Natinael


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


Brand Identity Designer
Video Editor
@Nati_Graphix
Personal Blogger

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


I hope you’ve heard about DeepSeek, new AI that was recently released. I finally got to try it out, and here is how it went on the first day.

it responded in the coolest way! 😁


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
@natinael_adisu
@natinael_adisu


የፊልሙ ርዕስ እና ዋና ገፀባህሪው ስም PK ይባላል በታዋቂው የBolllywood ተዋናይ Aamir khan የተሰራ ሲሆን ዋና ጭብጡ፦

በአለማችን ውስጥ ከእነሱ ውጪ ሌላ civilization ለማግኘት በሚደረግ ፍለጋ ወደ እኛ ፕላኔት Earth 🌍 መጥቶ ከኛ አለም ሰዎች ጋር ለመግባባት የሄደበትን መንገድ ፣ ስለ ማህበረሰባችን ፣ ስለ አስተሳሰባችን ፣ ስለ ሀይማኖታችን ለመረዳት እና ለማወቅ ብዙ ሲጥር እና ሲፈትን፣ብሎም የኛ የሰዎችን አስመሳይነት ለመቀበል ሲከብደው እና በሚጠይቃቸው አዝናኝ መስለው ግን በውስጡ ጥልቅ የሆኑ መልዕክቶች የተተላለፈበት የኔ የምን ጊዜውም ምርጥ እና Comedy & Philosophical ፊልም ነው!

ፊልሙን ለመጀመርያ ጊዜ high school እያለው በአንድ ጓደኛዬ ግብዣ ነበር ያየሁት ። ፊልሙ እና Pk የተባለው ገፀባህሪ በዛን ጊዜ ከነበረኝ ከእኔ ታሪክና ማንነት ጋር ካሳለፍኳቸው ነገሮች ጋር ይመሳሰላል ። ሁሌም ደጋግሜ ባየው የማይሰለኝ የድሮ እኔነቴን እና የዋህነቴን መልሶ እያሳየኝ በትዝታ ባህር የሚያስቀዝፈኝ ቢያንስ በየአመቱ ሁለቴ የምደግመው ምርጥ ፊልም ነው!🥹

ፊልሙን ከነትርጉሙ ከታች አስቀምጬላችኋለው👇👇


እራሳችሁን በአንድ ፊልም እና Character ግለፁት ብትባሉ የትኛው ፊልም እና የትኛው ገፀባህሪ እናንተን ይመስላል ?🤔


#በወጣትነትህ ከዕድሜህ በላይ ተደርገህ ትታያለህ ፥ በጎልማሳነትህ እንደ ለጋ ወጣት ትገመታለህ፥ በመንገድ ስትሄድ የማንም ፉንጋ አይዳርህም በሩንገና ከፍተህ ስትገባ መገኘትህ የራሱን ድባብ ሲፈጥር ታያለህ ... ትምህርት ቤት ወይ ካምፓስ አልፎም መስሪያ ቤት የማንም ወጠጤ በምንም መንስኤ ቡሊ ሊያደርግህ አይችልም ባንተ ፊት ወላጆችህ ላይ ማንም አፉን አይከፍትም ። ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።

#ብረት_ስትገፋ በወንዶች ትከበራለህ ሴቶችን ታማልላለህ ወንዶች የሚመኙት ሴቶች የሚሻፍዱት ቅርፅ ይኖርሃል። (በርግጥ አቶ ገንዘብ የመጣ ለታ ይሄን ሁሉ ቀዳዳ መሸፈን ቢችልም😁 ) ቢሆንስ ለምን እስከዛ ትጠብቃለህ🤷‍♂️

ቀልዱስ ቀልድ ነው ግን የምር ብረት ግፉ ስፖርት ስሩ በቅርብ የተጠና ጥናት እንደሰማሁት የእግር ጡንቻ ጥንካሬ እድሜን እንደሚያራዝም እና ለጤና ትልቅ ተፅዕኖ አለው ።

በነዚህ ሁለት ፎቶዎች መካከል ያለው ልዩነት 1 አመት ብቻ ነው! 🤫

ሰኔ 2015 ዓ.ም ሰኔ 2014 ዓ.ም


እሁድም አደል!
I want to introduce you all to the incredibly talented and underrated Ethiopian rapper, Siimbiie Lakew. Take a moment to listen to his music and judge for yourself.


