🔷
መንዙማና ሙስሊሞች ያልተረዱት አደጋው ▪️ ቁርኣን የወረደው ገዝተን ቤት ለማስቀመጥ ትዝ ስል አንስተን ለበረካው በአካላችን ልንተሻሸው ሳይሆን ልንተዳደርበትና ልንሰራበት ነው !
▪️ሶሃበዎች
የበላይነት የተቀዳጁት ከነበሩበት ውርደት የወጡት በህይወት እያሉ ጀነት ልመሰከረላቸው የቻለው በቁርኣን በመስራታቸው ነው ። ➻
ሙስሊሞች ቁርኣንን የበላይ ካደረጉ የበላይ ይሆናሉ። ከሰሩበትና ከተመሩበት የማይጠፋውን የደስታ ሀገር ጀነትን ይወርሳሉ !
➽
ተኝተው የማያድሩት ጠላቶቻችን ሙስሊሞችን ከተውሂድ ብርሃን አውጥተው ወደ ሽርክ ጽልመት እንዲገቡ ለማድረግ በሽርክና በኩፍር የተሞላውን መንዙማ በተላለኪዎቻቸው አሕባሾች እነ ሱፊዮች በኩል አመጡ ። በጣም የሚያሳዝነው በሙስሊሞች እምነትና ደም የሚነግዱት ኢኽዋኖች ይህንን የሽርክ መናሀሪያ የሆነውን መንዙማ ኢስላማዊ ኪነ ጥበብ ወይም ኢስላማዊ አርት ብለው በማስተዋወቅ እንዲሰራጭ ማድረጋቸው ነው አላሁል ሙስተዓን ።
➧ በዚህ በቁርኣን ወር ሙስሊሞች ከምንጊዜውም በላይ ፊታቸውን ወደ ቁርኣን በሚያዞሩበት ግዜ አላህ ካዘነለት በስተቀር ይህ የኩፍር መናሀሪያ በእያንዳንዱ የሙስሊሞች መኖሪያ ቤት ፣ ንግድ ቤት እንዲሁም ስልካቸው ለይ ተጭኖ ህፃኖች እየሸመደዱት ወጣቶችና ጎልማሶች ዲን አድርገው ይዘውት የተውሂድ ጠላት ሆነው ያረጁበታል ።
↪️አብዛኛው መንዙማ የአላህን ሐቅ ለፉጡር የሚይሰጥበት በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን ከነበሩ ከሀዲያን ክህደት የበለጠ ክህደት ያለበት ነው ።
መንዙማ ባዮች በኩፍር ግጥሞቻቸው የአላህንና የነቢያችንን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስም ደጋግመው እያነሱ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ነቢዩን በመውደድ ስም ሽርክን ያሰሩታል ።
➪ ይህ የተከበረው የረመዳን ወር የተከበረው ቁርኣን የወረደበት ወር ሲሆን በዚህ ወር ቁርኣንን መቅራት፣ ትርጉሙን ማስተንተን፣ ያዘዘውን መልእክት ትእዛዙን መተግበር ክልከላውን መራቅ መልእክቱን ተረድቶ የህይወት መመሪያ አድርጎ መያዝ የእያንዳንዱ ሙስሊም ግዴታ ነው ።
↪️ቁርኣን የህይወታችን መመሪያ፣ የልባችን ብርሀን፣ ለውስጥም ለውጭም በሽታችን መድሃኒት፣ የሁለት ሀገር ስኬት ቁልፋችን ነው።
▪️ሙስሊሞች የቁርኣንን በረካ ማግኘትና ድልን መጎናፀፍ ከፈለጉ ከቁርኣን ጋር ያለቸውን ግንኙነት ማስተካከል ይገባቸዋል
የሽርክና የቢደዕ መናሀሪያ የሆነውን መንዙማን በመተው ቁርንኣንን በመቅራትና ትርጉሙን በመማር ጌታቸውን አላህን በእውቀት ሊያመልኩት ይገባቸዋል ።
👌ለዚህ ደግሞ የሱና ዱዓቶች ትልቅ ስራ መስራት አለባቸው እየሰሩም ነው አህባሾችና እኽዋኖች ደም እነ እምነት ለመነገድ በሚራሮጡበት በዚህ ግዜ የሱና ሰዎች ለሙስሊሞች እምነትና ሚንሓጅ ከምንግዜውም በላይ ልፋት ይጠበቅባቸዋል ! ለዚህ ደግሞ እንደ እድል የሚቆጠረው በረመዳን ወር የሙስሊሞችን ወደ መስጂድ መመለሳቸውን ተጠቅመን እምነታቸውን እንዲገነዘቡ እነ እንዲጠብቁ ከአህባሽ ፣ እኽዋን እነ ሙመይዐህ እንዲጠነቀቁ በማድረግ የእድሉ ተጠቃሚ መሆን ያስፈልጋል ።
አላህ ለሁላችንም የጠራ እውቀትን በኢኽላስ ከጠንካራ ድፍረት ጋር ይስጠን
ረመዳንን በተሻለ መልኩ ፆመን የምንጨርሰው ያድርገን !!!
✍📝Abu Nuh ሚስባህ ሙሐመድ
የቴሌግራም ቻነል➷➴➘➷➴➘➷➴➘
https://t.me/MisbahMohammed_6682