ኢትዮ ግጥም እና ፍልስፍና ethio poem&philosophy


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Quotes


የግጥም ተሰጥዖ ያላችሁ አድሚን እናደርጋችኋለን በቦቱ ተመዝገቡ ግጥም ብቻ ሳይሆን መነባንብ ሆነ ሌሎችም ተሰጥዖ ያለው መሳተፍ ይችላል
For any comment👉 @e_t_l_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Quotes
Statistics
Posts filter


#ሶስተኛው የዓለም ጦርነት

ክፍል_አንድ
ከምኔው እንደ መሸ ስራዋን ገታ አድርጋ ስታስበው ተዓምር እንደሆነባት ለእራሷ መልሳ አጫወተችው- በእነ አቶ መኩሪያ ቤት ተከራይታ የምትቀመጠው ፍቅር።
"አቤቱ ፀሃይን በምስራቅ አውጥተህ በምዕራብ የምታጠልቅ አምላክ በሁሉም ሐይማኖቶች ስምክ ይባረክ..."ቧንቧው አጠገብ ቆማ የሃያ ሶስት ዓመቷ ወጣት በሆዷ አይኖቿን ወደ ሰማይ ልካ ታመሰግነዋለች።

ከሚወዳቸው ተማሪዎቹ ለሁለት ቀናት የተለያቸው የፍቅር ጎሮቤት የሆነው መምህር አየለ ስልክ እየነካካ ወደ ቧንቧው ሲመጣ ያላስተዋለችው መላዕክትን አስቶ የሚጥለውን ጀርባዋን ሰጥታው ስለቆመች እንጂ "..አንዴ መንገድ.."ሲላት በወንዳወንድ ድምፅ አትደነግጥም ነበር።

ሃብትን ከቁንጅና የያዘው ተቀጥራ የምትሰራበት ድርጅት ባለቤት የሆነው ዕዝራ ያላስደነገጣት፤ የቢሻው ሰውነት ያላስደመማት ቁንጅናን ከፈጣሪ የፈጠራ ክፍል ገዝታው የወረደች የምትመስለው ፍቅር እንደ በድን ደርቃ ቀረች።
ሰይጣን ንቀትን ከማን ተማረ ቢባሉ እና ከ አየለ ነው ቢሉ ምንም ስህተት የለውም።
አይኖቹን ከስልኩ ሳይነቅላቸው ሲቀር ሃሳቡን ለመሳብ ብላ "ወይኔ እግሬን"ብትል በአንድ አይኑ አጮልቆ ከገላመጣት በኋላ ምንም ሳይናገራት ቧንቧውን ዘግቶ በአሮንጓዴ ባልዲ የሞላውን ውሃ በቀኝ እጁ እንዳንጠለጠለው ወደ ቤቱ ገባ።
ፍቅር አበደች። አበደች ከምለው ይልቅ ሰይጣን ሆነች ይቀላል። ወደ መምህር አየለ ቤት እየተጣደፈች ሄደች...

አየለ እየተመለከተ የነበረውን የአለቃውን ትዕዛዝ በኢሜል ተቀብሎ እቅድ እያወጣ ሳለ የቤቱ በር ኃይል በተሞላበት ምት ተንኳኳ።
"... እንደሆነ የዚህን ወር የቤት ክራይ ከፍያለው፤ታድያ አቶ መኩሪያ ምን ፈለጉ?..."ጠየቀ እራሱን።

አሁንም ተንኳኳ። በመጀመሪያው ምንም አይነት መልስ ስላልሰጠ "ማነው?"አለ በተረጋጋ መንፈስ።
አሁን በዝግታ ተንኳኳ። እሱን እና እሱን ብቻ በምታስተኛው ትንሿ መሬት ላይ ከተነጠፈችው ፍራሹ ያን ፈርጣማ ሰውነቱን ተሸክሞ ብድግ አለ።
ሰፊ ከብቶች የሚሰማሩበት ከመሰለው ፊቱ እንደ ጥቅጥቅ የአማዞን ደን የበቀለው ፂሙ ላይ የመኮሳተር ስሜት ሲያሳይ፥ የጠዋት ኮከብ የመሰሉት ከዓይኖቹ በላይ ያሉት በፀጉር የተሸለሙት ቅንድቦቹ ግርማ ሞገስ ይሰጡታል።

እግዚአብሔር የእጁን ጣቶች አለስልሶ የፈጠረው እንዲፅፍበት ብቻ እንዳልሆነ ፍቅር የተረዳችው የተከራየበትን የእነ አቶ መኩሪያን ቤት በር በትህትና ሲከፍተው ነው።
ከአናቱ በላይ ያለው ጠቋቁር ፀጉሮች "...ተጨቆን ድረሱልን..."እንደሚሉ ለመረዳት ሰው መሆን በቂ ነው።
ከአናቱ ዝቅ ብሎ የሚገኙት መንቲያ ጆሮቹም ሲቆሙ መመልከት ያስፈራል።
የለበሰው ቁምጣ የእግሮቹን ማማር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

የለበሰው ሲሊፐር ግን መምህር እንደሆነ አይናገርም።"...አቤት..."አላት በሩን በቀኝ እጁ እንደያዘ ኮስተር ብሎ።
"...እእእ እንትን ፈልጌ ነበር..."ሳታውቀው ተርበተበተች። ፍርሃትን በስም እንጂ በአካል አታውቀውም፤ዛሬ ገና ተዋወቀችው።
በሆዱ "እንትንሽ እንትን ይሁንና..."
"እሺ ምን?"አላት
"...እንትን...ባልዲ ፈልጌ ነበር..."ፊቷ ይንቀጠቀጣል።

በቁም ያለ በድን ማንን ታውቃለክ ተብሎ አየለ በዚያ ጊዜ ቢጠየቅ ፍቅርን ነው ማለቱ እንደ ማይቀር የተረዳችው ልክ እሱ ባልዲው ሊሰጣት ሲግባ ከፊት ለፊቷ በተሰቀለው መስታወት ስትመለከተው ነው


#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot


ሰላም ቤተሰብ የውድድሩ አሸናፊዎች እንሆ ይዘን መተናል
1,
#code_2 Tigist
2,
#code_1 Helen
3,
#code_3 Sami
ከ1_3 የዎጣችሁ ከላይ ስማቸሰሁ የተጠቀሰው በቃላችን መሰረት ሽልማታችሁን መውሰድ ትችላላችሁ account ቁጥራችሁን ላኩልን በካርድ መልክ እምትፈልጉ ደግሞ ስልክ ቁጥራችሁን ለመላክ
👇👇
@e_t_l_bot

ቀጣይ የ5000ብር ውድድር ይዘን እንመጣለን እስከዛው ቻናል #share ማድረግ አይረሳ👍
ቼር ምሽት




🚨🚨ትብብር ለቤተሰቦቻችን በሙሉ

ቻናላችን ስልካቹ ላይ #MUTE የሚለው ላይ መሆኑን አረጋግጡ #UNMUTE የሚለው ላይ ከሆነ የምንለቃቸው መረጃዎች በፍጥነት አይደርሳችሁም!

ከላይ በምስሉ ላይ እንዳለው እንድታደርጉልን በትህትና እንጠይቃለን 🙏 ስለትብብራችሁ እናመሰግናለን። ❤

#ቻናሉን SHARE በማድረግ ቤተሰባዊነታችንን እናጠናክር ። 😍🙏

SHARE 
SHARE  SHARE SHARE


Forward from: ᴘᴀᴛʜ ᴏꜰ ʜᴇᴀᴠᴇɴ(ᴊᴇɴɴᴀʜ)
#ቀን ሲጥል
#ክፍል 2


በላይ ኤቤጊያ ብሎ ሲጣራ በድንጋጤ ብዛት ጭልፊት እንዳየች አይጥ ዘልዬ ወደውስጥ ገብቼ አልጋዬ ውስጥ ተደበቅኩ። በላይ ማለት በጣም እሚያናደኝ ልጅ ነው ኤቤግያን እንደምወዳት አውቆ ሁሌም ይፈታተነኛል ሞኝ የሆነ ልጅ ነው ፍቅር የማይገባው ብዙ ግዜ አንስማማም።

ሁሉም የዶርም ልጆች ሁኔታዬን እያዩ ይበልጥ ተሳሳቁብኝ ተናድጄ ተነሳውና በላይን ምን መሆንህ ነው ምትጠራት አልኩት መልስ አልሰጠኝም ዝምብሎ ይገለፍጣል ድሮም እንዲው ነው ከማግጠጥ ሌላ ምንም አያቅም ጅል!!! ወደ አልጋዬ ተመለስኩና በመስታወቱ በኩል ሆኜ ስታልፍ አየኃት አዬ እዳ ምን ቀን ነው ያየኃት ኤቤጊያ ካለፈች በኃላ ሁሉም ወደ ውስጥ ገቡ ኪያር ና ምሳ እንብላ አለኝ ወደ አልጋዬ አጮልቆ እያየ አልበላም አልኩት እሺ ብሎኝ ሄደ ኪያ ደስ እሚለኝ ለዚ ነው መጨቃጨቅ መጋተት ምናምን አይመቸውም እኔም አልወድም አልፈልግም ካልኩ አልኩ ነው ተመልሼ እንቅልፌን ለጠጥኩ።

10፡00 ሰአት አከባቢ ከእንቅልፌ ነቃው ዶርም ማንም የለም ሁሉም ክላስ ሄደዋል ከአልጋዬ ተነሳውና ወደሎከሬ ሄድኩ ልክ ሎከሩን ስከፍተው ሁለት ትንንሽ አይጦች ጫማዬን እያጣጣሙ ሲግጡት አየው ልክ እኔን ሲያዩ ተፈትልከው በእግሬ ስር እየተሽሎከሎኩ ፈረጠጡ እማማዬ .... ብዬ ለጉድ ጮህኩ ሲያስጠሉ ቀፋፊዎች ነብሴ መለስ ስትል ዝርክርክ ካለው ልብሶቼ ውስጥ እምለብሰውን ልብስ መፈለግ ጀመርኩ።

