Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


የሰው ሐቅ ካለብህ ከቻልክ መልስ፤ ካልቻልክ ዐውፍ አስብል። የሰው ሐቅ ሌሊቱን ሲሰግዱ በማደር፣ ቀኑን ጹሞ በመዋልና አንድ ሺህ ጊዜ ቁርኣን በማኽተም አይካካስም። አላህም በሰዎች መካከል ስላለው ሐቅ ጣልቃ እንደማይገባ ነግሮናል።

حقوق العباد لا تسقط
بطول قيام ولا حسن صيام ولا بألف ختمه قرءان…

1.8k 0 15 14 48

መጀመሪያ እንዳልስቅ ኑ አፌን ያዙልኝ።

ሲቀጥል የመንግስት ሆስፒታል ውስጥ የአንድ እምነት ተከታይ ብቻ አይገለገልም። ታዲያ የእምነቱ ተከታይ ባልሆኑትም ላይ ነው የጮኹባቸው? ኃይማኖትና መንግስት ይለያያል ይሉና ህጉ የሚተገበረው እስልምና ላይ ነው። አሁን ይህን እንደ ጀብዱ መዘገብ ምን ይባላል?

ይህኔ ሙስሊሞች ይህን ቢያደርጉ ኖሮ ቦምብ ሊያፈነዱ መጡ ሊሉ ይችላሉ።

ለማንኛውም ዘንድሮ ከእስከዛሬው አንፃር አደብ አስተውለናል! ምን ተገኝቶ ነው¿ ወይንስ ምን ታጥቶ ነው¿ ሁሉም በራሱ ቢዚ ሲሆንና ድካውን እያወቀ ሲመጣ ጥሩ ነው።

11k 0 19 105 369

አንድ የሚገርመኝ ነገር… ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሙስሊሞች በጣም ጠንካራና ጀግና የዲን ሰው መሆናቸው ነው። ሙስሊሙ በብዛት ባለበት አካባቢ ያለ ሙስሊም ይዘናጋል።

11k 0 0 18 244

የሆነማ የተምታታ ነገር አለ!


ስሙ'ማ…

የትኛውም አይነት (ኢስላማዊ ቢሆንም ባይሆንም) የአማርኛና የዐረብኛ ጽሑፍ ትርጉም ያለው በሶፍት ኮፒ ያላችሁ በውስጥ ላኩልኝ።
ልብ በሉ! የምትልኩልኝ ነገር፤ ለምሳሌ የአማርኛ የቁርኣን ተፍሲር አለ አይደል?
በአንድ በኩል ዐረብኛ፣ በሌላ በኩል አማርኛ ያለው፤ እንደዛ አይነት ነው የምፈልገው። ለምሳሌ፦ የተለያዩ ኪታቦች ትርጉም፣ የተለያዩ ማንኛውም አይነት ጽሑፍ ትርጉም፣ የዜና ሊሆን ይችላል። ብቻ ግን ትርጉም የራሱ መሆን አለበት። ከመክተባዎችም፣ በእጃችሁ ላይ ያለውንም፣ በአፕ መልክ ያለም ካለ ላኩልኝ ሁሉንም፤ ያገኛችሁትን ሁሉ።

በቴሌግራም t.me/Murad_Tadesse ላይ ላኩት! ኢሜይል ከፈለጋችሁም እሰጣችኋለሁ።



14k 0 12 13 55

ባሎች… አንዳንድ እህቶች በተዐዱድ ጉዳይ የማወራውን እንዳታዩ በማሰብ የኔን ቻነል እንዳትከታተሉ የሚጥሉባችሁ ማዕቀብና የሚደርስባችሁ ጭቆና እንዲሁም መሳቀቅ መረጃው ደርሶኛል¡ በቅርቡ መፍትሄ እንፈልጋለን።
ግን ይህን ያደረጉት ለክፋት ሳይሆን እንደማይሆንላችሁ ታዝበው ይሆናል።

እነርሱ ራሱ አምነውበት ከቶ እናንተ አቅሙ ካላችሁ ደግሰው እንዲድሯችሁ ሎቢ የማድረስ ሥራ እጀምራለሁ¡ ኢንሻ አላህ አንድም ላጤ ማየት አልፈልግም።

14.7k 0 6 129 250

Forward from: ሐላል ድጅታል ኔትወርክ (Halal Digital Network -HDN) 🇪🇹
ለአሏህ ብላችሁ እህቴን  አፋልጉኝ‼️

