Natnael Mekonnen


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Politics


በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Politics
Statistics
Posts filter


ቭላድሚር ፑቲን እጅግ አማላይ እና ቅንጡ የህይወት ዘይቤ ያላቸው ከበርቴ ሰው ናቸው ይላሉ አንዳንድ የመረጃ ምንጮች። በክሬምሊኑ አለቃ ዙሪያ አይናቸው ለሚቀላው የምዕራቡ ዓለም ሰዎች የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቅንጡ አኗናር ጭምር ንዴት ፈጣሪ ሆኖ ይታያል። በእርግጥ ግን የፑቲን የመጋረጃ ጀርባ ሕይወት ምን ይመስላል?! ቀጣዩን የዩትዩብ ሊንክ ስትከፍቱ ከብዙ በጥቂቱ 43 አውሮፕላኖች፣ 700 እጅግ ውድ መኪኖች እና 20 ያማሩ ቤተመንግስቶች አሏቸው ስለሚባሉት የሩሲያው መሪ አኗኗር በተመለከተ ብዙ ሚስጥራዊ ታደምጣላችሁ። እግረ መንገዳችሁን ቪዲዮውን ላይክ፣ ቻናሉን ሰብስክራይብ እንድታደርጉም በማክበር ተጋብዛችኋል፡፡
https://youtu.be/XPBbDroC0kw?si=uJCv_UyHlyXPWA4o


መስቀል በአንገታቸው የተሸከሙ የአውሬዎች ስብስብ!

የጽንፈኛው ፋኖ መሪዎች መስቀል በአንገታቸው ተሸክሞ የሀይማኖት አባቶች እና ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ ይገድላሉ!

የጽንፈኛው ቡድን አላማ የሌለው ተራ የመንደር ሽፍታ መሆኑን በተደጋጋሚ ተናግራናል። በዚህ ሰሞን መስቀል በአንገቱ ተሸክሞ የሚዞር የጎጀሙ ፋኖ መሪ ዘመነ ካሴ ያለምንም ርህራሄ የሀይማኖት አባቶችን ጨምሮ በርካታ ንፁሃን የአማራ ልጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ እየጨፈረ በመግደል አረመነያዊ ድርጊቱን በቪዲዮ ቅርፆ አሳይቶናል። ከዚህ በፊትም ቡድኑ በተለያዩ የአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሙስሊሞችን እና ክስቲያኖችን ሲገድል እንዲሁም አፍኖ በማገት በሚሊዮን ብር ተቀብሎ ሲለቅ እንደ ነበር ይታወሳል።

ቡድኑ በመከላከያ ሰራዊታችን ምት ክፉኛ የተጎዳ ሲሆን አሁን አሁን የፈሪ ዱላውን በንፁሃን ዜጎች ላይ በማሳረፍ ሞቱን በማፋጠን ላይ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ በውስጡ በተፈጠረው መፈራካከስና የእርስ በርስ መባላት ታጣቂዎቹን ተስፋ በማስቆረጥ ቡድኑ አላማ የሌለው የአረማኔዎች ስብስብ መሆኑን የተረዱ በርካታ ታጣቂዎች ለመከላካያ ሰራዊቱ እጅ ለመስጠት ውስጥ ለውስጥ ሽማግሌዎችን እየላኩ እንደ ሆነ መረጃዎች አመላክቷል።


የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዮስ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ ክብረ-በዓልን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፏል!!!

ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ ለእንኳን ሊቀ-መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ ከተማችንን ሀዋሳ እንደወትሮ ፍፁም ሰላማዊ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ የታላቁን ሊቀ መልዓክት አመታዊ የንግስ በዓልን አሰናድታ ምዕመን እንግዶቿን እየጠበቀች ነው።

በዚህም የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እንደ ዘርፉ ከሁሉም የሰላምና ፀጥታ አካላት ጋር ውይይቶች በማድረግ ከፌደራል ፖሊስ ጋር እና ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት ተቋም ጋር በልዩ ቅንጅት በመስራት ከአዲስአበባ - ሀዋሳ ያለውን መንገድ ደህንነቱ የተጠበቀ በማድረግ ተጓዟች ወደ ሀዋሳ ከተማ የምታደርጉ ምዕመናን ፍፁም ሰላም እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ መምጣት የሚያስችላችሁን ዝግጅት ያደረግን ሲሆን ምዕመኑንም በፈለገው የትራንስፖርት አግልግሎት በመጠቀም ወደ ከተማችንን ሀዋሳ በመምጣት የበዓሉ በረከት ተካፋዮች እንድትሆኑ እንደሁልጊዜውም የሰራን በመሆኑ ዳዎኤ-ቡሹ ብለን ምዕመን እንግዶቻችንን ለመቀበል ተዘጋጅተናል።

