ስኬትን የፈለገ የሰለፎችን መንገድ ይከተል


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ዐዋቂዎች አይደለንም አህሉል ቢድዓ ግን አይሸውደንም፡፡
[]~ ሰለፍያ~[]
የልባሞች እምነት የጀግኖች ጎዳና
መመሪያሽ ቁርአን የነቢዩ ሡና
በሀቅ የተካብሽው መጠለያ ቤቴ
ከጥመት መሸሻ ብርሀነ-ንጋቴ
ሁሌም የበላይ ነሽ ኢስላሜ ድምቀቴ
መንሀጀ-ሠለፍ ወሠጢያ እምነቴ!!
https://t.me/Menhaj_Asselefiya

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️📡
የመጀመሪያው ፕሮግራም
📣  ተጀመረ 🔈
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•

🎤
📚
      ተ
⭐️
             ጀ
⭐️
                  መ
⭐️
                          ረ
⭐️

ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም!
ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት‼

 ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘
https://t.me/tdarna_islam?livestream
https://t.me/tdarna_islam?livestream


ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት

ክፍል 14 የተውሂድ ጉዳይ አብይ የመወያያ ርዕስና የልዩነት መሠረት ነበር


ሙሽሪኮች የአላህን (ሱ.ወ)አንድነት ይቀበሉ ነበር። በዛት (በአካሉ)፣በሲፋቱ (በባህሪያቱ)እና በድርጊቶቹ አንድነቱን ይቀበሉ ነበር።አላሁ ተዓላ ፈጣሪ መሆኑን ሰማያትንና ምድርን፣በመካከላቸውም ያለውን ነገርና ሁሉንም ነገር የፈጠረ መሆኑን ያውቁና ይቀበሉት ነበር።የሁሉም ነገር ባለቤት መሆኑን፣የሰማያትና የምድር እንድሁም በመካከላቸው ያለውን ነገርም ሆነ የሁሉም ነገር ሥልጣን በእጁ መሆኑን፣ሰውን፣እንስሳትንና ሌሎች ሕይወት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ የሚረዝቅ ፣ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር የሚያዘጋጅ፣የትንሹንም ሆነ የትልቁን ነገር የብናኙንም ሆነ የጉንዳኑን ጉዳይ ሁሉ የሚያስተናብር፣ የሰማያትና የምድር፣ በመሀከላቸውም ያለው ነገር፣ የታላቁ አርሽና የሁሉም ነገር ጌታ መሆኑን፣ፀሀዩን ጨረቃውን ከዋክብቱን፣ዛፉን፣እንስሳቱን፣ጂኑን፣ሰውንና መላእክቱን፣ ሁሉ ያገራና ሁሉም ለሱ የሚተናነሱና የሚዋረዱ መሆኑን፣ የፈለገውን በፈለገው ላይ አሸናፊ የሚያደርግና በሱ ላይ ማንንም ምንንም በፍፁም አሸናፊ ማድረግ የማይቻል መሆኑን፣የሚያኖርና የሚገድል፣የፈለገውን የሚያደርግና የፈለገውን የሚፈርድ፣ለፍርዱም ተቺ የሌለውና ውሳኔው የማይመለስበት መሆኑን ይቀበሉ ነበር።

በዚህ መልኩ የአላህን አንድነት -በዛቱ፣በሲፋቱና በድርጊቱ-አንድነቱን በግልፅ ከተቀበሉ በኋላ እንድህ ይሉ ነበር፦አላህ ከባሮቹ እንደ ነቢያት፣ሩሱሎች፣ወልዮችና ሷሊሆች ባለሟሎች ስለ ፍጡሮቹ ጉዳይ የመፈፀም ከፊል ሥልጣን ይሠጣቸዋል። ልጅን መስጠት፣መከራን የመመለስ፣ጉዳዮችን የመፈፀም፣በሽተኛን የማዳንና የመሳሰሉትን ችሎታዎች በአላህ በአላህ ይሠጣሉ ። አላህ ይህን ሥልጣን የሰጣቸው ለሱ ቅርበት ስላላቸውና በሱ ዘንድ ስለተከበሩነው። አላህ ይህንን ስልጣንና ምርጫ ስለሰጣቸው ለሰው በማይታይና በማይታወቅ መንገድ(በገይብ)የባሮችን ጉዳዮች ይፈፅማሉ፣ጭንቅና መከራን ያነሱላችኋል፣የወደዱትን ሰው ወደ አላህ ያቃርባሉ፣ በአላህ ዘንድ ያማልዳሉ።ይሉ ነበር።

