Muke የግጥም'ጥም💧


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Other


እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጡ 🙌
ቻናላችንን ልዩ የሚያደርጉ ነገሮች 👇
🥇አዳዲስ የትም ያልተነበቡ #ግጥሞች እንደወረዱ፣
🥈በፈለጉት ርዕስ ግጥም ማዘዝ ይችላሉ፣
🥉ወቅታዊና ጊዜውን የጠበቁ ስራዎች እንደልብ ያገኙበታል።

ⒶⓃⓎ ⒸⓄⓂⓂⒺⓃⓉ & ⒸⓇⓄⓈⓈ👉 @Al_Meliku አናግሩኝ 💖

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Other
Statistics
Posts filter


💛ቁምነገር አዘል የሆነች ምርጥ ኢስላሚክ ቻናል ተጋበዙልኝ 🤗

🕌ወላሂ ሀቂቃ ማስታወቂያ ነው🕌


#ለሒጃቧ_ታጋይ🧕🗡
💎ጊዜውን የዋጀ ምርጥ ተከታታይ ታሪክ ተጀመረ🎊

ωανєя::::::↔️ @Waver_boy1




🍁🍁ርጉም ቀን🍁🍁

አዎይ..........አንቺ ቀን ተረገሚ፡
ከሌሎችም ተመርጠሽ ተለቀሚ፡
እርግማኔን ላውርድብሽ፡
በውሳኔዬም
   ክብር ላንቺ እንዳልሰጥሽ፡
አዎይ.............አንቺ ቀን ተረገሚ፡
ሰው አልፈልግ
     በሽታዬን አስታማሚ፡
ከቀን ቅዱስ ለኔ የራቅሽ፡
ከደስታዬ ጋር የምትሸሽ፡
በግፍ ቀኔን አንቺን ተነጥቄ፡
ከሚቀርበኝ ሰው እርቄ፡
እውላለሁ ተደብቄ፡
ለምን መልሱ
    ባንቺ ቀኔ
        ቅርሴን ሁሉ ተሰርቄ፡
አዎይ..........አንቺ ቀን
              አይሙላልሽ፡
ሀሳብሽ ሁሉ ይጉደልብሽ፡
ከኔ አንቺን ስላሰሽሽ፡
ከአፌ ወጦ በይ ልርገምሽ፡
ከቀኖች ሁሉ ብኩን ያርግሽ፡
የሀገሬን ፀሐይ ላጠፋሽ።

🌾🌾 ስለ ሀገሬ አነባው

✍✍✍


😔የተረታ ልሳን😔

ቃላትን ሰብስቤ ላሰፍር ስሜቴን፣
አስቤ ነበር ለመግለፅ ድካሜን፣
ግን ምን ያደርጋል ቃላቶቼም ሸሹኝ፣
አነሱም እንደሰው ሲቸግረኝ ከዱኝ፣
ልሳኔም ተረታ ማስረዳት አቃተው፣
ልቤም ተሰባብሮ አጣ ሚጠግነው፣
ሀዘኔን ሚጋራ ሰው ባጣ ግዜና፣
በብዕሬ ልፅፍ ላወራው ሻትኩና፣
ወረቀት ዘርግቼ ቀለም አነሳሁኝ ፣
የብሶቴን መድብል በእምባ ጀመርኩኝ፣
ከቀለሜ ቀድሞ እምባዬ ተዘራ፣
ነጩ ወረቀቴም ዥንጉርጉሩን ሰራ፣
በዕንባና ብዕር የተፃፈው ስሜት፣
ክብደቱ ግን ያው ነው አልቀነሰም ጥቂት፣
ብዕሬም ነጠፈ እምባዬም ደረቀ፣
በውሸት ፈገግታ ፊቴ እየደመቀ፣
ህይወቴ ቀጥሏል ወዳጄ እየራቀ፣

