MADO NEWS


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Your go-to source for the latest, most reliable news from Ethiopia and beyond! Get real-time updates, breaking stories, and insightful coverage from trusted sources. Stay ahead, stay informed, and never miss a beat! 📲
🔻ሼር በማድረግ እና ለወዳጆ በማጋራት ተባበሩን!

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


በአዳማ ከተማ በጥቁር ገበያ የነዳጅ ሽያጭ መስፋፋት ሳቢያ የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙና ዋጋው መጨመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21/ 2017 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ የጥቁር ገበያ የነዳጅ ሽያጭ በመስፋፋ ሳቢያ ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ እጥረት እያጋጠማቸው መሆኑን አሽከርካሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ በአዳማ ከተማ የሚኖሩ አንድ የከባድ መኪና አሽከርካሪ፤ በነዳጅ ማደያዎች ያለው የነዳጅ አቅርቦት በጣም ውስን መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ጠቁመዋል።

“በማደያዎች በየቀኑ ያለው የቤንዚን አቅርቦት በቂ ያልሆነ ወይም ሙሉ ለሙሉ የማይገኝ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ረጅም ወረፋ ለመጠበቅ ይገደዳሉ” ብለዋል።

አክለውም  ቤንዚን ለማግኘት እስከ ሶስት ቀን አልፎ ተርፎም አንድ ሳምንት ሊወስድ እንደሚችል ጠቅሰው “ነዳጅ ከማደያዎች ውጪ በጥቁር ገበያ በስፋት እየተሰራጨ ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሌላኛው በአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የባጃጅ አሽከርካሪ በበኩላቸው በከተማዋ ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ እጥረት መኖሩን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል።

“ከማደያ ነዳጅ ከቀዳሁ አንድ ሳምንት ሆኖኛል” ያሉት አሽከርካሪው አክለውም ቤንዚን ለመቅዳት ከሌሉት 9:00 እስከ ቀን 10:00 ድረስ ተሰልፎ ለመጠበቅ እንደሚገደዱ ተናግረዋል።

አክለው “ነዳጅ በጊዜ ለማግኘት አሽከርካሪዎች በማደያ ጣቢያው ተሽከርካሪዎቻቸውን ለማቆየት እና ለጥበቃ ተጨማሪ ክፍያ ለመክፈል ይገደዳሉ” ሲሉ ገልጸዋል።

አያይዘውም “አንድ ሰው ቤንዚን ሳይቀዳ አንድ ቀን ካለፈው ወይም አርፍዶ ከደረሰ ማደያው ይዘጋል እና ብቸኛው አማራጭ ነዳጅ ከጥቁር ገበያ መግዛት ነው” ሲሉ አክለዋል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም አንዳንድ ማደያዎች ለሁለትና ለሶስት ቀናት በቂ የሆነ ቤንዚን ያቀርቡ የነበረ ቢሆንም ይህ አሰራር አሁን ላይ መቆሙን አስረድተዋል።

አሁን ላይ ቤንዚን በጥቁር ገበያ ነዳጅ በሁለት ሊትር ከ280 እስከ 300 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት “አሽከርካሪዎች በትራንስፖርት ታሪፍ ላይ በእጥፍ ጭማሪ አድርገው እየጫኑ ይገኛሉ” ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ገሾ በሀገሪቷ በቂ የነዳጅ አቅርቦት ቢኖርም በህገ ወጥ መንገድ ላልተፈቀደለት ዓላማ በመዋሉ አልፎ አልፎ እጥረት አንዲከሰት ምክንያት መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።

በህገ ወጥ የነዳጅ ግብይት በተሰማሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል። በተደረገ የቁጥጥርና ክትትል ሥራም በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት አምስት ወራት ከ226 ሺህ ሊትር በላይ ህገ ወጥ ነዳጅ እና የነዳጅ ውጤቶች ተይዘው ወደ 13 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በህገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ላይ የተሰማሩ 44 ሰዎች ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰዱንና እስከ ሰባት ዓመት እስራት የተቀጡ መኖራቸውንም አመላክተዋል።