ሙዝሪኮች በዚህ አባባላቸው መሠረት እነዚህን ነቢያት፣ወሊዮችና ሷሊሆች ወደ አሏህ መቃረቢያ (ወሲላ) አደረጉዋቸው (ሙሽሪኮችንና አላህን የሚያቃርቡ ማለትነው።)ወደነዚህም የሚቀርቡበትንና ውደታቸውን የሚያገኙበትን ድርጊቶችንና ተግባራትን ፈጠሩ።እነዚህን ድርጊቶች ከፈፀሙ በኋላ ይተናነሱላቸዋል፣ጉዳዮቻቸውንም እንድፈፅሙላቸው ይለምኑዋቸዋል፣በመከራ ጊዜ እርዳታን ይጠይቁዋቸዋል፣በፍራቻ ጊዜም ይጠበቁባቸዋል(ጠብቁን) ይሉዋቸዋል።

ወደነዚህ ለመቃረብ የፈጠሩት ድርጊቶች ለነዚህ ነቢያት (አንቢያ) ወሊዮች፣(አውሊያ)እና ሷሊሆች (ሷሊሁን) የተወሰነ ቦታ ይመርጡላቸውና ቤቶችን ይገነለመቃረብና  ከዚያም በቤቶቹ ውስጥ ምስሎቻቸውን ሰርተው ያስቀምጣሉ። የሚቀርፁት ምስሎች የነቢያቶቹና የወሊዮቹ ትክክለኛ ምስሎች ወይም ሀሳባው ምስሎችናቸው። በነሱ አባባል የአንዳንዶቹን ወልዮችና ሳሊሆች መቃብሮች ሊያገኙ ይችላሉ። ይህ ከሆነ ግን ምስሎቻቸውን ሳይቀርፁላቸው ቤት ብቻ ይገነቡላቸዋል። ከዚያም ወደነዚህ ምስሎችና መቃብሮች በመሄድ በረከት(ረድኤት)ለማግኘት መቃብሮቹንና ምስሎቹን ያብሱዋቸዋል። ይዞሯቸዋል (ጠዋፍ)ያደርጉባቸዋል፣ያልቋቸዋል፣ያከብሯቸዋል፣ያወድሷቸዋል፣ወደነሱ ለመቃረብና ችሮታቸውን ለማግኘት ሲሉ ስለቶችንና ቁርባኖችን ያቀርቡላቸዋል። እነዚህ ሙሽሪኮች ለነዚህ ነገሮች የሚሳሉት አላህ ከሰጣቸው ሲሳዮች(ርዝቆች) ከእርሻው፣ከአትክልቱ፣ከእህሉ፣ከመጠጡ፣ከእንስሳቱ፣ከወርቁ፣ከብሩ፣ከእቃዎችና ከገንዘቦችነው። ይህን ሁሉ የሰጣቸው አላህ ሲሆን ለሌላ ስለት ወይም ነዝር ያደርጋሉ።
         ይቀጥላል

https://t.me/Menhaj_Asselefiya


ሙስሊም ካልሆነ ወንድ ጋር አጉል ቅርርብ ውስጥ የገባችሁ እህቶች በጊዜ ከሰመመናችሁ ውጡ። በፍቅር ምርቃና እንደ ዋዛ ያቆራረጡት አደገኛ መንገድ መመለስ ሲያስቡ ዳገቱ ልብን ሊፈትን ይችላል። ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው። መጨረሻችሁ ኩ- ፍ- ር ከመሆኑ በፊት በጊዜ ንቁ። ርቀቱ ሲጨምር መመለሻው ይከብዳል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️📡

