ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter








#_የአገልግሎት_ቅድመ_ዝግጅት!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች፣ እሑድ ታህሳስ 13 ጠዋት በአያት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ለሚኖረን አገልግሎት፣ ዛሬ ሐሙስ ታህሳስ 10 ከመልአከ መንክራት ከመምህር ግርማ ወንድሙ ጋር በአያት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ተገናኝተን፣ ስለ አገልግሎቱ ተመካክረን ጥሩ የበረከት ጊዜ አሳልፈናል!

አምላከ ቅዱስ ዮሐንስ እሑድ ታህሳስ 13 በተቀደሰው ሥፍራ ለበረከት ለፈውስ በደጁ ያገናኘን!

ታህሳስ 10 አዲስ አበባ!




#_የትምህርተ_ወንጌል_እና_የጸበል_አገልግሎት!

#_እሑድ_ታህሳስ_13_ጠዋት_2_ሰዓት

በመልአከ መንክራት በመምህር ግርማ ወንድሙ እና በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም!

ሼር በማድረግ መልእክቱን ለሌሎች አዳርሱ!

❤ #_የትራንስፖርት_መምጫው ፦

#_ከመገናኛ አያት መጥተው ከአያት በቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍረው አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ወርደው በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ይወርዳሉ

#_ከቦሌ አያት መጥተው ከዛ የቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍረው ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ወርደው በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ይወርዳሉ

#_ከቃሊቲ፣ ከቱሉ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጬ የምትመጡ አያት ወርዳችሁ ከአያት የቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍራችሁ አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ዳር ወርዳችሁ በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትወርዳላችሁ

#_ከለገ_ጣፎ አያት መጥታችሁ፣ ከአያት የቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍራችሁ አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ወርዳችሁ በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትወርዳላችሁ

ከጎሮ አያት መጥታችሁ ከአያት አያት አምስት ሳንሻይን አፓርታማ ጋር ወርዳችሁ በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትወርዳላችሁ

#_በግል_መኪና የምትመጡ ከየትኛውም አቅጣጫ አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ደርሳችሁ በመግቢያው ታጥፋችሁ ቀጥታ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትደርሳላችሁ።






ታህሳስ 6 በእለተ ሰንበት በአያት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የነበረን አገልግሎት ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል።

ስለ ሁሉም ነገር የድንግል ማርያም ልጅ አምላከ ቅዱስ ዮሐንስ ኃያሉ መድኃኔ ዓለም ክብር ምስጋና ይድረሰው! አገልግሎቱ ይቀጥላል ...




❤ #_የንስሐ_እና_የቄደር_ጥምቀት_ጥሪ!

❤ #_እሑድ_ታህሳስ_6_ጠዋት_2_ሰዓት

❤ #_ወደ_አገልግሎት_ተመልሻለሁ!

❤ #_አድራሻ :-_አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ገባ ብሎ በእመቤታችን_እና በመጥምቁ ዮሐንስ ቤተ_ክርስቲያን!

"ጥሩ ውኃንም እረጭባችኃለሁ እናንተም ትጠራላችሁ" ሕዝቅ 36፥25

"የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም"

❤ #_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው?

❤ #_ቄደር_ለምን_እንጠመቃለን?

❤ #_ቄደር_በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን?

#_የነፍስ_ጉዳይ_ነውና_ሳትቸኩሉ_በደንብ_አንብቡት!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_ሼር_በማድረግ_የነፍስ_ግዴታዎትን_ይወጡ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች በአሜሪካ የነበረኝ አገልግሎት አጠናቅቄ ወደ ሀገሬ ከተመለስኩ በኋላ ትንሽ እረፍት ላይ ነበርኩ። በእርግጥ እረፍት ባይባልም በነበረኝ ጊዜ መጽሐፍ እየጻፍኩ ነበር። አሁን ግን ወደ ቀደመ አገልግሎት ተመልሻለሁ!

❤ ከዚህ በኋላ እንደተለመደው በቋሚነት በአያት ዮሐንስ እና በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ከእሑድ ጀምሮ በሳምንት ሦስት ቀን አገልግሎት ይኖረናል።

❤ እሑድ እሑድ የንስሐ እና የቄደር ጥምቀት እንዲሁም የመደበኛው የጥምቀት አገልግሎት ይኖረናል። አርብ እና ረቡዕ ደግሞ የጥምቀት እና የቅብዓ ቅዱስ አገልግሎት ይኖረናል።

❤ ወዳጆቼ እሑድ ታህሳስ 6 ጠዋት 2 ሰዓት በአያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ገባ ብሎ ባለው በእመቤታችን እና በመጥምቁ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ንስሐ የመስጠት እና የቄደር ጥምቀት እንዲሁም የመደበኛ የጥምቀት አገልግሎት ስላለ መጥታችሁ ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ።

የጸሎት መርሃ ግብሩ ካለቀ በኃላ ብትጠመቁ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ለምሳሌ የጸሎቱ መርሃ ግብር ላይ አቡነ ዘበሰማያት 41 ጊዜ ካርያላይሶን 41 ጊዜ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ ወዘተ እንድትጸልዩ ስለሚሰጣችሁ እነዚህን ጸሎቶች ሳትካፈሉ ሰዓት አርፍዳችሁ ብትመጡ መጠመቅ አይቻልም። ስለዚህ የነፍስ ጉዳይ ነውና ሰዓት ይከበር።

❤ #_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው?

