🍌ባናና ሙዚቃ🎶የሙዚቃ ግጥሞች ™


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Music


🇪🇹 የዘፈን ዓለም 🌍

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Music
Statistics
Posts filter


🎈ታላቅ ቅናሽ📣
📢#ሸገር_መድሀኒት_ማከፋፈያ
#የስንፈተ_ወሲብ_ችግርና_የብልት_ቁመትን_በሳምንት_ውስጥ_መፍታት_የሚችል
❌☠ጥራት ከሌለዉ አደጋ አለዉ👹☠
🔴 እባኮን በተመሳሳይ ምርት እንዳይታለሉ
🔥 እባክዎን የተለያዪየስንፈተ ወሲብ መዳኒቶች ከመጠቀሞት በፊት እኛን ያማክሩን
🔸️የብልት ቁመትና ዉፍረት በዘላቂነት ለመጨመር
🔸️በግንኙነት ወቅት ቶሎ ለመጨረስ ችግር
🔸️ ለብልት ጡንቻ ጥንካሬ አና ለስሜት መቀዛቀዝ ችግሮች
🔸️💯% #original #Max_man #vimax ....
⚠️ወደ ክልል ከተሞች በተለያዩ አማራጭ ተደራሽ እናደርጋለን
👉Price 3000birr
Contact👇
☎️ 0926894416
🥌 በኢትዮጵያ ህጋዊ አስመጪ እና አከፍፍይ ሸገር መድሀኒት ቤት   #Sheger_Pharmacy
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇 #Ethiopia
+251926894416


የፍቅር አጋር እፈልጋለሁ
22 አመት በታች የተከለከለ
🔞 ጓደኛ ለማግኘት 🔞
ከታች ባለው ሊንክ ይግቡ👇


🔞💋ለመመዝገብ ከትች ይምረጡ 🔞💪
@Sex_gentbot
... @Sex_gentbot ...


Forward from: 🇪🇹Ethiopian Hot Sex💋❤™
🇪🇹 ምን አይነት ቻናል መቀላቀል ይፈልጋሉ?
👇👇👇🙄👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


ቃልአብ ክንፈ(ቃል ኪን)- ወስኗል / Kal kin – Wesenuwal

ሀሳብ ይዞሽይ ሆናል በእኔ እና አንቺ ነገር
እውነቱን ነው ብለሽ እንደ መደናገር
ካሳለፍሽው ህይወት ነው ነገሩ ገብቶኛል
የወደድኩሽ የእውነት ነው ልብ አምኖ ወስኗል

ወስኗል ልቤ ወስኗል ወስኗል
ወስኗል … ወዶሽ አምርሯል ወስኗል
ወስኗል ልቤ ወስኗል ወስኗል
ወስኗል.. በፍቅርሽ ወድቋል ወስኗል

ሰዉ እንደው ካለው ሳያገግም
ህመሙን አይፈልግም መድገም
ፍቅር እንደው አይሆንም በወሬ
ማሳየት የምሻ ነኝ ኖሬ

ጠርጣራ ያደርጋል አውቃለው
ፍቅርን መጀመር ተሰብሮ
ባልወድሽ የእውነት አምርሬ
አልሻም መጀመር ደፍሬ

ሀሳብ ይዞሽይሆናል በእኔ እና አንቺ ነገር
እውነቱን ነው ብለሽ እንደ መደናገር
ካሳለፍሽው ህይወት ነው ነገሩ ገብቶኛል
የወደድኩሽ የእውነት ነው ልብ አምኖ ወስኗል

ወስኗል ልቤ ወስኗል ወስኗል
ወስኗል … ወዶሽ አምርሯል ወስኗል
ወስኗል ልቤ ወስኗል ወስኗል
ወስኗል.. በፍቅርሽ ወድቋል ወስኗል

መልክ አልባ የሚሞቅ የሚበርድ
ጊዜ የሚያይ አደል የኔ መውደድ
ሚመሰል በፀሀይ ጨረቃ
አያውቅም የኔ ልብ ፈረቃ

መሬትም ጠላሁኝ አልሄድበት አልወድቅም አልልም
ወጀቡን አምኜ ጥሻ ከቶኝ መልኩ ቢያታልለኝ
አይደለም አንድ አይነት ሰው በሙሉ እንደ መልኩ ሁሉ
ጠይም ነው ጥቁር ነጭ የቀይ ዳማ ጥሬና ብስሉ

ኧረግ እናናዬ እናናዬ ኧረግ እናናዬ
እመኚኝ እናናዬ ወድሻለው እመኚኝ እናናዬ
ከልቤ ካንጀቴ ነው መውደዴ እመኚኝ እናናዬ
ምስክርም የለኝ እናናዬ ፍቅሬ ነው እምነቴ