⭐️የመተዋወሻ እና ለህፃን አቲካ
⭐️የትብብር  ፕሮግራም

በትዳር እና ኢስላም ቻናል

ኑ! በልብ ህመም እየተሰቃየች የምትገኘው ህፃን አቲካን ሰበብ እንሁናት

በእለቱም ተጋባዥ ኡስታዞች እና ወንድሞች:
⭐️
➡️ኡስታዝ አቡ ሂበተላህ🎤
➡️ኡስታዝ ዓብዱረዛቅ ባጂ 🎤
➡️ኡስታዝ ኢብራሂም ኸይረዲን 🎤
➡️ኡስታዝ አቡ ዑበይዳህ🎤
➡️አቡ ሁዘይፋህ (ሰዒድ)🎤
➡️አቡ ማሂ (ሙሐመድ ኢድሪስ)🎤

የህፃን አቲካ ህመም ምንድነው?👇
t.me/tdarna_islam/4859?single
t.me/tdarna_islam/4863
⬆️
✅ቀን እና ሰዓት ነገ እሁድ 22/03/2017
ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ➡️

✅የሚተላለፍበት ቻናል✨
⭐️ t.me/tdarna_islam href='https://t.me/tdarna_islam' rel='nofollow'>
      t.me/tdarna_islam ⭐️


ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት

ክፍል 13 ደዕዋን ለመዋጋት ቁረይሾች የተጠቀሙት የተለያዩ ዘደዎች


ይህም ማለት ወህይ፣ቁርኣን ፣ነቢይነት (ኑብዋ)እና መልእክተኛነት (ሪሳላ)የአላህ ችሮታዎች ስለሆኑ ችሮታውን እንዴት እንደሚያከፋፍል፣ የት እንደሚያስቀምጣቸው ፣ለማን እንደሚሰጣቸውና ማንን እንደሚከለክላቸው የሚያውቀው እርሱ አላህ ብቻነው። አላህ እንድህ ይላል፦

اللَّهُ أَعْلَمُ حَيْثُ يَجْعَلُ رِسَالَتَهُۗ۝١٢٤፡
አላህ መልእክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ ይበልጥ አዋቂነው።( አል-አንኣም 6:124)

ከዚህ በኋላ ደግሞ ወደ ሌላ ማስመሰያ(ሹብሃ) ተዘዋወሩ። መልእክተኛ(ረሱል) መሆን ያለበት ከምድራዊ ነገስታት አንዱ ነው።በንግስናው ምክንያት ክብርንና ግርማን የተጎናፀፈ፣አገልጋዮች፣አጃቢዎች፣አትክልቶች ገንዘብና የመሳሰሉት ነገሮች ያሉት፣ግብርና ዝና ባላቸው ጠባቂዎችና አጃቢዎች ታጅቦ የሚሄድ መሆን አለበት አሉ።ሙሐመድ ደግሞ የእለት ጉርሻውን ለማግኘት በገበያ ውስጥ ከሰው ጋር እየተጋፋ የሚሄድ የአላህ መልእክተኛ ነኝ ይባላልን?አሉ።


لَوْ لَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مَلَكࣱ فَيَكُونَ مَعَهُ نَذِيرًا۝٧أَوْ يُلْقَیٓ إِلَيْهِ كَنزٌ أَوْ تَكُونُ لَهُ جَنَتٌّ يَأْكُلُ مِنْهَاۚ وَقَالَ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلࣰا مَسْحُورًا۝٨

ከርሱ ጋር አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ወርሱ መልአክ (በገሃድ)አይወርድም ኖሯልን?አሉ፦ወይም ወደርሱ ድልብ አይጣልለትንም?ወይም ከርሷ የሚበላላት አትክልት ለርሱ አትኖረውምን?(አሉ)በዳዮችም (ላመኑት)የተደገመበትን ሰው እንጂ ሌላን አትከተሉም አሉ። (አል ፉርቃን25:7-8)

