🤓 ሰው ሲኖር-Sew Sinor‍


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


💟 እንኳን በደህና መጡ። 🙏 ቸር አይለፋችሁ ክፉ አያግኛችሁ
😊😍 ገፁን ከተቀላቀሉበት ሰከንድ አንስቶ እጅጉን ጠቃሚ ነገሮችን ያገኙበታል።
በተጨማሪ📚 በpdf ማግኘት የሚፈልጉት ማንኛውም መፅሐፍ ካለ 👉 @Sewsinor1_bot ይጠቀሙ።
ማስታወቂያ ለማሰራት፣ማንኛውም ጥያቄ ፣ ሀሳብ ፣ አስተያየት ለመስጠት👇 Inbox 👇
👉 @Sewsinorbot
👉 @CheramlakT

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱


'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
              'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'> ክፈት        ክፈት               
               ክፈት        ክፈት               
                                                   
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
                                                    
                                                   
                                                    
                                                    
                                                     
               ክፈት         ክፈት              
               ክፈት         ክፈት


#ገንዘብ_ደስታን_አይገዛም_ይሉሃል

🤦‍🗣ብድር......ድብርትን እንደሚገዛ
🤦‍🗣ድህነት.......ስቃይን እንደሚገዛ
🤦‍🗣ውጥረት....እንቅልፍ አልባ ሌሊትን እንደሚገዛ ግን አይነግሩህም😏

🤝ብሮ ውሸታሞች በላቸው አንተ ብቻ ወጥረክ ስራ!!!

🗣
ንባብ ለህይወት
@Sewsinor @Sewsinor


"ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። "

የምናደርገው ነገር ትርጉም መስጠት ያቆመበት በሚመስልበት ጊዜ ላይ ነን። እዚህ ሀገር ልጅ እንወልዳለን። የምናወርሰው ሀገር ግን ሲዖል ነው። ምሽቶች ባሎቻቸው ድንገት በወጡበት ይቀራሉ። ይታፈናሉ፥ ይታገታሉ። ልጆች ያልጠገቡትን፥ በውል ያለዩትን አባቶቻቸውን ባልጠበቁት ቅጽበት ይሰናበታሉ። ለሀገራቸው ውለታ የዋሉ ዋርካ ሰዎች በልጅ እግሮች ይገደላሉ። ደም ይፈሳል —በየመንገዱ፥ በየጫካው።  አድባራት አንድ ባንድ ይፈርሳሉ። ማንም ምንም ማምጣት የሚችል አይመስልም። ድንገት ኢምንትነት እንዲሰማህ ትሆናለህ።

ሞት እየጠራህ ትማራለህ? ሞት እያነፈነፈህ ታከማቻለህ? በደጅህ ሞት እያደባ ታገባለህ? ሀገር እየተቃጠለ ትሰርጋለህ? ቆንጆ ቆንጆ ልጆች የጥይት እራት እንዲሆኑ ትወልዳለህ? መሣሪያ የታጠቀ ወንበዴ ቤትህን እየሠረሠረ ታንቀላፋለህ? የዓለም ምጽዓት አንተ ጋር እስከሚደርስ ትተኛለህ?

ሀገሩ የባለጌ ነው። ማን ጌታ እንደሆነ አይታወቅም። በመንገድ ስታልፍ ረግጦህ የገላመጥከው ሰው ዘመደ ብዙ ነው። የጦር መሣሪያ አለው። ባታውቀውም የጎበዝ አለቃ ነው። ትንሽ መንግሥት ነው። ሕይወትህን ከአፈር ይደባልቀዋል። ያየህ እስከማይገኝ ድረስ ድራሽህ ይጠፋል። ወዝህ ያስቀናው ሰው ዳር ሊያስይዝህ ይችላል።

ሀገርህ ከየት እስከየት እንደሆነ አታውቅም። እግርህ ከቤት ወጣ እንዳለ የጠላት ሀገር ነህ። በካርታ ባይከለልም የተበጀ ድምበር አለ። ድንገት  ትጨመደዳለህ፥ እጅ ትሰጣለህ። ብትማረክም ትገደላለህ። ከቀን ውሎህ ተርፈህ፥ በሰላም ወጥተህ ከገባህ እድለኛ ነህ።  ከሄድክበት ስትመለስ ቤትህን በገነባህበት ስፍራ ላታገኘው ትችላለህ። ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። እስከዚያው ያንተ ተራ እስኪደርስ  ታንቀላፋለህ? ወይ የተኛህ ትመስላለህ? ዝም ካልከው በራፍህን አንኳክቶ መምጣቱ አይቀርም
አልነገሩኝም እንዳትል!!