ኧረግ እናናዬ እናናዬ እመኚኝ ናናዬ

እመኚኝ

@Musziqahiwote_lyrics
@Musziqahiwote_lyrics


ተአምር ግዛዉ-ምነዋ / Teamer Gizaw -Minewa


አያምጣዉ ነዉ እንጂ አያድርስ
የሰዉ ሰዉ ተወዶ የታል ክስ
ምነዉ ፍቅርህ ትጥቄን ሊያስፈታ
በኔዉ በጭምቷ በረታ

ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ምነዉ በሆንኩኝ ግድ የለሽ
ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ልቤን ከፍቅርህ እንዳሸሽ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

በማላዉቀዉ ነገር ድንገት
ተሰብስቤ ካለሁበት
ባትነካካኝ ምን አለበት
ምነዋ ምነዋ

በማለዳዉ ፍቅር ገብቶ
ልቤን በአንተ አስደስቶ
የነገርከኝን ሰንብቶ
ምነዋ ምነዋ

ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ምነዉ በሆንኩኝ ግድ የለሽ
ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ልቤን ከፍቅርህ እንዳሸሽ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

አያምጣዉ ነዉ እንጂ አያድርስ
የሰዉ ሰዉ ተወዶ የታል ክስ
ምነዉ ፍቅርህ ትጥቄን ሊያስፈታ
በኔዉ በጭምቷ በረታ

ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ምነዉ በሆንኩኝ ግድ የለሽ
ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ልቤን ከፍቅርህ እንዳሸሽ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

ፅኑ ፍቅሬም ላያባራ
ምኞት ህልሜን ላትጋራ
ልቤን ባልሰጥ ላንተ አደራ
ምነዋ ምነዋ

ይቀል ይሆን በምን ብርታት
ሁለት ፀፀት ሁለት ቅጣት
አንተን ማግኘት አንተን ማጣት
ምነዋ ምነዋ

አድሮ እንደጥርስ ህመም ለሚጠዘጥዘኝ
ለዚህ ለዚህ ነዉ ወይ ያንተ ፍቅር የያዘኝ
በቅናት ላይ ቅናት እየደጋገመኝ
ስንቴ ሞቼ ነበር ሳልል አመመኝ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

@Musziqahiwote_lyrics
@Musziqahiwote_lyrics


ሄዋን ገ/ወልድ – ከምኔው / Hewan G/weld – Keminew

ወይ ላትናገር ወይ ላትረዳ
ወዲ ወዲያ እያልክ ደርሶ እንደ እንግዳ
ማረግህ ሳያንስ እኔን ባለዳ

ሁሉን ካሟላው ካካልህ በላይ
ከአይኔ አልፎ ድንገት ቀያይሮ ፀባይ
ምኔው ተገኘ ፍቅርህ ልቤ ላይ

ምኔው ለምጄህ ለምጄህ አረፍኩ ወድጄህ
ምኔስ ነው ስፍስፍ ነው ስፍስፍ ያረከኝ ክንፍ

አሆሆ ባልሞቁበት ፀሀይ
እህህ ባልተጠጉት ዋርካ
አሄሄ ደርሰው ልክ እንዳንተው
እህህ ማረፍ አለ ለካ

አሆሆ አካሌን ለመውረስ
እህህ እንዲ በትካዜ
አሄሄ መች እስካስብ እንኳን
እህህ ፍቅርህ ሰጠኝ ጊዜ

ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነውሳ
ልበ ቢስ የሆንኩት ባንተው የተነሳ

ከምኔው ከምኔው ከምኔውደሞ
እንዳልተው ያረገኝ ናፍቆትህ አዳክሞ

[ እንዳልተውህ እንዳልተውህ
ሰበብስ የት አለኝ ያላንተው

እንዳልተውህ እንዳልተውህ
ወይ ከኔ አካል ጎሏል ወይ ካንተው] 2x

ምነው ለምጄ ለምጄ አረፍኩ ወድጄህ
ምኔስ ነው ስፍስፍ ነው ስፍስፍ ያረከኝ ክንፍ

አሆሆ አልሰለችሽ አለኝ
አህህ ሳስብህ መዋሉ
አሆሆ ደርሶብኝ ነው ባንተ
አሄሄ የፈራሁት ሁሉ
አሆሆ እንጃልኝ መውደድህ
አህህ ምን እንደፈለገ
አሄሄ ይመልሰኝ ጀመር
እህህ ወሰድ እያረገ

ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነውሳ
ልበ ቢስ የሆንኩት ባንተው የተነሳ

ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነው ደሞ
ብክንክን ያረገኝ ናፍቆትህ አዳክሞ

[ እንዳልተውህ እንዳልተውህ
ሰበብስ የት አለኝ ያላንተው

እንዳልተውህ እንዳልተውህ
ወይ ከኔ አካል ጎሏል ወይ ካንተው] 2x

ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነውሳ
ልበ ቢስ የሆንኩት ባንተው የተነሳ

ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነው ደሞ
ብክንክን ያረገኝ ናፍቆትህ አዳክሞ

@Musziqahiwote_lyrics
@Musziqahiwote_lyrics


ሀሌሉያ ተ/ጻዲቅ- ካንተ ጋር / Haleluya T/tsadik – Kantegar

መለያየት ሞት ነው በሚለው ዘፍን …. በሚለው ዘፍን
በእምባ ታጥበን ነበር ስቴድ ተቃቅፈን … ስቴድ ተቃቅፈን
መሄድህን እንጂ መቅረትክን አላምነው .. መቅረትክን አላምነው
ዛሬ ነገ ሳትል ፍቅሬ ሳልሞትብህ ብትመጣልኝ ምነው