ሁሉም ልብስ ከታጠበ በጣም ቆይቷል በግ በግ ይሸታል ደና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ አደል ያለችው አያቴ ከበክት ውስጥ ትንሽ የበከተውን ልብስ መፈለግ ጀመርኩ አንድ ድሮ ሳውቀው ነጭ የነበረ አሁን ግን መንችኮ ቡኒ የሆነ ሰፊ ሸርት አገኘው ለበስኩት ከታችም ቆሻሻ የቃመ ሰፊ ሰማያዊ ጅንስ አርጌ ቅድም አይጦቹ የገጠቡትን ጫማ ያለካልሲ አድርጌ ከዶርም ወጣው ወዴት እንደምሄድ አላውቅም እግሬ ወደመራኝ ብቻ ከዚ ግቢ ውጪ ብቻ ይሁን ድንዝዝ ብዬ ከግቢያችን ወጣው ናዝሬት የለመደባትን ፀሃይ በአናት በአናቴ ትለቅብኛለች።

 
#የግቢያችንን በር አልፌ ፊትለፊት ወዳለው ሱቆች ሄድኩ ባለሱቁ ደስታ ሁሌም ያቀኛል ሳልጠይቀው አንድ ፓኮ ሲጋራ እጄ ላይ አስቀመጠልኝ ብሩን ከኪሰ በርብሬ አውጥቼ ከፍዬው መንገዴን ቀጠልኩ የግቢያችን ተማሪዎች ታክሲ አጥተው መደዳውን በር  አከባቢ ተደርድራው ይጠብቃሉ አንድ ኮሳሳ ታክሲ ስትመጣ ተሯሩጠው እየተጋፉ ይገባሉ።

በእግር መንገዴን ወደ መብራት ሃይል አደረኩ ደስታ ከሰጠኝ ፓኮ ሲጋራ ፈልቅቄ አንዷን አውጥቼ አፌ ላይ ሰክቼ ኪሴ ውስጥ ክብሪት ፍለጋ ማሰንኩ የቅድሙ ሱሪ ውስጥ እንደረሳሁት ትዝ አለኝ ተበሳጨው አከባቢዬ ላይ የእሳት ምንጭ የሚገኝበት መንስኤ ማሰስ ጀመርኩ ከርቀት አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ልጅ በተሰበረ ምድጃ እሳት ስታቀጣጥል አየው እየሮጥኩ ወደሷ ሄድኩ እሙዬ እሳት ልጫር አልኳት እሺ አለችኝ ሲጋራውን ከአፌ ሳልነቅል አጎንብሼ አፌ ላይ እንዳለ የእንጨቱን ጭስ እየታጠንኩ ለኮስኩት ልጅቷ ገርሟት ታየኛለች እኔ ግን መንገዴን ቀጠልኩ ብቻዬን በሃሳብ አለም እየዋለልኩ እግሬ ወደሚወስደኝ ቀጠልኩ።

ኤቤጊያን እንዴት እንደዚ እስከምሆን ድረስ ላፈቅራት ቻልኩ ሁሌም ስለሷ ሳላስብ አይነጋም አይመሽም እሚገርመው ግን እሷ እኔ አይደለም እንደምወዳት ቀርቶ ማን እንደሆንኩ እንኳን አታውቅም ኤቤግያ የአዲስ አበባ ልጅ ናት እኔም የዛሬን አያድርገውና የፒያሳ ልጅ ነበርኩ ነቄ ሁሉን ያየው ግን ምን ያደርጋል ፍቅር ሲይዝ ሳያስጠነቅቅ ነው ልክፍት ነው የኔማ ሳያት ሁላ እምገባበት ነው ሚጠፋኝ።

#እንዲ በሃሳብ እየተብሰለሰልኩ መብራትሃይል አከባቢ ደረስኩ ግማሹ ፓኮ ሲጋራ አልቋል ሆዴን በምግብ ሳይሆን በጭስ የሞላሁት መሰለኝ  ከነጋ አልበላሁም 11፡30 ሆኗል ሆዴ ያኮረፈ ይመስል ያጉረመርማል አስፓልቱ ዳር ካሉት የተቀቀለ ድንች ሻጮች ጋር ሄድኩና ሁለት እንቁላል በዳባና ሚጥሚጣ እዛው አጠገባቸው አስፓልት ዳር ሆኜ በላውና ተነስቼ መንከራተቴን ቀጠልኩ ድንገት የሞባይል ቤት አየውና አንድ ሃሳብ መጣልኝ

ለአቤጊያ ብቻ እምደውልበት አዲስ ሲም ማውጣት! ወደሱቁ ገብቼ አንድ አዲስ ሲም ገዝቼ ወጣው ከዛ ወደለመድኩት ባር ሄድኩ ድራፍቴን ስጋት ስጋት ስጋት አመሸው ማታ ላይ ወደግቢ ስመለስ አዳልጦኝ አንድ ቱቦ ውስጥ ወደቅኩ በቆሻሻ ውሃ ጨቅይቷል ኤጭ የራሱ ጉዳይ! እዚው አድራለው ቀን የገዛሁትን ሲጋራ በጣም የሚሸተው ውሃ ውስጥ ካለው ኪሴ አውጥቼ ያልበሰበሱትን አውጥቼ  ባር ውስጥ በተቀበልኩት ላይተር ለኩሼ ሁሉንም አፌ ውስጥ ሞጀርኳቸው ....

