ስለከፈለ አንቺ የምትከፍይው ነገር የለም ሁሉንም ውሰጅው አለ።
ውድ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ስለሰጠን ነገር ክፍያ ቢጠይቀን ምን ይውጠን ነበር?
ዘማርያኑ ስለተሰጣቸው ድምጽ
ሰባክያኑ ስለተሰጣቸው ጸጋ
ጸሐፍያኑ ስለተሰጣቸው ጥበብ ክፍያ ቢጠየቅበት ማን ጠቢብ ማንስ ባለጸጋ ይኖር ነበር.....ፍቅር፣ ትህትና፣ደግነት በነጻ ተሰጥተውናልና እንጠቀምባቸው።
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
✞@MENFESAWItsufoche✞
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤


https://t.me/yeaelafat_zimare
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የአእላፍ ዝማሬ ኦርቶዶክሳዊ ቻናልን ይቀላቀሉ የመዝሙር ጥናቱን አብረው ያጥኑ።
አንደበት ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመብፕስግን፡፡
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
@MENFESAWItsufoche


🕯🕯🕯🕯🕯️🕯️
🕯ፅዩን ማርያም🕯
🕯🕯🕯🕯🕯🕯

ፅዮን ማርያም አማላጅዋ
ግሩም ድንቅ ነው ከለላዋ
ተነግሮ አያልቅ ጥበቃዋ።
ስሟን ስጠራ ተጨንቄ
ፅዮን ማርያም ስላት አጥብቄ
ሰለምናት ለመንገዴ እንድትሆነኝ ስንቄ ፣
ተናግሬ ሳልጨርስ
ከተፍ አለች እኔኑ ልታድስ።
ልትመራኝ ደግፋ ልትሆነኝ ተስፋ
ልትታደገኝ በይፋ።
ምኞትህ መልካም ነው ልጄ፣
አትጥፋ እንግዲ ከደጄ
ብፅዕት ነሽ በለኝ አሁንም ወዳጄ
አስታርቅሃለሁ አማልጄ፤
እያለች ስታፅናናኝ
ፅዮን ማርያም እመቤቴ
መታወቂያ የእኔነቴ
መንገድ መሪዬ መስታወቴ
የኑሮዬ ትርጉም የልማቴ
የድካም ሁሉ ብርታቴ
ምቹ ማረፊያ የስደቴ።
ርቄ ብሄድ ባህር ማዶ
መቼ ሆነ ቤቴ ማዶ
እንባዬ ታብሶልኝ
ፀሎቴ ተሰምቶልኝ
መውደዴ ተቆጥሮልኝ
ፅዮን ማርያም አብራኝ መጣች
ጣፋጭ ቃሏን እያሰማች
ብፅዕት ነሽ በለኝ እያለች።
* * */ /* * *
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር።
**********
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!!!
የእናታችን ፂዮን ረድኤት እና በረከት በሁላችንም ላይ ይደር አሜን!!!
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔

🕯❖🕯❖🕯❖🕯❖🕯❖🕯
✨ @MENFESAWItsufoche✨
🕯❖🕯❖🕯❖🕯❖🕯❖🕯


Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
~ኅዳር 21~

እንኳን-ለቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ🙏🙏

  ~ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች ~።

በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን  አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

#ድምፀ_ተዋህዶ


+++ድንቅ ልዩነት ተመልከቱ+++

በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ፈርዲናንድ ማጄላን ዓለምን በመርከብ ዞረ።

👉ሐዋርያቱ ደግሞ መርከባቸውን ጥለው ዓለምን ዞሩ!

ዛሬ ይዘንባል እያሉ ትንቢት የሚተነብዩ ሜትሮሎጂስቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልያስ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ ዳግመኛም ዝናብን ያዘነበ ከቶ የለም።

በላብራቶሪው ተመራምሮ ህሙማንን የፈወሰ ሞልቷል።

👉እንደ ጴጥሮስ ጥላው ድውይ የፈወሰ ከቶ አላየሁም።

በዘፈኑ አጋንንትን የጠራ እንደ ማይክል ጃክሰን ሞልቷል።

👉እንደ ዳዊት በበገና መዝሙሩ አጋንንትን ያስወጣ እስከ ዛሬ አልተገኘም።

ከረቫትና ሱፉን ለብሰን የምንጎራደድ ሞልተናል።

👉የልብሱ ቁጨት አጋንንት ያስወጣ እንደ ጳውሎስ ከቶ አልተገኘም።

የግብጽ ነገሥታት አጽማቸው በክብር ይቀመጣል።

👉ዐጥንቱ ሙት ያስነሳ እንደ ኤልሳዕ ከቶ አላየንም።

በአሜሪካ የነገሥታትን ምሥጢር የሚሰልሉ ድርጅቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልሳዕ በእስራኤል ሆኖ በሶሪያ ቤተመንግሥት የሚደረገውን ምሥጢር ያወቀ አልተገኘም።

