😊ዛሬ ፈገግ በሚያደርግ መልኩ 3 የተማሪ አይነቶችን ላጋራችሁ comment ላይ እናንተ ከየትኛዎቹ እንደሆናቹ ፃፉልን
ተማሪዎች የተለያየ አይነት የአጠናን መንገድ ይከተላሉ ከነዛም ውስጥ በጥቂቱ እንመልከት
1️⃣የመጀመሪያወቹ
ሁሉን ብላ ይባላሉ። የቀረበለትን ሳያስተርፍ እንደሚበላ ሰው ማለት ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች መፅሐፉ ላይ የተፃፈውን ነገር አንድም ሳያስቀሩ የሚቀረጣጥፉት ናቸው።
⛏ምንም ነጥብ አይዘሉም። የመፅሀፉን ገፅ ሁሉ ሳይቀር ሸምድደውታል።
🛫
ታዲያ እነዚህ ተማሪዎች ጥያቄው concept የሆነ ቀን ጉዳቸው ፈላ።2️⃣ሁለተኛዎቹ
ሚስጥረኞቹ የሚባሉት ሲሆኑ የሚያነቡትን የሚያውቁ፣ ሁሉን የማያግበሰብሱ ናቸው። በቃ ከሚቀርብላቸው ትንሽ ተመግበው። ኩኪስ፣ ቡና ምናምን እንደሚሉ አይነት ማለት ነው።
⭐እነዚህ አይነት ተማሪዎች ፈታ ማለት ያበዛሉ። ብዙ አያነቡም። ፈተና ሲደርስ ግን እንደነሱ ጥያቄውን የሚሰራው የለም።
⭐ይሄ አይነት strategy በጣም የሚመከር ቢሆንም። ከህፃንነት ጀምሮ የዳበረ ትልቅ ልምድን ይጠይቃል። ለአዲስ ጀማሪዎች የሚመከር አይደለም።
3️⃣ሶስተኛዎቹ ደግሞ ብዕረኞቹ ይባላሉ። ለነዚህ ትምህርት ማለት የፅሑፍ ሂደት ነው።
✍️class ውስጥ ይፅፋሉ፣ ሲያጠኑ ይፅፋሉ✍️፣ ደብተራቸውም ሆነ እጃቸው ጀማሪ ሰዓሊ የተለማመደበት ሸራ ነው ሚመስለው።
😊አስረዳኝ ብለህ ስትጠጋቸው ደብተርክ የእነሱ እስኪመስል ይጠበቡበታል። የእነሱ strategy ጊዜ ይፈልጋል እንጂ ማንም ሰው ቢሞክረው ቀላል ነው።
የትኞቹ ተማሪ ናችሁ? comment ጋ ፃፉልን።
JOIN:@Remedial2017batch✅