ክፍል ሶስት እንዲቀጥል
👍👍

#share and join us
@ethiokeld3
@ethiokeld3
@ethiokeld3


Forward from: ᴘᴀᴛʜ ᴏꜰ ʜᴇᴀᴠᴇɴ(ᴊᴇɴɴᴀʜ)
#ቀን_ሲጥል
ክፍል 1

ከደስታ ብዛት ሳይታወቀኝ ያ ቀጭን አለንጋ የመሰለ እጇን ጥብቅ አርጌ ይዣት አብረን እየሄድን ነው እንደሞኝ ያረገኛል ዝም ብዬ እየተገላፈጥኩ ከራስ ፀገሯ እስከ እግር ጥፍሮቿ አተኩሬ አያታለው ፀጉሯን ብኒ ቀለም ተቀብታው ተፈርዟል ከሩቅ ሲታይ የዛገ የእቃ ማጠቢያ ሽቦ ይመስላል ደነገጥኩ እንደዚ ስላት ሰምታኝ ይሆን ሆ..ሆ..ሆ አፌን ብሰበስብ ይሻላል በስንት ስለት ያገኘኃትን ልጅ የዛገ ሃገሬ ሽቦ ብያት ልጣት እንዴ ፊቷ ደሞ እንዴት እንደሚያምር ውውውይ ቀይ ረዘም ያለ ፊት ነው ያላት አይኖቿ ትላልቅ ከንፈሮቿን ደማቅ ቀይ ቻፒስቲክ ተቀብታዋለች።

የለበሰችው ጥቁር ቦዲ እና ሰማያዊ ጅንስ እላይዋ ላይ ጥብቅ ብሎ እሚያምረው ሰውነቷን ጉልት አድርጎ ያሳያል ፍዝዝ ብዬ እያየኃት እያለ አውራ እንጂ አለችኝ እ...እእ እሺ አወራለው አልኳትና ድጋሚ ዝም አልኩ ምን እንደማወራት አላውቅም።

ኤቤጊያ በጣም እምታምር ልጅ ናት አልመጥናትም አውቀዋለው እሷ የቆንጆዎች ቆንጆ እኔ ደግሞ ገጣባ! የጀዝባዎች ጀዝባ ሞሮ አዬዬዬ መከራ አለች አያቴ እንዴት ይሆን እንደምወዳት እማስረዳት ዝም ብዬ ስብሰለሰል ሳመኝ አለችኝ እ.. ም ምን አልኳት አይኗን ጨፍና ከንፈሯን አሹላ ወደኔ ስትጠጋ ደነገጥኩ ፍርሃቴን እየደበቅኩ እኔ አይኔን ጨፍኜ ወደሷ.... ጀርባዬ ቅቤ ይወጣው ይመስል  እንደጉድ ይንጠኛል ናዲ.... ናኦድ አንተ ናኦድ አረ በጌታ ክላስ ረፈደ ተነሳ አንተ ምናባክ ነው ማትነሳው ትከሻዬን ለጉድ ይነቀንቀኛል ከንፈሬን እንዳሾልኩ አይኔን እያጨናበስኩ ነቃው አጠገቤ ኤቢጊያ የለችም ያለው በእጄ ጭምቅ አርጌ የያዝኩት በላብ የሞጨሞጨ ትርሃስ ብቻ ነው ከወገቤ ቀና እያልኩ ወደኃላ ዞርኩ።

እንደቅቤ እሚንጠኝ ልጅ  ጓደኛዬ ኪያር ነው ከጣፋጭ ህልም ውስጥ ስለቀሰቀሰኝ በጣም ተበሳጨው ምናባክ ላርግህ ማን ቀስቅሰኝ አለህ አንተ የኔ አላርም ማናባክ አረገህ ብዬ ቀወጥኩት ባክህ አትጩህብኝ ክላስ እየረፈደብን ነው ተነሳና እንሂድ አለኝ አልሄድም ብዬ ቁርጥ ያለ መልስ ሰጠሁት አንተ ጀዝባ ፈተና አለን እኮ ዛሬ ተነስ ብሎ ብርድልብሴን ገፈፈኝ ውይ ኪያ በናትህ ተወኝ ምን እኔ ፈተና ሲያመልጠኝ መጀመሪያዬ ነውደ

#እንዴ ብርቅ አስመሰልከው እኮ ብዬ ብርድልብሱን በሃይል ነጠቅኩትና ድጋሚ ተጠቅልዬ ተኛው ኪያር ደብተሩን አንስቶ ጥሎኝ ወጣ ኪያር ጥሩ ጓደኛዬ ነው ብዙ ግዜ ስድብና ቁጣ ይቀናዋል ልቡ ግን የዋህ ነው ደስ እሚለኝ የባህርዳር ልጅ ነው ከፍሬሽ ጀምሮ ስከአሁን አራተኛ አመት ድረስ አንድም ቀን እንኳን ሳንቀያየም አለን የዛሬን አያድርገውና በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ ሁሉ እሚቀናብኝ ብዙ ጓደኞች የነበሩኝ ግን ምን ያደርጋል ኤቤግያን ካፈቀርኩ በኃላ ሁሉም ገደል ገባ እኔም ራሴን ጣልኩ ጀዘብኩ ሁሉም ሰው ጀዝባው ሞሮ እያለ ሲጠራኝ ኪያር ብቻ ነው በስሜ ሚጠራኝ እሱም ሲበሳጭብኝ እንደነሱ ጀዝባው ይለኛል ግን ምንም አይመስለኝም።

