የ2015 አ.ም የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ፈተና ክስተት ወ/ሮ ጸሃይ መሃመድ ኡመር እና ሁለቱ ልጆቻቸው፣
ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 22/11/2015 ዓ.ም
====================
ትምህርት እድሜ እንደማይገድበው ማሳያ የሆኑት ወ/ሮ ጸሃይ መሃመድ ከሁለት ልጆቻችው ጋር የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ፈተናን በጋራ በመውሰድ ለቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ የ2015 ዓ.ም የፈተና ወቅት ገጠመኝ መሆን ችለዋል::
የግል ተፈታኝ የሆኑት እናት ከከሚሴ 02 መቶሆሮ አጠ/ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ከሆነችው ልጃቸው ሲሃም እንድሪስ ጋር የ12 ክፍል አገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ በግቢያችን ቆይታ ያደረጉ ሲሆን፣ ወንድ ልጃቸው ተማሪ ሪድዋን ሁሴን ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ በመሆኑ በዛሬው እለት ግቢውን የሚቀላቀል ይሆናል::
ከአንድ ቤት ውስጥ ወላጅ እናትን ጨምሮ ሶስት ተፈታኞች በአንድ ተቋም ውስጥ ለፈተና መቀመጣቸው ድምቀት ከመሆናቸው ባሻገር አስተማሪ ሆኖ አግኝተነዋል ። ተቋማችንም በዚህ አጋጣሚ መልካም ውጤትም ይቀናቸው ዘንድ ይመኛል !!!