Orthodox Mezmur Channel


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


✞✞✞ Orthodox Mezmur Channel ✞✞✞

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቆየት ያሉ እና አዳዲስ መዝሙሮችን ያገኛሉ።
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All

ለማንኛውም ሀሳብ ፣ ጥቆማ ፣ አስተያየት
👇👇👇
@Orthodox_Mezmurs
@Orthodox_Mezmurs

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


ደግፊኝ ልቁም አግዢኝ ማርያም | ዘማሪት ሰላማዊት ሶርሳ

ነይ ሶልያና ተጫምተሽ ደመና
ነይ አዛኝቱ እመ ትህትና
አግዢኝ እናቴ
ይሙላልኝ ጉድለቴ
አቅርቢኝ ከፊቱ
ይማረኝ ምሕረቱ
አዝ

እኔ የማላውቀው ብዙ ነው ጉድለቴ
ጥሪት አልቆብኛል ባዶ ነው ሌማቴ
ምርኩዝ ያደረኩት ድንገት ተቀየረ
የእኔ ያልኩት ሁሉ የወረት ነበረ
ደግፊኝ ልቁም
አግዢኝ ማርያም
አሳስቢ ስለ እኔ
ይቅለል ሃዘኔ
አዝ

በሃዘን ተከብቤ ሰላም እርቆኛል
ወገን ዘመድ ሁኚኝ እናቴ ከፍቶኛል
የሚያጽናናኝ የለም አይዞሽ ባይ ከጎኔ
እመ አምላክ አብሺው እንባዬን ከዓይኔ
ደግፊኝ ልቁም
አግዢኝ ማርያም
አሳስቢ ስለ እኔ
ይቅለል ሃዘኔ
አዝ

ዙሪያዬን ያጠረው በእሾህ አሜኬላ
ጠላቴ እንዳይውጠኝ ሁኚልኝ ከለላ
እኔ ኃጢያተኛ ነኝ የለኝ መልካም ምግባር
ልጅሽ ፊት አልቆምም በደሌ ቢቆጠር
ደግፊኝ ልቁም
አግዢኝ ማርያም
አሳስቢ ስለ እኔ
ይቅለል ሃዘኔ
አዝ

ሸክሙ ከብዶብኝ ቀሏል ማንነቴ
አሳስቢልኝ ማርያም የእንባ ነው እራቴ
ከስደት መልሺኝ አልሁን ወገን አልባ
ከናፈቀኝ ደጅሽ መባን ይዤ ልግባ
ደግፊኝ ልቁም
አግዢኝ ማርያም
አሳስቢ ስለ እኔ
ይቅለል ሃዘኔ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ደጅ ጠናሁ | ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሃዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን /2/
አዝ

የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንችን ተጠግቼ የአለሟን  ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንችም ደግነት
ባርያሽን ሰወረኝ ከአስጨናቂው ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ
አዝ

ልቤ በአንች ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባሪያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላኑን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ
አዝ

እጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ
በመርገም ምክራቸው ሊለያዩኝ ሲሹ
እሱ የሰጠኝን እሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብዬ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ
አዝ

ከአውደ ምህረቱ ሆኜ ስጠራት
ዘንበል ብላ አየችኝ ኪዳነ ምህረት
ሀሳብሽን ምንም የለም የሚመስለዉ
እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነዉ
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


በምን እፅናናለሁ | ዘማሪ ሚኪያስ አረጋዊ

በምን እፅናናለሁ ከሌለኸኝ
በምን ልበረታ ካላገስከኝ
አንተ ስላለህ ነው መድኃኒቴ
ቆሜ መታዬቴ /2/
አዝ

ሸክም ለከበደ ማረፊያ ነህ
እጅግ የቀለለ ቀንበር ያለህ
ፍቅርህ ነው የሚያሰማራኝ
በለምለም መስክ ያቆመኝ
/2/
ቸር አምላክ የእውነት ዳኛ
አማኑኤል የእኔ መታመኛ/2/
አዝ