ከእምነቱ አባቶች ብሎም ከእምነቱ ተካታይ ወጣቶች ጋር ባደረግነው ውይይት መሰረት በዓሉ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ እንዲውል ምዕመናን ከፀጥታ አካላት ጋር በአንድነት አብሮ በመስራት እንዲተባበር ስል ጥሪ አስተላልፋለሁ ብለዋል።

አቶ አለማየሁ አክለውም በዓሉን ምክንያት በማድረግ በአልጋ ዋጋ ላይ ዋጋ የሚጨምሩ አልጋ ቤቶች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያስጠነቀቁ ሲሆን ምዕመኑም የተጋነነ ጨማሪ በተመለከተ ጊዜ ወዳያውኑ ለፀጥታ አካላት እንዲያሳውቅ አሳስበዋል።

እንግዶችም የተለየ ነገር በገጠማቸው ጊዜ በከተማችንን በርከት ያሉ የፖሊስ መረጃ በመቀበያዎች 24 ሰዓት የሚሰሩ ሲሆን በተጨማሪም #7614 #0462201046 ስልኮች በፈልጉት ሰዓት በመደወል ያሳውቁን ሲሉ አሳውቀዋል።

በመሆኑ በከተማችን በዓመት ሁለት ጊዜ በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን ሊቀ-መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ከዚህም ውስጥ በድምቀት ከሚከበርባቸው አንዱ ሐምሌ 19 ሲሆን በዓሉን የክልሉ የፀጥታ ሃይል በአንድነት በጉጉት ምዕመኑን እየጠበቀ እንገኛል ዳግም እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ኣመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ ሲል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


ጎፋ ከአደጋው ማግሥት

ጎፋ፦በመሬት መንሸራተት አደጋው በአሁኑ ወቅት ከ40 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከአፈር በታች ይገኛሉ የሚል ጥርጣሬ መኖሩን የገዜ ጎፋ ወረዳ ባለሥልጣናት ዐሳውቀዋል ። ከትናንት በስቲያ ሰኞ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ አምስት የባለቤታቸው ቤተሰብ አባላትን የቀበሩም አሉ ።

አደጋው አስከፊና በቃላት ለመግለጽ እንደሚከብድ የተናገሩት አቶ ዘለቀ “ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ከአፈር ናዳ ሥር ለማግኘት ያለውን ፈተና ከባድና የሚጨንቅ ነው ብለዋል። ከተጫነው ናዳ ሥር የወጡ ሟቾች በጭቃ የተለወሱ ናቸው ። ሰዎች የቤተሰብ አባሎቻቸውን የሚለዩት የአስክሬኖችን ፊት በማጠብ ነው ። 16 የቤተሰብ አባላቱን ያጣ ፣ ስምንት ልጆቿን ያጣች እናት አለች ፣ ቤተሰቦቹ አልቀውበት ብቻው የቀረ ህጻን አለ ፡፡ ሁኔታ ዘግናኝና አስጨናቂ ነው “ ብለዋል ። በቀበሌው የደረሰው አደጋ ቁጥሩ ቢለያይም እያንዳንዱን ቤት ለከፋ ሐዘን መዳረጉን ተጎጂዎች ለዶቹ ቬለ ተናግረዋል ።

በመሬት መንሸራተት አደጋው ሕይወታቸው ያለፈ ቀሪ ሰዎችን የመፈለጉ ሂደት አሁንም መቀጠሉን የወረዳ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማስረሻ ማንአየ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል ።

Via DW ከጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ


ውድ መንገደኞቻችን የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እ.ኤ.አ. 21 ጁላይ 2024 ለአየር መንገዳችን በላከው ደብዳቤ እ.ኤ.አ. ከሴፕቴምበር 30 ቀን 2024 ዓ.ም. ጀምሮ አየር መንገዳችን ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን ሁሉንም በረራ ማገዱን አሳውቆናል።