#እውነትም ጀዝቢያለው ለምንም ነገር ግድ አይሰጠኝም ቀኑን ሙሉ አልጋዬ ላይ ተሰፍቼ ስለ ኤቤግያ ብቻ ሳስብ እውላለው ማታ ደሞ ራሴን በአልኮሆልና በጭስ  ውስጥ ተደብቄ አገኘዋልው ቀንና ለሊት ኤቤግያን ሳስብ እውላለው አድራለው እሷ ግን ማን እንደሆንኩ መፈጠሬን እንኳን አታውቅም ኤቤግያ ኤቤግያ ኤቤግያያያ... እንደው ምን ልሁን ምን ይሻለኛል ኤጭ ብርድልብሴን ሸፈንኩና የቅድሙን ህልም ፍለጋ ተመምኩ ግን ቴዲ ህልም አይደገምም ብሎ የለ አጣሁት ከየት ይምጣ ተበሳጨው እርሜን ኤቢን ከጎኔ ሁና ባያት ልስማት ስል ኪያ ቀሰቀሰኝ ተኛው ምሳ ሰአት ኪያር እየሮጠ መጥቶ ድጋሚ ቀሰቀሰኝ ለጉድ ጮህኩበት አንተ ቃጭል ታወኝ በቃ ልተኛበት አልኩህ አይደል እንዴ ምን ላርግህ አልኩት።

እየሳቀ ናዲ ኤቤግያ በኛ ብሎክ ጋር እያለፈች ነው አለኝ ከምኔው ተስፈንጥሬ ከአልጋዬ ወርጄ የዶርማችን በረንዳ ጋር እንደተሰየምኩ አላውቅም ኪያ ከት ብሎ ሳቀ ሁሉም የዶርሜ ልጆች ነገረ ስራዬ አስቋቸው እየሮጡ መጥተው አብረውኝ ቆመው እኔን ማየት ጀመሩ።ግድ አልሰጠኝም አቢ ቀይ ቅድም በህልሜ ያየኃቸውን ልብሶቿን ለብሳ በኛ ዶርም አከባቢ እያለፈች ነው ልቤ ፍስስ ሲል ተሰማኝ ድንገት አንዱ የዶርሜ ልጅ ጮክ ብሎ ኤቤግያ ብሎ ተጣራ
ይቀጥላል
...

#Share and join us👇
@ethiotibeb3
@ethiotibeb3
@ethiotibeb3


#Code_5

✍🎧🎶esttif

Join and share
👇👇
@qdist
@dist


#Code_4

---ዳግመኛ ከመልካም ስብዕና ተወለድ!!
--------------------------------------------------
ሰው ሆነህ መኖርህ አንተንና ሌሎችን ካልጠቀመ ገና አልተወለድክም........!!የሰው ልጅ በፍጥረቱ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር ላይ ቢፈጠርም(ቢወለድም) ሰው ለመሆን ግን ከመልካም ስብዕና ማህፀን ዳግመኛ መወለድ ይኖርበታል።ብዙዎች ከዚህ ማህፀን ስላልተወለዱ (ስላልወጡ)ዛሬ ለምናያት ሀገራችን ችግር መንስኤ ሆነው እናያቸዋለን ከሀገርም አልፎ ለአለም የችግር ምንጭ ሆነው ይኖራሉ።

ሰው ሲኖር ለግሶ እንጂ ተቀብሎ መኖር የለበትም ከራስ በላይ በዙሪያው ለሚገኙ ሰዎች ኖሮ ማለፍ አለበት ሰው ሆኖ መገኘት ቀላል ሆኖ ሳለ የሰው ልጅ ግን ሰው መሆንን ይፈራል.. ምክንያቱም ሰው በመሆን ውስጥ ስለራስ ጥቅም ማሰብ ስለሌለ,ሰው በመሆን ውስጥ ማግበስበስ ስለሌለ ሰው በመሆን ውስጥ ዬኔ የሚባል ነገር ስለሌለ ሰው በመሆን ውስጥ ራስን ማበልፀግ ስለሌለ...ሰዎች ሰው መሆንን ይፈራሉ ለዚህም ነው ዳግመኛ ከስብዕና ማህፀን ያልተወለዱ ሰዎች በኔነት ስሜትና በራስቸው ደስታ ብቻ መኖር የሚያስደስታቸው።

እነዚህ አይነት ሰዎች ከራሳቸው ዘላቂ ደስታ ውጭ የወንድማቸው ችግር ለነሱ ምንም ነው የሰውን ችግር መስማት ለነሱ ምቾት ይነሳቸዋል ስለዚህ በራሳቸው የተጣመመ የህይወት መንገድ ጉዟቸውን ያደርጋሉ።አንተ ግን ሰው ሁን ዳግመኛ ከስብዕና ማህፀን ተወለድ ከራስህ ደስታ ይልቅ ለሌሎች ደስታ ኑር ከራስህ በላይ ሌሎችን ወደህ ተገኝ ለሌሎች አርአያ ሆነህ የደስታቸው ምንጭ ለመሆን ጥረት አድርግ ለችግሮቻቸው የመፍትሔ ሀሳብ አቅርብ።ያኔ ሰው መባልህ ብቻ ሳይሆን ሰው ሆነህ መፈጠርህ ዘላለማዊ ጥቅሙ ይገባሀል።