ጨለማን አላውቅም በጉዞዬ
በህይወቴ ሁሉ ነህ መሪዬ
ተጓዝኩኝ ሌቱን በብርሃን
በአንተ አየሁኝ መሻገርን
/2/
ቸር አምላክ የእውነት ዳኛ
አማኑኤል የእኔ መታመኛ
አዝ

ማቀርቀሬን ሰበርክ አልኩኝ ቀና
በርትቼ ተራመድኩ እንደገና
ቃልህ ኃይሌ የሚያጸናኝ
በአለት ላይ የተከልከኝ
/2/
ቸር አምላክ የእውነት ዳኛ
አማኑኤል የእኔ መታመኛ
አዝ

እንባዬ ታበሰ ስታፅናናኝ
ግን የሆነው ሆኗል ስትረዳኝ
በጠላቴ ፊት ሞገስ ሆንከኝ
ለባህሪያህ ድል ሰጠኸኝ
/2/
ቸር አምላክ የእውነት ዳኛ
አማኑኤል የእኔ መታመኛ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ልቤ ያውቀዋል ያደረክልኝን ነገር | ዘማሪ ዲያቆን ነብዩ ሳሙኤል

ልቤ ያውቀዋል ያደረክልኝን ነገር
የሠራህልኝን ሥራ
መድኃኔዓለም አወጣኸኝ ከመከራ
በቃል ጉልበት አይወራ
አዝ

መስቀል ተሸክመህ በደም ርሰህ
እኔን በመከራ ዳግም ወልደህ
በክብር ተሻገርኩ ክሰህልኝ
በህይወት አቆምከኝ ወድቀህልኝ/2/
አዝ

የበደሌን ጋራ አቀበቱን
የባርነት ሰነድ እዳ ክሱን
አጥፍተኽው ጌታ መዳን ሆነ
እርቃኔ በእርቃንህ ተሸፈነ/2/
አዝ

በፍቅርህ መአዛ ረክቷል ልቤ
በማይቆም መውደድህ ተከብቤ
የህይወቴ ወደብ መስቀልህ ነው
ወጀብና ነፋስ የማይነቅለው/2/
አዝ

የሾህ አክሊል ደፍተህ ኤልሻዳይ
እፎይ አለ ልቤ ከስቃይ
ሆኖልኛል መዳን አንተ ታመህ
ነፃ ወጣሁ ሸክሜን ተሸክመህ/2/
አዝ

ዙፋንህን አስተወህ የኔ ፍቅር
ከሰማይ ሀገርህ መጣህ ከምድር
ታየህ ስትፈልገኝ ልጄ ብለህ
ፈራጅና አፅዳቂ አምላኬ ነህ /2/

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


“ትህትናሽ ግሩም ነው”

ትህትናሽ ግሩም ነው ደግነትሽም/2/
እናቱ ሆነሻል ለመድኃኔዓለም/2/
አዝ

ንፅሕት ስለሆንሽ   እመቤቴ እመቤቴ
እንከን የሌለብሽ    እመቤቴ እመቤቴ
የፍጥረታት ጌታ   እመቤቴ እመቤቴ
ባንቺ አደረብሽ   እመቤቴ እመቤቴ
የድንግል መመረጥ  እመቤቴ እመቤቴ
ዜናው አስገረመን   እመቤቴ እመቤቴ
እሳቱን ታቅፈች    እመቤቴ እመቤቴ
የማይቻለውን   እመቤቴ እመቤቴ
አዝ

ምርኩዜ ልበልሽ  እመቤቴ እመቤቴ
ጥላ ከለላዬ    እመቤቴ እመቤቴ
ጋሻዬ ነሽ አንቺ  እመቤቴ እመቤቴ
ለእኔ መመኪያዬ    እመቤቴ
በዓለም እዳልጠፋ እመቤቴ እመቤቴ
ሕይወቴ መሮብኝ እመቤቴ እመቤቴ
እንደ ወይን አጣፍጪው እመቤቴ እመቤቴ
ድንግል ድረሽልኝ  እመቤቴ እመቤቴ
አዝ