ነቢዩ (ﷺ)ለሁሉም የሰው ልጅ አይነት፦ለትንሹም ለትልቁም፣ለደካማውም ለጠንካራውም፣ለተራውም ለክብሩም፣ለባሪያውም ለነፃውም (ለጨዋውም)የተላኩ መሆናቸው የሚታወቅነው ከላይ እንደተባለው ግርማ ያላቸውና የሚፈሩ፣በአገልጋዮች፣በአጃቢዎችና በታላላቆች የታጀቡ ቢሆን ኖሮ የኅብረተሰቡን አብዛኛውን ክፍል የሚወክሉት ደካሞችና ትንንሾች ሊጠቀሙባቸው ስለማይችሉ የሐልእክቱ(የሪሳላው)ዋና አላማ ሳይፈፅም ይቀር ነበር።እስካሁን የሚወሳና ሊጠቀስ የሚችል ጠቅም ባላስገኝም ነበር።ስለዚህም ሙሽሪኮች ለዚህ ጥያቄያቸው ሙሐመድ(ﷺ)መልእክተኛ ነው የሚል መልስ ነው የተሰጡት። በርግጥ መልእክተኛ መሆናቸው ሁሉንም የሙሽሪኮች ማምታቻ ጥያቄዎች ፉርሽ ለማድረግ በቂ ነው ።መልእክተኛ እንድኖሩት የጠየቃችሁት መፈራት፣ግርማ፣አጃቢና ገንዘብ ለብዙሃኑ ሕዝብ መልእክት የማድረሱን ኣላማና ተግባር የሚፃረር ጥያቄ ነው።መልእክት እንድደርስ የሚፈለገው ለሁሉምነውና።

በዚህ ሹበሀቸው ላይ መልስ ሲሰጥበት ሌላ እርምጃ ተራመዱ።ለእምቢተኝነትና ነቢዩን ለማታከት ተአምራትን እንድያሳዩአቸው ጠየቁዋቸው። በዚህ ጉዳይ በነቢዩና (ﷺ)በነሱ መካከል ክርክርና ውይይት ተካሄደ።ወደፊት የተወሰኑትን ለማምጣት እንሞክራለን ኢንሻ አላሁ ተዓላ።

       ይቀጥላል

https://t.me/Menhaj_Asselefiya


እውነት / ሀሰት 
((1)) ሸሪአዊ እውቀት መፈለግ መማር ግዲታ ነው ??

ጥያቄ ትክክለኛው መልስ ሰታገኙ የሚያመጣላችሁን add አድርጉለት 👇


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የዚህ ቻናል ቤተሰቦች እንደት ከርማችሁነው ይቅርታ ተቋርጦ የነበረው ፅሁፌ በአላህ ፈቃድ ከዛሬ ጀምሮ ይቀጥላል እናንተም ሳትሰለቹ አንብቡ


ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት

ክፍል 12 ደዕዋን ለመዋጋት ቁረይሾች የተጠቀሙት የተለያዩ ዘደዎች

وَقَالُوٱ مَالِ هَاذَا ٱلرَّسُولَ يأْكُلُ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشِی فِی ٱلأَسْوَاقِۙ۝٧

"ለዚህም መልዕክተኛው ምግብን የሚበላ በገበያዎችም የሚሄድ ሲሆን ምን (መልዕክተኛነት)አለው ?--አሉ" (አልፉርቃን25:7)

አላህ እንድህ አለ፦

بَلْ عَجِبُوٓٱ أَن جَآءَهُمْ مُنذِرࣱ مِنْهُمْ فَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَذَا شَیْءٌ عَجِيبٌ۝٢

"ይልቁንም ከነሱ ጎሳ የሆነ አስፈራሪ ስለመጣላቸው ተደነቁ  ከሐድዎችም ፦ይህ አስደናቂ ነገር ነው አሉ።(ቃፍ50:2)