ከዚህ በፊት በአማራ ክልል ያሉ አሽከርካሪዎች በተከሰተው ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እና በዋጋ ንረት ምክንያት መቸገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

እንዲሁም በሲዳማ ክልል ርዕሰ ከተማ በሆነችው ሀዋሳ የቤንዚን እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እየተባባሰ እንደሚገኝ እና ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆናቸውን ለዚህም ዋነኛ መንስኤው በከተማዋ ተስፋፍቶ የሚገኘው የነዳጅ ጥቁር ገበያ ሽያጭ መሆኑንም አሽከርካሪዎቹ ለአዲስ ስታንዳርድ መግለጻቸው ይታወሳል።

ጉዳዩን በተመለከተ በወቅቱ ከኢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሲዳማ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ሃላፊ ቡርቃ ቡጡላ በበኩላቸው ችግሩ ማጋጠሙን አምነው የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ከሚመለከተው የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የሚቀርበውን ነዳጅም በአግባቡ እንዲሰራጭ አሽከርካሪዎች ፕሮግራም ወጥቶላቸው እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። አስ

The post በአዳማ ከተማ በጥቁር ገበያ የነዳጅ ሽያጭ መስፋፋት ሳቢያ የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙና ዋጋው መጨመሩ ተገለጸ appeared first on Addis standard.

via Addis standard (author: Biruk)


ታህሳስ 21፣2017 - 70 የሚደርሱ የሀገር ውስጥ አምራቾች የተሳተፉበት ኤግዚቢሽን ዛሬ ተከፈተ

70 የሚደርሱ የሀገር ውስጥ አምራቾች የተሳተፉበትና ከታህሳስ 18 እስከ 27፣2017 ዓ.ም የሚቆይ ኤግዚቢሽን ዛሬ ተከፈተ፡፡

የኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች ምርቶቻቸውን ይዘው የቀረቡት ካሳለፍነው ዓርብ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ቢሆንም፤ መክፈቻው ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 21 ቀን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ፍል ውሃ አካባቢ በሚገኘው አዲስ አውትሌት ሴንተር ተከናውኗል፡፡

’’የእኛ ምርት ለእኛ’’ በሚል መሪ ቃል በተሰናዳው ኤግዚቢሽን ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የተጋበዙ በጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳ ውጤቶች፣ በምግብና መጠጥ ማቀነባበር፣ በኬሚካል፣ በእንጨትና ብረታብረት ውጤቶች ምርት ላይ የተሰማሩ አምራቾች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ያገኘናቸው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና የገበያ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚው አቶ ስዩም ሁጅራ ተቋማቸው የኤግዚቢሽኑ 70 በመቶ ወጪ በመሸፈን የአምራቾቹን ገበያ ለማስፋት እንደተሰናዳ ነግረውናል፡፡

በሀገር ውስጥ የተሰሩ ምርቶች ብቻ የቀረቡበት ኤግዚቢሽኑ እስከ ገና በዓል ዋዜማ ታህሳስ 27 ቀን 2017ዓ.ም እንደሚቆይ ሰምተናል፡፡

ምንታምር ፀጋው

via Sheger 102.1FM (author: sheger1021fm)


የአዘርባጃኑ ፕሬዝደንት የተከሰከሰው አውሮፕላን ከሩሲያ ተተኩሶበት እንደነበር ተናገሩ

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ክሬሚሊን "ዘግናኝ አደጋ" ሲል ለገለጸው የአውሮፕላን አደጋ የአዘርባጃኑን ፕሬዝደንት አሊየቭን ይቅርታ ጠይቀዋል

via جديد አል ዐይን ኒውስ


በአዋሽ ፈንታሌ እየተከሰተ ባለዉ ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ሳብያ ከ2,500 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉ ተነገረ

ትናንት ምሽት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

በአፋር ክልል በአዋሽ ፈንታሌ አከባቢ በሚከሰት ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ከ100 በላይ ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን፤ 2 ሺሕ 560 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና እንሰሳት መሞታቸውን የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አስተዳደር አቶ አደም ባሂ ተናግረዋል።

አስተዳደሩ አክለውም ይህ ክስተት በሚድያ እንደሚባለዉ በቀን ሦስቴ እና ሁለቴ የሚከሰት ሳይሆን ከዚያም በላይ አስጊ እየሆነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በአካባቢዉ ያለዉ ተፈናቃይ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን ያነሱት አቶ አደም፤ መጠለያ፣ ምግብ እና መሰረታዊ ግብአቶች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል። የክልሉ የአደጋ ስጋት ድጋፍ እንዲያደርግም እንደጠየቁ ገልጸዋል።
(አዩ)


የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ፣ ኢትዮጵያና ሱማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት የደረሱበትን የባሕር በር ስምምነት አገራቸው በቅርበት እየተከታተለች መኾኗን መናገራቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

አል ሲሲ፣ ስምምነቱ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ሊረዳ ይችላል ብላ ግብጽ ተስፋ እንደምታደርግ ገልጸዋል ተብሏል።

ሲሲ ይህን የተናገሩት፣ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ በተወያዩበት ወቅት እንደኾነ ተገልጧል።

ግብጽ በኹለትዮሽ ትብብርም ይኹን በአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በመሳተፍ፣ በሱማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ድጋፍ እንደምትሰጥ አል ሲሲ ማረጋገጣቸውንም ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።


የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሠኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 በኦንላይን እየተሠጠ ነው-ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

AMN – ታኀሣሥ 21/2017 ዓ.ም

የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሠኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 በኦንላይን እየተሠጠ መሆኑን ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ወቅቱ የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት የመጨረሻ ቀናቶች ላይ የሚገኝ በመሆኑ የንግዱን ማህበረሰብ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሲባል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዲሁም የተወሠኑ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከሠኞ- ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 የኦንላይን የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ እንደሚገኙ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል፡፡

በመሆኑም የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት በበጀት ዓመቱ ከሀምሌ 1/2016 እስከ ታህሳስ 30/ 2017 ዓ.ም ድረስ ያለቅጣት የሚታደስ መሆኑን ያስታወሰው ሚኒስቴሩ ከሠኞ እስከ ቅዳሜ እስከ ምሽቱ 2፡30 በሚሰጠው የኦንላይን አገልግሎት የንግዱ ማህበረሰብ አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት የንግድ ስራ ፈቃዱን አስቀድሞ እንዲያድስ አሳስቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review

Submit Review
The post የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሠኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 በኦንላይን እየተሠጠ ነው-ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር appeared first on አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ.

via አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (author: AmnAdmin)
የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሠኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 በኦንላይን እየተሠጠ ነው-ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር - አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ
AMN – ታኀሣሥ 21/2017 ዓ.ም የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሠኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 በኦንላይን እየተሠጠ መሆኑን ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ወቅቱ የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት የመጨረሻ ቀናቶች ላይ የሚገኝ በመሆኑ የንግዱን ማህበረሰብ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሲባል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዲሁም የተወሠኑ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከሠኞ- ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 […]


በሃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እርጅና ምክንያት በተለያዩ ከተሞች እያጋጠመ ያለዉን የሃይል መቆራረጥ ለማስተካከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች 96 በመቶ ደርሰዋል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስድስት ከተሞች የኃይል ማሰራጫ መስመር የመልሶ ግንባታ እና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም 96 በመቶ ደርሷል ብሏል፡፡

በመልሶ ግንባታ ፕሮጀክቱ የተካተቱት ስድስቱ ከተሞች በምዕራፍ አንድ ወላይታ ሶዶ እና ሐረር፣ በምዕራፍ ሁለት ሻሸመኔ እና ደብረማርቆስ፣ በምዕራፍ ሶስት ጎንደር እና ኮምቦልቻ ናቸው፡፡

