ትምህርት ሚኒስቴር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support Us🙏
for promotion contact - @Pro_ad23_bot


Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት በቅርቡ ይፋ ይሆናል።

🔰ዉጤት ልክ እንደወጣ ዉጤታቹን የምታዩበት websites እነዚህ ናቸው ::

1. 
result.neaea.gov.et
2. 
result.ethernet.edu.et
3.  Telegram
@moestudentbot
4. 9444 SMS

#ትምህርት_ሚኒስቴር

"SHARE"


🌼YOHA STUDIO🌼
አንኳን ለብርሀነ መስቀሉ አደረሳቹ።

YOHA የስነጥበብ ቻናል የእናንተን ምናብ ለመማረክ ልዩ እና አስደናቂ የሆኑ የጥበብ ስራዎችን ይዘናል። በኪነጥበብ አለም በምናደርገው ጉዞ ይቀላቀሉን እና የፈጠራን ውበት ያግኙ።
👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFjZPFRFztpGwFmHoQ


በጊዜ ማጣት ምክንያት ከታች በተዘረዘሩት ዙርያ እገዛ ካስፈለግዎ @Eyoriica ያናግሩ በጥራት እና በታማኝነት ሰርተን እናስረክቦታለን:-        

👉Assignment
👉CV/Application letter
👉Business plan
👉Essay Writing
👉Report Writing
👉Internship report
👉Power point for presentation

እና ለሌሎችም ተያያዥ ስራዎች በ https://t.me/Eyoriica ላይ ይላኩልን


የአዲሱ ስርአተ ትምህርት መፅሀፍ ከKG - University (Share) ፣ የሁሉንም መፀሀፍት በሚከተለው ሊንክ ያገኙታል።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የKg
https://t.me/Moe_Ethiopia/9869
ከ1 - 6ኛ ክፍል
https://t.me/Moe_Ethiopia/9875
የ9ነኛ ክፍል
https://t.me/Moe_Ethiopia/9885
የ10ኛ ክፍል
https://t.me/Moe_Ethiopia/9895
የ11ኛ ክፍል
https://t.me/Moe_Ethiopia/9905
የ12ኛ ክፍል
https://t.me/Moe_Ethiopia/9915
ለFresh Man ኮርስ
https://t.me/Timihirt_Minister/116

ለሁሉም ተማሪዎች እንዲደርስ በቅንነት ሼር ያርጉ 🙏
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት!

በፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተናቸውን ያልጨርሱ ተማሪዎች ፈተና መውሰድ ጀምሯል። ስለዚህ የነሱ ፈተና እስከ መስከረም 15 ድረስ ታርሞ ይጠናቀቃል።

የ ሁሉም ተማሪዎች ውጤት አንድ ላይ ይለቀቃል። የተማሪዎችን ውጤት እስከ መስከረም 18-20 ድረስ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተብሏል።

ተማሪዎች ውጤታችሁን በትዕግስት እንድትጠብቁ  እና Share እና Follow በማድረግ እንድትከታተሉን እያሳሰብን ውጤት ሲለቀቅ  በዚሁ @Moe_Ethiopia ቻነል በፍጥነት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


ሁለተኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ( Exit Exam ) ጥር ወር ላይ ይሰጣል

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በትናንትናው ዕለት ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ላይ ተቋማት የመደበኛ ተማሪዎቻቸውን እንዲሁም 2015 ላይ የመውጫ ፈተና ወስደው ያላለፉ ተማሪዎችን መረጃ እስከ ጥቅምት 10/2016 ድረስ ይልኩ ዘንድ አሳስቧል።

ባለስልጣኑ ለግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ላይ ቀጣዩ ማለትም ሁለተኛው የመውጫ ፈተና ጥር ወር ላይ በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰጥ ጠቁሟል።

የመውጫ ፈተና በየ ስድስት ወሩ የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚንስቴር መግለፁ ይታወሳል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


የድህረ ምረቃ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል።

የድህረ ምረቃ ተፈታኞች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የGAT መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ላይ ምዝገባ የሚያደርጉበት ጊዜ ተራዝሟል።

ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው መልዕክት በGAT ፖርታሉ ላይ የተፈታኞች ምዝገባ የሚከናወነው ከመስከረም 21 እስከ 25/2016 ዓ.ም ድረስ በበይነ-መረብ መሆኑ ተገልጿል።

የመግቢያ ፈተና መስከረም 28 እና 29/2016 ዓ.ም በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በበይነ-መረብ ይሰጣል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


በአማራ ክልል የ2016 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 11/2016 ዓ.ም ተራዝሟል፡፡