إِذْ قَالُوٱ مَآ أَنزَلَ اللهُ بَشَرࣲ مِّن شَیْءࣲ۝٩١

አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም አሉ።(አለ አንኣም (6:91)
ለዚህም አላህ የሚከተለውን መልስ በመስጠት እምነታቸውን ፉርሽ አደረገባቸው ፦

قُلْ مَنْ أَنزَلَ ٱلْكِتَٰبَ ٱلَّذِی جَآءَ بِهِ مُوسَیٰ نُورࣰا وَهُدࣰی لِّلنَّاسِۖ۝٩١

ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ሆኖ ሙሣ ያመጣውን መጽሐፍ ማን አወረደው በላቸው (አል-አንዓም 6:91)

አላህ (ሱ.ወ)የነቢያትንና የመልክተኞችን ታሪኮችና በነሱና በሕዝቦቻቸው መካከል ተደርጎ የነበረው ክርክር ተረከላቸው።ሕዝቦቻቸው እነሱን በመቃወም " እናንተ ብጤያችን ሰው እንጂ (ሌላ)አይደላችሁም "ማለታቸውን በቁርኣኑ ተረከላቸው። መልክተኞቹ ደግሞ የሚከተለውን ማለታቸውን ነገራቸው፦

قَالَتْ لَهُمْ رُسُلُهُومْ إِن نَّحْنُ إِلّا بَشَرࣱ مِثْلُكُمْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّه يَمُنُّ عَلَیٰ مَن يشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۖ۝١١

"መልዕክተኞቻቸው ለነርሱ አሉ፦እኛ ቢጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለንም፣ግን አላህ ከባሮቹ ውስጥ በሚሻው ሰው ላይ ፀጋውን ይለግሳል
" (ሱረቱል ኢብራሒም5:11)

ነቢያትና ሩሱሎች ሁሉም የሰው ልጆች ነበሩ። መልእክተኛ ከመላኢካ ከሆነ ሰው በመላኢካ መመራት ስለማይችል የመልእክትና የመልእክተኛነት አላማ ሊሳካ አይችልም።ጥርጣሬውም (ሹበሃው)እንደነበረ ይቆያል ማለትነው። አላህ እንድህ ይላል፦

وَلَوْ جَعَلْنَٰهُ مَلَكࣰا لَّجَعَلْنَٰهُ رَجولࣰ وَلَلَبَسْنَا عَلَيْهِمْ مَّا يَلْبِسُونَ۝٩

"(መልእክተኛውን)መልአክም ባደረግነው ኖሮ ወንድ (በሰው ምስል)ባደረግነው ነበር። በእነርሱም ላይ የሚያመሳስሉትን ነገር ባመሳሰልንባቸው ነበር።" (አል-አንኣም 6:9)

ሙሽሪኮች ኢብራሂም፣ኢስሚኢልና መሳ(ዐ.ሰ)መልእክተኞች መሆናቸውንና የሰው ልጅ መሆናቸውን ያውቁትና ይቀበሉትም ስለነበር በዚህ ማስመሰያቸውና ማጠራጠሪያቸው ሊገፉበት አልቻሉም።ሌላ ማስመሰያ አመጡ።"አላህ መልእክቱን የሚያደርስለት ከዚህ የቲምና ሚስኪን ሌላ ሰው ማግኘት አልቻለምን?አሉ። አላህ መልእክተኛ ቢልክ ኖሮ የቁረይሽንና የሰቂፍን ምርጦችና ታላላቅ ሰዎች ትቶ ይህንን የሙት ልጅ አይልክም ነበር" አሉ።

وَقَالُوا لَوْ لَانُزِّلَ هَذَا ٱلْقُرْءَانُ عَلَیٰ رَجُلࣲ مِّنَ ٱلْقَرْيَتَيْنِ عَظِمٍ۝٣١

"ይህ ቁርኣን ከሁለቱ ከተሞች በታላቅ ሰው ላይ አይወርድም ኖሯልን?አሉ።" ከመካና ከጧኢፍ ማለታቸው ነው።(አል-ዙኽሩፍ 43:31)
 
