MY SOROBAN ETHIOPIA - ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


ማይሶሮባን በተለያዩ ከተሞች 👇👇👇
A.A👉 @MySorobanAA
BDR👉 @MYSOROBANBDR
Derie👉 @DERIEMYSOROBAN
Sodo👉 @SODOMYSOROBAN
Adama👉 @AdamaMysoroban
Bishoftu👉 @BishoftuMySos
Gondar👉 @GondarMySos
Harer👉 @HarerMysoroban
D/Birhan👉 @DBmysoroban
Hawasa👉 @HawasaMySos

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


አስደሳች ዜና

የማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ሲስተም
ለምዝገባ ዝግጁ ሆነ።

ተወዳዳሪ ተማሪዎች በሲስተም ብቻ ይመዘገባሉ ።

ሲስተሙ ለተወዳዳሪዎች መታወቂያ ቁጥር ስለሚሰጥ ያለመታወቂያ ቁጥር መፈተን አይቻልም። የተፈተነ ተማሪ ካለም ውጤቱ አይያዝም።ሌላ ፈተናም አይፈተንም።


ነገ አርብ ጥቅምት 1/2017ዓ.ም

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የ2017ዓ.ም ስራዎቹን ይጀምራል።

የ2016ዓ.ም አሸናፊ ትምህርት ቤቶች ነፃ የአባከስ ስልጠና ለመምህራኖች ስለምንሰጥ
ስልክ እየደወላችሁ ተመዝገቡ።


ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ከSCHOOL OLYMPIDA ጋር በጋራ ሊሰራ ነው።


የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የውድድር አይነቶች

1. ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር
( የምርጫ እና አጭር መልስ)

2. በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጀመረው
1% የሒሳብ ትምህርት ውድድር ከውድድሩ መጀመሪያው እስከ መጨረሻው(ጥያቄዎቹ ሙሉ ለሙሉ አጭር መልስ መስጠት ነው።)

3. የአባከስ ውድድር


ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ስራ ሊጀምር ነው

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የ2017ዓ.ም ስራዎቹን
ጥቅምት 1/2017ዓ.ም ይጀምራል።


መልካም በዓል

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ መስከረም 25 እና 26/2017ዓ.ም ለሚከበረው የኢሬቻ
በዓል መልካም በዓልን ይመኛል።


የአባከስ ስልጠና

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የአባከስ ስልጠና እድሜያቸው ከ6 ዓመት እስከ 12 ዓመት ለሆኑ ተማሪዎች ከህዳር 1/2017ዓ.ም ጀምሮ በየከተማው በተመረጡ  ትምህርት ቤቶች መስጠት ሊጀምር ነው።

ስልጠናው የሚሰጠው ከመደበኛ የትምህርት ሰዓት ወጪ በየትምህርት ቤቶቹ ሲሆን የስልጠና ቁሳቁሶችን ጨምሮ በወር 200 ብር ነው።

ስልጠናው የሚሰጠው ከህዳር እስከ ግንቦት/2017ዓ.ም ለ 7 ወር ነው።

የአባከስ ስልጠናው በአጠቃላይ ለ7 ወር ለ50 ፔሬድ ነው የሚሰጠው ።

ሰኔ ፈተና ነው።

በፈተናው የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ውድድር
ላይ ለከፍተኛ ሽልማት ይወዳደራሉ።

የስልጠናው ክፍያ የሚከፈለው በአንዴ ነው።

መመዝገቢያ 150 ብር ነው።

"ጉብዝና ያሸልማል"


ሰበር ዜና

ዋው በጣም ይገርማል!

በኢትዮጵያ ብቸኛው ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ

የ2017ዓ.ም ፈተናዎችን በኦንላይን መፈተን

ሊጀምር ነው።

  "ጉብዝና ያሸልማል"


የስራ ማስታወቂያ

በመላው ሀገሪቱ ለምትገኙ

በ2017ዓ.ም ሀገር አቀፍ ውድድር ላይ የሚሳተፉ በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች ላይ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን የማስተባበር ልምድ እና ብቃት ያላችሁ በ0960114545 የፅሁፍ መልዕክት አስቀምጡልን።


ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ በ2017ዓ.ም 5 አይነት ውድድሮች ሲኖሩት ከነዚህ ውስጥ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጀመረው 1% የሒሳብ ትምህርት ውድድር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ቁጥር ከአንድ ከተማ 10 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

ውድድሩ ምን አይነት ይሆን?