በምድር ላይ ካንተ በላይ ደስተኛ አይኖርም በመጨረሻም በምድር ላይ ሰው ተብለህ መጥተህ ዳግመኛም በመልካም ተግባርህ ከስብዕና ማህፀን ተወልደህ ህያው መሆንህን ታረጋግጣለህ።
✍ገዛኸኝ መስፍን


#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot


#Code_3

#ሳትስሚኝ በፊት

...አንዴ ስሚኝ
የምነግርሽ አለኝ
የምታዳምጪኝ
 አዎ
ስለኖርኩት የልቤ ሀቅ
ስለሳቅኩት የጥርሴ ሳቅ
...ደሞ
ሳይቀያየሙ ስለመታረቅ
      እየተያዩ ስለመናፈቅ
        ስለመነፋፈቅ
          ፍቅርን ስለመኖር
           ፍቅርን ስለማኖር
...ብቻ በጣም ብዙ ነገር
     ልነግርሽ እያሰብኩኝ ነበር
...ግና
  ከዝርዝሩ በፊት
       ከሁሉም ከሁሉም
  አለኝ ደግ ምርቃት
        ለኔም ሆነ ላንቺም
    በይ ተቀበይ
    የወዳጅ ምርቃት
             ከቶ አይናቅም

  ...እስኪ አሜን በይ
  ...እስኪ ይሁን በይ
      ልመርቅ ተቀበይ
              
  ከጠላቴ ልታረቅ
            ጠላትሽም ይናቅ
              አሜን!
  ክፉዬ ካንቺ ይጥፋ
       ክፉሽ ከኔ ይራቅ
            አሜን!
  ቀኔ ባንቺ ይፍካ
     ቀንሽ በኔ ይድመቅ
              አሜን!
   ከኔ ተደበቂ
     ባንቺ ውስጥ ልደበቅ
              አሜን!
   ከኔ ይሁን እንባሽ
        ካንቺ ይሁን ሳቄ
              አሜን!
   አወጪኝ "ከዚ አለም"
      ላውጣሽ ነጥቄ                    
   አሜን አሜን አሜን!
    ሁሉም ይሁን ያፌን
  ...ታዲያ
     በስሜ የማልኩት
      በስምሽ ያስማለኝ
       ሁሉንም ያስባለ
    "እነግርሻለሁ"
           ልኩት ሁሉ
            ምርቃቴ ውስጥ አለ
    አዎ...አሜን በይ
    አዎ...ይሁን በይ
    አሁን ግን
    ላንድ አፍታ አንዴ
     ...ሁሉንም ተይ
  
 ዕድሜሽን ሳልቀማው
               ዕድሜዬን ሳትቀሚኝ
    ለማንም ሳላማሽ
     ለማንም ሳታሚኝ
    ከበሽታሽ ዕድን ዘንድ
                   እንድታስታምሚኝ
   ሁሉንም ተይና
      አሁን በይ
    ...ጥግ ድረስ ሳሚኝ!
✍ሳሚ     

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot


Code 2

ሚስት ከመሞቷ በፊት ባሏን እንዲህ ብላ ጠየቀችዉ "እኔ ከሞትኩ በኋላ ሌላ ሚስት ታገባለህ"? የቀብርሽ አፈር እስከሚደርቅ ድረስ በፍፁም አላገባም አላት። እሷም ማናችንም ወደማንቀርበትከእለታት በአንዱ ቀን አረፈች።

ከጊዜያት በኋላ ማግባት ፈለገና ቃሉን ለመሙላት የሚስቱ መቃብር አፈር መድረቅ አለመድረቁን ለማወቅ ሲሄድ... አልደረቀም እርጥበት አለዉ በሁለተኛዉም ቀን በሶስተኛዉም ቀን እርጥብ ነው። እዲህ እያለ ለ13 አመታት በሙሉ ሁሌ የቀብሯ አፈር እርጥበት እንደያዘ ነዉ።

እሱም በቃሉ መሰረት አላገባም አንድ ቀን ከወትሮ በተለየ ጎህ ከመቅደዱ በፊት ወደ መቃብሯ ቢሄድ ወንድሟ የመቃብሯን አፈር ዉሀ እያጠጣዉ ተመለከተ በአግራሞት ደርቆዐቀረ "ለምን"? ብሎ ጠየቀ። ወድድሟም እንዲህ ሲል መለሰ እህቴ ከመሞቷ በፊት በህይወት እስካለሁ ድረስ ሁሌ ጎህ ሳይቀድ መቃብሯን ዉሀ እንዳጠጣዉ በኑዛዜ መልኩ ቃል አስገብታኛለች ለዛ ነው ሁሌ ከመንጋቱ በፊት ውሃ እማጠጣው ሲል መለሰለት።

ባልም በሃዘን ውስጥ ሁኖ ከዚህ በኋላ ቃልህን እኔ እፈፅማለው በማለት ከዛ ቀን ጀምሮ የመቃብራን አፈር እራሱ እያጠጣ አመታቶች ነጎዱ በመጨረሻም የሂወት ሰሌዳዉ አበቃና ለፍቅሩ ታማኝ እንደሆነ እሱም ሞተና ተጎራበታት... እናም አፍቃሪዋ ሞታም ፍቅሯን ለማንም ሳታስነካ ዝንተዓለም የራሷ ብቻ አድርጋ ያዘችዉ። ፍቅር እንዲህ ነው
😍😘
✍ Tigist