@Sewsinor @Sewsinor


በአፍላ ትጀምራላችሁ.....በወረት ትተውታላችሁ።

ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ....ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ።

የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ....የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ።

ምኞታችሁ ልክ የለውም...አምሮታችሁ ብዙ ነው።

ያማራችሁን ስታገኙ ወድያው ይሰለቻቹሃል...ተው የተባላችሀትን ትሽራላችሁ።

የተከላከላችሁትን ትደፍራላችሁ...የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ።

ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደ ፊት ቤተ መቅደሱን በመስታወት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ።

ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ....በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም። ሁሉ አላችሁ ግን ባዷችሁን ናችሁ።

ሃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም ቀጥሉ አባ...ሰውነታችሁ እንደ ቅኔ ዘራፊ በስሜት ይናጣል።

📕እመጓ....ገፅ 162

🗣
ንባብ ለህይወት
------------------------------------------------
ቤተሰብ ሁኑ👇👇
@Sewsinor @Sewsinor


አንድ ናይጄሪያዊ የሂሳብ መምህር፣ለማስተማር ወደ ክፍል ሲገባ፣ተማሪዎቹ መቀመጫ ወንበሩን ጣሪያ ላይ አንጠልጥለውት ይመለከታል።

ምንም እንኳ የተማሪዎቹ ተግባር ቢያበሳጨዉም፣ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ፣በፈገግታ ሰላምታ ከሰጣቸዉ በኋላ፣ለፈተና እንዲዘጋጁ ነግሯቸዉ፣ወደ ሰሌዳዉ በመዞር  ''ጣሪያዉ ላይ የተሰቀለዉን ወንበር መሰረት በማድረግ ከታች ያሉትን ጥያቄዎች መልሱ '' በማለት ይፅፋል....

  #ጥያቄ 1. በወንበሩና በወለሉ መሃል ያለዉን ርቀት አስሉ??   (1 Mark)

  #ጥያቄ 2.  በወንበሩና በጣሪያዉ መሃል ያለዉን ግንኙነት  አግኙ ?  (1 Mark)

    #ጥያቄ 3. ወንበሩን ጣሪያዉ ላይ የሰቀለዉን ተማሪ እንዲሁም ወንበሩን በመስቀል የተባበሩትን ተማሪዎች ስም ዘርዝሩ (16 Mark)

ተማሪዎቹም 3ተኛው ጥያቄ ብዙ ነጥብ መያዙን ተመልክተዉ፣ወንበሩን ጣሪያ ላይ የሰቀለዉን ተማሪ እስከነ ተባባሪዎቹ ፃፉ።

መምህሩም "መምህር የሆንኩት ተምሬ እንጂ በእድል አይደለም!!!!"በማለት፣ወንበሩን ጣሪያ ላይ የሰቀሉትን ልጆች ከክፍል አስወጣቸው።

.......  Always use your mind, to solve  problems!!!!!

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
         @Sewsinor
         @Sewsinor


ከጅብ መንጋጋ ልጇን ያስጣለችው እናት‼️
በሀዲያ  ዞን በሆሳዕና ከተማ በጀሎ ናራሞ ቀበሌ መንደር 16 ነዋሪ  ወይዘሮ  ደንባሌ አሥራት ጥር 11/2017  ዓ/ም  ከጠት 3 ስዓት  አከባቢ ላይ  ሽላንሻ  ወንዝ ልብስ ለማጠብ  የ12ዓመት ሕፃን አሥከትላ በመሄድ ሥራዋን  መከወን ላይ እያለች  ጅብ ወደ እነርሱ  ይመጣል። በአጠገብ ከነበረች  ከሌላ ሴት  ጋር  በመሆን  ይህንኑ  ህፃን በመሀል አሥገብተዉ ቆመው  ያያሉ ።