የምሥራቅ ደጃፍ ነሽ እመቤቴ እመቤቴ
የሁላችን ደስታ. እመቤቴ እመቤቴ
እሙ ለጸሐይ ፅድቅ   እመቤቴ እመቤቴ
የሁሉ ጠበቃ. እመቤቴ እመቤቴ
ድንግል የድል አክሊል እመቤቴ እመቤቴ
ድንግል የፅድቅ ሥራ. እመቤቴ እመቤቴ
ድንግል መሰላል ነሽ እመቤቴ እመቤቴ
የተዋህዶ ተስፋ እመቤቴ እመቤቴ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


አኑሮኛል ቸርነትህ | ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

አኑሮኛል ቸርነትህ ልክ የሌለው ደግነትህ
እንዳንተ አይነት ከየት ይገኛል
ሁሉም ነገር ትዝ ይለኛል/2/
እዝ

ያቺ ፈዋሽ አዳኝ እጅህ
ዛሬም ለኔ ተዘርግታ
በሐጢያት ርቄ እንዳልጓዝ
አስረኸኛል በውለታ
ደግሞስ ህይወት ምርጫ ቢሆን
ካንተ ወደማን ይኬዳል
አባቴ ፍቅርህ እኮ
ጌታዬ ፍቅርህ እኮ
አለምን ያስክዳል
እዝ

ሞቼ ነበር ተቀብሬ
ጌታ ወደ እኔ ባትመጣ
አንተ ሞቴን ባትሞትልኝ
ወዴት ነበር የእኔ እጣ
ከንቱ ነበር ማንነቴ
ተሽናፊ ለዚች ዓለም
ግን አንተ የያዝከው
አባቴ የያዝከው
ይኖራል ዘላለም
እዝ

መቅደስህን ተጠግቼ
አይቻለሁ ብዙ ነገር
በልቤ ውስጥ ያስቀመጥኩት
እንዲህ ለሰው ማይነገር
ግን የሆነው ሁሉም ሆኖ
የለም ዛሬ ያላረፈ
የመከራው እሳት
የፈተናው እሳት
ባንተ እየታለፈ
እዝ

አይጠፋኝም ያ ፈገግታ
ልጄ ብለህ ያሳየህኝ
አመፀኛ መጥፎም ሆኜ
በትክሻህ ላይ ያኖርከኝ
እንዲህም አይነት ወዳጅ አለ
እየጠሉት የሚያፈቅር
ስሙም ኢየሱስ ነው/2/
የፅድቃችን ሚስጥር
እዝ

ስነፈርቅ ሳለቅስብህ
እሺ እያልከኝ ሁሉም ሆነ
ማይሆንለት ነገር የለም
ለካስ ባንተ የታመነ
መቸኮሌ መጣደፌ
አምላኬ ሆይ በከንቱ ነው
መፈፀሙ ላይቀር/2/
ጌታዬ አንተ ያልከው

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ/2/
መከራ ቢገጥመኝ ለበጎ ነው ብዬ አልፋለሁ/2/
አዝ

በሰንሰለት አስረው በወህኒ ቢጥሉኝ
መከራን አብዝተው እጅግ ቢያስጨንቁኝ
ለበጎ ነው ብዬ ተስፋ አድርጌያለሁ ይሁን አንተ ያልከው እገዛልሃለሁ
አዝ

በመከራው ፅናት ጉልበቴ ደከመ
ትካዜ ከቦኛል ተስፋዬም ጨለመ
ነገር ቢሆን ባይሆን አንተን እንዳከብር
አድለኝ በፀጋ ጌታ ያንተን ፍቅር
አዝ