Bejai Nerash Naiker ቤት በድጋሚ እድላችንን ፍቀናል ይሄኛውም ዙር በዳኛ ስለሆነ እስቲ ገባ በሉና በዳኞች እይታ ቅድሚያ እንዲገባ Like እና ድጋፋችሁን ከታች ባለው Link እየገባችሁ እንደባለፈው አሳዩኝ 🙏
👇
Click Here


Forward from: Photo Art
Whatsup Fam 😊

Again with another Fire 🔥 Branding Projects this time for #Nimrode_Network company focusing on student scholarship consultation and I loved designing these and wanted to share them with you all. If you were the client, How do you feel for this Brand Project?

Let me know your opinion in the comments I’d love to hear your thoughts again! 🤗💜

Dm 📥: @Natigraphix
Cal ☎️ 0933602944

Telegram
Facebook
Instagram
Linkedin
Tiktok


እንደኔ ብዙ #follower የሌላችሁ ግን አሪፍ አሪፍ የቢዝነስ ሀሳብ ያላችሁ ጀለሶች Bejai Nerash Naiker ቤት እንደ ትላንትናው 100% በዳኞች የሚወሰን ውድድር ሲኖር ለመሳተፍ ሀሳባችሁን በፅሁፍ አዘጋጅታችሁ አስቀምጡ (ሀሳብን አደራጅቶ መፃፍ ከቸገራችሁ አግዛችኋለው በውስጥ ፃፉልኝ ፅድት ባለች አማርኛ እሰድርላተችኋለው😉

በተረፈ ላበረታታችሁኝ ሀላችሁም ክብረት ይስጥልኝ🙏 በዚ ዙር ባይሳካም በቀጣዩ ግን እንደማሸንፍ ይሰማኛል😎 ማነው ለቀጣዩም የሚያበረታታኝ?


ወንድ ልጅ የሆዱን ብሶት Open up ማድረግ የለበትም ባይ ነኝ!

ወንድ ስለሆንክ ብሶትህን ብታወራውም ማንም የምታውቀውን ልክ understand አያደርግህም አጎት አክስት ጓደኛ ዘመድ የገዛ እናትህም ብትሆንም እንኳን ላትረዳህ ትችላለች ፣ ስሜትህን ህመምህን እንኳ በቅጡ የሚረዳ እና ግድ የሚሰጠው ያገኘ ሰው ታድሏል።

ያ ግን የወንድ መንገድ አደለም ወንድ በመከራ ፣ በመከዳት፣ በበደል፣ በግፍ ፣ በብቸኝነት ፣ በጭንቀት ፣ በውጥረት ፣ ፈላጊ በማጣት ስሜት አልፎ የአለምን ትክክለኛ ገፅታ ማየት አለበት።

ወንድ ስትሆን የችግሮችህ መፍትሔ ያለው አንተ እና አንተ ጋር ብቻ ነው ፤ ስለዚህ ወይ ታግለህ ታሸንፋለህ ወይም እየታገልክ ትሞታታለህ🤷‍♂️ እውነታው ይሄ ነው!!

በዚች ጨካኝ አለም ወንድ ሆኖ መፈጠር ከባድ ቢሆንም ግን አንዴ ወንድ ሆነህ ተወልደሀልና ወንድ ሆኖ መኖር ግድ ነው።

ብዙ ጊዜ ሰዎች ብሶታቸውን ለሌላው በማማረር ስሜታቸውን የሚረዳላቸውን ሰው ለማግኘት ሲጥሩ አያለው ግን ብሮ ማን ደልቶት እየኖረ ያለ ይመስልሃል ?
ሁሉም በራሱ አለም የሚዋጋው ጦርነት አለውና ሰው አልተረዳኝም ብለህ አታለቃቅስ !