አላህ የሚከተለውን መልስ ሰጣቸው

أَهُمْ يَقْسِمُونَ رَحْمَتَ رَبِّكَۚ
እነርሱ የጌታህን ችሮታ ያከፋፍላሉን ? (አል-ዙኽሩፍ 4:32)

ይቀጥላላል
https://t.me/Menhaj_Asselefiya


✅ይህ ቻናል ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ባጠቃላይ
እጅግ ጠቃሚ ቻናል ነው
ወደ ቻናሉ ተቀላቀሉ ዛሬ ባይጠቅማችሁ
ነገ ይጠቅማችኋል⭐
👇
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0




🔠🔠🔠🔠

  

    

      
   ረ 

ገባ ገባ በሉ


🖋ርዕስ    ✅ኹሹዕ ፊ ሰላህ ⚫️

🎙አቅራቢ ፦✅ ከማል አህመድ ✅

የሚተላለፍበት ሊንክ

⬇️
t.me/tdarna_islam?livestream
t.me/tdarna_islam?livestream


🛜ዛሬ እና ነገ የሚደረጉ የዳዕዋ ፕሮግራሞች

ዛሬ ምሽት በትዳር እና ኢስላም ቻናል

t.me/tdarna_islam/4730
t.me/tdarna_islam/4730

ዛሬ ምሽት በኢብኑ ተይሚያህ ቻናል
⚫️
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13943
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13943
⭐️
ነገ እለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ
በደሴ ከተማ
🌟
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy/19805
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy/19805

🛜ከላይ ባለው ልንክ እየገባችሁ ሙሉ ተጋባዥ እንግዶች እና ርዕስ አንብቡ✅


Forward from: Abu_Oubeida~channel
✏️ መልካም ዜና

ከ"አል_ሁዳ"የሩቃ አገልግሎት መስጫ፦

የአላህ ፈቃድ ሁኖ ሸሪአውን በጠበቀ አሰራር፡የሩቃ አግልግሎት ጀምረናል።ከየትኛውም ቦታ ለሚመጡ አገልግሎት ፈላጊዎች፡ቤታችን ክፍት ነው።ከምንሰጣቻው አገልግሎቶች ውስጥ፦

☑ የሲሕር     
☑ የቡዳ
☑ የጅን
☑ የዛር=>እና ሌሎችም
ከህጻናት እስከ አዋቂ በህመሙ ለተጠቁ ሁሉ አገልግሎቱን እንሰጣለን።

📍አድራሻ ኬሚሴ ከዶ/ር ሰኢድ ክልኒክ ፊት ለፊት ባለው ኮብሊስቶን #300ሟ አካባቢ ገባ ብሎ።

#⃣0930827492
1⃣ላይ በቦት መረጃ ለመጠየቅ ከፈለጋችሁ፡@AbuOubeida90_bot

የቴሌግራም ቻነል፦
t.me/AbuOubeida


የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲሱ  ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው  ✅
በሀገር ውስጥም ይሁን ካሀገር ውጪ ያላችሁ
የሱና ወንድም እና እህቶቻችን 
ይህ ቻናል ይጠቅማችኋል ተቀላቀሉ
👇
join request የሚለውን በመጫን✅️
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0




Forward from: ኢህሳን Advertising
📣የትኛውም የስራ ማስታወቂያ ሲኖር
በእነዚህ username ሹክ በሉን
👇
1️⃣ @twhidfirst1
🐽@Tolehaaaaaa
ማሳሰቢያ🔻 ምንም አይነት ክፍያ አንጠይቅም።
- ስለ ስራው ግን እናጣራለን አጣርተን ቀጥታ በቻናሉ እንለቃለን ✅