ከሀገር ወጥቼ በዱር መሰደዴ
ከባዕዳን ሀገር እርቄ መሄዴ
ለበጎ ነውና መቼ ይከፋኛል
ፈጽሞ እንዳልጠፋ እጄን ይይዘኛል
አዝ

ትላንትናም ዛሬም አንተ ያው አንተ ነህ
ፍቅርህ አይቀየር ወረትም የለብህ
ስምህን መጥራቴ ሞገስ ሆኖልኛል
ጠላቴ ቢፎክር መች ያሸንፈኛል

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ስምሽን ጠርቼ | ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ
ማርያም ብዬ መች እወድቃለሁ
የምጽናናበት ስምሽ ነውና
ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና
አዝ

ጨለማ ውጦኝ በጠላት ሀገር
ለዘመናትም ስረገጥ ስኖር
ዲያብሎስ ማርኮ ሲያሰቃየኝ
የዓለሙን መድን ወለድሽልኝ
ከአባቶቼ ርስት ከሀገር ወጥቼ
በአሕዛብ አገር ስኖር ተሸጬ
ደርሰሽ አጽናንተሽ አከበርሽኝ
ብቸኝነቴን አስረሳሽኝ
አዝ

ድንኳኑ ሞልቶ ሰዉ ታድሞ
አስተናባሪው በጭንቀት ቆሞ
ምን አቀርባለሁ ብዬ ስቸገር
ምልጃሽ ደርሶልኝ ዳንኩኝ ከማፈር
ያሰብኩት ሐሳብ ደመና ሆኖ
ቢበተንብኝ እንደ ጉም ተኖ
ይሆናል ያልኩት ሳይሆን ቢቀርም
በእመ አምላክ እኔስ ተስፋ አልቆርጥም
አዝ

እናት አባቴ ባያስታውሱኝ
ይህች ዓለም ንቃ ገፍታ ብትተወኝ
አንቺ ካለሽኝ ምን እሆናለሁ
አውሎ ነፋሱን ባሕሩን አልፋለሁ
ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝ
መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም
አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና
ውለታሽ ድንግል አለብኝና
አዝ

ክፉዎች ደርሰው ቢዝቱብኝ
አንቺን መውደዴን አያስተውኝ
በአሕዛብ መሐል ስምሽን ስጠራ
መከታ ሁኚኝ እናቴ አደራ
ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝም
መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም
አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና
ውለታሽ ድንግል አለብኝና

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ኃይልህ ሲገለጥ በሰማይ | ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ

ኃይልህ ሲገለጥ በሰማይ/2/
አቤት ማን ይቆም ይሆን ከፊትህ
ማን ይቆም ይሆን/2/
ከፊትህ ማን ይቆም ይሆን

አቤት ቀንደ መለከት ሲነፋ
አዋጅ ሲታወጅ በይፋ
ጻድቃን ሲጠሩ ለተድላ
ምን ይሆን የእኛ ተስፋ
አዝ

አቤት መላእክት ሰማዩን ሲያርሱት
ቀድመው ሲሰሙ መባርቅት
ያልታየና ያልተሰማ
ድምጽ ሲሰማ ከራማ
አዝ

አቤት ሰባቱ ነፋስ ተከፍተው
ምድርን ሲያውኳት ቀዝፈው
ሲታዘዝ የባሕር ሞገድ
ምድሪቷን ሊከድናት ለፍርድ
አዝ

አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን
መልካም የሰሩ ቡሩካን
በምድር የሰሩ ትሩፋት
ሲያቀርቡ ለአምላክ ስብሐት  
አዝ

አቤት ኃጥአን ግን ለፍርድ ሲጠሩ
በጨለማ ዓለም ሊቀሩ
የማይጠቅም ዋይታ ሆኖ
መዋረድ ይሆናል አዝኖ
አዝ

አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን  
መልካም የሰሩ ቡሩካን
በምድር የሰሩ ትሩፋት
ሲያሰሙ ለአምላክ ስብሐት

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ፈተና ወጀብ ቢበዛ | ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ

ፈተና ወጀብ ቢበዛ
አይተናል ሕዝቡን ሲያበዛ
በሕይወት አንዴ ጠርቶናል
እግዚአብሔር መች ይተወናል/2/
አዝ

ፍቅር ነዉ የናርዶስ ሽቶ
ወደደን ተሰቅሎ ሞቶ
ነጎድጓድ መብረቅ ቢሆንም
በህይወት አለን አሁንም/2/
አዝ

መኳንንት ደጁን ክፈቱ
የፀጋዉ  ፈልቷል ዘይቱ
ተራግፏል ሸክማችን
ምህረቱ ቢፈስልን/2/
አዝ

ተጽናንቷል አርፏል ልባችን
በእሳት ታጥሮአል ቅጥራችን
አንወድቅም አንሸነፍም
ይዞናል የአምላካችን ስም/2/
አዝ

ሕይወት ነህ የፅድቅ ጥላ
ያውቅሐል ቃል የተመላ
ነህ አንተ ጣፋጭ ምግባችን
እግዚአብሔር ቸሩ አምላካችን/2/

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


አለፍኩኝ ድንግል ማእበሉን | ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

አለፍኩኝ ድንግል ማእበሉን
አለፍኩኝ ድንግል ውጣ ውረዱን
ምርኩዜ ስለሆንሽ ስጠራ ስምሽን
አዝ

አለፍኩኝ ድንግል  በእመቤቴ ምልጃ
አለፍኩኝ ድንግል  ወንዙን ስሻገር
አለፍኩኝ ድንግል  ያባረረኝ ጠላት
አለፍኩኝ ድንግል  ቀረ ሰምጦ ባህር
አለፍኩኝ ድንግል  ከበሮውን ላንሳ
አለፍኩኝ ድንግል  እንደ ሙሴ እህት
አለፍኩኝ ድንግል  ምስጋና ልሰዋ
አለፍኩኝ ድንግል  ለዓለም እመቤት
አዝ

አለፍኩኝ ድንግል  ወንድሞች ቢሸጡኝ
አለፍኩኝ ድንግል  አሳልፈውኝ
አለፍኩኝ ድንግል  በባዕድ ከተማ
አለፍኩኝ ድንግል  ድንግል ሾመችኝ
አለፍኩኝ ድንግል  በቅን የማመልከው
አለፍኩኝ ድንግል  ልጅሽ ክርስቶስ
አለፍኩኝ ድንግል  ምልጃሽን አስቦ
አለፍኩኝ ድንግል  ሰጥቶኛል ሞገስ
አዝ

አለፍኩኝ ድንግል  በስምጥ ሸለቆ
አለፍኩኝ ድንግል  ሆኜ ባጣብቂኝ
አለፍኩኝ ድንግል  የምደገፍበት
አለፍኩኝ ድንግል  አንዳች ሳይኖረኝ
አለፍኩኝ ድንግል  ባንቺ ተርፌአለሁ
አለፍኩኝ ድንግል  ምርኩዝ ሆነሽኝ
አዝ

አለፍኩኝ ድንግል  ሰው የለኝም እና
አለፍኩኝ ድንግል  ድንግል አትራቂኝ
አለፍኩኝ ድንግል  አንቺው ነሽ እናቴ
አለፍኩኝ ድንግል  የማትሰለቺኝ
አለፍኩኝ ድንግል  ውለታዋ ብዙ
አለፍኩኝ ድንግል  የድንግል ማርያም
አለፍኩኝ ድንግል  እርሷን ለእኔ የሰጠ
አለፍኩኝ ድንግል  ይክበር ዘለዓለም