ከ እድሜ ጋር ተያይዞ በሚመጣ Anxiety እና Depression ጋር ከተዋወቅን ድፍን አራት አመት ምናምን ግን በማንም understood መደረግ አልፈልግም በስሜቴ ጉዳይ የማንንም እርዳታ አልሻም። ነገሮች እንደ እቅድህ ባይጓዙ ማዘን መከፋት ሰዋዊ ባህሪ ቢሆንም እንደ ዮሴፍ ሄደህ በአእልፍኝህ አልቅሰህ እንባህን ጠራርገህ ተመለስ እነጂ ለማንም Open up አታድርግ ።

ባጠቃላይ ወንድ ልጅ ስሜቱን አውጥቶ ማሳየት አለበት ብዬ አላምንም ፣ የሰዎች አዘኔታ ማግኘት ደካማ እና ልፍስፍስ ሰው ነው የሚያደርገው ማንም ስሜትህን ሊረዳህ(understand) አይገባም።


#thetruthis…


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
Especially after you Delivered the Final Project 😁😌


#አንዳንድ ምክሮች እና አባባሎች ከተለመደው ለየት ስላሉ ወይም ጥልቅ መልዕክት ያላቸው ስለሚመስሉ ልክ ናቸው ማለት አይደለም!

በActing ስሙ Petyr Baelish ይባላል በ Game of Thrones ተከታታይ ፊልም ከማይረሱ ገፀ ባህርያት አንዱ ነው ።

በርግጥ ፊልሙን ያየሁት ከሰው ሁሉ ዘግይቼ ቢሆንም ለኔ የመቼውም ጊዜ ምርጥ Series Movie ነው።

እናም Lord Belish የሚታወቀው ከሁሉም ጋር ተግባቢ መሆኑና በአስመሳይነቱ ቢሆንም በአንድ ክፍል ላይ ለ Sansa stark የተናገረው ይህ አነጋገሩ በወቅቱ በግርምታ speechless አድርጎኝ ነበር።

“𝘿𝙤𝙣’𝙩 𝙛𝙞𝙜𝙝𝙩 𝙞𝙣 𝙩𝙝𝙚 𝙉𝙤𝙧𝙩𝙝 𝙤𝙧 𝙩𝙝𝙚 𝙎𝙤𝙪𝙩𝙝. 𝙁𝙞𝙜𝙝𝙩 𝙚𝙫𝙚𝙧𝙮 𝙗𝙖𝙩𝙩𝙡𝙚 𝙚𝙫𝙚𝙧𝙮𝙬𝙝𝙚𝙧𝙚, 𝙖𝙡𝙬𝙖𝙮𝙨, 𝙞𝙣 𝙮𝙤𝙪𝙧 𝙢𝙞𝙣𝙙. 𝙀𝙫𝙚𝙧𝙮𝙤𝙣𝙚 𝙞𝙨 𝙮𝙤𝙪𝙧 𝙚𝙣𝙚𝙢𝙮, 𝙚𝙫𝙚𝙧𝙮𝙤𝙣𝙚 𝙞𝙨 𝙮𝙤𝙪𝙧 𝙛𝙧𝙞𝙚𝙣𝙙. 𝙀𝙫𝙚𝙧𝙮 𝙥𝙤𝙨𝙨𝙞𝙗𝙡𝙚 𝙨𝙚𝙧𝙞𝙚𝙨 𝙤𝙛 𝙚𝙫𝙚𝙣𝙩𝙨 𝙞𝙨 𝙝𝙖𝙥𝙥𝙚𝙣𝙞𝙣𝙜 𝙖𝙡𝙡 𝙖𝙩 𝙤𝙣𝙘𝙚. 𝙇𝙞𝙫𝙚 𝙩𝙝𝙖𝙩 𝙬𝙖𝙮 𝙖𝙣𝙙 𝙣𝙤𝙩𝙝𝙞𝙣𝙜 𝙬𝙞𝙡𝙡 𝙨𝙪𝙧𝙥𝙧𝙞𝙨𝙚 𝙮𝙤𝙪. 𝙀𝙫𝙚𝙧𝙮𝙩𝙝𝙞𝙣𝙜 𝙩𝙝𝙖𝙩 𝙝𝙖𝙥𝙥𝙚𝙣𝙨 𝙬𝙞𝙡𝙡 𝙗𝙚 𝙨𝙤𝙢𝙚𝙩𝙝𝙞𝙣𝙜 𝙩𝙝𝙖𝙩 𝙮𝙤𝙪’𝙫𝙚 𝙨𝙚𝙚𝙣 𝙗𝙚𝙛𝙤𝙧𝙚.”

