*ወደ እኔ ነይ*
ታላቁ ጻድቅ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጸሎታቸው እንዲህ ይላል:
✝️በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! ከነቢያት ማኅበር ሁሉ ጋር *ወደ እኔ ነይ* ፣ ከአንደበታቸው የወጣውን የምስጋናሽን ኃይለ ቃል ልብ ታስደርጊኝ ዘንድ።
✝️ድንግል ሆይ የቃልን ከአንቺ ሰው መሆን ሥጋ መልበሱንም ጽንፍ እስከ ጽንፍ ካስተማሩ፣ በልጅሽም ዕርፈ መስቀል የአሕዛብን ምድር ካረሱ፣ የቃሉንም ድልብ በምድር ሁሉ ከዘሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ጋር *ወደ እኔ ነይ* ።
✝️ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ሆይ በሥጋቸው የልጅሽን መከራ ከተሸከሙ የሰማዕትነታቸውን ደም ከተቀቡ ሰማዕት ከእነርሱም ማህበር ጋር *ወደ እኔ ነይ* ።
✝️ድንግል ሆይ በማመንዘር እድፍ ነፍሳቸውን እና ሥጋቸውን ካላረከሱ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ከሆኑ ንጹሐን ደናግል ማህበር ጋር በበረከትና በረድኤት *ወደ እኔ ነይ።*
✝️ድንግል ሆይ ስለ መንግሥተ ሰማያት ራሳቸውን ጃንደረባ ካደረጉ ፍጹማን መነኮሳት ማኅበር ጋር በበረከት እና በረድኤት *ወደ እኔ ነይ* ።
✝️በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ እመቤቴ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ሆይ በየጊዜው እና በየሰዓቱ ምስጋና እና ቅዳሴ ከማያቋርጡ ከትጉኃን መላዕክት ማህበር ጋር ለምህረት እና ለረድኤት *ወደ እኔ ነይ።*
ምንጭ አርጋኖን ዘዓርብ ምዕራፍ 1:1-6
✝️ *በእውነቱ ይህ ታላቅ ጸሎት ነው እንደጸሎታቸውም አባታችን አባ ጊዮርጊስ በእመብርሃን ተጎብኝተዋል፣ በእጆቿም ተባርከዋል። የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አባ ጊዮርጊስን እንደጎበኘሽ፣ቅድስት ኤልሳቤጥ ቤትም እንደገባሽ፣ በእኛም ቤት ግቢ፣ ባርኪን፣ ቀድሽን፣ ከልጅሽ አማልጂን፣ *ወደ እኛም ነይልን።ወደ ኢትዮጵያ ነይልን**
✝️ *እመብርሃን በየቤታችን ትግባ። የእናታችን የቅድስት ኄራኒ የዓመት ክብሯ በረከት በየቤታችን ይግባ። አሜን*