አገልግል


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education



Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


ከጎንደር❗❗
በጎንደር ትናንት በነበረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን ሳይጨርሱ መውጣቸውን አረጋግጫለሁ። ይሄ ለክልሉ ትልቅ ኪሳራ ነው።
እስካሁን ያልተሳ አስኬረን አለ። መንገድ ዝግ ነው።


በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር መባባስ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ክልሉ የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለመሰረዝ መገደዱን አስታወቀ። አየር መንገዱ ከትናንት ጀምሮ ወደ ጎንደር፣ ላሊበላና ኮምቦልቻ የሚያደርጋቸውን በረራዎች መሰረዙን ለማወቅ ተችሏል። ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት በምገኘው አዘዞ ከተማ፣ ዛሬ በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የከባድና ቀላል መሳሪያ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ መዋሉን፣ ዋዜማ ከሥፍራው ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።


በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተዛውረው የተመረቁ ተማሪዎች መመረቂያ ዲግሪያቸው እንዳልተሰጣቸው ገለፁ‼️
የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ ከአክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው በዘንድሮው ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የመመረቂያ የምስክር ወረቀት (ቴምፖ) ሳይሰጣቸው ከግቢው እንዲወጡ መደረጉን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎቹ "የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 13/2015 ተማሪዎቹን አስመርቆ የመመረቂያ ወረቀት በመስጠት የሸኘ ቢሆንም፤ ከአክሱምና መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ለመጣን ተማሪዎች ግን "እንድናስተምር እንጂ ቴምፖ እንድንሰጥ የሚያስገድደን አካል የለም።" የሚል ምላሽ መስጠቱ ትልቅ ቅሬታ አሳድሮብናል።" ሲሉ ተናግረዋል።


ሰራተኛ ሲያስፈልግ ቅጥር ይፈፀማል‼️
በአዲሱ አመት ቅጥር አይፈፀምም ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከአውድ ውጪ ነው ተብሏል።
ለሥራ የሚያስፈልግ ኃይል ሲኖር ቅጥር ይፈፀማል፣ መንግሥት ምንም ዓይነት የሠራተኛ ቅጥር እንደማይፈጽም እንዳስታወቀ ተደርጎ መልዕክቱ እንዲዛባ የተደረገው ሆነ ተብሎ አንዳች የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው ሲሉ የተናገሩት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ናቸው።


መረጃ❗
ራያ ዩንቨርስቲ ሰኔ 6 ጀምሮ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አሳውቋል።


ትምህርት ሚንስቴር በትግራይ ክልል በሰሜኑ ጦርነት የመማር ማስተማር ሥራቸውን ያቋረጡት መቀሌ፣ አዲግራትና ራያ ዩኒቨርስቲዎች በሐምሌ ወር ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምሩ መናገሩን የመንግሥት ዜና ወኪሎች ዘግበዋል። ሦስቱም ዩኒቨርስቲዎች በቀጣዩ ዓመት መስከረም መደበኛ መማር ማስተማር አገልግሎታቸውን እንደሚጀምሩ ሚንስቴሩ መግለጡን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ራያ ዩኒቨርስቲ ከአሁኑ ተማሪ መቀበል እንደጀመረ የገለጠው ሚንስቴሩ፣ በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት አክሱም ዩኒቨርስቲ ግን ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግቶ ይቆያል ብሏል። ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚቀበሉት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያልተመደቡ 20 ሺህ ተማሪዎቻቸውን እንደኾነ ሚንስቴሩ ጨምሮ አስታውቋል።


በ2016 አዲስ ቅጥር የለም ተባለ‼️
መንግስት ከአንድ ወር በኋላ ሃምሌ 2015ዓ.ም በሚጀምረው አዲሱ የ2016 ዓ.ም በጀት አመት ምንም አይነት የመንግስት ሰራተኛ ቅጥር እንደማይፈጸም የገንዘብ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከጥቂት ቀናት በፊት በሚንስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የተላከውን የ2016 ዓ.ም የመንግስት በጀት አስመልክተው ሰኔ 1 ቀን 2015  ዓም በፓርላማው ቀርበው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሚንስትሩ የ2015 ዓም የኢኮኖሚ አፈጻጸምና የበጀት ረቂቁን በተመለከተ ባቀረቡት ማብራሪያ  የ2016 የመደበኛ በጀት በየመ/ቤቱ ያለውን አዲሱን አደረጃጀት ታሳቢ በማድረግ፣ የበጀት አጠቃቀም በቁጠባና በውጤታማነት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ጠቅሰው በቀጣይ በጀት አመት አዳዲስ የመንግስት ሠራተኛ ቅጥር እንደማይኖር ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ በጀት መሆኑን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡


ኢንዶሚ ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው
በአገራችን በህጋዊ መንገድ ከውጪ አገር የሚገባ የኢንዶሚን ምርት የለም ተብሏል

በካንሰር የመያዝ እድልን የሚያስከትል ንጥረ ነገርን ይዟል በተባለው ኢንዶሚን ኑድልስ ላይ የተለያዩ አገራት ምርመራ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ማሌዥያና ታይዋን በኢንዶሚን ላይ “ኢቲሊን ኦክሳይድ” የተባለውን ካንሰር አምጪ ንጥረ ነገር በማግኘታቸው ምርቶቹን ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን፣ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ከውጪ አገር የሚገባ የኢንዶሚን ኑድልስ ምርት አለመኖሩን አመልክቷል፡፡ የባለስልጣኑ ምግብ ተቋማት ቁጥጥር ሃላፊ አቶ በትረ ጌታሁን ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በባለስልጣኑ ተመዝግቦ በህጋዊ መንገድ ከውጪ አገር የሚገባ ኢንዶሚን የተባለ ምርት አለመኖሩን ጠቁመው፤ በአገር ውስጥ የሚመረትና በባለስልጣኑ ቁጥጥር የሚደረግበት ምርት አለ ብለዋል። ጉዳዩ እንደተሰማ በዚሁ የአገር ውስጥ ምርት ላይ ምርመራ መደረጉን የገለፁት ሃላፊው በምርቱም ላይ የተባለውን ዓይነት ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር አለመገኘቱን አመልክተዋል፡፡ በካንሰር የመያዝ እድልን ያስከትላል የተባለውን ንጥረ ነገር ይዟል በተባለው የኢንዶሚን ምርት ላይ ምርመራ ማድረግ ከጀመሩ የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ናይጄሪያ ስትሆን፤ ከኢንዶሚን ኑድልስ ምርት የተለያዩ ናሙናዎችንና ቅመማ ቅመሞችን በመውሰድ ኢቲሊን አክሳይድ የተባለው ንጥረ ነገር መኖር አለመኖሩን ለማወቅ ምርመራ እያደረገች መሆኑን አስታውቃለች፡፡በማሌዥያና ታይዋን ልዩ የዶሮ ጣዕም ባለው የኢንዶሚን ምርት ላይ ካንሰር አምጪው አደገኛው ንጥረ ነገር በመገኘቱ ምርቶቹ ከገበያ እንዲሰበሰቡ ተደርገዋል፡፡
ኢንዶሚን የተባለውን ኑድልስ የሚያመርተው የኢንዶኔዥያው ግዙፍ የምግብ አምራች ተቋም “ኢንዶፍድስ” የምግብ ምርቱ ጤናማ መሆኑን በመግለፅ እየተከራከረ ነው፡፡


በመንግስትና በኦነግ ሸኔ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ያለስምምነት ተጠናቀቀ

ዋዜማ- በመንግስትና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) መካከል ላለፈው አንድ ሳምንት ሲደረግ የነበረው ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን የመንግስት ዋና ተደራዳሪ ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።

ሬድዋን በፅሁፍ መግለጫቸው ሁለቱ ወገኖች በታንዛኒያ በመጀመሪያው ዙር ያደረጉት ድርድር ገንቢ እንደነበር ነገር ግን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መድረስ አለመቻሉን ገልፀዋል። ስምምነት ያልተደረሰባቸውን ጉዳዮች ግን አልተናገሩም።

የሰላም ድርድሩ አስፈላጊነት ላይ በሁለቱም ወገን መግባባት መኖሩንና በቀጣይ ተመሳሳይ ድርድር ለማድረግ ዝግጁነት መኖሩንም ሬድዋን አመልክተዋል። አደራዳሪዎችን ያመሰገኑት ሬድዋን መንግስት ለሰላም ዝግጁ መሆኑንና በሀገሪቱ ህገመንግስት ማዕቀፍ ውስጥ ማናቸውንም ግጭቶች ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን አመልክተዋል።
በድርድሩ ዙሪያ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) በኩል ይህ ዘገባ እከተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ የተባለ ነገርየለም።


በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ትናንት እንደገና መከፈት እንደጀመሩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለጡን ጠቅሶ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በክልሉ በኮሮና ወረርሽኝና ከዚያም በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ኹሉም ትምህርት ቤቶች ከሦስት ዓመታት በላይ ተዘግተው ነበር። በክልሉ የሚገኙ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች በጦርነቱ ከባድ ወይም ከፊል ጉዳት እንደደረሰባቸው ሲገለጽ ቆይቷል።






ለራያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች


ለአክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች


በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው የትምህርት ተቋማትን ዳግም ሥራ ለማስጀመር ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉና እንዲተባበሩ የዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች ጥሪ አቀረቡ።

በትግራይ ክልል ሥራ ያቆሙ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

በዚህም መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ኢዜአ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲዎች የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