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


በድንኳኔ እልልታ ሙሉ ነው | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

በድንኳኔ እልልታ ሙሉ ነው
በድንኳኔ ዝማሬ ሙሉ ነው
በማንነቴ ላይ እግዚአብሔር ታላቅ ነው
አዝ

ፍላፃውን የጠላቴን ቁጣ
መከተልኝ ወደ እኔ እየመጣ
በራራልኝ በእርሱ በወዳጄ
ሰላም ሰፍኗል በጓዳ በደጄ
አዝ

የመንገዴን ጥርጊያውን አቅንቶ
የሰለለ ጉልበቴን አፅንቶ
ከፊት ለፊት በድል ቀድሞልኛል
በምስጋናው  ከኋላ ስቦኛል
አዝ

ስላልተወኝ አንዳች አጣህ ብሎ
ሙሉ ሰው ነኝ የለኝም ጎዶሎ
በከፍታ ብኖር በዝቅታ
ደስተኛ ነኝ ሁልጊዜ በጌታ
አዝ

ማማረርን ማጉረምረም ትቻለሁ
አንደበቴን ቅኔ ሞልቻለሁ
ቢፈራረቅ ብርሃን ጨለማ
ከቶ አልወርድም ከምስጋና ማማ/2/

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ሰዎች ፈረዱብኝ | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ሰዎች ፈረዱብኝ
አንተ ግን አዳንከኝ /2/
አምላኬ ሆይ ተመስገንልኝ
ጌታዬ ሆይ ተመስገንልኝ
ሌላ ምን ቃል አለኝ
አዝ

ሊያልፉኝ አልወደዱም ነውሬን ሊሰውሩ
ሰዎች ፈጠኑብኝ በደሌን ሊያወሩ
አንተ ግን ሰብስበህ በፍቅር ሸፈንከኝ
በመተላለፌ አዝነህ ሳትለየኝ
ይህ ፍቅርህ ሰበረኝ አጣበቀኝ ካንተ
ደጅህ ያመጣኛል ሁሌ እየጎተተ /2/
አዝ

መርከሴን አውጀው ሲያነሱብኝ ድንጋይ
ሰወረኝ ተዓምርህ ልጅ ሳልሰቃይ
ወደህ ስለማርከኝ ክፉዎች ተከዙ
ይህ አይደለም ብለው የኃጢአት ደሞዙ
ካነተ በላይ ጌታ ማን ሊያውቀኝ ይችላል
የፍቅርህን ሚዛን ማንስ ያዛባዋል /2/
አዝ

ማዳንህ ይደንቃል ለወደኩት ልጅህ
ምህረትህ ይደፋል ሁሌ በሚዛንህ
እንደሰው አይታይ ፍርድህም ይለያል
ለባርያህ አርነት በምህረት ፈርደሃል
ፍቅር እየዘረዘርክ መንገዴን የጠረክ
ስለልጅህ ጽድቅን ለድህነት የፈረድክ /2/
አዝ

እኔ አልፈርድብህም በሰላም ሂድ አልከኝ
ዳግም እንዳልበድል በፍቅር እያየኸኝ
ወደፅድቅህ ህጎች ነፍሴን አፈሳለሁ
እንዲህ ከወደድከኝ ወዴት እሄዳለሁ
አልለይም ካንተ ከፍቅር መድረኬ
አመልካለሁ አንተን ፊትህ ተንበርክኬ /2/

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


እውነት ነው አዎ እውነት ነው | ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ

እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው
አዝ

ወደ እግዚአብሔር አብ የምንደርስበት
አንድያ ልጁን የምናምንበት
የህይወት መንገድ እርሱ ብቻ ነው
የባሕርይ አምላክ ብለን ስናምነው
አዝ

በማርያም ስጋ የተገለጠው
ወልድን ስናውቅ ነው አብን ያወቅነው
አብ በእርሱ እንዳለ እርሱም በአብ አለ
በኃይል በሥልጣን የተካከለ
አዝ

ሥጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ
ህይወት የሰጠን በደልን ክሶ
እኛም ዳሰስነው በላን ጠጣነው
በዝግ ቤት ሳለን ገብቶ ያየነው
አዝ

ፈቅዶ ቢወሰን በአጭር ቁመት
ረቂቁን ቢገዝፍ በጠባብ ደረት
መንሹ በእጁ ነው ሁሉን ያጠራል
በዓለም ሊፈርድ ዳግም ይመጣል

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ምን ሊለውጠው ያንተን ውለታ | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