🔗ሼር በማድረግ አሰራጩት
የስራ ማስታወቂያ የሚለቀቅበት ቻናል
👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከጭፍን ተከታይነት መጠንቀቅ
~
ከሱና ሰዎች አበይት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ የፈለገ ቢገንኑ ለዑለማዎች ጭፍን ወገንተኛ አለመሆን ነው፡፡ የፈለገ ብንወደው ማንም ቢሆን የተናገረው ሁሉ ልክ አይሆንም፡፡ ስለሆነም ለማንም ጭፍን ወገንተኛ ልንሆን አይገባም፡፡ ዑለማዎቻችንን ስለወደድናቸው ብቻ ንግግራቸውን ሁሌ እንደወረደ አንወስድም፡፡ ይህንን በተግባር ያስተማሩን ራሳቸው ዑለማዎቹ ናቸው፡፡ ለአብነት ያክል የአራቱን መዝገቦች ኢማሞች ንግግሮች ላስፍር፡-

[ሀ] የአቡ ሐኒፋ ንግግሮች፡-

1. “አንድ ሐዲሥ ትክክለኛ ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው፡፡”
2. “ከየት እንደወሰድነው ካላወቀ ለማንም አቋማችንን ሊወስድ አይፈቀድለትም፡፡”
3. “ማስረጃዬን ያላወቀ ሰው በኔ ንግግር ፈትዋ ሊሰጥ ሐራም ነው፡፡”
4. “እኛ ሰዎች ነን፡፡ አንድ ንግግር ዛሬ እንናገርና ነገ ከሱ እንመለሳለን፡፡”
5. “የላቀውን አላህ መፅሐፍና የመልእክተኛውን ﷺ ንግግር የሚፃረር ንግግር ከተናገርኩኝ የኔን ንግግር ተውት፡፡”

[ለ] የማሊክ ንግግሮች፡-

1. “እኔ ሰው ነኝ፡፡ እስታለሁ፣ አገኛለሁ፡፡ ስለዚህ እይታየን ተመልከቱ፡፡ ቁርኣንና ሱና ጋር የገጠመውን በሙሉ ያዙት፡፡ ቁርኣንና ሱና ጋር ያልገጠመውን ተውት፡፡”
2. “ከነብዩ ﷺ በስተቀር ንግግሩ የሚያዝለት ወይም የሚመለስበት ያልሆነ አንድም የለም፡፡”
3. “ከነብዩ ﷺ በኋላ ከንግግሩ የሚያዝና የሚተው ያልሆነ አንድም የለም፡፡ ነብዩ ﷺ ሲቀሩ፡፡"

[ሐ] የሻፊዒይ ንግግሮች፡-

1. “አንድ የነብዩ ﷺ ሱና የተገለፀለት ሰው ለማንም ንግግር ሲል እሷን (ሱናዋን) መተው እንደማይፈቀድለት ሙስሊሞች በሙሉ ኢጅማዕ አድርገዋል፡፡”
2. “በኪታቤ ውስጥ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ሱና የሚፃረር ነገር ካገኛችሁ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ሱና ተከተሉ፡፡ የኔን ንግግር ተውት፡፡”
3. “ሐዲሥ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው፡፡”
4. “እኔ ከተናገርኩት በተቃራኒ በዘርፉ ምሁራን ዘንድ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ትክክለኛ ዘገባ የመጣበት ርእስ ሁሉ እኔ በህይወት ሳለሁም ሆነ ሞቼ ከሱ ተመልሻለሁ፡፡”

[መ] የአሕመድ ንግግሮች፡-

1. “የአውዛዒይ ግላዊ አስተያየት (ረእይ)፣ የማሊክም ግላዊ አስተያየት፣ የአቡ ሐኒፋም ግላዊ አስተያየት ሁሉም አስተያየት ነው፣ እኔ ዘንድ፡፡ መረጃ ያለው ከነብዩ ﷺ እና ከሶሐቦቹ ቅሪት ዘንድ ነው፡፡”
2. “ማሊክንም፣ ሻፊዒይንም፣ አውዛዒይን፣ ሠውሪይን በጭፍን አትከተል፡፡ እነሱ ከያዙበት ያዝ፡፡”