የተፈላጊዋ ስም ሻዱ ተማም እ/ኮርማ ትባላለች የአንድ ልጅ እናት ስትሆን አድራሻዋ ሳንኩራ ወረዳ ጃታ ቀበሌ ሲሆን በቀን 6/5/2017  ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም ተፈላጊዋ ከቤት ስትወጣ ሰማያዊ ጅልባብ ለብሳ እንደነበርና እኛ ቤተሰቦቿ ትመለሳለች ብለን ብንጠብቅም መመለስ ስላልቻለች በተለያዩ አማራጮች የማፈላለግ ሥራ የተሰራ ቢሆንም ተፈላጊዋን ማግኘት ባለመቻላችን ቤተሰቦቿ በጭንቅ ላይ መሆናችንን እየገለፅን እህታችንን ያገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው ስልክ ቁጥር በመደወል እንድታሳውቁን ስንል  በአሏህ ስም ይጠይቃሉ።

ስልክ ቁጥር:-
             0916181538
             0916715993
             0916268571


በሐኒፍ ኢስላማዊ ድርጅት አዘጋጅነት ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በአፋር ክልል ወረር ከተማ እና አከባቢዋ ሲካሄድ የቆየው የኮርስ እና የዳዕዋ መርኃግብር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል!

በመርኃግብሩ ለተማሪዎች አጫጭር የዐቂዳ ፣ የሐዲስ እና የፊቅህ ኪታቦች በኮርስ መልኩ የተሰጡ ሲሆን በከተማው እና አጎራባች አከባቢዎች የጁሙዓ ኹጥባ ፣ የመስጂድ እና የጎዳና ዳዕዋዎች ተደርገዋል።

መርኃ ግብሩ የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱ የክልሉ መጅሊስ አመራሮች ፣ የመስጂድ ኢማሞች አና ከጎናችን ለነበሩ ወንድሞች በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እያቀረብን ፤ አላህ ስራቸውን እንዲቀበላቸው እና በመልካም ስራ ሚዛናቸው ላይ እንዲያኖርላቸው እንማፀናለን።

Hanif Islamic Organization ∣ مؤسسة حنيف الإسلامية


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ግን አላህ የዋለልንን ልዩ ጸጋዎች አስታውሰን አልቅሰን እናውቃለን⁉️

16k 0 29 11 188

«ዛሬ Business class እና Economy class እያልክ የምትመርጥበት አውሮፕላን፤ ነገ በCargo class ልትሳፈርበት ትችላለህ።»
ሰዒድ


Forward from: Mizan Tv - ሚዛን ቲቪ 🇪🇹
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ②①②⑧]👌


#ቁርኣን


Forward from: Mizan Tv - ሚዛን ቲቪ 🇪🇹
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ②①②⑧]👌


#ቁርኣን


Forward from: Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ከሸይኽ ዶ/ር ሷሊሕ ፈውዛን ጋር ፈገግ በሉ!


አንዷ እንዲህ ብላ ጠየቀቻቸው፦

«ባሌን 2ኛ ሚስት ብድረው ችግር አለው ወይ? የገንዘብ አቅሙ የለውም። የሚተዳደረው በኔ ገንዘብ ነው። ሁለተኛይቱንም ካገባ ያቺንም የሚያስተዳድርበት ገንዘብ እኔ እችለዋለሁ።» ብላ ጠየቀች።


ሸይኹ ራሱ ገርሟቸው «የት ነው የምትገኘው?» አሉ!
«እንዲህ አይነቷ'ማ ከተገኘች ያልተለመደ እንግዳ ነገር ነው!» አሉ።
ለማንኛውም ችግር የለውም ብለዋል።


እንዲህ አይነቷን ካገኛችኋት ፈላጊዎቿ ብዙ ናችሁ ኣ¿

||
t.me/MuradTadesse

16.6k 0 86 53 304

19/ 🌙 رجب
لا تقل من أين أبدأ ..
طاعة الله البداية ..
لا تقل أين طريقي ..
شرع الله الهداية ..
لا تقل أين نعيمي ..
جنة الله كفاية ..
لا تقل غدًا سأبدأ ..
ربما تأتي النهاية .. ‏


