1️⃣3️⃣
ሙሉው ድርሳነ ሩፋኤልን ያድምጡ
https://youtu.be/E5HK3j8lJao?si=HQhsnDx-CjE3Wu93 👉 ጌታችንም ሩፋኤልን የክብርህን ታላቅነት ያውቁ ዘንድ ስምህን ለሐዋርያት ንገራቸው አለው ።
👉 የመላእክት አለቃ ሩፋኤልም ሐዋርያትን እንዲህ አላቸው ፤ እኔ ሩፋኤል እባላለሁ ፤ የዋህ ነኝ ፤ ከመላእክት አለቆችም ሦስተኛው ነኝ ።
፨ እግዚአብሔር በሃያ ሦስት ነገደ መላእክት ላይ የሾመኝ እኔ ሩፋኤል ነኝ ።
፨ በደብረ ጽዮን በሺው ዓመት ሠርግ ለወዳጆቹ በጎ ነገርን እሠጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘኝ እኔ ሩፋኤል ነኝ ።
፨ በዚያች በድኀነትና በደስታ ቀን ለክርስቲያን ከዕፀ ሕይወት እሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር የአዘዘኝ እኔ ሩፋኤል ነኝ ።
፨ ሰማያውያን መዛግብት በእጄ የሚጠበቁ እኔ ሩፋኤል ነኝ።
፨ እግዚአብሔር እንደ አዘዘኝ የምዘጋቸውና የምከፍታቸው እኔ ሩፋኤል ነኝ ። ( ድርሳነ ሩፋኤል ጳጉሜ )
የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሩፋኤል አማላጅነቱ ጸሎቱ በረከቱ ከኛ ጋር ይሁን ። ለዘለዓለሙ አሜን ።