አሄ ሰው ሲያየኝ የተሸኮረመምኩተ
አሄ በዘፈን ማልቀስ የጀመርኩት
አሄ የፍቅር ደብዳቤ የፃፍኩት
ባንተ ነው ሁሉንም የሆንኩት

ካንተ ጋር በምሽት ደምቀናል
ካንተ ጋር በዝናብ ታጥበናል
ካንተ ጋር ተጣልተን ታርቀናል
ካንተ ጋር ሁሉንም ሆነናል

(በላኽው አንጀቴን በላኽው
እመጣለው ብለህ ሄደህ የቀረኸው) 2x

መለያየት ሞት ነው በሚለው ዘፍን …. በሚለው ዘፍን
በእምባ ታጥበን ነበር ስቴድ ተቃቅፈን … ስቴድ ተቃቅፈን
መሄድህን እንጂ መቅረትክን አላምነው .. መቅረትክን አላምነው
ዛሬ ነገ ሳትል ፍቅሬ ሳልሞትብህ ብትመጣልኝ ምነው

አሄ ፀሀይን ሲነጋ እምሞቃት
አሄ ጨረቃን ላይኔ የምናፍቃት
አሄሄ አበቦች ያልኩት ማማራቸው
ያኔነው ካንተጋር ሳያቸው

ካንተ ጋር አለም ትሞቃለች
ካንተ ጋር ቀኔ ትዋባለች
ካንተ ጋር ሁሉም ደስ ያሰኛል
ካንተ ጋር ሺ ዘመን ያንሰኛል

በላኽው አንጀቴን በላኽው
እመጣለው ብለህ ሄደህ የቀረኸው

@Musziqahiwote_lyrics
@Musziqahiwote_lyrics


ብጠራኝማ አለው አቤት
ስትልከኝ ማለቴም ወዴት
የኔ መውደድ ላንተ በደል
አርጎት ነበር ለካ ቀለል

ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ዋ ለኔ ዋ ለኔው

ያሻግርህ ያሻግርህ
ያሻግርህ ምን አለ
ያንተ መልካም ለኔ በትዝታ እስካለ
ካሻ ኑር ካሻ ኑር ይሙላልህ ያሰብከው
ደጉን ገላ ለምደህ የኔን ክፉ ካልከው

ከንፈር መምጠጥ መፀፀቱ
ባያስጥልም ከትዝብቱ
የኖሩት ቃል በሰቀቀን
ግርም ይላል ትዝ ያለ ቀን

ገረመኝ ገረመኝ
ገረመም ግር አለኝ
ትዝታን በስለት መቁረጥ ቢቸግረኝ

አመመኝ አመመኝ
አመመኝ በፅኑ
የኔ ልብ እንዳንተ አለመደንደኑ

ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ዋ ለኔ ዋ ለኔው

ብጠራኝማ እላለው አቤት
ስትልከኝ ማለቴም ወዴት
የኔ መውደድ ላንተ በደል
አርጎት ነበር ለካ ቀለል

ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ዋ ለኔው ዋ ለኔው

ያሻግርህ ያሻግርህ
ያሻግርህ በግዜ
መውደድ እስካረገኝ የትዝታ ሚዜ
ካሻ ኑር ካሻ ኑር ባሰብክበት ቦታ
ደፋ ቀና እላለው እኔው ለኔ ደስታ

ከንፈር መምጠጥ መፀፀቱ
ባያስጥልም ከትዝብቱ
የኖሩት ቃል በሰቀቀን
ግርም ይላል ትዝ ያለ ቀን

ገረመኝ ገረመኝ
ገረመም ግር አለኝ
እርሙሙ ስቶ ሆዴ
አንተን አንተን ሲለኝ
ሙሾ ባላሶርድ ደረቴን ባልመታ
አልቅሼው የለም ወይ ሳጣህ መንታ መንታ

ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ዋ ለኔው ዋ ለኔው

@Musziqahiwote_lyrics
@Musziqahiwote_lyrics


ታምራት ደስታ የምትወዱት

#ከዛሰፈር
በፍቅራችን ጊዜ ባንድላይ ላፍታም እንኳን ሳንለያይ..
የታየንበትን ያን ስፍራ ዛሬስ አይኔ ሊያየው ፈራ ..።
በቃ አልሄድም እኔ አልሄድም
#ከዛሰፈር እግሬ አይረግጥም
በቃ አልሄድም እኔ አልሄድም
#ከዛሰፈር እግሬ አይረግጥም ።