እነዚህንና መሰል ወርቃማ ንግግሮችን ከሸይኹል አልባኒይ “ሲፈቱ ሶላቲ ነቢይ” ኪታብ መግቢያ ላይ እናገኛለን፡፡

ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! እኛ ከዚህ ምን እንማራለን? ለየትኛውም ዓሊም ጭፍን ተከታይ አንሁን። ከላይ ያለፉትን ንግግሮች በአንክሮ እናስተውል፡፡ የህይወታችን ቋሚ መመሪያም እናድርጋቸው፡፡ “ማሊክንም፣ ሻፊዒይንም፣ አውዛዒይንም፣ ሠውሪይንም በጭፍን አትከተል” የሚለውን የኢማሙ አሕመድ ንግግር እናስተውል። እነዚህን የኡማው ከዋክብት በጭፍን መከተል ካልተፈቀደ ከነሱ በእጅጉ የሚያንሱትንስ በጭፍን መከተል ይፈቀዳልን? ጤነኛ ለሆነ ሰው መልሱ አይጠፋውም፡፡ እናም ተመሳሳይ ነገር ልበል፡፡
- ኢብኑ ተይሚያንም፣ ኢብኑል ቀይምንም፣ ዘሀቢይንም፣ ኢብኑ ከሢርንም፣ … በጭፍን አትከተል፡፡
- ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወህሃብንም፣ ዐብዱረሕማን ብኑ ሐሰንም፣ ዐብዱለጢፍ ኣሊ ሸይኽንም፣ ሰዕዲይንም፣ ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ኢብኑ ባዝንም፣ አልባኒይንም፣ ኢብኑ ዑሠይሚንንም፣ ሙቅቢልንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ፈውዛንንም፣ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድንም፣ ሙሐመድ አማን አልጃሚይንም፣ ረቢዕ አልመድኸሊይንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- በሰፈርህ፣ በአካባቢህ፣ በሃገርህ ያሉ መሻይኾችንም፣ ተማሪዎችንም የፈለገ ብትወዳቸው በጭፍን አትከተል፡፡ የተወሰኑትን ከሌሎች ለይተህ የሐቅ መለኪያ ሚዛን አታድርጋቸው፡፡ ማንም ይሁን ማን፡፡
እዚህ ላይ ይህ ፅሑፍ ዑለማን ከማክበርና ትንታኔያቸውን ከመጠቀም ጋር የሚፃረር የሚመስለው ካለ የፅሑፉን መልእክት ፈፅሞ አልተረዳም፡፡ የዚህ ፅሑፍ አላማ ግለሰቦችን የሐቅ መለኪያ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል ፈተና መጠንቀቅ እንደሚገባ ማሳሰብ ብቻ ነው፡፡ እንጂ የቁርኣንና የሐዲሥን ማብራሪያ የምንወስደው ከዑለማዎች እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን የአንዱ ዐሊም ትንታኔ ከሌላው የሚፃረርበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም በጭፍን ልንከተል እንደማይገባ የሚያሳይ ነው፡፡ ዛሬ ግን ታላላቅ መሻይኾችን ቀርቶ በአካባቢያቸው የሚገኙ ዝቅ ያሉ አስተማሪዎችን ጭምር በጭፍን በመከተል የወደዱትን የሚወዱ፣ የጠሉትን የሚጠሉ፣ የነኩትን የሚነኩ፣ የፈቀዱትን የሚፈቅዱ፣ የከለከሉትን የሚከለክሉ፣ ያስጠነቀቁትን የሚያስጠነቅቁ ብዙ ናቸው፡፡ የሚከተሏቸው ሰዎች በሆነ ምክንያት አቋም ሲቀይሩም ያለምንም ማገናዘብ ሰልፋቸውን በመቀየር ዥዋዥዌ ይጫወታሉ፡፡ ይሄ ፈፅሞ ሊሆን አይገባም፡፡ አላህ ማስተዋሉን ያድለን፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 07/2010)
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

* የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M

* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL







20 last posts shown.