መጭው ግዜ የቡድኔ ነው💪
ከኢንተርናሽናል ብሬክ በኋላ እጅግ የናፈቀን ክለባችን አርሰናል እነሆ በሜዳ ላይ ልናየው ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። በፈጣሪ እርዳታ ፀሎታችን ተሰምቶ ሁሉም በሰላም ተመልሰውልናል። ምናልባት እንዲ ስል እያጋነንኩ ሊመስል ይችላል ግን ያሳለፍነውን ግዜ የተመለከተ የምር ይረዳኛል።
በውነት ነው ምላችሁ እኔ እስካሁን ባየሁት የአርቴታ ዘመን ውድድሮች ላይ ጉዳትና ቅጣት እንደዘንድሮ ሲበረታብን አላየሁም። ሁለት እና ከዛ በላይ ወሳኝ ወሳኝ ልጆች በየጨዋታው እናጣ ነበር የአመቱን ውድድር ከ1/4ኛ በላይ አገባደናል ነገር ግን ምንም ደስ አይልም ነበር! ውጤት ፊቷን አዙራብን ከርማለች!
ከዚህ በኋላ ግን የምር ጥሩ ነገር እንደሚመጣ ነው የሚሰማኝ በርግጥ አሁንም የጉዳት ዜናዎች አሉ ነገር ግን የቡድኑ አይነኬ ሞተሮች እንደ ሳሊባ ኦዴጋርድ ሳካና ራይስ የመሳሰሉ ልጆች አብረው ከተሰለፉ መላ ቡድኑ በራሱ በስነልቦና ልዕልና ጫፍ ላይ ይደርሳል! እናም ባለፉት አመታቶች እንዳየነው ሁሉ ለተጋጣሚዎች አርሰናልን በቀላሉ ማሽነፍ እማይታሰብ ነው የሚሆነው።
ይህ ደግሞ ሮድሪን ለሙሉ ውድድር አመቱ ላጣው ሲቲም ሆነ እስካሁን በምርጥ ብቃት ጨዋታዎችን እያሸነፈ ለሻምፒዮንነቱ ማስተማመኛ ሊሆን የሚችል ፍንጭ ሊያሳይ ላልቻለው ሊቨርፑል በራሱ ጫና ውስጥ እየከተታቸው መምጣቱ አይቀርም።
እናም ሰዎች ምንም እንኳን ነጥቡ የሰፋ፣ ደረጃችን የራቀና የአቋም መውረድ የታየብን ቢመስልም አርሰናል ከዚህ በኋላ ግን የዘመናት ረሀቡን አስታውሶ፣ ጥርሱን ስሎና ጥፍሩን ሞርዶ ተቀናቃኞቹን በሙሉ ከአፈር ሊቀላቅል ከነገ በስቲያ በውቧ ቅዳሜ ይመለስልናል!
አርሰናል Vs ኖቲንግሃም
📆ህዳር14⌚ምሽት12:00🏟ኤምሬትስ
መልካሙ ሁሉ ለውዱ ለክለባችን አርሰናል🙏