#ራዚ✍

🔺መታሰቢያነቱ🔺

"እንደኔ የህይወት ትርጉም ጠፍቶባችሁ ልባችሁ ተሰብሮ በውሸት ፈገግታ ችግራቹን ደብቃችሁ ለምትኖሩ ይሁንልኝ"


አ ን ድ ጓ ደ ኛ አ ለ ኝ

አንድ ጓደኛ አለኝ በጣም የሚወደኝ፣
እኔ ብርቀውም እሱ የማይርቀኝ፣
ወዳጄ ሲሸሸኝ ያመንኩት ሲከዳኝ፣
ዛሬ ጥሎኝ ሲሄድ ትናንት የወደደኝ፣
ዙሪያዬ ጨልሞ መድረሻ ሲጠፋኝ፣
ሀዘንና ድብርት ዱካክ ሲጫጫነኝ፣
አይዞህ እያለ ውስጤን ሚያክመኝ፣
በጣም የሚወደኝ አንድ ወዳጅ አለኝ፣
እሱም አምላኬ ነው ለዚህ ያደረሰኝ፣

    #ራዚ✍


....... የኛ ነገር .......
ተዋወቅን _ ተሳሳቅን
ተጣበቅን _ ተላቀቅን
ተኳረፍን _ ተታረቅን
ደግሞ _ ደግሞ
ከርሞ _ ከርሞ
ተኳረፍን _ ተታረቅን
ዃላ ዃላ _ ተናናቅን
መጨረሻ
.
.
.
.
.
.
.
.
.

.
.





😏

#ሼን ✍

1k 0 11 2 13

Video is unavailable for watching
Show in Telegram
Kebisha🤞

Like & Share
😘


ስተን
ስተን ጥሩውን ከመጥፎ መለየት አቅቶን
ጥሩ እንዳይርቀን ፊቱን እንዳይነሳን
ሰግተን
ዳር ድንበሩን አይተን ጦርነት ፈርተን
ንጉሱ ባጠፋው እኛ ህይወት ሰተን
ጥረን
ጥረን ለህይወታችን ብለን መኖርን ፈልገን
አንገት አቀርቅረን ጉልበታችን ሰብረን በእንብርክክ ሄደን
ለምነን
ለምነን ከፊታቸው ወድቀን
እጃችን ዘርግተን ምረትን ጠይቀን
አሸርግደን
ሞቱ ለማይቀረው ለህይወታችን ሰግተን
ፈጣሪ እያለ ለንጉሱ ሰግደን
ተቸግረን
ተቸግረን የምንበላው አተን
ፈጣሪን ሳንጠይቅ እነሱን ለምነን
ጠይቀን
ትልቁ እያለ ትንሹን ተማፅነን
ሀያሉ እያለ ለአቅመ ቢስ ወድቀን
ደንዝዘን
ፈጣሪን በመያዝ መጠንከር ሲገባን
በህይወት እያለን በቁማችን ሞተን
ገሀነም ሳንገባ እዚው ተቃጠልን
ጥፋታችን
ዋ ጥፋታችን እንደው መከራችን
በህይወት እያለን በቁም መሞታችን
✍ ABD


😔ይድረስ ለነንትና😔
✍ራዚ...😉

እኔ ስወዳችሁ፣ይበልጥ ስቀርባችሁ፣
እናንተ ጠልታቹኝ፣እጥፍ የራቃችሁ፣
ለደስታችሁ ብዬ ደስታዬን በተውኩኝ፣
እንደ ሞኝ ቂላቂል ፋራ ያያችሁኝ፣
ትልቁን ንብረቴን ልቤን ብሰጣችሁ፣
ለሌላ 'ን 'ኳ እንዳይሆን ሰብራችሁ ሄዳችሁ፣
ህመሜን ሸሽጌ ራሴን አክሜ፣
ያለፈ ስህተቴን ላልሰራ ደግሜ፣
ከሄድኩኝ ቡሃላ ሁሉን ነገር ትቼ፣

ደሞ ምን ቀርቷችሁ ወደ ኔ መጣችሁ፣
የልቤ መሰበር ክፉኛ ጎድቷችሁ?
ወይስ ስላልሞትኩኝ እቅድ ከሽፎባችሁ?