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን በእግሩ የረገጠ ዩሪ ጋጋሪ ዛሬ ብዙዎቹ አድርገውታል።

👉እንደ ኢያሱ ፀሐይን ያቆመ ከቶ አልተገኘም።

በነገራችን ላይ በተፈጥሮ ሕግ መሰረት ፀሐይ በመሃል ቆማ መሬት ዙሪያውን ትዞራለች። በፀሐይ ፊት ያለው የመሬት ክፍል ቀን ሲሆን ሌላኛው ጎን ደግሞ ማታ ይሆናል።

እነ ኢያሱ በሚዋጉበት ጊዜ መሬት ከፀሐይ ፊቷን አዙራ ቀኑ ሊጨልም ነበር።

👉ኢያሱ ግን መሬት እንዳትዞር አደረጋት! ፀሐይን በገባኦን አቆመ ተባለ! መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ

ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።

👉 እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና ((እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።))
የዓለም መሪዎች ከአስር በላይ ቋንቋ መናገራቸውን እንጃ፤

👉ሐዋርያቱ ግን 72 ቋንቋ ተገለጠላቸው።

ኃያላን ነገሥታት ድውይ እንኳን መፈወስ አይችሉም።

👉ቅዱሳኑ ግን የ70 የ80 ዘመን ሬሳ አስነሱ።

👉ጠቢባን ነን የሚሉ ጸሐፍት ፈሪሳዊያንን ምላሽ ያሳጣቸው ዘንድ ጥበብ ያልነበራቸውን ዓሳ ወጋሪ የነበሩ ሐዋርያትን መረጠ።

ኃያላን ነገሥታት የመሰሉ መሪ ዳዊትን የመሰሉ ነገሥታትን የወለዱ የከበሩ እናቶች ሞልተዋል።

👉የነገሥታትን ንጉሥ ክርስቶስን የወለደች እናት ግን አንድ ብቻ ናት።

ይህችውም ከሴቶች መካከል ተለይታ የተባረከችው ድንግሊቱ 👉 ማርያም ናት 👈


ስብሐት ለእግዚአብሔር!

📌📌📌📌📌📌📌📌📌
@MENFESAWItsufoche


እንኳን ለፆመ ነብያት/የገና ፆም/
በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
የበረከት ፃም ይሁንልን 🙏
ህዳር 15/2017 ዓ.ም የፆሙ መግቢያ ነው ።
✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨
@MENFESAWItsufoche
✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨


#እንኳን_ለሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል_ክብረ_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ_አደረሰን♥♥♥

          #ጎጆ_ቀለስኩልህ

         (በሰመረ ፍስሃ)

በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ
ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ
የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ
እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡
...................ወዲህ ሲመልሰኝ

ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ
...................ጉድፌን አፅድቶ
ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል
ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡

ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ
በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡

ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ
የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ
አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል
አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡

የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም
አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም
ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ
የማይቻል የለም እኖራሎህ ችዬ፡፡

ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ...
የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ
ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ
አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ
ሁሌ  'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡
ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል
ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡

እናም ሚካኤል ሆይ....
ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ
በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡
❖==✿==❀==✞==❀==✿==❖
@MENFESAWItsufoche
✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧


