…ቀልብን የሚሰብሩ ክስተቶች አጋጣሚ ሳይሆኑ ቀደር ናቸው። ቀልብን ይሰብሩ፣ አንገት ያስደፉ ይሆናል። ነገርግን የጥበብ በርን ይከፍታሉ። ይህ የሚሆነው ግን ህመሙን ከተረዳነው፣ በኢማን ከተጋፈጥነው እና ስቃዩን ከተቀበልነው ብቻ ማለት ነው!… በበርካታ ሶላት፣ ጾም… ያልተገኘ የሩህ ብልፅግና በመከራ ውስጥ ይገኛል!… በመከራ ውስጥ ይታደጋል! ከፍታ ይገኛል!…
ሁሉም ነገር የአላህ ስራ ነው። የአላህን ጥበብ በሁሉም ስራዎች ውስጥ እንፈልገው። እኛ እና ዱንያ ያለን ግንኙነት የፈተና እና የተፈታኝ ግንኙነት አይነት ነው። ዛሬ ባለ ነገር ስኬት አይለካም። ዛሬ የስራና የሙከራ ጊዜ ነው። የውጤቱ ጊዜ አላህ ዘንድ ያለው ቀን ነው!
💚ደህና እደሩ!💚