በጨረቃ ብርሃን ታጅበን ፈክተን እንደ አደይ ፤
እናስቀና ነበር ላስተዋለን አብረን ስንታዪ ።
ያንን ጣፋጭ ፍቅር ያን ዘመን ያን ጊዜ ባልረሳም ፤
አንቺ የሌለሽበት እኔ አልሄድም እግሬን አላነሳም ።

ይቅር ይቅር እንኩዋን ሌላው አንቺም ቀርተሻል ፤
ይቅር ይቅር መቼም ላላገኝሽ ሄደሻል ።

**************************************
እስቲ የሚያውቀው ካለ ይጨርሰው ።


Forward from: 🍌ባናና ሙዚቃ🎶የሙዚቃ ግጥሞች ™
አርቲስት: አብነት አጎናፍር
#_ማነው ያለው

ማነው ያለው አልልም አልጠይቅም፣
ማነው ያለው ብዬም አልጨነቅም፣
ማነው ያለው ምን አሉኝ ደግሞ ብዬ፣
ላልቆም ነገር ከመንገድ ከጉዞዬ።
ማነው ያለው ብዬ እኔ ሰው አልወቅስም፣
ማነው ያለው ውስጤን ላያውቀው ማንም፣
ማነው ያለው ስቆ ማለፍ መተው ነው፣
የሚያኖርም የሰራም ደግ አባት ነው።
አአአአአአይይይ
ለማን ብዬ ባዶነት ለሞላው፥
ለማን ብዬ ለገለባው ክብሬ፣
ለማን ብዬ ካበደው ጋር ልበድ፥
ለማን ብዬ ከጠፋው አብሬ፣
ለማን ብዬ እልህ ተጋብቼ፥
ጨካኝ ልሁን መራራቴን ትቼ።
ለማን ብዬ ባልተረጋገጠ፣
ለማን ብዬ መሬት ባረገጠ፣
ለማን ብዬ በደለበ ወሬ፣
ለማን ብዬ በወለደ በሬ፣
ለማን ብዬ ስጦታው ሰላሜን፣
ለማን ብዬ ልነጠቅ ደስታዬን።
ማነው ያለው ካልኩኝ ብዙ እሰማለሁ፣
ማነው ያለው ብልስ ማንን አምናለሁ፣
ማነው ያለው አውቀዋለሁ ባይ ብዙ፣
በሞላበት ያደክማል ጓዝ መዘዙ።
እ እ እ እ እህ እህ . . . እ እ እ እ እህ እህ . . .
እራስን ክቦ ለክብር ዝና፣
ይራመዳል ሰው በሰው ጎዳና፣
ሞልቶ ላይሞላ ለሽንቁር ኑሮ፣
እንዴት ይገፋል ይሄ ተጨምሮ፣
ሰው ለቁርሱ እጁን አጣጥፎ፣
ጫፍ ይዞ መሄድ ሆዱን ታቅፎ፣
ላላዩት እውነት አሉ ላይረባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ቢዋል ሳታምን ግባ።
አአአአአአይይይ…ምምምም
ማነው ያለው አልልም አልጠይቅም፣
ማነው ያለው ብዬም አልጨነቅም፣
ማነው ያለው ምን አሉኝ ደግሞ ብዬ፣
ላልቆም ነገር ከመንገድ ከጉዞዬ።
ማነው ያለው ብዬ እኔ ሰው አልወቅስም፣
ማነው ያለው ውስጤን ላያውቀው ማንም፣
ማነው ያለው ስቆ ማለፍ መተው ነው፣
የሚያኖርህ የሰራም ደግ አባት ነው።
እ እ እ እ እህ እህ . . . እ እ እ እ እህ እህ . .
ለማን ብዬ አለኝ ያሉት በምድር፣
ለማን ብዬ ፈጥኖ ለሚያሳፍር፣
ለማን ብዬ ከዘመኔ ስፍር፣
ለማን ብዬ ቅንጣት ለማልጨምር፣
ለማን ብዬ ወዳጅ ላፍራ ብዬ፣
የሰው ላድንቅ የኔን ቀን ገድዬ።
ለማን ብዬ ቃላት ከማይመርጠው፥
ለማን ብዬ ለከት ካጣ አንደበት፣
ለማን ብዬ ከማይጠቅም ምክር፥
ለማን ብዬ እርግማን ካለበት፣
ለማን ብዬ የኮኮብ ድምቀቴን፣
ለማን ብዬ ላጥፋው ማንነቴን።
ማነው ያለው ካልኩኝ ብዙ እሰማለሁ፣
ማነው ያለው ብልስ ማንን አምናለሁ፣
ማነው ያለው አውቀዋለሁ ባይ ብዙ፣
በሞላበት ያደክማል ጓዝ መዘዙ።
እ እ እ እ እህ እህ . . . እ እ እ እ እህ እህ . . .
እራስን ክቦ ለክብር ዝና፣
ይራመዳል ሰው በሰው ጎዳና፣
ሞልቶ ላይሞላ ለሽንቁር ኑሮ፣
እንዴት ይገፋል ይህ ተጨምሮ፣
ሰው ለቁርሱ እጁን አጣጥፎ፣
ጫፍ ይዞ መሄድ ሆዱን ታቅፎ፣
ላላዩት እውነት አሉ ላይረባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ቢዋል ሳታምን ግባ።
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
አሉ ተባለን ሳታምን ግባ።
እ እ እ እ እህ እህ . . .