#እኔ_ግን

እናንተን አልሻም በራሴ ቆሚያለሁ፣
በፈጣሪ ፈቃድ አቅሜን አውቂያለሁ፣
ከአስመሳይ ሰዎች መራቅ ወስኛለሁ፣
የራሴ የምለው ጓደኛ አግኝቻለሁ፣
ከሰዎች ተገልሎ መኖር መርጫለሁ፣
እናንተም ላትመጡ እኔም ርቄያለሁ

ገጣሚ:ዑስማን|ራዚ...😉|


ግጥም

ከቃላት ስብስብ ከመፃፍት ማህደር
ከሊቅ ፀሐፍቶች ከአዋቂዎች መንደር
የቅን ልብ መግለጫ አንቺን የሚመስልሽ
ፈልጌ አስፈልጌ ቃል አጣሁ ሚገልፅሽ!።

አለኝ ብዙ መውደድ አለኝ እልፍ ፍቅር
መግለፅ ስላልቻልኩኝ ፍፁም እንዳይልሽ ቅር
ብቻ እንድታውቂው እኔ ደስ እንዲለኝ
አንድ ነገር ልበል በልብሽ ፃፊልኝ!

እ - ወ - ድ - ሻ - ለ - ው ❤️🔥


ትስማማላችሁ

Like👍


ተያዘ
በቅስበት አምልጦኝ በድንገት ጮሀብኝ
እሱም በድርጊቴ በጣምም ሳቀብኝ
ያኔ ያኔ ነውር ነው ብሎኛል እሱ እንደማይፈሳ
ማይደርስ ቀን የለም ይሀው አሁን ያዝኩት ከፊታችን ፈሳ
✍ABD


''ቱ በል ልምታልህ'' አለችው
ሲያለቅስ አቀፈችው

''ቱ አለ

በእጇ መታችለት በጥፊ መሬቱን
ማልቀሱ አበቃ አቆመ ምሬቱን


      ''አደገ ትልቅ ሆነ"

ህይወትን ቢቀየም
ለብቻው አዘነ በዕንባ ላይወጣለት

ዛሬ ሰው የለውም
ጊዜን ማን ይምታለት
❓😢


#የሟቹ_ኑዛዜ

የምንዱቡን ትንፋሽ
ሞት በግፍ ቢነጥቅም
ሟች ቀኑን ያጣ ቀን
ገዳዩ አይታወቅም ፤
አፋኙ ጣረ ሞት
አንደበቱን ይዞ ነፍሱን የነጠቀው
በምን ይናገራል ገዳዩንስ ቢያውቀው
ብቻ ጀምበር እድሜው
በመአልቱ ጽልመት ማልዶ የታገተ
እስከሽበት ዘልቆም አፍ ሳይፈታ ሞተ
ምናልባት ምናልባት እንደመልካም እጣ
ድንገት በለስ ቀንቶኝ የኔም ቀን ከመጣ
ሚጠይቁም ካሉ
ያሟሟቱ ነገር እንዲህ ነበር በሉ
'ሲለው መሶብ መስሎ ጎድሎ እንዳጎደለው
ሲሻውም ቀን ሁኖ ከፍቶ እንደበደለው
እድሜዉን በልቶ ነው ዘመን የገደለው!

✍ ኢዛና መስፍን


ምን አለን ከጊዜው ምን አለን ከቀኑ፣
በአቆጣጠር ብቻ ቢለወጥ ዘመኑ።

ዘመን ተቀይሮ አዲስ ነው እንዲባል፣
ሰውም እንደ ጊዜው ሊቀየር ይገባል::


©Wendme


ሴት አይቅናው !

ሄዱ አብረው ጊዜና እሱ
ወዴት ቆሙ የት ደረሱ ?
ማን ተጠጋው ?
ማን አወጋው?
ማን አለፈው ?
ማን አቀፈው ?