Forward from: STEM with Murad 🇪🇹
«ሰሞኑን በተቀናጀና በተደራጀ መልክ በሕገ ወጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ወይም ግብር መክፈል ሲገባቸው ግብር የማይከፍሉ ዜጎችን ሕጋዊ ለማድረግ በርካታ አዳዲስ ሕጎች እየወጡ እንደሆነ እያየንና እየሰማን ነው። የክፍያ ተመኑ የተጋነነና ውጤቱ ፈታኛ ቢሆንም፣ ሁሉም ዜጋ እንደ ዜጋ ከሚያገኘው ገቢ ላይ ተመጣጣኝ፣ አቅሙ የሚፈቅድለትን ፍትሐዊ ግብር መክፈሉ የሚያነጋግር ጉዳይ አይደለም። የዜግነት፣ የሞራልና የፍትሐዊነት ግዴታ አለበት።

ነገር ግን ፤ በ20ና በ25 ሺ ብር ደሞዝ የ70 ሺ ብር ኮትና ሱሪ ለብሰው፣ የ15 ሺ ብር ሸሚዝ አድርገው ፣ የ30 ሺ ብር ጫማ ተጫምተው፣ የ15 ሺ ብር ሰዓት አስረው የ7 ሚሊየን ብር ተሽከርካሪ እያሽከረከሩና የ30 እና የ40 ሚሊየን ብር ቤት ውስጥ የሚምነሸነሹ ተሿሚዋች፣

ሴቶቹ ከሆኑ ደግሞ የ50 ሺህ ብር ሒውማን ሔይር ተላብሰው፣ የ60 ሺ ብር ካፓርት ደርበው፣ የ20 ሺህ ብር መነጽር አንጽረው፣ የ30 ሺህ ብር ጫማ ተጫምተው፣ የ36 ሺ ብር ቦርሳ አንግተው መድረክ ላይ እየተውረገረጉ ምንጩ ያልታወቀ ሐብት በዝቷል እንወርሳለን፣ ነጋዴውና ባለሀብቱ ሙሰኛ ነው፣ ኦዲት እናደርገዋለን፣ ሕዝቡ በቂ ግብር ስለማይከፍል ላቡን አንጠፍጥፎ በሰራው ቤት ላይ በነጻ ስለሚኖር ግብር መክፈል አለበት የሚሉ ሰዎችን ማዳመጥ የሚሰቀጥጥና የሚያሸማቅቅ ነገር ነው ።

ይሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ እንዲሉ መጀመርያ ማን ማንን ነው የሚወቅሰው? ኦዲት የሚያደርገው ? እራሱ ግብር ሳይከፍል ግብር የሚያስከፍለው ? ምንጩ ባልታወቀ ሐብት የሚንፈላሰሰው፣ በሙስና ስለተገኘና ምንጩ ባልታወቀ ሐብት መጠርጠር፣ መመርመርና ኦዲት መደረግ ያለበትስ ማን ነው ?!

በኑሮ፣ ውድነት የሚፈተነው ሕዝብ፣ ነጋዴውና ባለሐብቱ፣ እድሜ ልኩን ጥሮ ግሮ ባፈራው ጥሪት መኖርያ የቀለሰው ታታሪ ደሞዝተኛ ወይስ በ20 እና በ30 ሺ ብር ደሞዝ በውድ ሸቀጣ ሸቀጥ የሚንቆጠቆጠው፣ ውድ ሽቶ የሚርከፈከፍው፣ በቅንጡ ተሽከርካሪ ከነቤተሰቡ የሚምነሸነሸውና በመንግሰት ደሞዝ ልጆቹን ውጭ ሀገር እያስተማረ በዓመት ሁለቴ ዱባይ ካናዳና አሜሪካ የሚመላለሰው !!??»
ሙሼ ሰሙ

||
Join:
https://t.me/STEMwithMurad

15.8k 0 21 20 279

ላጤዎች… ረስቻችሁ አይደለም።

የሆነ ገራሚ እቅድና ፕሮፖዛል እያዘጋጀሁላችሁ ነው! (መቼም የናንተ ነገር እንቅልፍ እንደሚነሳኝ ታውቃላችሁ¡)

3 ሃሳቦች አሉኝ፦

①) ገንዘብ እያለው፣ የማስተዳደር አቅም ኖሮት ትክክለኛ ጥንዱን ማግኘት የተቸገረ አለ። ብዙዎቻችን ገንዘብ ካለ ቀጥታ ትዳር መያዝ ቀላል ይመስለናል። ግን ሁሉ ነገር ተሟልቶ ትክክለኛ አጋርን ማግኘት ከባድ ነው።