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot




Code 1

የፍቅር አልሜ የሂወት ምዕራፎ
አንተን ያለምኩ ለት መስመሬን አልፎ
ያኔ ይጀምራል መራራው ሂወቴ
ገና ባፍላ እድሜዬ በጨቅላ አንደበቴ
ያኔ በልጅነት በለጋው እድሜዬ
በማላውቀው ስሜት ያነገስኩህ ስዬ
ደሰ የሚል ስቃዬ እልፍ አላፍ ብሶቴ
ገና አይንህን ሳየው ጠፍቶኝ እኔነቴ
አንዳች ስሜት መቶ ውስጤን ተቆጣጥሮ
መናገር ስሞክር ቃሌ ተሰባብሮ
ይሰማኛል ድምፄ ትርጉም አልባ ሁኖ
የውስጥ ስሜቴ ከሀሳቤ በኖ
እንጂማ ባወጋህ ድፍረቱን ታድዬ
ውስጤን አዳምጬ አንደበቴን ሰዬ
እኋው ልማልልህ ልጅነቴን ይንሳኝ ብዬ ተገዝቼ
               አንተን ይንሳኝ ብዬ አለሜን አጥቼ
እኔ እንደምወድህ እራሰህን አቶድም
የኔን ፍቅር ብታይ ማፍቀርን አታውቅም

ድንገት ብታይማ ለማየት አድሎህ
በዕንባ ዘለላዬ ብዕሬን አቅልሜ
በዜማ ተውቦ የውሰጥ ህመሜ
በልቤ ያረፉት ረቂቃ ቃሎቼ
እልፍ አላፍ ግጥሞቼ
ይናገሩ ነበር ካንደበቴ በላይ የውስጤን አጉልተው
ቃል የሌለው ፍቅር መሆኑን ተረድተው

እንጂማ ባወጋህ ድፍረቱን ታድዬ
ውስጤን አዳምጬ አንደበቴን ስዬ
እኋው ልማልልህ ልጅነቴን ይንሳኝ ብዬ ተገዝቼ
                 አንተን ይንሳኝ ብዬ አለሜን አጥቼ
እኔ እንደምወድህ እራስህን አቶድም
የኔን ፍቅር ብታይ ማፍቀርን አታውቅም
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
አንዳንዴ ሲብሰኝ እምባዬ ሲቀድመኝ😥
አፌ ተቆላልፎ የውስጤን ሸሽጎ
በይመጣል ናፍቆት ነገን ተስፋ አድርጎ
በመጠበቅ ደዌ በማይልቅ ለቅሷ
አንተነትህ ነግሷ ከልቤ ምሷሷ
ፊት ለፊት ላወጋህ ያጣሁትን ድፍረት
ብዕሬን አውግቼው ውስጤ ያለውን እውነት
ልሂድ ወይስ ይምጣ እያልኩ ሳንገራግር
ስሜቴን ሸሽጌ  በይሉንታ አጥር
በመሀል እረፍዶ
ጆሮዬ ቢያሰማኝ የሰረግህን መርዶ
ሊያገባ ነው ቢሉኝ ከኔ ሌላ ወዶ
ዳግም ላይመለስ
ጎጆውን ሊቀልሰ
ሊሄድ ነው ሊያገባ አንቺን ይሉንታ አጥሮሽ
ሸሽገሽ ያኖርሺው እውነተኝ ፍቅርሽ
እንዲያ ብለው ሲሉኝ
ያኔ እንኩዋን ሳያገርመኝ
ከገደበኝ አጥር የይሉንታ መንደር
የዕድሜ እኩሌታዬን የጠበኩት ፍቅር
ከደስታው ታድሜ
ከሰርጉ ሙዚቃው
እሰክሰታና ፌሽታው
የልጅነት ህልሜን ዳርኩት እያለቀስኩ
ያብርሀም የሳራ ትዳር ይሁን እያልኩ

✍ Helen

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot


እንሆ ተጀመረ ለአንድ ተወዳዳሪ የሚሰጠው 24ሰዓት ነው #view እሚያዘው በ24ሰዓት ውውጥ ነው መልካም እድል


ሰላም ቤተሰብ ማንኛውም የምለቀቀው link የማስታወቂያ ስራ ነው እኛን አይወክልም


Forward from: ᴘᴀᴛʜ ᴏꜰ ʜᴇᴀᴠᴇɴ(ᴊᴇɴɴᴀʜ)
#ጥበብ ማለት ምን ማለት ነው?

