🌹#ወር በገባ በ24 #አባ_ኖብ ሰማዕት📕
♨••እንኳን ለአባታችን ለአባ ኖብ ሰማዕት ወርሀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በምድረ ግብጽ ከታዩ ታላላቅ ከዋክብት አንዱ ቅዱስ ኖብ በሃገረ ንሒሳ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ዘመኑም ዘመነ ሰማዕታት (3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው:: ወላጆቹ በልጅነቱ ብዙ ሃብት ትተውለት ያርፋሉ:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ካህኑ ስለ ምናኔና ሰማዕትነት ሲሰብክ ይሰማዋል::
ገና በአሥራ ሁለት ዓመቱ በቤቱ የነበረውን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ መስቀለ ክርስቶስን ሊሸከም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምስክርነት አደባባይ -የክርስቲያኖች መገደያ ቦታ) ተጓዘ:: በዚያም በጉባዔ መካከል ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ ምክንያት በሰብዓዊ አካል ሊሸከሙት የማይችሉትን መከራ በልጅ ገላው ተቀብሏል::
በዚያው ልክም ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: በተአምራቱና በጣዕመ ስብከቱም ከመቶ ዘጠና ሺህ በላይ አሕዛብን ወደ ክርስትና መልሶ ሁሉም ተሰይፈዋል:: በእሳት: በስለት: በሰይፍ: በባሕርና በየብስ መከራን ከተቀበለ በኋላ በዚህች ቀን አክሊለ ክብርን ይቀበል ዘንድ አንገቱን ተከልሏል::
ጌታችን የገባለት ቃል ኪዳኑ ግሩም ነውና ዛሬ በግብጽ በድምቀት ይከበራል:: ምንም በእድሜ ልጅ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን አባ (አባታችን) ኖብ ትለዋለች::
የአባኖብ ሰማዕት በረከታቸው ይደርብን፤ጸሎታቸው ይጠብቀን፤ለመንግሥተ ሰማይ መሪ በትር ይሁነን፤ድካማቸው ከጠላት እጅ ያድነን፣የትዕግሥታቸው ሀይል ከእሳት ባሕር ያድነን
አሜን አሜን አሜን
ቤተሰብ ይኹኑ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc