በዚህ ጉዳይ አንድ ያልተመቸኝን ነገር ልናገር ( አስታየት የምሰጠው እንደ ሀይማኖተኛ ሳይሆን እንደ ፖለቲከኛ )
ሰሞኑን እኚህ አባት " ፍጡር ቤዛ ሊሆን አይችልም ። ቤዛችን ክርስቶስ ብቻ ነው " ብለው ባስተማሩት ትምህርት ላይ ብዙ ውዝግቦች እየተነሱ የእምነቱ ተከታዮች ግራ እየተጋቡ እንደሚገኙ እና ቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ መጥራቱ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ አንዳንድ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጉዳዩን ወደ ብሄር ለመውሰድ እየሞከሩ ያሉት ነገር ምንም አልተዋጠልኝም።
የፖለቲከኞቹ አካሄድ " እከሌ የተባሉ የአማራ ጳጳስ ከዚህ በፊት ከክርስቶስ ውጪ አማላጅ የለም ብለው ቢናገሩም ምንም አልተባሉም ። እኚህ አባት ግን ኦሮሞ ስለሆኑ ነው የተጠቁት " የሚል አስቂኝ አካሄድ 😅😅😅😅
እረ ወገን በትክክል እናስብ እንጂ ። እሳቸው የተናገሩት ንግግር ከቤተክርስቲያኑ አስተምሮ አንፃር ተፈትሾ ትክክል ካልሆነ መተረም ትክክል ከሆነ ደግሞ ትክክል ናቸው ተብሎ ሊነገር ይገባል ።
የናንተ ጥያቄ መሆን ካለበትም መሆን ያለበት የአማራውም ጳጳስም ንግግራቸው እንዲፈተሽ የሚጠይቅ ዘመቻ ማድረግ ነው እንጂ ያኛው ዝም ስለተባሉ እኚህም ዝም ይባሉ የሚለው መንገድ አያስኬድም ።
ከቻልን ፐለቲከኞች ሀይማኖት ውስጥ ገብተን አንፈትፍት ። ሀይማኖተኞች ወደ ፖለቲካው ከመጡ ብቻ ጣልቃ እንግባ
@my_oromia