ደብዳቤው ለክልከላ ውሳኔ ያደረሱ ምክንቶችን አልጠቀሰም። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳዩን አስመልክቶ የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ጉዳዩም በበጎ መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ያለውን ዕምነት ይገልጻል። በዚሁ አጋጣሚ አየር መንገዱ ተጨማሪ መረጃዎች እንደተገኙ ለውድ ደንበኞቹ እንደሚያሳውቅ ለመግለፅ ይወዳል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አልያንስ አባል


ስራችን ከቃላችን ጋር ሮያሎች ነን
📍📍በጃክሮስ ሜታ ካቶሊክ ሚሽን ትምህርት ቤት ጋር
በካሬ  86,500ብር ለውስን ቤቶች ብቻ
ማለትም
🌟 ባለሁለት መኝታ 138 ካሬ
🌟ባለሦስት መኝታ 173 ካሬ
ያስተውሉ ከሮያል ቤት ሲገዙ ዘየዱ ለምን ካሉ
      ✨ ግንባታው 80% መድረሱ
      ✨ በአጭር ጊዜ የሚረከቡት መሆኑ
      ✨ለገበያ ለትምህርት ቤት ለጤና ተቋም ለቤተ እምነቶች በቅርብ መሆኑ
      ✨የመኪና ማቆምያ የልጆችመጫዎቻ ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዠግጁ

🌟በ10% ቅድመ ክፍያ
ለበለጠ መረጃ 🤳0935088808


"የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ለአለም የምናስተዋወቅበት መድረክ ይሆናል::"
አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ

የቱሪዝም ሚንስቴር በፓሪስ ኦሎምፒክ ለሚሳተፉ አትሌቶች የሽኝት መርሀ ግብር አድርጏል::

አርብ የሚጀመረውን የፓሪስ ኦሎምፒክ 1.5 ቢሊየን የአለም ህዝብ በቴሌቪዥን መስኮት ከ 8 ሚልዮን በላይ ህዝብ ደግሞ በአካል በመገኘት እንደሚመለከተው ይጠበቃል::

በዚህ ትልቅ አለም አቀፍ መድረክ የኢትዮጵያን ምድረቀደምትነት እና ያሉንን የቱሪዝም ሀብቶች ከመክፈቻው እለት አንስቶ በሁሉም አትሌቶቻችን በሚሳተፉባቸው ውድድሮች የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራ የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ተናግረዋል::

ለዚህም የሚሆን የተለያዩ የህትመት ስራዎች እና አልባሳት በቱሪዝም ሚንስቴር አማካኝነት መዘጋጀታቸውንም ገልፀዋል::

አትሌቶቻችን በሚያደርጏቸው ውድድሮች ካሸነፉ በሁዋላ ለ 1 ደቂቃ ያህል በስታዲየምዎች ውስጥ የሚከፈት የኢትዮጵያን ምድረ-ቀደምትነት የሚገልፅ ሙዚቃ እና ምስልም ይፋ ሆኗል::

አምባሳደር ናሲሴ አትሌቶች፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፓሪስ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ለማስተዋወቅ ሚንስቴር መስሪያቤቱ ያቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው ለሚያደርጉት አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበዋል::

ለአትሌቶቻችን መልካም እድል እንመኛለን!


“ሙዐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት መፅሃፍ ሳይሆን የፃፍከው ኢትዮጵያ ነው የሳልካት”-ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

ሙዐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ‘የትርክት ዕዳና በረከት’ የተሰኘ 35ኛ መፅሃፉን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት አስመርቋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላፈ‍ኡት መልእክት፤ ዳንኤል ክብረት 34 መፅሃፍ ፃፈ ይሄኛው መፅሃፍ ግን ተጠበበት። ሙዐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት መፅሃፍ ሳይሆን የፃፍከው ኢትዮጵያ ነው የሳልካት ብለዋል።

“የትርክት ዕዳና በረከት” መፅሐፍ በ46 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ 575 ገፆች ያሉት ነው፡፡

የትርክት ዕዳና በረከት በኢትዮ ፋጎስ መጻሕፍት መደብር (ከአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አጠገብ)
ያገኙታል።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr


ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተገኙበት የሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት "የትርክት ዕዳና በረከት" የመፅሃፍ ምረቃ ስነ-ስርዓት በምስል13 last posts shown.