ተቋማቱን ሥራ ለማስጀመር ከትምህርት ሚኒስቴር ፈቃድ በተጨማሪ ለመማር ማስተማር አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ለማሟላት በጀት ሊመደብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በመሆኑም ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉና እንዲተባበሩ የዩኒቨርሲቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮቹ ጥሪ አቅርበዋል።


#Amhara-Tigray‼️
በትግራይ የትምህርት ሁኔታ ለመምከር በሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የተመራ የፌደራል የልዑካን ቡድን መቀሌ ገብቷል።
የመቀሌ ዩንቨርስቲ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፕሮፈሰር ክንድያና ገብረህይወት የባህርዳር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው፣የደብብርሃን ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰን ጨምሮ በመቀሌ ተገናኝተው እንዲህ ተቃቅፈዋል።


በመቀለ ዩኒቨርሲቲ ተመድበን የነበርን እና በተፈጠረው ሀገራዊ አለመግባባት ምክነያት ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በጊዜያዊነት ተመድበን ትምህርታችንን መጨረሳችን ይታወቃል። ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ ዛሬ ባህርዳር ጥበበ ጊዮን specialized hospital ለመዎዳደር ሄደን እናንተን አይመለከትም ተብለን ሳንመዘገብ ተመለስን  ለሚመለከተው ሰው ብታሳውቅልን?


#ትግራይ‼️
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት አድርገው ሾሙ 🤭🫣
በትግራይ በተቋቋመው ግዚያዊ አስተዳደር በእጩነት ዶ/ር ደብረጽዮን በቅድሚያ ቀርበው ውድቅ ያደረገው የፌደራል መንግስቱ የጌታቸው ረዳን እጩ ፕሬዝዳንትነት መቀበሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አሳውቋል።


#ሰበር ቀልድ (ቀንድ)‼️
አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳን የሽግግር መሪ (ፕሬዚዳንት) አድርጎ ሾሙዋል። ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ጌታቸው ረዳ በአብላጫ ድምፅ ተመርጧል።


በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ለሰራተኞቻቸው ደመወዝ መክፈል ሊጀምሩ ነው ተብሏል‼️
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለሰራተኞቻቸው ደመወዝ ለመክፈል በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ አስታወቁ።የገንዘብ ሚኒስቴር ለሰራተኞች ውዝፍ ደመወዝ መክፈያ እና የአንድ ወር የስራ ማስኬጃ በጀት፤ ባለፈው አርብ መጋቢት 1፤ 2015 እንደፈቀደላቸው ዩኒቨርሲቲዎቹ ተናግረዋል።

ተጠሪነታቸው ለፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሆኑ አራት ዩኒቨርስቲዎች በትግራይ ክልል ይገኛሉ። በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት የመማር ማስተማር አገልግሎታቸውን አቋርጠው የሚገኙት እነኚህ አራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፤ የመቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርስቲዎች ናቸው።

የመቐለ፣ አክሱም እና ራያ እና ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፤ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ላላፉት 20 ወራት በዩኒቨርሲቲዎቹ ለሚሰሩ ሰራተኞች ደመወዝ አለመከፈሉን ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር፤ የሰራተኞችን ውዝፍ ደመወዝ ጉዳይ ከገንዘብ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር በነበራቸው ስብሰባ ወቅት ገልጸዋል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ የሚኒስቴሩ ኃላፊዎች፤ “ ‘ሌላውን የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛም ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ መንግስት ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል’ የሚል ምላሽ መስጠታቸውንም አስታውሰዋል። የዚሁ ስብሰባ ተሳታፊ የነበሩት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ገብረየሱስ ብርሃነ በበኩላቸው፤ “መንግስት በልዩ ሁኔታ የሚወስነው ውሳኔ እንዳለ ነው የተነገረን” ሲሉ የሰራተኞች ውዝፍ ደመወዝን በተመለከተ ጉዳዩ ከሚመለከተው የፌደራል ተቋም የቀረበውን መልስ ጠቅሰዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ይህ ስብሰባ በተካሄደ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባሳለፈው ውሳኔ፤ የዩኒቨርስቲዎቹ ሰራተኞች ደመወዝ እንዲከፈል በጀት መልቀቁ ታውቋል። የፌደራል ተቋማት ለሆኑት አራቱ ዩኒቨርስቲዎች ሰራተኞች የደመወዝ ክፍያ የሚሆን ገንዘብ መተላለፉን የገንዘብ ሚኒስቴር ምንጮች አረጋግጠዋል። “የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ገና ስላልተመሰረተ፤ ለክልሉ የተላከ ገንዘብ የለም” ሲሉም የሚኒስቴሩ ምንጮች አክለዋል።

20 last posts shown.

1 008

subscribers
Channel statistics