ይጨንቀኛል ....

የለሁበት በህይወቱ የለሁበት በመንገዱ
ይቃዠዋል ልቤ እብዱ

ምን ቤት ቤቴ ? ምን ቤት ጣሪያው?
የሚስለው ዙሪያ ገባው
ለሄደ ሰው ምን አገባው

ምን ቤት ልቤ ምን ቤት አይኔ እየሳቡ የሚያመጡት
ምን ይገዳል ምንስ ቢሆን ከእጅ ያወጡት??

እንጃ..!!

ብቻ..
የተኛበት እንዳይሞቀው        
እመኛለሁ ሴት ባያውቀው
እመኛለሁ ሴት ባያቅፈው
ሄዋን ሳያውቅ እድሜ ቢያልፈው

እመኛለሁ ባይዳበስ
እመኛለሁ ባይታበስ
እመኛለሁ ለፍቅር ያለው ባይሳካ
እንኳን ገላው የፀጉሩ ጫፍ ባይነካ

ይጨንቀኛል ...

ቁርጥ አርጎ ለሄደ ሰው ልቤን ሐሳብ እየጠናው
እመኛለሁ በደፈናው
እመኛለሁ ሴት ባይቀናው...
.
.
.
ሴት አይቅናህ ..... 😞


ኧረ በላይክ አለን በሉኝ😭❤️❤️


ስጦታ
ልክፈተው? ሰጦታውን
ምን ይኖረው ይሁን?
ልብሽ ነው ያለበት?
ወይስ ባዶ ነው
ስጦታ የሌለው
ውጪው ያማረ
ውስጡ የተራበ
ሀዘን ያነገበ
ወይስ ስጦታ አለው?
የድሮ ማንነትሽ ውስጤ የተራበው
ተጎዳሁ አልልም
እንደ አቅመ ቢስ እኔ አላለቅስም
ብትቀየሪም
ሌላ ሰው ብትሆኚም
ከባድ አውሎ ንፋስ ከኔ ቢነጥቀኝም
በአካል ብርቂኝም መልክሽን ባላይም
እኔ አላለቅስም
ህፃን አይደለሁም
✍ABD


ዛሬ
ዛሬ ምንድነው ቀኑን ጠይቁኛ
ዛሬ ልደቴ ነው ሆኛለው ደስተኛ
ኑ ተቀላቀሉኝ ደስታ ተካፈሉኝ
ያለኝን ልስጣቹ ያላቹንም ስጡኝ
ደስታ ብቻ ነው ሀዘን ምንም የለም
መጠጡ ባይኖርም ፓሪ ባይዘጋጅም
ስጦታ ባላይም ኬክ ባይቆረስም
በቃ ኑ ደስታዬን ልስጣቹ ደስታቹንም ስጡኝ
ያለኝን እንካፈል ያላቹን አካፍሉኝ

መልካም ልደት ለኔ
✍ ABD


ፍጥጫ
እያሰኘኝ ሳይኖረኝ ምንም ላላገኝ ያለአቅሜ ስመኝ
እላይ እላይ እያሰብኩ ከመሬት ላይ ስገኝ
በሀሳብ ወጥቼ መገኛዬን ትቼ
እታቹን ፈርቼ የላዩን አይቼ
እላይ እላይ አስቤ ለታቹ ቀርቤ
በሀሳብ ጠግቤ በእውነት ተርቤ
ሀሳብ ሆነ ብቻ የሌለው መክፈቻ
ሁሌ ሽኩቻ ከእውነት ጋር ጥላቻ
መነሻ ሳይኖረኝ መዳረሻ እያልኩኝ
ሀሳብ ብቻ ሆነብኝ ሀዘን አመጣብኝ
ከፍታውን ብተው መነሻዬን ባየው
ችግሬን ባገኘው ስቃዬን ባስበው
ይሄኔ እላይ ነኝ
ሀሳብ የነበረው እውነታ ሆኖልኝ
✍ABD

20 last posts shown.