፨የአፎምያ አጽናኝ፨
            🕯
     🕯🕯🕯🕯
            🕯
            🕯
            🕯
ከቀደመው መንገድ ከላይ በተሰጠን
ዕድሳት በማያውቅ በማይሻርው ዘመን
በድንቅ ምስክሮች ብርሃን በሆኑን
እንድንጓዝ ሁሌም የአፎምያ አጽናኝ
ጠላት ቀስቱን ሰብቆ ሊያጠፋን ሲመጣ
እንደ ቋጥኝ ከቦን የዚህ አለም ጣጣ
በከንቱ ስንሮጥ ኋላ እንዳንቀጣ
አማልደን መላኩ የነፍሳችን ዕጣ
የሁሉንም ጸሎት ከአምላክ የምታደርስ
ፍቅር እና ርህራሄ በሰው የምታለብስ
ልክ እንደ ትላንቱ ዛሬም ፈጥነህ ድረስ
በአንደበትህ ፍሬ ውስጣችን ይታደስ
የዳንኤል አጽናኝ የአፎምያ ረዳት
በህይወት የቀየርክ የባህራንን ጽሕፈት
በለአምን የታደክ ከእርግማን መቅጸፍት
እኛንም ጠብቀን ከምናየው መአት
የምጽአት ዋዜማ ለመሆኑ ምስክር
በመጽሐፍ ያለው ቃሉ ሲተገበር
መተማመን ጠፍቶ ሲቀዘቅዝ ፍቅር
በወንጌሉ አንድምታ ልባችን ይታጠር
ይቅርታ ምህርቱ ይምጣልን የእግዚአብሔር
እረኛ እንደሌለው ሲጨነቅ ትውልዱ
ተመሳስሎ ቆሞ ሲያስት በመንገዱ
ግራ በመጋት ስንቶቹ ተጎዱ
በየዋህነታቸው አብረው ተሰደዱ
ዘንዶ አፉን ከፍቶ ነፍሳት እንዳይወጥ
የተዋህዶን መዝገብ እውነቱን ለመግለጥ
የቆመውን ሁሉ በአውደ ምህረቱ
ያበረታን አምላክ እሰከ ምጽአቱ።

           🕯🕯🕯
እንኳን ለሊቀመላአኩ ለቅዱስ ሚካኤል ክብር በዓል በሰላም አደርሳቹ አደረሰን የመላአኩ ረድኤት እና ምልጃው አይለየን አሜን!

✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
  @MENFESAWItsufoche
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤


ቀፀላ መንግስቱ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
@MENFESAWItsufoche


፨ጨረስኩ ሳልጀምረው፨ 📝✏️
ከፊደላት ተራ ከሆህያት ገብቼ
ክብርሽን ለመግለጽ አሙልቼ አስፍቼ
አበው ሲናገሩ ስላንቺ ሰምቼ
ቃላትን ከቃላት መርጬ አሳክቼ።
ብዬ ጀመርኩኝ ልናገር ጸጋሽን
መጽሐፍ ከሚለው በልቢም ያለውን
አባቶች ቅዱሳት ያስተላለፉትን
በሕይወት ከነሱ የተቀበልኩትን።
ከነ ነጎርቤት ከነ አዝማዳት
በሰባት በሰባት ከተከፋፈሉት
ከላይ እስከታች የተደረደሩት
እስከነ ድረስ ከተሰበሰቡት።
ያንንም ሳወጣው ይንንም ስመዘው
ጥንት የመረጥኩትን መልሼ ስተወው
ፊት ያስገባሁትን ኃላ ስመልሰው
አንዱን አስገብቼ ሌላውን ሳወጣው
ፈጽሜአለሁ ብዬ የፃፍኩትን ሳየው
ድንግል ውዳሴሽን ጨረስኩ ሳልጀምረው።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

ተፈፀመ ማህሌተ ፅጌ
@MENFESAWItsufoche
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺


እንኳን ለቁስቋም ማርያም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
@MENFESAWItsufoche
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺


*እቴ ውቤ*
እቴ ውቤ ሙሽራዬ/2/
የባሕርየ መመኪያዬ
የክብር አክሊል መጽናኛዬ፡፡
ምሥራቅ ሆነሽ ፀሐይን ወልደሽ
ደኅንነት ሰላም በእጅሽ ይዘሽ
ለዲያብሎስ መርዶ ሆነሽ፡፡
ሻማ ሆነሽ ልታበሪ
ድርሺልኝ ስትበሪ፡፡
ሱላማጢስ አንቺ እናቴ/2/
ፈጥነሽ ነይ እመቤቴ
በአንቺ ሊጠግ የአዳም ቁስሉ
ሊጠፋልን ሊከስምልን
ያ የሲኦል ነበልባሉ፡፡
እቴ ውቤ እመቤቴ/2/
ፍጠኚልኝ ነይ በሞቴ
ለእርቃኔ ልትሆኚኝ ልብስ
ለሕመሜ ልትሰጪኝ ፈውስ
ረሀቤም እንዲታገስ
ሕብስት ይዘሽ ሆነሽ መቅደስ
ውዴ ነይ ከሊባኖስ፡፡
ክብር ሰጥቶሽ ህያው ልጅሽ
ወረቅ ለብሰሽ ተጎናፅፈሽ
የምትቆሚ በልጅሽ ቀኝ
እኔ ኃጡኧን አማልጅኝ አክብሪኝ
ውዴ እርሺው ያን ቤትሽን
የቀድሞውን ያባትሽን፡፡
ውቤ ውዴ እመቤቴ/2/
የክብር ማማ ሰገነቴ
መርሕ ፋና ለህይወቴ
ፈጠኚልኝ ነይ በሞቴ/2/
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
✞@MENFESAWItsufoche✞
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤


ንግስተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል/×2
ተፈፀመ/×5 ማኅሌተ ፅጌ
እንኳን ለማኅሌት ፅጌ ፍፃሜ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
@MENFESAWItsufoche
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺


፨ስደቷ ፍቅር ነው፨
ከአረጋዊው ዮሴፍ ጋር-ኤልሻዳይን አዝላ
ሰሎሜም ሳትቀር-ወጡ ከገሊላ
የአስራአምስት ዓመቷ-ድንግል ማርያም
በግብፁ በረሀ-ገጠማት ድካም።
ዐፈሩ ረመጥ ነው-እጅግ የሚያቃጥል
አሸዋ ድንጋዩ-እንደ ብረት የሚግል
አየር እንፋሎቱ-ልብን የሚሰውር
የነበረው ስቃይ እንደምን ይዘርዘር?
ያስጨንቃል በጣም-የመከራሽ ነገር።
በትንቢተ ሆሴዕ-የተጻፈውን
ምስጢራዊ ትንቢት -ሄደ ሊከውን
የድንግል ማርያምን ልጅ-እየሱስ መድኽን
እፁብ ድንቅ ያሰኛል-የእግዚአብሔር ማዳን።
በፈጣን ደመና-ወደ ግብጽ በረረ
በማለት ኢሳይያስ -ተናገረ
ፈጣኗ ደመና-ወለተ ኢያቄም
ማህደር መለኮት-ነጻነቱ የአዳም።
ከሶስቱ አካል አንዱ-ኢየሱስ ክርስቶስ
ተወልዷል በበረት-ሞትን ሊደመስስ
በገባው ቃልኪዳን -በቀጠሮ መጣ።
በከብቶቹ በረት-ቢታይ በትህትና
የሕይወት እንጀራ-የሰማዩ መና
የዳዊት የሙሴ-የነቢያቱ ዜና
ተፈፅሞ ስናይ-ዘመረን በበገና።
እረኞች በቦታው-ከመላእክት ጋራ
ስብሐት ለስላሴ-ብለዋል በጋራ
ንጉሥ ተወለደ-በዳዊት ከተማ
እሰይ የምስራች-በዓለም ይሰማ
ነበረ የዚያን ጊዜ-የደስታቸው ዓርማ።
መወለዱን የሰማው-የሄሮድስ በውሸት ተነስቶ
ብዙ ህጻናትን-ቦታው አስጠርቶ
እርዳታ ልሰጥ ነው- በሚለው ትዕዛዝ
የዋሃን እናቶች-የሆዳቸውን ፍሬ ወደ እሱ አበጋዙ።
ገስግሰው ሲደርሱ-የሆነው ሌላ ነው
ለጨካኝ ሰራዊት -ደም ለጠማቸው
የህፃናቱን አንገት-ቆራርጡት አላቸው
ለወንበር ለስልጣን -ስለ ተማረከ
የስላሴን ዘፍጥረት-በሰይፉ አወከ።
የሰባሰገሎች-ጥበብ ስላልገባው
የተወለዱትን-በሙሉ አስጠራቸው
የተባለው ትንቢት-እንቅልፍ ስለነሳው
የነገስታትን ንጉሥ -አስቦ ሊያገኘው
ከዚህ ድንቁርና-ሰውረን ማለት ነው።
የነፍሳቱ ደም-ወረደ እንደ ጎርፍ
በዚያች ከተማ-ቤቴሌሔም ደጃፍ
በከንቱ ሰዋቸው-በመሰለው ነገር
ህፃኑ ግን ሸሽቷል-ወደ ሌላ ሀገር
የስላሴ ጥበብ -ከቶ አይመረመር።
ዛሬም በዚህ ዘመን-አሉ ብዙ ሞኞች
በአለማዊ ጥበብ -በባዶ ተሟጋች
ማመን አለማመን-የነሱ ድርሻቸው
እውነትን መመስከር -የልጅ ግዴታ ነው
ሂዱና አስተምሩ-መልሱ ነው የሚለው።
ሰለኛ ተሰዳ-ተስፋን ለሰጠችን
በልጇ ቸርነት-ስለተጎበኘን
እንደ ቅዱሳኑ-ነይ ነይ እንላለን።
በአፀዷ በቅጽሯ-ጽዮንን ከበናል
የአባ ጽጌ ድንግል-በረከት ደርሶናል
በሰማያዊው ስልት-ማኅሌት ቆመናል
አቤት ያለው ደስታ-ዓለምን ያስረሳል።
ዶግማ የማይሻር-ከቶ የማይታደስ
ሕጉ አምላካዊ-በፍፁም የማይፈርስ
ሕጉ አምላካዊ-በፍጹም የማይፈርስ
ቀኖና ፍትሐዊ-ጭንቀት የሚበጥስ
ትውፊት ታሪካዊ-ለልጅ ልጅ የሚደርስ
የእውነት ቅብብሎሽ-አንዱም አይፋለስ
በዋሻ ገደሉ-ጤዛውን በመላስ
ተግተው ይቆማሉ-እንዳለው ጳውሎስ።
በምድራችን ሰላም-እንዲሆን ደስታ
ትውልዱ እንዲጠግብ-በአጋፔው ገበታ
በንስሐ ታጥቦ-ልቡ እንዲበረታ
ድንግል ሆይ አሳስቢ-ለታቀፍሽው ጌታ።
የቤሌሖር ልጅ-ወድቆ እንዲሰበር
ዳጎናዊው መንገድ-በእውነት እንዲታጠር
የዲያብሎስ ውጊያ -በቃልህ እንዲሞት
አስነሳልን አምላክ-የበረታ አባት
ለመንጋው እራርቶ-የሚያፀና በእምነት።
ነኽምያን ላከው-ያንጽ ቤተመቅደስ
የአምልኮ ስፍራ-ለሁሉ እንዲደርስ
ሳሙኤልን ስጠን-ወንጌልን ሰባኪ
በፀጋው በጥበብ -ራዕይን አሳኪ።
አባታችን ሙሴ-የማርያም ወንድም
ስማን አሳስብልን-ለመድሃኒዓለም
በኑፋቄ ባሕር -ገብተን እንዳንሰጥም
ክፍልና አሻግረን-ተጨንቀናል በጣም
በተሰጠን ጊዜ -ለመኖር አልቻልንም።
ከውብ ዜማው ጋራ-ቅዱስ ያሬድ ይምጣ
ምስጢር በማፋለስ -ከሕግ እንዳንወጣ
እናንብብ እንጠይቅ-እንማር ከአበው
ከእውነተኛ መምህር -ለኛ ከሚገባው
አምላክ ይሰውረን -ለኛ ከሚገደው
አምላክ ይሰውረን -አሁን ከምንሰማው።
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
✞@MENFESAWItsufoche✞
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤


መድሃኔዓለም ነው!
📍📍📍📍

ከሰማያት ወርዶ
ከድንግል ተወልዶ
ክብሩን ሁሉ ትቶ
ያከበረኝ ሞቶ
የነፍሴ ቤዛዋ
ዘውድ ማአረጉዋ
የንጉሶች ንጉስ
የድኩማን ሞገስ
አምላኬ የምለው
መድሃኔዓለም ነው።
         ✍ቃልኪዳን ተፈራ

📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌
  @MENFESAWItsufoche
☔☔☔☔☔☔☔☔☔

20 last posts shown.

24 361

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

🌿"#ሰማዕቷ #ቅድስት #አርሴማ" ቅድስት አርሴማ እናታችን ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡ ቤተሰቦቿ እግዚአብሔ...
፨ልዩ ነው ህይወቱ፨ በማህፀን ሳለ ለአምላኩ የሰገደ በናዝራዊነቱ ምድር በዳ ያደገ የብሉይ መደምደሚያ የሃዲስ ኪዳን መግቢያ የእውነት ምስክር ነብይ ሐዋ...
✝✝ የገነት መደብር ✝✝ ከእለታት በአንድ ቀን በሕይወት ጎዳና ስጓዝ #የገነት መደብር# የሚል ጽሑፍ የተለጠፈበት አንድ መሸጫ አይቼ ወደ እርሱ አቀናሁ ...
የንጉስ ጭካኔ ፥ ክንዱ ቢበረታ፤ ለጣዖት ሳንሰግድ፥ እኛ ሳንረታ፡፡ የምናምነው አምላክ፥ ሊያድነን ወደደ፤ ገብርኤል መጣና፥ እሳቱ በረደ፡፡ ፤ ፍላፃና ሠ...
👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴 🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ 🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ን...