በእነዚህ ከተሞች በእርጅና ምክንያት በኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ መስመሮች እያጋጠመ ያለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ ነዉ ተብሏል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና አላማ በእነዚህ ከተሞች ያለውን የመካከለኛ እና ዝቅተኛ የኃይል ማሰራጫ መስመሮች አቅም በማሳደግ፤ በከተሞቹና በዙሪያቸው ያለውን የኃይል አቅርቦት አስተማማኝ ለማድረግ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በቀጣይ አዲስ ኃይል የሚጠይቁ ደንበኞችን ለማስተናገድም እንዲያስችል ነው ተብሏል፡፡

በፕሮጀክቱ እስከ አሁን በተከናወነ ስራ 6መቶ4.8 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣4መቶ1.51 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ተካሂዷል፡፡

በተጨማሪም 1መቶ23 ነባር የዲስትሪብዩሽን ትራንስፎርመር ማሻሻያ ስራ፣ 1መቶ34 አዳዲስ የዲስትሪብዩሽን ትራንስፎርመሮች ተከላና 28 ሺህ 2መቶ23 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራዎች መከናወናቸዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በሻሸመኔ፣ ወላይታ ሶዶ እና ሀረር ከተሞች የኮሚሽኒንግ ስራ ተጠናቆ ርክክብ እየተከናወነ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ በሁለት የቻይና እና በአንድ የህንድ ኩባንያዎች አማካኝነት እየተከናወነ ሲሆን፤ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ግንባታም በዚህ በጀት ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

እስከዳር ግርማ

ታኀሣሥ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

via Ethio FM 107.8 (author: Ethio Admin)


ከ499 ሺህ በላይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል

እስካሁን 499 ሺህ 200 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በአገልግሎቱ የተፈታኞች ምዝገባ፣የፈተና ዕርማትና ውጤት ጥንቅር ዴስክ ሀላፊ ማዕረፉ ሌሬቦ÷በ2017 የትምህርት ዘመን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በመደበኛና በግል 750 ሺህ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የመደበኛ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን ከታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ሲሆን÷ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ሃላፊው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

የኢንተርኔት አማራጭ በሌለባቸው አካባቢዎች ተማሪዎች ከኢንተርኔት ውጭ ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሰራበት አካባቢ ሄደው መረጃቸውን ወደ ኦንላይን መጫን እንደሚችሉ ተናግረዋል።

በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በመግለጽ እስካሁን ድረስም 82 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች ለፈተናው ምዝገባ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረው እስካሁን ድረስ 1 ሺህ 100 ተማሪዎች መመዝገባቸውን አመላክተዋል።

ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎች እንደማይስተናገዱ እና ፈተና ላይ እንደማይቀመጡ ተጠቁሟል፡፡ #FBC


ሩሲያ ከፍተኛ ባለስልጣንን እና የጦርነት ጸኃፊን ለመግደል የተወጠነውን ሴራ ማክሸፏን አስታወቀች

ኤፍኤስቢ እንደገለጸው ከ 1 1/2 ኪሎግራም ከሚመዝን ቲኤንቲ ጋር የሚመጣጠነው ቦምቡ በተንቀሳቃሽ የሙዚቃ ድምጽ ማጉያ ውስጥ ተጠምዶ ነበር

via جديد አል ዐይን ኒውስ


በሲዳማ ክልል ሰርገኞችን ባሳፈረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር 74 ደረሰ

በትላንትናው እለት በሲዳማ ክልል፣ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ልዩ ስሙ ጋላና ድልድይ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ሰርገኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና በመገልበጡ  የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ብስራት አስቀድሞ መዘገቡ ይታወሳል።

በደረሰው የትራፊክ አደጋ 68 ወንዶች እና 3 ሴቶችን ጨምሮ የ71 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ
ሶስት ሰዎች ከአደጋው የተረፉ ሲሆን ሶስቱም ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከል እና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  ዋና ኢንስፔክተር  ዳንኤል ሳንኮር ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ተሽከርካሪው ገላና ድልድይ ላይ ሲደርስ  ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ ነው አደጋው የደረሰው ሲሆን  ከአንድ ቤተሰብ እስከ 4 ሰዉ መሞታቸው ተገልጿል። ብስራት ዘግየት ብሎ በደረሰው መረጃ የሟቾች ቁጥር 74 ደርሷል።