ልክ እንደዚሁ ተፋተውም ሆነ በውርስ አሊያም ሠርተው የገንዘብ አቅም ያላቸው እህቶች አሉ። ግን ጥሩ የትዳር አጋር አጥተዋል። ገንዘባቸው እንኳን ለነርሱ ለሌላም ይተርፋል። ታዲያ ለዚህች አይነቷ ጎበዝ ልጅ ፈልገን ድረን በጉልበቱ ገንዘቧን እየሠራ የበለጠ ያስተዳድግላታል፤ ከዛ አብረው በሰላም ይኖራሉ፤ መልካም ትውልዶችንም ያፈራሉ።


②) መጀመሪያ ቁጥር 1 ላይ ያሉትን ካገባደድን፤ «በሉ! እናንተ ያላችሁበትን ጸጋ ሌሎችም ይቋደሱ!» ብለን የተወሰነ ያክል ኪሳቸው ሳይጎዳ እንቀበላቸውና፤ በገንዘብ ምክንያት ትዳር ለመያዝ የፈሩ ወንድሞችን ቢቻል የግል ቢዝነሳቸውን በማቋቋም፤ አሊያ ግን በየወሩ ቋሚ ደመወዝተኛ ከሆኑ የሰርግ ቀን ወጪያቸውንና የቤት ሙሉ አስፈላጊ ማቴሪያሎች እናሟላላቸዋለን።


③) በተለያዩ ምክንያቶች (በበሽታ፣ በአካል ጉዳት) ወዘተ ከትዳር የታቀቡ ካሉ አምሳያቸውን በመፈለግ ማገናኘት።

በተለያዩ ሰበቦች እድሚያቸው የገፉ ወንድምና እህቶችም አሉን። በእድሚያቸው ስንቱ ሲመኛቸው እንዳልነበር፤ ስንቱን የወላጆቻቸው ደጅ እንዳልረገጠ፤ ዛሬ ግን ማንን ባገኘሁ የሚሉ። አላህ ይፈርጃቸውና!

ይህ ሁሉ የሚሆነው አንድ ራሱን የቻለ የዘርፉ ብቁ ባለሙያዎች ያሉበት ነገር አቋቁመን፤ ሳይጋቡ በፊት በቂ ስልጠና የሚሰጥ፣ ከተጋቡ በኋላ የሚያማክር፣ እነርሱን ብቻ ሳይሆን ፍች እየበዛ ስለሆነ የሚያማክር አነስተኛ ተቋም መስርተን ነው።


ትስማማላችሁ⁉️ እናንተ የትኛው ላይ ናችሁ?
እስኪ ያለውን ፍላጎት ለማጥናት በውስጥ አስፍሩልኝ!


||
@MuradTadesse

19.3k 0 62 603 673

لا تزرع في أرضي شوكا
لعلك غداً تأتني حافيا

20.4k 0 24 38 171

ማታ ነው፤ ጨልሟል። ለራት መስሪያ ማገዶ ውጭ ላይ ስለነበር፤ ሚስት ወጥታ ለማምጣት ፈራች፤ አውሬ እንዳይበላት። ባሏን «አምጣልኝ!» አለችው። ለካ እርሱም ፈርቷል። ምን ቢል ጥሩ ነው፦ «ብቅ በይልኝና ላምጣልሽ!»

ብቅ ካለች'ማ ራሷ ታመጣው የለ እንደ!
★
እንደው ሌላው ቢቀር ተከተሉኝና ልምራችሁ የሚለን ተቋም እንደት አጣን?

21.9k 0 22 74 616


20 last posts shown.

93 422

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

እነሆ… ተጀምሯል‼ ============== (የመረጣችሁበትን ስክሪን ሹት ኮመንት ላይ ላኩት፤ እናጠለቅልቀው፤ ዘመቻውን እንቀላቀል!) || ✍ 10 ሚሊዮን ...
መልኩንም ስሙንም ሐፍዙት፤ በመዝገብ ላይ አስፍሩት‼ ከታች በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ግለሰብ ስዩም ካሕሳይ ይባላል። ሙስሊሞችን ከሰው አይቆጥርም ማለት ...
እና አልሞትንም ትላላችሁ⁉️ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብ መልበስ ተከልክለው ጸጉራቸውን ገልጠው እየተማሩ ያሉ መኖራቸውን ሰምታች...
Post #38830: Video
ሙስሊም ሲሆን ወንጀለኛ የተባለው (ያው ሳይረጋገጥ)፤ ስሙ ከነ አያት ቅማቱ ይጻፋል። የጎጃም፣ የጎንደርና የወለጋ የንፁሐን ደም መጣጭ አሸባሪ ሲሆን ግን ...