የ2017ዓ.ም የውድድር እና የስልጠና ዓይነቶች

በኢትዮጵያ ብቸኛ በሆነው ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ በ2017ዓ.ም የሚከናወኑ የስልጠና እና የውድድር አይነቶች

1ኛ ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር

ውድድሩ የሚከናወነው
ከ3ተኛ እስከ 12 ክፍል

2ተኛ የአባከስ ስልጠና እና ውድድር
ስልጠናው እና ውድድሩ የሚከናወነው
ከ 1ክፍል እስከ 8 ተኛ ክፍል

3ተኛ የስሌት ስልጠና እና ውድድር
ከ3ተኛ እስከ 8ተኛ ክፍል

4ተኛ አንድ ደቂቃ የቴሌቪዥን ውድድር እና

5ተኛ 1% የሒሳብ ትምህርት ውድድር


ተማሪዎች ምንም አይነት ክፍያ የሚያከናውኑት
በባንክ ብቻ ሲሆን ክፍያ የሚከፍሉት በመታወቂያ ቁጥራቸው ብቻ ነው።

ማስታወሻ
የመታወቂያ ቁጥር የሚሰጣችሁ በማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ዌብ ሳይት ነው።


የ2017 ዓ.ም አጠቃላይ መረጃ
ለሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድሩ ብቻ

የምዝገባ ጊዜ
ከጥቅምት እስከ ታህሳስ 2017ዓ.ም

      የመመዝገቢያ ክፍያ 
በጥቅምት ወር ለሚመዘገቡ 115 ብር
በህዳር ወር ለሚመዘገቡ 125 ብር
በታህሳስ ወር ለሚመዘገቡ 150 ብር

1ኛ ዙር ፈተና የሚከናወንበት ቀን አንደየከተማው ይለያያል በታህሳስ ወይም በጥር ወሮች ይከናወናል። 

ለፈተና የሚከፈል ክፍያ በነፃ ነው።

ማስታወሻ
በማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የተዘጋጀ የመታወቂያ ቁጥር በእያንዳንዱን ፈተናዎች ለመፈተን አስፈላጊ ነው።

ያለ መታወቂያ ቁጥር የተፈተነ ተማሪ ውጤቱ አይያዝም
ሌላ ፈተናም አይፈተንም።

2ተኛ ዙር ፈተና በየካቲት ወር ይከናወናል
  የመመዝገቢያ ክፍያ 400 ብር

3ተኛ ዙር ፈተና በመጋቢት ወር ይከናወናል።
ለውድድሩ 450 ብር ይከፈላል።

4ተኛ ዙር ፈተና በሚያዚያ ወር ይከናወናል
 ለውድድሩ 450 ብር ይከፈላል።

5ተኛ ዙር ፈተና በግንቦት ወር ይከናወናል።
   ለውድድሩ 300 ብር ይከፈላል።

6ተኛ ዙር የ2017 ዓ.ም የመዝጊያ መርሃ ግብር
በወቅቱ የሚወሰን የመስተንግዶ ክፍያ ይከፈላል።
 ከሐሙስ ሐምሌ 24 እስከ እሁድ ሐምሌ 27/2017ዓ.ም

በውድድሩ ለሚያሸንፉ በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ይሸለማሉ።


ለ2016ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር ተማሪዎች የመጨረሻ መልዕክት

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የእያንዳንዳችሁን ውጤት ለየከተሞች እና ክ/ከተሞች ትምህርት ጽ/ቤቶች እስከ ጥቅምት 1/2017ዓ.ም ድረስ ይልካል።

ማስታወሻ

ውጤታችሁን አይታችሁ አሳማኝ ነገር ብቻ ካገኛችሁ ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ያሳውቃል።


እናመሰግናለን!

በሀገራችን የሚገኙ ትልልቅ ድርጅቶች የ2017ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድርን በመደገፍ በጋራ ለመስራት ፍቃደኝነታቸውን ገለፁ።

ቅዳሜ መስከረም 11/2017ዓ.ም የ2017ዓ.ም ውድድር እና ስልጠና አጠር ያለ ገለፃ እናቀርባለን።


ብቸኛው ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ በ2017ዓ.ም በሀገራችን
በሚገኙ 100 ከተሞች እና ክፍለ ከተሞች ላይ የአባከስ ስልጠና እና የሒሳብ ትምህርት ውድድር ለማከናወን ሙሉ ለሙሉ ዝግጅቱን አጠናቀቀ።

የተሟላ መረጃ መስከረም 10/2017ዓ.ም
እናሳውቃለን።




መልካም በዓል።

2017ዓ.ም በጉብዝናችሁ የምትሸለሙበት አመት ይሁንላችሁ።


እንኳን አደረሳችሁ።

የመጨረሻ የ2016ዓ.ም አሸናፉ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር በጋዜጣ እስከሚታተም
ድረስ ነገ በሚለቀቀው የመጨረሻ የ2016ዓ.ም አሸናፊ ተማሪዎች ስም ዝርዝር እና የገንዘብ መጠን ላይ ሙሉ ለሙሉ አሳማኝ ነገር ከተገኘ ማይ ሳሮባን ኢትዮጵያ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ያሳውቃል።

ከበደ አጥናፉ
ዋና ስራ አስኪያጅ።

አዲሱ አመት በጉብዝናችሁ የምትሸለሙበት ዓመት ይሁንላችሁ።



20 last posts shown.