በተደጋጋሚ በአካባቢው አደጋ እንደሚከሰት እና የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ዳንኤል ሳንኮር ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም


የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው አረፉ

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ካርተር ከፕሬዚደንትነታቸው በፊት  በለውዝ ግብርና ስራ እንዲሁም በጆርጂያ ግዛት አስተዳዳሪነት ሀገራቸውን አገልግለዋል።   ካርተር በአውሮፓዊያኑ አቆጣጣር ፣ ጥር 20 ቀን 1977 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ሆነው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ "እንደ ሀገሪቱ ህዝብ ሁሉ  መልካም መንግስት" እንደሚመሰርቱ  ቃል ገብተው ነበር።  አራት ዓመት የስልጣን ዘመናቸው ግን ርጋታ የራቀው ነበር።ያሻቀበ የዋጋ ንረት እና የስራ አጥነት ቁጥር መጨመር አስተዳደራቸው ቅድሚያ ሊሰጣቸው ያቀዳቸውን ጉዳዮች  አስተጓጉሏል። በግብፅ እና በእስራኤል መካከል  የሰላም ስምምነት እንዲደረስ በማድረግ እና የፓናማ ካናል ስምምነትን እውን በማድረግ  በውጭ ፖሊሲ መስክ ድሎችን አስመዝግበዋል። ኢራን ውስጥ...

via የአሜሪካ ድምፅ


እሁድ ሌሊት ከደብረ ሲና 52 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

👉 በቅርብ ቀናት ከተከሰቱት ርዕደ መሬቶች በመጠኑ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል

እሁድ ታህሳስ 20 ቀን 2017ዓ.ም ሌሊት 7:20 ላይ የተከሰተው ይህ ርዕደ መሬት 5.1 ሆኖ በሬክተር ስኬል እንደተመዘገበ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታውቋል፣ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ንዝረቱ እንደተሰማቸው እየጠቆሙ ይገኛሉ።

ይህ በቅርብ ቀናት ውስጥ በአብዛኛው አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ከተከሰቱት ርዕደ መሬቶች በመጠኑ ከፍተኛው እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ የተጠጋ ሆኖ ተመዝግቧል።

የሰሞኑን ተደጋጋሚ ክስተት ተከትሎ በርካታ የጥንቃቄ መልእክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ።

Meseret Media


በትግራይ ክልል የምርመራ ዘገባ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ከሰዓታት እስር በኃላ ተፈቱ

በትግራይ ክልል ፣የመንግስታዊው ትግራይ ቴሌቭዥን  ጋዜጠኞች  ቡድን አባላት ከሰዓታት "እስር " በኃላ በዛሬው ዕለት መለቀቃቸው ተሰምቷል። የክልሉ መንግስት ንብረት የሆነው ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች ቡድን አባላት ፣ ለእስር በተዳረጉበት ወቅት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ የምርመራ ዘገባ እየሰሩ እንደነበር ታውቋል። ቴሌቭዥን ጣቢያው ጋዜጠኞቹ በአስገደ ወረዳ ፣ በሚይሊ ቀበሌ ተገኝተው ለወርቅ ማዕድን ማውጣት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ኬሚካሎች  የፈጠሩትን ጉዳት በተመለከተ ምርመራ እያደረጉ እንደነበረ አረጋግጧል። ለደህንነት ሲባል ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የጣቢያው የቅርብ ምንጮች ለቪኦኤ እንደገለፁት አንድ ጋዜጠኛ፣ አንድ የካሜራ ባለሙያ እና ሾፌራቸው ለእስር ተዳርገዋል። ቆየት ብሎ ከቴሌቭዥን ጣቢያው የወጣው መግለጫ...