ቀደር ለመጠመቅ የሚያበቁን ኃጢአቶች ለምሳሌ ረቡዕ ብና አርብ የፍስክ ከበላን፣ ውርጃ ከፈጸምን፣ ከሃይማኖታችን ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ከፈጸምን፣ በልጅነት እና ካደግን በኃላ ግብረ ሰዶም ከፈጸምን፣ ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ካደረግን፣ በልጅነት መሬትን ካወሰብን፣

ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ከፈጸምን፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን በዝሙት ከወደቅን፣ በቅዱስ ቁርባን አግብተን ባል በሚስት ላይ ሚስት በባል ላይ ከዘሞተች፣ ኢ- ሩካቤ ከፈጸምን ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ከፈጸምን፣ የአሕዛብን ምግብ ከበላን፣ ኦርቶዶክስ ሆነን ወደ ሌላ እምነት ገብተን ከተመለስን፣

ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ከገበርን፣ የተገበረውን መስዋዕት ከበላን፣ ጠንቋይ ቤት ከሄድን፣ ዛር አንጋሽ ጋር ከሄድን፣ ግለ ወሲብን ከፈጸምን፣ ሴት የወር አበባዋን ሳትጨርስ ግንኙነት ካደረገች፣ ወንድም የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት ካደረገ፣ ጫት ሲጋራ ከተጠቀምን ወዘተ ቄደር የግድ መጠመቅ አለብን።

ወዳጆቼ ልብስ በሳሙና ይታጠባል በመጨረሻ በኦሞ ተዘፍዝፎ ይለቀለቃል። በዚህም ጸዐዳ ይመስላል። ንስሐ ኃጢአታችንን የምናጥብበት ሳሙና ነው። ቄደር ደግሞ ኦሞ ነው ያነጻናል።

በተለይ ንስሐ ገብታችሁ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያሰባችሁ ቄደር ተጠምቃችሁ ብትቀበሉ መልካም ነው። በንስሐ ያላካተትነው ኃጢአት በቄደር ይነጻልና። እንዲሁም በቄደር ነጽተን ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል ይሰምርልናል።

ሌላው ንስሐ ለመግባት አስባችሁ የንስሐ እድሉን ያላገኛችሁ እና ንስሐ አባት የሌላችሁ እሑድ ታህሳስ 6 ጠዋት 2 ሰዓት መጥታች በደብሩ ካህናት ንስሐ መግባት ትችላላችሁ።

የእናንተን ችግር የሚረዱ በተለይ ለካህናት መናገር የምትጨነቁበትንና የምታፍሩበትን ለምሳሌ ግለ ወሲብንና የወሲብ ፊልምን የተመለከቱ ወዘተ ዘመን አመጣሽ ኃጢአትን የሚረዱ ካህናትን ስላዘጋጀን መጥታችሁ በነፃ ንስሐ ግቡ፣ የኃጢአት ሸክምን በእናታችሁ ቤት አራግፉ።

የወለላይቱ እመቤት ልጆች የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም።

የእኛ ኃጢአት የደም ጠብታ ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ደግሞ ውቅያኖስ ነው። ስለዚህ የደም ጠብታ የውቅያኖስን ውሃ እንደማያደፈርስ ሁሉ የትኛውም የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቸርነት አይበልጥም። ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ።

ስለዚህ እሑድ ታህሳስ 6 ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት በአያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ገባ ብሎ የሚገኘው በእመቤታችን እና በመጥምቁ ዮሐንሰሰ ቤተ ክርስትያን ኑ። ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይጀመራል መጥታችሁ ተጠመቁ።

❤ #_የትራንስፖርት_መምጫው ፦

#_ከመገናኛ አያት መጥተው ከአያት በቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍረው አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ወርደው በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ይወርዳሉ

#_ከቦሌ አያት መጥተው ከዛ የቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍረው ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ወርደው በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ይወርዳሉ

#_ከቃሊቲ፣ ከቱሉ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጬ የምትመጡ አያት ወርዳችሁ ከአያት የቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍራችሁ አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ዳር ወርዳችሁ በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትወርዳላችሁ

#_ከለገ_ጣፎ አያት መጥታችሁ፣ ከአያት የቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍራችሁ አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ወርዳችሁ በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትወርዳላችሁ

ከጎሮ አያት መጥታችሁ ከአያት አያት አምስት ሳንሻይን አፓርታማ ጋር ወርዳችሁ በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትወርዳላችሁ

#_በግል_መኪና የምትመጡ ከየትኛውም አቅጣጫ አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ደርሳችሁ በመግቢያው ታጥፋችሁ ቀጥታ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትደርሳላችሁ

ታህሳስ 3-4-17 ዓ.ም
አዲስ አበባ







14 last posts shown.