Join 👇👇👇
https://t.me/joinchat/U74a12ayrXpK_aSM




እዮብ_መኮንን
# የጋበዝኳቸው
ወጣው ከ እልፍኜ ቆምኩኝ ከበሩ
የጋበዝኳቸው ሁሉም ቢቀሩ
እንባ እንዳጋቱ ሁለቱ አይኖቼ
መንገድ ስጀምር ድግሱን ትቼ
(አሀሀ ታራንታንታራ አሀሀ ታራንታንታራ)(2x)
ከጥሪው መዝገብ ስምሽ ሳይሰፍር
በሌሎች ግብዣ አመጣሽ ፍቅር
(አሀሀ ታራንታንታራ አሀሀ ታራንታንታራ)(2x)
ከጥሪው መዝገብ ስምሽ ሳይሰፍር
በሌሎች ግብዣ አመጣሽ ፍቅር
አክባሪ ያጣው ደጋሽ እልፍኜ
ያልታለምሽውን አንቺን አገኘ
በምድር ይሁን ወይስ ከሰማይ
ኬት መምጣትሽን ባይኔ ሳላይ
ድንገት ፊቴ ተከስተሽ አስደነቅሽኝ
ልቤን ገዝተሽ(2x)
አሀሀ ሃይሎጋ ካንቺጋ(4x)
ወጣው ከ እልፍኜ ቆምኩኝ ከበሩ
የጋበዝኳቸው ሁሉም ቢቀሩ
እንባ እንዳጋቱ ሁለቱ አይኖቼ
መንገድ ስጀምር ድግሱን ትቼ
(አሀሀ ታራንታንታራ አሀሀ ታራንታንታራ)(2x)
ከጥሪው መዝገብ ስምሽ ሳይሰፍር
በሌሎች ግብዣ አመጣሽ ፍቅር
(አሀሀ ታራንታንታራ አሀሀ ታራንታንታራ)(2x)
ከጥሪው መዝገብ ስምሽ ሳይሰፍር
በሌሎች ግብዣ አመጣሽ ፍቅር
አክባሪ ያጣው ደጋሽ እልፍኜ
ያልታለምሽውን አንቺን አገኘ
በምድር ይሁን ወይስ ከሰማይ
ኬት መምጣትሽን ባይኔ ሳላይ
ድንገት ፊቴ ተከስተሽ አስደነቅሽኝ
ልቤን ገዝተሽ(2x)
አሀሀ ሃይሎጋ ካንቺጋ(6x)
አሀሀ ሀይሎጋ
አሀሀ ሀይሎጋ.....

@Fiker_ma


#Meek1_One
#ሸግዬ_ሸጊቱ
🎼🎼🎼🎼🎼🎼
ስምል ባንቺ ስምል በሄድኩበት ቦታ
ትንሽ አይደል ትልቅ የማገኘው ደስታ
ስምል ባንቺ እኔስ ስምል በሄድኩበት ቦታ
ትንሽ አይደል ትልቅ ሁሌም የማገኘው ደስታ
አዬ ወይ ነዶ
ልቤ ያንቺን ፍቅር ተላምዶ
አዬ ወይ ነዶ
ልቤ ያንቺን ፍቅር ተላምዶ
እኔ የወደድኳት
እሷ የጠላቺኝ
እኔ የወደድኳት
እሷ የጠላቺኝ
ስማዳ ስማዳ
ስማዳ ገባቺኝ
ስማዳ ስማዳ
ስማዳ ገባቺኝ አዬ
🎼🎼🎼🎼
🎼🎼🎼🎼
ሸግዬ ሸጊቱ
የሴት እመቤት
ከመልክም አንደኛ
መልከ-መልካሚት አዬ
የቀሚስሽ ጥለት
ብዙ ነው አይነቱ
ያንቺስ የብቻው ነው
ጠላትሽ መብዛቱ
🎼🎼
በዝቶ ሰው በዝቶ
አየነው ዝናሽን
በዝቶ ሰው በዝቶ
ሰው ገዳይ መሆንሽን
በዝቶ ሰው በዝቶ
አየነው ዝናሽን
በዝቶ ሰው በዝቶ
ሰው ገዳይ መሆንሽን
🎼🎼
በይ ነይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ንገሪኝ
በይ ነይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ንገሪኝ አዬ
🎼🎼🎼🎼
🎼🎼🎼🎼
እኔ የወደድኳት
እሷ የጠላቺኝ
እኔ የወደድኳት
እሷ የጠላቺኝ
ስማዳ ስማዳ
ስማዳ ገባቺኝ
ስማዳ ስማዳ
ስማዳ ገባቺኝ አዬ
🎼🎼🎼🎼
🎼🎼🎼🎼
ወንጀለኛ ልባል
ባንቺ ይክሰሱኝ
ስሜም ባንቺ ይጥፋ
የሷ ካስባለኝ
አልኩኝ ብድግ ብድግ
ዘንድሮስ ቀለለኝ
አንጀቴን አውጥተሽ
በላሽው መሰለኝ
እንደታሪክ ሳወራ
አልሰለች ስምሽን ስጠራ
እንደታሪክ ሳወራ
አልሰለች ስምሽን ስጠራ
🎼🎼🎼
ፍቅርሽ ከኔ ሆኖ
ዘወትር አርበኛ
ቀልቤን እየገዛው
አርጎኛል ምርኮኛ
በይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ድገሚኝ ሳሚኝ
በይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ድገሚኝ ሳሚኝ
በይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ድገሚኝ ሳሚኝ
በይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ድገሚኝ ሳሚኝ
🎼🎼🎼🎼
ተው ተው ሲሉኝ የኔን ፍላጎት
ዘውድ አይሉ ጎፈር ምርጫ እንደሰጡት
ተው ተው ሲሉኝ የኔን ፍላጎት
ዘውድ አይሉ ጎፈር ምርጫ እንደሰጡት
አዬ
አሃ
@Fiker_ma