via የአሜሪካ ድምፅ


በአዋሽ አካባቢ ዛሬ ምሽት በሬክተር ስኬል 5.0 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

🔴በዛሬው ዕለት ብቻ ሰባት የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል

በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ከሰሞኑ ከደረሱት የመሬት መንቀጥቀጥ ክሰተቶች በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ ርዕደ መሬት ዛሬ እሁድ ምሽት መከሰቱን የጀርመን የጂኦሳይንስ የምርምር ማዕከል አስታወቀ።

በአካባቢው ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ10 ላይ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በሬክተር ስኬል 5.0 የደረሰ እንደሆነ የማዕከሉ መረጃ አመልክቷል።

በሬክተር ስኬል የመለኪያ መሳሪያ ከ2.5 እስከ 5.4 መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጦች አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደሆኑ በዘርፉ ምርምር የሚያደርጉ ተቋማት ይገልጻሉ።

በዚህ መጠን የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች ንዝረታቸው በበርካታ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባሉ ከተሞች ጭምር የሚሰማ እንደሆነም የተቋማቱ መረጃ ያሳያል። የምሽቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ጭምር ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየ ንዝረት አስከትሏል።

ከአዋሽ ከተማ 14 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ ስፍራ የተከሰተው የምሽቱ ርዕደ መሬት፤ በዛሬው ዕለት ብቻ በአካባቢው የተመዘገቡ መሬት መንቀጥቀጦችን ቁጥር ሰባት አድርሶታል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)


ዛሬ 20/04/2017 ዓ.ም በሲዳማ ክልል በቦና ዙሪያ ወረዳ በጋላና ወንዝ ድልድይ ላይ በደረሰው  አደጋ ከ60+ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

አደጋ የተከሰተው አንድ አይሱዙ መኪና ከ60+ የሠርግ አጃቢዎች አሳፍሮ ወደ ዳዬ በንሳ መሥመር እየተጓዘ እያለ በጋላና ድልድይ ተምዘግዝጎ ወደ ወንዙ በመግባቱ እንደሆነ የዓይን እማኞች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

በጋላና ድልድይ ተመሳሳይ የትራፊክ አደጋ ሲደርስ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ይህ እጅግ የከፋ አደጋ ነው ብለዋል።
የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እንደሚችል ምንጮች ገልፀዋል።

ነፍስ ይማር፣መፅናናትን ይስጥልን።

(Ayu)


የኤር ካናዳ አውሮፕላን ለማረፍ ሲሞክር በእሳት መያያዙ ተነገረ

ታሕሣሥ 20/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ንብረትነቱ የኤር ካናዳ የሆነ አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር አጋጥሞት ለማረፍ ሲሞክር በእሳት ተያይዞ እንደነበር ተገለጸ። የበረራ ቁጥር 2259 የሆነ ይህ አውሮፕላን ትናንት ማታ በሃሊፋክስ ስታንፊልድ ዓለም…

The post የኤር ካናዳ አውሮፕላን ለማረፍ ሲሞክር በእሳት መያያዙ ተነገረ appeared first on .

via https://waltainfo.com/am/feed/ (author: yenework mekonnen)


የሱማሌያው ኘሬዝዳን ከጂቡቲ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የኢትዮጵያን አየር ክልል ላለመጠቀም ወይም ለመሸሽ በሶማሌ ላንድ በኩል በማለፍቸው ሶማሌ ላንድ የአየር ክልሌ ተጥሷል በማለት ከሳለች ።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የሶማሌላንድን ሉዓላዊ የአየር ክልል ያለፈቃድ ጥሰው በመግባት ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና የሶማሊላንድን የግዛት መብቶች በመጣስ እየተከሰሱ ነው።

ፎከር 70 5Y-KBX በሚል ስም የተመዘገበ እና በኬንያ አየር መንገድ ስካይዋርድ ኤክስፕረስ የሚተዳደረው አውሮፕላኑ ከሶስት ሰአት በፊት የሶማሌላንድን የአየር ክልል አልፎ ወደ ሞቃዲሾ ሲመለስ የኢትዮጵያን ግዛት በመሸሽ ነው።