ይህ ጅብ  ማለፍ  ይቅርና በ2ቱም  ሴቶች  መከከል  ያለውን  ህፃን ዘሎ ቀኝ እግሩን ነክሶ  በመያዝ ለመውሰድ ሲሞክር   ወላጅ እናት ቀኝ እጇን  በጅብ  አፍ  ውሥጥ  በመክተት  የጅቡን ጉሮሮ በግራ እጅ  አንቃ በመያዝ በላዩላይ ትወድቃለች  አብረው   የነበረችው  ሴት ከጅብ አፍ ህፃኑን   ነጥቃ  በማውጣት   ትታደጋለች ።  በጩኸት   የወጡ ሰዎች ህፃኑን ሊባላ  የቋመጠውን ጅብ  ብዙም  ሳይሄድ  በአካባቢው ሰዎች ርብርብ መገደሉን ከሀዲያ  ዞን  ፖሊስ  መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
=======================
አዩ ዘ ዘበሻ

@Sewsinor




ዮሐንስ ክርስቶስን ያገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ አልነበረም፡፡ ከሠላሳ ዓመታት በፊት ሁለቱም በእናቶቻቸው ሆድ ውስጥ ሆነው ተገናኝተዋል፡፡

‘’በእናትህ ሆድ ሳለህ አውቄሃለሁ’’ ብሎ የተናገረውን ፈጣሪውን እኔም ‘’በእናትህ ሆድ ሳለህ አውቄሃለሁ’’ ብሎ ማነጋገር የሚችል ከመጥምቁ ዮሐንስ በቀር ማን አለ? ‘ከማኅፀን ጀምሮ ባንተ ታመንሁ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ‘’ ብሎ የዳዊትን መዝሙር ለመዘመር የሚችል እንደ መጥምቁ ያለ ማን አለ?

ቅዱስ ያሬድ ‘እምከርሠ እሙ አእመረ ሰገደ ወአንፈራዓፀ’’ ‘በእናቱ ማኅፀን አወቀ ሰገደ ዘለለም’ ብሎ በድጓው የዘመረለት ዮሐንስ ለጌታው ለመስገድ ከእናቱ ማኅፀን እስኪወጣም አልታገሠም፡፡ ጉልበቱ ሳይጸና መስገድ የጀመረ ፣ በዓይኑ ማየት ሳይፈልግ አምልኮ የጀመረ ከዮሐንስ በቀር ማንም የለም፡፡

አሁን በእናቱ ማኅፀን ያገኘውን ጌታ ሁላችንን ወደምትወልደው ወደ ማኅፀነ ዮርዳኖስ ሲመጣ አየው፡፡ ዮሐንስና ጌታ ከሠላሳ ዓመት በፊት ተገናኝተዋል ግን አልተያዩም ነበር ፣ መልእክት ተለዋውጠዋል ነገር ግን አልተነጋገሩም፡፡ ለዚህ ነው ዮሐንስ ስለ ጌታ ‘’አላውቀውም ነበር‘’ ያለው፡፡ /ዮሐ 1፡31/ አሁን ግን ጌታውን አየው፡፡ ወደ እርሱ ሊጠመቅ መምጣቱን ተመለከተ፡፡

እንኳን አደረሳችሁ!


​​የሞት ማምለጫ.....

አዲሱ ቴክኖሎጂ ሰዎች ከሞቱ በኋላ ዳግም ህይወት ሊዘሩ ይችላሉ በሚል የተፈጠረ ነው😎

አዲሱ የሞት ማምለጫ ቴክኖሎጂ ይሳካለት ይሆን?

የሰው ልጅ በየጊዜው ህይወትን ቀለል የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

በእስካሁኑ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች አስደማሚ እና ሊሆን አይችልም የተባሉ ፈጠራዎች በሰው ልጆች ተሰርተዋል።

ይሁንና እስካሁን ሞትን ማምለጥ የሚያስችሉ ፈጠራዎችን መስራት ያልተቻለ ሲሆን ቱሞሮ ባዮ የተሰኘ ኩባንያ ግን ባልተሞከረውን መንገድ እየሄደ ይገኛል።

ይህ ኩባንያ አንድ ቀን ይሳካልኝ ይሆናል በሚል መሞታቸው በሐኪሞች የተረጋገጡ ሰዎችን አስከሬን በማጠራቀም ላይ ነው።

የዚህ ኩባንያ ዓላማ ሰዎች ህይወታቸው ከላፈ በኋላ በበጎ ፈቃደኝነት አስከሬናቸውን እንዲሰጡት ካደረገ በኋላ ወደ ማቀዝቀዣ ቦታ ይወስዳል።