ምን ሊለውጠው ያንተን ውለታ
ምን ሊቀይረው ያንተን ስጦታ
ለዘላለም ታትሞ የሚኖር
ማን ይስተካከላል ጌታ ያንተን ፍቅር
አዝ

ጎብጬ ስኖር በሃዘን
እዘራው ነበር እንባዬን
ሩህሩህ አምላኬ ደረስክና
ሰው አደረከኝ እንደገና/2/
አዝ

ሲሸሸኝ ሁሉም ሲርቀኝ
ሳትፀየፈኝ ቀረብከኝ
ዘይት ያፈሰስክ በቁስሌ ላይ
ወዳጅስ ማነው ካንተ በላይ/2/
አዝ

አዳም ወዴት ነህ እያልከኝ
በፍቅር ድምጽህ ፈለከኝ
አልብሰህኛል ነጩን ልብስ
እወድሃለሁ ኢየሱስ አከብርሃለሁ ክርስቶስ
አዝ

አልመለስም ወደኋላ
አያይም ዓይኔ ካንተ ሌላ
አልፈራም የጠላትን ዛቻ
አድነኸኛል አንተ ብቻ
ሞተህልኛል አንተ ብቻ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ቸርነትህ ነው | ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከ ዛሬ
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ /2/
አዝ

መክሊቴን ቀብሬ ባሳዝንህ
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታ እንዳትረሳኝ
በፍቅር ጎብኝተህ ከሞት አውጣኝ
ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ
በረሀብ በእርዛት ተቸገርኩኝ
አምናለሁ አምላኬ እንድትምረኝ
ለይቅርታ መጣሁ ተቀበለኝ
አዝ

አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ
በአንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታ ለባሪያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቆሜ ለመዘመር
ስራህን ለትውልድ ለመመስከር
እኔ ማንነኝ ብዬ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ
በሰው እጅ መመካት አቁሜያለሁ
አዝ

እረዳቴ አንተ ነህ አውቄያለሁ
አንተ ከጠበቅከኝ በሕይወቴ
ቅጥሬ አይደፈርም መድኃኒቴ
የኔን ሥራ ተወው ተግባሬን
የመስቀሉን ነገር መርሳቴን
አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ
እየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ልጁ ነኝ የሚካኤል ልጁ | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

ልጁ ነኝ የሚካኤል ልጁ
በቤቱ ያደኩኝ በደጁ
የልቤ ብዬ የምጠራው
ሚካኤል ለኔ አባቴ ነው
የልቤ ብዬ የምጠራው
ሚካኤል አዎ አባቴ ነው
አዝ

በክንፎቹ እኔን በእጁ ሰይፍ ይዟል
ሚካኤል ሊረዳኝ ቆሟል
እንዳስፈሪ እንደ ንጉሥ ሰራዊት
በቀኜ ነው በቀንና በሌሊት
ሚካኤል አባቴ ለዚህ እኮ ነው መመካቴ
ሚካኤል አባቴ ጋሻ ክብሬ ነው ማለቴ
ሚካኤል አባቴ ጎኔ ቆመህ እንዳቆምከኝ
ሚካኤል አባቴ እኔ ለዓለም ምስክር ነኝ
አዝ

ልናገር ላውራ ላዚም ልዘምር
ከፍ አርጌ ልመስክር
መች ይረሳል ልጅነቴ ያሳደገኝ
እቅፍ አርጎ በክንፎቹ የከለለኝ
ሚካኤል አባቴ እስከዛሬ ያላልኩትን
ሚካኤል አባቴ በልቤ ውስጥ ያኖርኩትን
ሚካኤል አባቴ ዛሬ ላውራው በአደባባይ
ሚካኤል አባቴ እረድቶኛል ከአባት በላይ
አዝ

ከተኛሁበት ከእንቅልፌ አንቅቶ
ነጻ አወጣኝ እስሬን ፈቶ
በጨለማ በወኅኒው ቤት በእስር
አብሮኝ ነበር ጠባቂዬ ሚካኤል
ሚካኤል አባቴ በክፋ ቀን ያለ ጎኔ
ሚካኤል አባቴ ያልተለየኝ በድካሜ
ሚካኤል አባቴ ሰው የሚወድ የማይንቅ
ሚካኤል አባቴ በጌታ ፊት የሚያስታርቅ
አዝ

