በ84 ኮሌጆች የሚማሩ ተማሪዎች፤ እስከ ጥር ወር መጀመሪያ ወደ ሌሎች የትምህርት ተቋማት እንዲዘዋወሩ ትዕዛዝ ተሰጠ
የፌደራል የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፤ 84 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እስከ መጪው ጥር ወር መጀመሪያ ድረስ ተማሪዎቻቸውን ፈቃድ ወዳላቸው ተቋማት እንዲያዘዋውሩ ትዕዛዝ አስተላለፈ። ባለስልጣኑ ይህንን ትዕዛዝ የሰጠው፤ በድጋሚ ሳይመዘገቡ ለቀሩ እና በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን ለማቋረጥ ለወሰኑ ኮሌጆች ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባወጣው “አዲስ ስታንዳርድ” መሰረት፤ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቦ የነበረው ባለፈው መስከረም ወር መጀመሪያ ነበር።
በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚንቀሳቀስ ማንኛውም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፈቃድ የመስጠት፣ የማደስ እና ቁጥጥር የማድረግ ስልጣን ለመስሪያ ቤቱ የሰጠው በ2014 ዓ.ም. የተሻሻለው የባለስልጣኑ ማቋቋሚያ ደንብ ነው።
መስሪያ ቤቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ፈቃድ ወይም እድሳት የመሰረዝ ስልጣንም በዚሁ ደንብ አግኝቷል።
በዚሁ መሰረት 84 የሚሆኑ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት “ከከፍተኛ ትምህርት የፈቃድ ስርአት እንዲወጡ” የሚያደርጋቸውን ውሳኔ ባለስልጣኑ ከሁለት ሳምንት በፊት አስተላልፏል።
ዘጠኝ በሚሆኑ የትምህርት ተቋማት ላይም ተመሳሳይ ውሳኔ በቅርቡ እንደሚተላለፍ ከባለስልጣኑ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2024/14683/