Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Economics


የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Economics
Statistics
Posts filter


"መልካም ስነምግባር ያለው ሰራተኛ ማፋራት ስንችል ያቀድነውን ገቢ በብቃት በመሰብሰብ ውጤታማ መሆን እንችላለን " - ወ/ ሮ ሂሩት መብራቴ በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስና ጉሙሩክ ስልጠና ማዕከል ኃላፊ

ታሕሳስ 21/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ከክልሎች ፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ቅርጫፍ ጽ/ቤቶች ለተውጣጡ የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል አመራሮች እና ሰራተኞች በዲስፕሊን ጥፍቶች እና ምርመራ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ እና ጉሙሩክ ስልጠና ማዕከል ኃላፊ ወ/ ሮ ሂሩት መብራቴ ስነ-ምግባርን በመላበስ አሰራር እና መመሪያን አውቆ የሚተገብር ሰራተኛ እና አመራር ለማፋራት ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሰራተኛው እና አመራሩ የአሰራር ስርዓቶችን አክብረው እንዲሰሩ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመው የአሰራር ወጥነት እንዲኖር ሕጉን አውቆ እና በተቀናጀ መልኩ በመስራት መልካም ስነ-ምግባር ያለው ሰራተኛ ማፋራት ስንችል ያቀድነውን ገቢ በብቃት በመሰብሰብ ውጤታማ መሆን እንችላለንም ብለዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/DOZfS


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የጨረታ ማስታወቂያ

በገቢዎች ሚኒስቴር የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ከፋይ ስም ዳሞታ የትምህርት አገልግሎት የሚፈለግባቸውን ግብር/ታክስ ብር 13,059,030.15/(አስራ ሶስት ሚሊዬን ሀምሳ ዘጠኝ ሺህ ሰላሳ ብር ከአስራ አምስት ሳንቲም) ስላልከፈሉ አድራሻ፡- ክልል -ደቡብ ኢትዬጵያ ከተማ ወ/ሶዶ የሆነውን የታክስ ባለዕዳውን ሀብቶች በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ጨረታው እስከ ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል፡፡


📌ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋል ማሻሻያ መመሪያ

#የታክስ_ደረሰኝ_አጠቃቀም_እና_አስተዳደር_መመሪያ_/ማሻሻያ/_ቁጥር_188/2017

ታሕሳስ 21/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ እና በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቶ ስራ ላይ ማዋሉ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም የመመሪያውን ሙሉ ክፍል ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፡-
https://shorturl.at/jS3A3


ዘመናዊና ቀልጣፋ የጉምሩክ አገልግሎት ማስፈን ለኢትዮጵያ ፈጣን ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

ታሕሳስ 19/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የሻንጋይ ጉምሩክ ዩኒቨርስቲ ከጉምሩክ ኮምሽን የተለያዩ ቅርንጫፎች የተውጣጡ ሃምሳ (50) የጉምሩክ ባለሞያዎችን ለተከታታይ ሰላሳ (30) ቀናት በዓለማቀፍ የጉምሩክ አሰራር፣ የጉምረክ መረጃ ትንተና እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም አሰልጥኖ አስመረቀ፡፡

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ለተመራቂዎች ሰርተፊኬት የሰጡት እና ንግግር ያደረጉት የጉምሩክ ሕግ ተገዥነት ምክትል ኮምሽነር አቶ አዘዘዉ ጫኔ ዘመናዊና ቀልጣፋ የጉምሩክ ስርዓት ለመገንባት ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለባለሞያዎች መሰጠት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ይህንን ስልጠና በተሳከ ሁኔታ ለሰጡት የሻንጋይ ዩኒቨርስቲና የቻይና ጉምሩክ ጠቅላላ አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል:: በቀጣይ ተቋሙ ለሚስራው የአቅም ግንባታ ስራ የቻይና መንግስት በተጠናከረ ሁኔታ ድጋፉ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት አክለዋል::

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚና የንግድ አማካሪ የሆኑት Mr. Xue Wei በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ቻይና አለማቀፍ የጉምሩክ ስርዓት ለማስፍን እየሰራች እንደምተገኝ ገልፀዋል፡፡

በማያያዝም ቻይና በአቅም ግንባታና በስልጠ ዙሪያ ለአፍሪካ ሀገራት የምታደረገው ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል፡፡

ለተከታታይ ሰላሳ (30) ቀናት ስልጣናውን የተከታተሉ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባለሞያዎች ከስልጠናው የገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ ሀገራቸውን በተገቢው መንገድ እንደሚያገለግሉ ገልፀዋል፡፡

በበኃይሉ ሽመልስ
ፎቶ፡- ክፍሌ አዳፍሬ
.






በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንትሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተከሰሱ

ታሕሳስ 18/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንትሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር ምርመራ ሲያጣራ ቆይቶ ክስ መስርቶባቸዋል።

ግለሰቦቹ የተከሰሱት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ)(ለ)፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ አዋጅ 285/94፣ የፌዴራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 116(2)፣ 125(1) እና 132 እንዲሁም ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29(1)(ሀ)(ለ)(ሐ) እና አንቀጽ 2(መ)(ሠ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/L9tZo


ለታክስ አከፋፈል የሚቀርብ ዋስትና
👉ባለስልጣኑ የመንግስትን ገቢ ለመጠበቅ አስፈላጊ መስሎ ሲታየው አስፈላጊ ነው በሚለው መጠንና አኳኋን ታክስ ከፋዩ ዋስትና እንዲያቀርብ ሊያስገድደው ይችላል፡፡
👉ታክስ ከፋዩ ዋስትና እንዲያቀርብ የሚጠየቀውም፡-
1. የመክፈያ ጊዜው ለደረሰ ወይም የመክፈያ ጊዜው ለሚደርስ ታክስ መክፈያ፤ ወይም
2. በታክስ ሕግ መሰረት ተመላሽ ለሚጠይቅ ታክስ ከፋይ ቅድመ ሁኔታ ይሆናል፡፡
👉 የሚሰጠው ዋስትና ባለስልጣኑ የሚጠይቃቸው ተገቢ ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ዋስትና ሊሰጥ ይችላል፡፡
👉ታክስ ከፋዩ ዋስትና ማቅረብ ግዴታ የሚኖርበት ባለስልጣኑ፡-
1. የሚፈልገው የዋስትና መጠን፣
2. ዋስትናው የሚቀርብበት አኳኋን፣ እና
3. ዋስትናው የሚቀርብበትን ቀን የሚገልጽ የጽሑፍ ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ የሰጠ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
👉ታክስ ከፋዩ ያቀረበው የዋስትና መጠን የታክስ ከፋዩ ያልተከፈለ ታክስ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡


380 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

ታሕሳስ 17/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ባለፉት አምስት ወራት 380 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ገለፁ።

ሚኒስትሯ ባለፉት የለውጥ አመታት የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸምን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፤ በሀገር ደረጃ የተያዙ የልማት ዕቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ዋነኛ አቅም ተደርጎ የሚወሰደው የሀገር ውስጥ ገቢን ማሻሻልና ማሳደግ ነው ብለዋል።

ይህም የህዝብ የልማት ፍላጎትን ደረጃ በደረጃ የሚመልሱ መሰረተ ልማቶችን መገንባት እንደሚያስችል ገልጸው፤ ከዚህ አኳያ በገቢ አሰባሰብ ሂደቱ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የገቢ አቅምን ማሻሻል የሚያስችሉ መሰረታዊ ለውጦች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ለአብነትም የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን ማሻሻልና አገልግሎት አሰጣጡን ማሳለጥ የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን መዘርጋት መቻሉን አንስተው፤ ማሻሻያዎቹ በገቢ አሰባሰብ ሒደቱ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንዳስቻሉ አመልክተዋል።

በዚህም በ2010 ዓ.ም የፌደራል ገቢ 176 ቢሊየን ብር እንደነበር አስታውሰው÷ አሁን ላይ በአምስት ወር ብቻ 380 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

እንደ ሀገር የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ሊደግፍ የሚችል እና አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ እንዲኖር የገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ ሊደግፍ የሚችል የሀገር ውስጥ የፋይናንስ አቅም መገንባቱንም አረጋግጠዋል።


ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እና ሙስናን ለመታገል የተለያዩ ተግባሮችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገለጸ

ታሕሳስ 17/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች 21ኛውን ዓለም ዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል” በሚል መሪ ሃሳብ አክብረዋል፡፡

በመድረኩ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኪሮስ ደበሱ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እና ሙስናን ለመታገል የተለያዩ ተግባራቶችን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ አክለውም የሙስናን አስከፊነትና በሀገራችን ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዩች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ ነው ያሉ ሲሆን በየደረጃው ያለው አመራር እና ሰራተኛ በተለይም የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች በፀረ-ሙስና ትግሉ ባለቤትና ቁርጠኛ ሆነው ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን መታገል አለብን ብለዋል።

በዕለቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የመወያያ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሙስናን በመታገል በመንግስት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጥብቅ ዲሲፕሊን እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡

10 last posts shown.