› ጂጂ
› ትናገር አድዋ

➖➖➖➖➖➖➖

የሰው ልጅ ክብሩ
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቶል ሰው ሊያድን
ሰውን ሲያከብር
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ
በክብር ይሄዳል ሰው ሊኖር
ሰው ሞቶ

የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል
ከደም እና ከአጥንት

ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር
ትናገር አድዋ ትናገር ሀገሬ
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታቹ ዛሬ

በኩራት
በክብር
በደስታ
በፍቅር

በድል እኖራለው ያው በቀን በቀን
በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን

አድዋ ዛሬናት አድዋ ትናንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለነሱ ለአደዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች

የ ጥቁር ድል አንባ አድዋ
አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ
እእእእ ተናገሪ...

°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°


️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️


•════•••🍃🌺🍃•••════•

@Fiker_ma


› ዳዊት ፅጌ
› ደስ አለኝ

•════•••🍃🌺🍃•••════•

ኧረ እንዴት ነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
የምን ሳቅ ጨዋታ ደግ ተሸኝቶ
ቀየውም መንደሩም ተክዞ ሰንበቶ
እምም የተፈጥሮም ነገር የውበትም ነገር
እምም አንቺን ናፍቆ መዋል አንቺን ናፍቆ ማደር
ኧረ እንዴት ነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
እህምምም
ደስ አለኝ እመጣለሁ ስትይ ሰምተዋል መሰለኝ
ደስ አለኝ ዘማመሩ ወፎቹ ዜማቸው ደስ አለኝ
እመጣለሁ ስትይ ሰምተዋል መሰለኝ ደስ አለኝ
ዘማመሩ ወፎቹ ዜማቸው ደሳለኝ
የአበቦቹ ድምቀት አቤት ውበታቸው
ከደጃፌ ደርሰሽ እስክታስንቂቸው
ድንጉላው ተነሳ እንጀራውን ትቶ
ሊቀስምሽ መሰለኝ መምጣትሽን ሰምቶ
አቤ... ት አቤት አቤት አቤት
ኧረ ፈኩ ፈኩ አበቦች ከመስኩ
ለመለሙ ወፎች ተሳሳሙ
ዘማመሩ ዜማቸው ደስ አለኝ
መምጣትሽን ሰምተዋል መሰለኝ
አሀሀ
አፈረች ጀምበሯም አፈረች
አፈረች አይንሽን እያየች
እያየች ተመኘች ደጄ ተቀምጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
እያየች ተመኘች ደጄ ተቀምጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
አፈረች ጀምበሯም አፈረች
አፈረች አይንሽን እያየች
እያየች ተመኘች ደጄ ተቀምጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
እያየች ተመኘች ደጄ ተቀምጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
ኧረ እንዴት ነሽ
እህህህህ
ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ


°°°
°°°
°°°
°°°
°°°

️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️


•════•••🍃🌺🍃•••════•

@Fiker_ma


› ዳዊት ፅጌ
› ደግሞ በዚህ ላይ

•════•••🍃🌺🍃•••════•

ወርቅ አልማዝ ብልሽ ይገልፅሻል ወይ
ዉድ እንቁ ብልሽ ይገልፅሻል ወይ
ስም አጣሁልሽ የኔ ስጦታ
መቼም ልዩ አርጎ ፈጥሮሻል ጌታ
ስም አጣሁልሽ የኔ ስጦታ
ሁሉን ሙሉ አርጎ ፈጥሮሻል ጌታ