#ጥበብ ከአልማዝ ከእንቁ ከወርቅ ይልቅ ውድ ናት ጥበብ በባህር ዘንድ የለችም ሞትም አላቃትም ይላል። ጥበብ እንዳለች ሁሉም ያቃል  መኖሪያዋን ግን ማንም አያውቅም፡፡

አሁን በየትኛውም ስፍራ የሚያሰፈልገን ጥበብ ነው። ሰዎች ጥበብ ስለሌላቸው ሣይሆን የሚጎዱት ጥበብ ስላነሳቸው ነው። ብዙ ትዳሮች የፈረሱት በጥበብ ማነስ ምክንያት እንጂ በአጋንንት ምክንያት አይደለም።

#ጥበብ መብራት ናት የመብራት አላማ ማሣየት እንጂ መብራት አይደለም ማሣየት ማለት የሌለህን ነገር ይሰጥሃል ማለት አይደለምደለም ያለህን ነገር ግን ያጎላልሃል። ብዙ ሰዎች ያለቦታቸው የተቀመጡት ውስጣቸው ያለውን ነገር ባለማየት ነው። ጥበብ ስታበራልህ ግን ታያለህ።

ጥበብ በብዙ ላብ የምታገኘውን ነገር ወዲያው እንድታገኘው ትረዳሃለች። ጥበብ ማለት መስራት ሳይሆን አሠራር ነው።ጥበብ ሲመጣ አደረገ ሳይሆን እንዴት አደረገ የሚለውን እንድታቅ ታደርግሃለች። ጥበብ አደራረግን ታሳውቃለች

ቼር ሌሊት

#share & join 👇
@ethiotibeb3
@ethiotibeb3
@ethiotibeb3

#If you have any comment or question 👉 @e_t_l_bot


ሰላም ቤተሰብ ማንኛውም ችሎታ ያለው ሰው በዉስጥ መስመር ያናግረኝ ሁለተኛው ከ8000 በላይ ተከታዮች ያለው ቻናላችን በአዲስ መልክ እየተዋቀረ ነው

እናም ለእናንተ እድሎችን ይዘን መተናል
#ማንኛውም ችሎታ አለኝ የሚል ችሎታውን ሰውን እያዝናና ሃሳብ እየተቀበለ ማዳበር እንዲችል እድሉን ይዘንላችሁ መተናል

#ግዴታ በፅሁፍ ይሁን አንልም #በመነባንብ በትረካ መልኩ ወይም በግጥም መልክ #record እያደረጋችሁ መልቀቅ ትችላላችሁ

admin መሆን እሚፈልግ እና ችሎታው ያለው
@betsi_e1 ማናገር ይችላል
ቻናሉ👇👇
@ethiotibeb3
@ethiotibe
b3
@ethiotibeb3
ቼር ምሽት ቤተሰብ🙏


Thank you 4k subscribers family😍


የት ነሽ ኢትዮጵያ

#እናቴ ሀገሬ
የት ነሸ
የት ነው የቀበሩሽ
የት ነው የደበቁሽ
የነገሩን ሃገር አንቺ እኮ አይደለሽም
እኛ የሰማነው ለኛ የነገሩን

ጥበብ የሞላባት
ፍቅር ያደገባት
እውቀት የተረፋት
ሰይጣን የቀናባት
የጥበብ መፍልቂያ የፍቅር መገኛ
አንዲት አቢሲኒያ
ኢትዮ ኢትዮጵያ
የቅዱሳን ምድር የሃያላን እናት
የነ ያሬድ ምድር የነ ላሊበላ
የነ አክሱም አባት የነ ጎንደር እናት
እድሜ የማይሽረው ጥበብን ያነፁት
እንደ ታሪክ ሁኖ የሰማነው እውት
ከመስማትም በላይ የወረስነው እውት
ምነው ተቻኮልን ታሪክን ለማጥፋት
ሀገር ለመበትን ጎጥን ለማስፋፋት
ቆይ ግን
ማን ነው የናፈቀው የኢትዮጵያ ሰላም የኢትዮጵያ እድገት

ማን ነው የናፈቀው የኢትዮጵያ መዝሙር
ማን ነው የናፈቀው
ተቀላቅሎ ማየት ሰማንያውም ብሄር
አንድ ሁኖ ሲሰራ አንድ ሁኖ ሲዘምር
የናፈቀው ማን ነው የኢትዮጵያ ሰላም?

ያች አንድ ኢትዮጵያ የጥበብ መፍለቂያ
ኧየ የት ነው ያለች እናቴ ኢትዮጵያ
?😭
#share
@esttiff

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot


አለመኖር

አርቆ ማሰብ ጠፍቶብናል መኖር ለዛሬ ብቻ መስሎናል መኖር ግን በእውነቱ ዛሬ ብቻ ነው ነገ እና ትላንት ሁለቱም አለመኖር ናቸው። በመወለዳችን ምን ያህል እድለኞች እንደሆንን አናውቅም።

እስኪ ያልተወለዱትን አስቧቸው መኖር እኮ በአለመኖር ጥልቅ ውስጥ የተሰጠን ስጦታ ነው። ከዚህ በፊት አልነበርንም፣ ወደፊትም አንኖርም። ይህን ማስተዋል ለምን ተሳነን?  ምክንያቱም ከሁሉም ህመማችን ስር የተሰወረብን እውነት ይህ ነው።
✍️ ዶ/ር  ዳዊት

#ከወደ
ለወዳጅመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot


Forward from: ᴘᴀᴛʜ ᴏꜰ ʜᴇᴀᴠᴇɴ(ᴊᴇɴɴᴀʜ)
የሞባይል ካርድ እንድሞላ ቁጥሩን ልኮልኝ "ስሞክረው አይሰራም" እለዋለው

ምን ቢለኝ ጥሩ ነው🙈
"እኔ ጋ ሰርቷል ደጋግመሽ ሞክሪው
😂😂😂
#share @funnytime433

20 last posts shown.