ፊልሙን በትክክል ተመስጦ ላየ ሰው በሚያደርጋቸው ነገሮች እና በሚያስበው ሀሳቦች Petyr Baelish ይህን አባባል የህይወቱ አካል አድርጎት ኖሮት እንደነበር ግልፅ ነው ።

በመጨረሻም ግን እኔም የተደነቅኩለት ይህ አስተሳሰቡ እሱ ሌሎችን እንዳስገደለው ከመገደል ፥ እሱ ሌሎችን እንደካደው ከመከዳት ፥ እሱ ሌሎችን እንዳስደነገጠው ከመደናገጥ አላተረውም።

ሁሉንም ወዳጅ ሁሉንም ጠላት አድርጎ ወዲና ወዲያ ወላዋይ መሆን መጨረሻው አይሰምርም።

ብዙ ጊዜ ፊልሞች ላይ አይታችሁ ከሆነ ጠላት አንድን አከባቢ ለመውረር ሲል መጀመርያ አከባቢውን በደምብ የሚያውቅ የዛ ሀገር ተወላጅን በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ደልለውት እንደ ሰላይ ይጠቀሙበትና በመጨረሻም የገቡለትን ቃል ስልጣን እና ሀብት ሳይሰጡት “ለወገንህ ያልታመንክ ለኛ በምን ትታመናለህ “ ከተጠቀሙበት እና ግባቸውን ካሳኩ በኋላ በጥይት ግንባሩን ብለው ይሸኙታል።

ይህ አይነት ሰው ልክ እንደ Loard Baelish ወዳጅ እና ጠላቱን በአንድ ደበላልቆ የሚመለከት ሰው ነው።
መጨረሻው ከሁሉም አለመሆን እና የራስ የሚሉትን ወገን ማጣት ነው።

በህይወት ስንኖር ልንወስናቸው ከሚገቡ ትላልቅ ውሳኔዎች መሀከል ወዳጅንና ጠላትን መለየት አንዱ ነገር ነው።

እንደ Lord Baelish አጉል ብልጣብልጥ ልሁን አትበል ሁሉንም ሰው አትጠራጠር ህሉንም አትመን ፣ ለሁሉም ጓደኛ አትሁን ከሁሉም ጋር ጠላትነትን አትፍጠር ፣ በተቻለ መጠን የፀና አቋም ይኑርህ !

በተለይ ኢትዮዽያ ውስጥ ለሚያይህ ሁሉ ነጭ ካልሆንክ ጥቁር ሁን እዚህ ካልሆንክ እዛ ሁን ፣ ቀኝ ካልሆንክ ግራ ሁን ፣ ትኩስ ካልሆንክ ቀዝቃዛ ሁን ፣ እንጂ አጉል አመዛዛኝ ስትል ሁሉም በአንድ ላይ ተነስተው እንዳይቅጡህ አትምሰል እንዲሁ ለብ ያልክ ውሃ አትሁን ፣ ባረፍክበት ቅርፅ ይዘህ ተቀመጥ ።