ሶማሊያላንዳዊያን>እያሉ ነው።


ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ታሕሣሥ 20/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ። ተጠርጣሪዎቹ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ሀና ማርያም…

The post ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ appeared first on .

via https://waltainfo.com/am/feed/ (author: yenework mekonnen)


በእንግሊዝ ታራሚዎች ከእስር ቤት እየወጡ ስራ ሰርተው እንዲመለሱ እንዲፈቀድላቸው ሀሳብ ቀረበ

እንግሊዝ በአውሮፓ ከፍተኛ የእስር ቤቶች መጨናነቅ ከሚታይባቸው ሀገራት ተርታ ትመደባለች

via جديد አል ዐይን ኒውስ


ትግራይ ቲቪ ጋዜጠኞቹ መታገታቸው አስታወቀ

ጣብያው በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ከህገወጥ የወርቅ ማውጣት ሂደት ጋር በተያያዘ መረጃ በማሰባሰብ ላይ የነበሩ ጋዜጤኞቹ  በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸው ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ያለውን ህገወጠ የወርቅ ማዕድን የማውጣት ሂደትና የጎንዮሽ ጉዳቶቹ ምን ይመስላሉ የሚለውን ለመታዘብ ብሎም ዘገባ ለመስራት ወደ ስፍራው ያቀናው የጋዜጠኞች ቡዱን በታጣቂዎች እግታ እንደተፈፀመበት ትግራይ ቴሌቭዥን ገልፆል።

ሶስት ሞያተኞች የያዘው የጋዜጠኞች ቡዱኑ ዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ/ም ጥዋት 3 ሰዓት በአስገደ ወረዳ፣ መይሊ ከተባለው ስፍራ ወጣ ብሎ በሚገኘውን መንደር በታጣቂዎች ስለመያዛቸው ዳጉ ጆርናል ቴሌቪዥን ጣብያው ባጋራው መረጃ ላይ ተመልክቷል።

ጋዜጠኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት በቦታው በመገኘነት ስላለው ነገር ከአከባቢው ነዋሪዎች መረጃዎችን ሲያሰባስቡ ቆይተዋልም የተባለ ሲሆን በተለይም በመይሊ አከባቢ መዓድናቱን ለማውጣት በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙ የተለያዩ ጎጂ ኬሚካሎች እያደረሱት ያለውን ጉዳት በተመለከተ መረጃዎች እየሰበሰቡ ነበርም የተባለ ቢሆንም በመሀል ግን በታጣቂዎቹ ስራቸውን እንዲያቋርጡ ብሎም ሊታገቱ መቻላቸው ጣብያው አስታውቋል።

ጣብያው አክሎም የጋዜጠኞቹን ደህንነት ለማረጋገጥና ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የገለፀ ሲሆን ነገር ግን ከረፋድ 4 ሰዓት በኃላ የጋዜጠኞቹ ስልክ ዝግ በመሆኑ ምክንያት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘተ አለመቻሉ ገልፆል።

በሚሊዮን ሙሴ

20 last posts shown.

1 324

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋን ወደ ቻይና ለመላክ አቅዳለች ተባለ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያሏትን ውስን የስጋ ምርት ተቀባይ ሀገራትን ቁጥር ለመጨመር እና ከዘ...
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከሰው በበለጠ የማሰብ ችሎታን ይጎናጸፋል – ኤለን መስክ ታሕሣሥ 14/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመጪው ዓመት መጨረሻ አርቲፊሻል ኢ...
በፈንታሌ ተራራ ፍንዳታና ጭስ የታየበት በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ  የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6...
ወላድ እናት አሳፍሮ ወደ አዲስ አባባ ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ከሌላ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞ...
የአየር ሁኔታን ለመመልከት የሚያግዙ ሦስት የራዳር ጣቢያዎች ዘንድሮ ወደ ሥራ ይገባሉ-የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት via አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (a...