የሚገርመኝ አይንሽን ሳይ
ያጥብያ ኮኮብ ነሽ መልከ ፀሐይ
ደሞ ሲመሽ ጀምበር ጠልቃ
ትፈኪያለሽ እንደ ጨረቃ
እንደ ጨረቃ ፈክቶ
መልክሽ ሲያበራ መሽቶ
የሰውነትሽ ቅኔ
ግርም ይለኛል እኔ
አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አቤት...
አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አ ...
ደሞ በዚ ላይ ፀባይ
ደሞ በዚ ላይ ዉበት
ደሞ በዚ ላይ .
ደሞ በዚ ላይ ...
አቤት አቤት አቤት

ወርቅ አልማዝ ብልሽ ይገልፅሻል ወይ
ዉድ እንቁ ብልሽ ይገልፅሻል ወይ
ስም አጣሁልሽ የኔ ስጦታ
መቼም ልዩ አርጎ ፈጥሮሻል ጌታ
ስም አጣሁልሽ የኔ ስጦታ
ሁሉን ሙሉ አርጎ ፈጥሮሻል ጌታ

የቁንጅና ዉብ ምሳሌዋ
ደሞ እንዳንቺ ማነው ጨዋ
አቻሽ ጠፋኝ በዚዓለም ላይ
ቸር ደግ አርጎሽ ከሰው በላይ
አልመስልሽም እንቁ
ልብሽ ነው ለኔ ብርቁ
ማን ብዬ ልጥራሽ እኔ
ቃል አጣሁልሽ ቅኔ
አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አቤት...
አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አ ...

ደሞ በዚ ላይ ፀባይ
ደሞ በዚ ላይ ዉበት
ደሞ በዚ ላይ .
ደሞ በዚ ላይ ...

አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አቤት...
አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አ ...
ደሞ በዚ ላይ ፀባይ
ደሞ በዚ ላይ ዉበት
ደሞ በዚ ላይ .
ደሞ በዚ ላይ ...
አቤት አቤት አቤት
ደሞ በዚ ላይ .
ደሞ በዚ ላይ ...
ደሞ በዚ ላይ .
ደሞ በዚ ላይ ...

°°°
°°°

️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️


•════•••🍃🌺🍃•••════•

@Fiker_ma


› ዳዊት ፅጌ
› ደሀ አይጣላ ከውሃ

•════•••🍃🌺🍃•••════•

አንዲት ሴት ነበረች የቤት ሰራተኛ
ቀን ስትደክም ውላ ሌትም የማተኛ
ኑሮዋ ሆነና የአርባ ቀን እድሏ
ልጅ እያጠባች ነው የተለያት ባሏ
ላንድ ልጇ ስትል በነፃ እየሰራች
ደሞዟን ሳትል ነው ለፍታ ያሳደገች
እንደወጣ ቢቀር ያ ባሏ ያ ጎበዝ
ስትረግም ትኖራለች ያሻገረውን ወንዝ
ለራሷ ምትቀምሰው ምትልሰው ሳይኖራት
ምን ለታጠባ ነው የምትወልደው ሲሏት
ልጅ ስጦታ አይደለም ከመጣ በኃላ
ብላ ተስፋ ቆርጣ ሄደች አገር ጥላ
አገር ጥላ ጠፍታ ተሰዳ በሩቁ
ትኑር ትሙት እንኳን አንዳቸው ሳያውቁ
ስንት ዘመን አልፎ ናፍቃ ብትመለስ
ይሄው ፊት አስነሳት የታቀፈቺው ነፍስ
ምናለ ብተወው የባሏን እሮሮ
ያሻገረውን ወንዝ መርገም በንጉርጉሮ
ወንዙን አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
እሷም አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
ካገር አገር ስትዞር ተሸክማ ጕዟን
ስንት አሳር አይታለች ለማሳደግ ልጇን
እርፍት እንኳን ሳታውቅ በነፃ እየሰራች
ወዟን አራግፋ ነው ለፍታ ያሳደገች
ታዲያ አንድ ቀን ጠዋት ማለዳ ተነስታ
ቅጠል ለቅማ መጣ ሳታርፍ እንኳ ላፍታ
ልጇን ባንቀልባ አዝላ ውሃ ልትቀዳ
ከለመደቺው ወንዝ መሸት ሲል ወርዳ
ጎንበስ ባለችበት በድካም ስሜቷ
አመለጣት ልጇ አይ እድሏ ህብቷ
ደራሽ ወሰደባት የት ገባ ፀሎቷ
የምትወደው ልጇ ሆነ የውሃ ሽታ
ምን ያደርግላታል ብታለቅስ ብትረግመው
ከውሃ ተጣልታ የትም ለማትደርሰው
እሷም አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
እሷም አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ ድሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
አይ ደሃ ...
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ ድሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ

°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°


️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️


•════•••🍃🌺🍃•••════•

@Fiker_ma


› ዳዊት ፅጌ
› እትቱ

•════•••🍃🌺🍃•••════•

እትቱ እትቱ በረደኝ
እትቱ በቀን በፀሀይ
እትቱ ናፍቆትሽ ክረምቱ
እትቱ ይዞት ገባ ወይ
ዛሬስ ዛሬስ ከዓይኔ ባጣሽ
ዛሬስ ድንገት በማርፈድሽ
ዛሬስ ላምባዬን አንስቼ
ወጣሁኝ ወጣሁ ልፈልግሽ
ዛሬስ ወጣሁ ልፈልግሽ

እትቱ እትቱ በረደኝ
እትቱ በቀን በፀሀይ
እትቱ ናፍቆትሽ ክረምቱ
እትቱ ይዞት ገባ ወይ

ዛሬስ ስፍስፍ አልኩኝ ባንቺ
ዛሬስ ሰውነቴም ከዳኝ
ዛሬስ በልቤ አለ ነገር
በሰው በሰው አፍ ላይዳኝ
ዛሬስ በሰው አፍ ላይዳኝ

በቀን መብራት ይዤ ተቆጠርኩ እንደ ጅል
እኔስ ባንቺ ጉዳይ በል ፈጠን አልከጅል
ሳልምሽ አምሽቼ ሲናፍቅሽ አይኔ
አንቺን ካላገኘው መንጋቱስ ለምኔ ዋ
የጨዋታሽ ማማር የሳቅሽ ፏፏቴ
ውሃውን አስረሳኝ ሲፈስ ወደ አንጀቴ
ወንዙ ዳር አጥምቂኝ መልክሽ ይታየኛል
አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል
አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል
በወግ ያልነኩትን ዘራፍ ሲሉት ሸሽቶ
ይታገለኝ ጀመር ፍቅርሽ ጦር አንስቶ
አንቺው ምከሪልኝ ዘንጉን ይመልሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
አቤት አቤት አቤት ሃሃሃ
አቤት አቤት አቤት ሃ...

°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°


️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️


•════•••🍃🌺🍃•••════•

@Fiker_ma


› ዳዊት ፅጌ
› ባየው ባየው

•════•••🍃🌺🍃•••════•

አይንሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
አይንሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
መልክሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
መልክሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
እንዲህ ውብ ተፈጥሮን የታደለ ማነው?
አይንሽን አልሰለችህ አለኝ ባየው
የገላሽን ማማር የሰራ አካልሽን
የአይን አገላለጥሽ ያሰባበርሽን
እንዲህ ውብ ተፈጥሮን የታደለ ማነው?
አይንሽን አልሰለችህ አለኝ ባየው
ሆድዬ ተይ አውጊኝ ምሽቱ ሳይነጋ
ልቤ እንዲረጋጋ
ሆድዬ ተይ አውጊኝ ምሽቱ ሳይነጋ
ልቤ እንዲረጋጋ
አንቺዬ ከነጋማ ወዲያ ብርሀን ነው
ተይ አውጊኝ ገና ነው
አንቺዬ ከነጋማ ወዲያ ብርሀን ነው
ተይ አውጊኝ ገና ነው
ከነጋማ ወዲያ
ፀሀይ ከደመቀ
ምንም ሳላወጋሽ
ለሊቱ ካለቀ
ኋላ ብትናፍቂኝ ተጠያቂው ማነው?
አይንሽን ቀን ከሌት
አልሰለችህ አለኝ ባየው
አይንሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
አይንሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
መልክሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
መልክሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
እንዲህ ውብ ተፈጥሮን የታደለ ማነው?
አይንሽን አልሰለችህ አለኝ ባየው
ማየቱንስ ያያል
ሁሉም እንደህልሙ
ያንቺ ግን ይለያል
ብዙ ነው ትርጉሙ
ይሄን ውብ ተፈጥሮ
የተረዳው ማነው?
አይንሽን አልሰለችህ አለኝ ባየው
ሆድዬ ፈገግታሽ የጥዋት ጮራ ነው
አለም ሚሞቀው
ሆድዬ ፈገግታሽ የጥዋት ጮራ ነው
አለም ሚሞቀው
አንቺዬ የልቤን ለልብሽ ልንገረው
እይታሽ ፈራጅ ነው
አንቺዬ የልቤን ለልብሽ ልንገረው
እይታሽ ፈራጅ ነው
በአይኖችሽ ብርሀን ደምቆ በፈገግታሽ
የዘላለም ፍቅሩን
አሜን ነው የሚልሽ
ይሄን ታላቅ ውበት
የተረዳው ማነው?
አይንሽን ቀን ከሌት
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው(አይንሽን)
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው(ጥርስሽን)
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው(አይንሽን)
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው(ጥርስሽን)
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው
አልሰለችህ አለኝ ባየው

°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°


️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️


•════•••🍃🌺🍃•••════•

@Fiker_ma

20 last posts shown.

2 272

subscribers
Channel statistics