ብርቱና ኃያል ጽኑ ነው ስሙ
ሚካኤል ሞገስ የሆነው
ምን ይሆናል ሚካኤልን የያዘ ሰው
ምግቡ መና ደመና ነው ሚጋርደው
ሚካኤል አባቴ የአባቶቼ መንገድ መሪ
ሚካኤል አባቴ በእኔም ሕይወት ተዓምር ሰሪ
ሚካኤል አባቴ በመንገዴ ቀድሞ ፊቴ
ሚካኤል አባቴ ይስበኛል ወደ ርስቴ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


“ኦ ሚካኤል ሊቀ መላእክት”

ኦ ሚካኤል/2/ ሊቀ መላእክት
በኃጢያት እንዳንወድቅ እንዳንሞት
ፈጥነህ ተራዳን አፅናን በእምነት
አዝ

ለያዕቆብ ነገድ       ሚካኤል
ለእስራኤል            ሚካኤል
ጠባቂያቸው ነህ     ሚካኤል
መልአከ ሀይል        ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረትን
ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት /2/
አዝ

ነፀብራቃዊው        ሚካኤል
ተክኖ ልብስህ           ሚካኤል
ሀመልማለወርቅ      ሚካኤል
አይኑ ዘርግብ          ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረትን
ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት /2/
አዝ

በስእልህ ፊት        ሚካኤል
እሰግዳለሁ          ሚካኤል
ፈጥነህ አነጋግረኝ   ሚካኤል
አለሁ በለኝ            ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረትን
ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት /2/
አዝ

በክንፍህ ጥላ         ሚካኤል
ተጠልለናል             ሚካኤል
ቅዱስ ሚካኤል         ሚካኤል
ተከልለናል                 ሚካኤ
ፍቅርን አድለን ምህረትን
ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት /2/
አዝ

ቅሩበ  እግዚአብሔር      ሚካኤ
ታማኝ ባለሟል               ሚካኤ
ደራሽ ሲጠሩህ               ሚካኤ
ለታመኑ ሀይል                ሚካኤ
ፍቅርን አድለን ምህረትን
ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት /2/

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ሚካኤል ስለው | ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

ሚካኤል ስለው ስሙን ስጠራ
የአምላኬ ብርሃን በላዬ በራ
አዛኝ ነው በእውነት ፍፁም አዛኝ
የሚጠብቀኝ የሚያጽናናኝ
/2/
አዝ

ከአለቆች ጋራ ሕዝቡን የመራ
የሚመላለስ በእሳት ተራራ
ባህሩም ሸሸ ከማደሪያው
የጌታ መልዓክ ሲያናውፀው
ዘንዶን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል /2/
አዝ     

ከባዱ ጋራ ሜዳ ሆኖኛል
የወህኒው መዝጊያ ተከፍቶልኛል
አልናወፅም ከቶም አልፈራ
የጌታ መልዓክ ነው ከእኔ ጋራ
ዘንዶን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል /2/
አዝ

ትዕቢተኛውን አሸንፎታል
ዲያቢሎስ አሁን ዝናሩን ፈቷል
ታላቅ ፀጥታ በሰማይ ሆነ
እግዚአብሔር ብቻ ስሙ ገነነ
ዘንዶውን አሽንፏል ስሙን በክብር ጽፏል /2/
አዝ

ሚካኤል ሲቆም ፈጥኖ ደራሹ
የሚቃወሙን አጥብቀው ሸሹ
ታላቁ መልዓክ ከፊት ቀደመ
ታሪክ ተሰራ እንባችን ቆመ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል /2/

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


የብርሃን መልአክ ነህ | ዘማሪ ቀሲስ ካሳሁን ደምሴ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All

20 last posts shown.