#በመጨረሻም ከ 𝐑𝐨𝐛𝐞𝐫𝐭 𝐆𝐫𝐞𝐞𝐧𝐞 48𝐋𝐚𝐰𝐬 𝐨𝐟 𝐏𝐨𝐰𝐞𝐫 መፅሐፍ የተመቸኝን ክፍል አስነብቤ ለቀየስ

𝑳𝑨𝑾 19 - 𝑲𝑵𝑶𝑾 𝑾𝑯𝑶 𝒀𝑶𝑼'𝑹𝑬 𝑫𝑬𝑨𝑳𝑰𝑵𝑮 𝑾𝑰𝑻𝑯 - 𝑫𝑶 𝑵𝑶𝑻 𝑶𝑭𝑭𝑬𝑵𝑫 𝑻𝑯𝑬 𝑾𝑹𝑶𝑵𝑮 𝑷𝑬𝑹𝑺𝑶𝑵𝑳𝑨𝑾

- 𝙏𝙝𝙚𝙧𝙚 𝙖𝙧𝙚 𝙢𝙖𝙣𝙮 𝙙𝙞𝙛𝙛𝙚𝙧𝙚𝙣𝙩 𝙠𝙞𝙣𝙙𝙨 𝙤𝙛 𝙥𝙚𝙤𝙥𝙡𝙚 𝙞𝙣 𝙩𝙝𝙚 𝙬𝙤𝙧𝙡𝙙, 𝙖𝙣𝙙 𝙮𝙤𝙪 𝙘𝙖𝙣 𝙣𝙚𝙫𝙚𝙧 𝙖𝙨𝙨𝙪𝙢𝙚 𝙩𝙝𝙖𝙩 𝙚𝙫𝙚𝙧𝙮𝙤𝙣𝙚 𝙬𝙞𝙡𝙡 𝙧𝙚𝙖𝙘𝙩 𝙩𝙤 𝙮𝙤𝙪𝙧 𝙨𝙩𝙧𝙖𝙩𝙚𝙜𝙞𝙚𝙨 𝙞𝙣 𝙩𝙝𝙚 𝙨𝙖𝙢𝙚 𝙬𝙖𝙮. 𝘿𝙚𝙘𝙚𝙞𝙫𝙚 𝙤𝙧 𝙤𝙪𝙩𝙢𝙖𝙣𝙚𝙪𝙫𝙚𝙧 𝙨𝙤𝙢𝙚 𝙥𝙚𝙤𝙥𝙡𝙚 𝙖𝙣𝙙 𝙩𝙝𝙚𝙮 𝙬𝙞𝙡𝙡 𝙨𝙥𝙚𝙣𝙙 𝙩𝙝𝙚 𝙧𝙚𝙨𝙩 𝙤𝙛 𝙩𝙝𝙚𝙞𝙧 𝙡𝙞𝙫𝙚𝙨 𝙨𝙚𝙚𝙠- 𝙞𝙣𝙜 𝙧𝙚𝙫𝙚𝙣𝙜𝙚. 𝙏𝙝𝙚𝙮 𝙖𝙧𝙚 𝙬𝙤𝙡𝙫𝙚𝙨 𝙞𝙣 𝙡𝙖𝙢𝙗𝙨' 𝙘𝙡𝙤𝙩𝙝𝙞𝙣𝙜. 𝘾𝙝𝙤𝙤𝙨𝙚 𝙮𝙤𝙪𝙧 𝙫𝙞𝙘𝙩𝙞𝙢𝙨 𝙖𝙣𝙙 𝙤𝙥𝙥𝙤𝙣𝙚𝙣𝙩𝙨 𝙘𝙖𝙧𝙚𝙛𝙪𝙡𝙡𝙮, 𝙩𝙝𝙚𝙣-𝙣𝙚𝙫𝙚𝙧 𝙤𝙛 𝙛𝙚𝙣𝙙 𝙤𝙧 𝙙𝙚𝙘𝙚𝙞𝙫𝙚 𝙩𝙝𝙚 𝙬𝙧𝙤𝙣𝙜 𝙥𝙚𝙧𝙨𝙤𝙣.





15 last posts shown.