በክልሉ የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል። እስካሁን 2.5 ሚሊዮን ተማሪዎች መመዝባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ተማሪዎች እንዲመዘገቡና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራው መስከረም 14/2016 ዓ.ም እንዲጀመር ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


በትግራይ ክልል የ2016 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሒደት ዛሬ መስከረም 09/2016 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

የ2016 ዓ.ም መማር ማስተማር ሒደቱን ለማስጀመር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

በዚህም ከመስከረም 03/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት 37 ሺህ ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ቢሮው ገልጿል፡፡
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 29 ጀምሮ ይሰጣል

በትግራይ ክልል ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፊታችን መስከረም 29 ቀን ጀምሮ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ ከፌደራል ፖሊስ ሃላፊዎችና ከክልሉ የፈተና አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


በአዲስ አበባ ከተማ የመማር ማስተማር ስራ ነገ ሰኞ መስከረም 7 በይፋ ይጀምራል።

ነገ ለሚጀምረው ትምህርት በየክፍለ ከተሞቹ የሚገኙት የትምህርት ፅህፈት ቤቶች እንዲሁም የትምህርት ተቋማት በቂ የሆነ ዝግጅት አድርገው የተማሪዎችን ለዓመቱ ትምህርት መገኘት ብቻ እየጠበቁ ይገኛሉ ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፤ ለ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ዝግጅት በከተማው ያሉ ትምህርት ቤቶችን የማደስ፣ ግብዓቶችን የማሟላት ፣ ከአጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰቡ ጋር የመምከር ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

በነገው ዕለት በከተማዋ ትምህርት የሚጀምረው በሁሉም የትምህርት ተቋማት ውስጥ ነው።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት የፊታችን ሰኞ መስከረም 7 በሁሉም ትምህርት ተቋማት እንደሚጀምር አስታወቀ።

ቢሮው የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት መስከረም 14 እንደሚጀመር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ የተሳሳተ ነው " ብሏል።

ቢሮው በየትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ እንደተሰራጨ በግልፅ አላሰፈረም።

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ ባደረገው የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር መሰረት ከመስረም 7 እስከ 11 ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።

መስከረም 14 ደግሞ የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


ትምህርት ሚኒስቴር መስከረም 14 የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል።

የአጠቃላይ ትምህርት የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር ይፋ ሆኗል።

በዚህም መሰረት ፤ ከመስረም 7 እስከ 11 ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።

የአንደኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 እንደሚሰጥ የሚያሳየው የትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር ከየካቲት 4 እስከ 8 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው የተማሪዎች ፈተና የሚታረምበት ውጤት የሚጠናቀርበትና የሚገለፅበት ወቅት እንደሆነ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር እንደሚያሳየው የካቲት 18 የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት የሚጀምር ሲሆን ከግንቦት 12 እስከ ግንቦት 23 የአጠቃላይ የትምህርት ማጠቃለያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ይሰጣል።

ከግንቦት 26 እስከ 30 የ6ኛ ክፍል አንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 3 እስከ 7 የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ የማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ጊዜ እንደሚሆን ይፋ ተደርጓል።

የሁለተኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ወቅትም ከሰኔ 17 እስከ 21 ሲሆን ከሰኔ 24 - 28 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው ፈተና የማረም፣ ውጤር የሚጠናቀርበት ፣ እና የሚገለፅበት እንደሚሆን ካሌንደሩ ያሳያል።

ሰኔ 30 ወላጆች እና የትምህርት ማህበረሰቡ በተገኙበት የአመቱ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ እንደሚደረግ ማሳስቢያ ሰጥቷል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

የድህረ-ምረቃ ነባር የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 07/2016 ዓ.ም

የቅድመ  ምረቃ ነባር (ከ3ኛ ዓመት በላይ) የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 08 እና መስከረም 09/2016 ዓ.ም  

የተከታታይ የማታ መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 12 እና 13/2016 ዓ.ም

የሁሉም ፕሮግራሞች ትምህርት መስከረም 14/2016 ዓ.ም እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia


👆አዲሱን ስርአት ትምህርት መጽሀፍ ለቀናል

✅የኬጅ

✅ከ1ኛ-8ኛ

✅ከ9ኛ-12ኛ ክፍል

Share እና Follow በማደረግ ለሁሉም ተማሪ ያድርሱ።

@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
G11-Biology-STB-2023-web.pdf
38.7Mb
👆👆የአዲሱ ስርአተ ትምህርት መጽሀፍት 11ኛ ክፍል - Share
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia

17 last posts shown.