የአስከሬኑ ቅዝቃዜ ዜሮ ድግሪ ሴንትግሬድ ከደረሰ በኋላ አስከሬኑ በቅዝቃዜ እና በሌሎች ተፈጥሯዊ ምክንያቶች እንዳይበሰብስ የሚያደርግ የተለያዩ ኬሚካሎችን ተጠቅሞ ባለበት እንዲቆይ ያዱርጋል።

ኩባንያው ይህን የሚያደርገው ሟቾች ወደ ዳግም ህይወት መመለስ ይቻላል የሚል ዕምነት ስላለው እና ሰዎችም ረጅም እድሜ በህይወት የመኖር ፍላጎት አላቸው በሚል ነው።

ሰዎች ይህን አገልግሎት ለማግኘት 200 ሺህ ዶላር መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን አብዛኞቹ ከፋዮች ምን አልባት ቴክኖሎጂው ከሰራ ብለው የሚያምኑ ናቸው ተብሏል።

ከኩባንያው መስራች አንዱ የሆኑት ኢምል ኬንድዚዮራ ለቢቢሲ እንዳሉት ሀሳቡ የተጀመረው አንዲት ስዊድናዊ በልብ ህመም ህይወቷ አልፏል ተብሎ በማቀዝቀዣ ውስጥ ከቆየት ከሁለት ሰዓት በኋላ ዳግም ዳግም ህይወት መዝራቷን ተከትሎ ነው ብለዋል።

እንዲሁም የሞተ የአይጥ አዕምሮን በዚህ የማቀዝቀዝ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ዳግም እንዲመለስ እና በቀዶ ጥገና መልክ በሌላ አይጥ ካይ ተገጥሞ መስራቱ እንደተረጋገጠም ተገልጿል።

ይህ ተስፋ ሰጪ ምልክት በሰዎች ላይ ሊሰራ ይችላል በሚል እየሞከርነው ነው የሚሉት የኩባንያው መስራች የደንበኞቻቸው ቁጥር እየጨመረ እንደሆነም ተናግረዋል።

በተለይም በኮሮና ቫይረስ ወቅት ሞት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቅርብ መሆኑን ተከትሎ ከቫይረሱ መከሰት በኋላ የደንበኞቻቸው ቁጥር ጨምሯልም ተብሏል።

የአንድን የሰውነት አካል በቀዶ ህክምና ወደ ሌላ ሰው መተከት ህክምና ሲጀመር ሰዎች ብዙ ተገርመው ነበር የተባለ ሲሆን ምን አልባት ከ10 ወይም ከ100 ዓመት በኋላ የሞቱ ሰዎችን ዳግም ወደ ህይወት መመለስ ሊጀመር እንደሚችልም ተስፋ ተደርጓል::

ዘገባው የአልዐይን አማረኛ ነው::
ጉርሻ
😎😎😎

🌴🌴🌴

@Sewsinor


ኧረ ሰዎች መረጃ ነጣቂዎቹ በርትተው እየሰሩ ነው እናንተም እንዳትሸወዱላቸው ፤ እንደዚህ አይነትና መሠል ሊንኮችን አትክፈቱ።

ሊንኮቹ የሚላኩት በምታውቋቸው ሰዎች ነው... ጭራሽ ካወራችሁ አመታት ያለፈ ምናምን... ይሁንና ሊንኩን የሚልኩት ግን መረጃ ጠላፊዎቹ ናቸው። ሊንኩን የላኩላችሁን ወዳጆቻችሁን እንዳትቀየሟቸው ከነሱ እውቅና ውጪ ነው።

ዞሮ ዞሮ ግን ሊንኮቹን አትክፈቷቸው።

ሼር አድርጉት ፤ ሌሎችም አውቀው ይጠንቀቁበት።

Join @Sewsinor




በአሜሪካ አዲስ የሰድ እሳት ተቀሰቀሰ‼️
በሎስ አንጀለስ የተቀሰቀሰውን የሰደድ እሳት ለማጥፋት እየታገለች ያለችው አሜሪካ በደቡባዊ #ካሊፎርኒያ ቬንቱራ ግዛት አዲስ ሰደድ እሳት ተቀስቅሶባታል።

“አውቶ ፋየር” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሰደድ እሳቱ ሌሊት 7፡45 ሰዓት ላይ የተቀሰቀሰ ሲሆን በፍጥነት በሚጓዝ ነፋስ ታግዞ እየተስፋፋ  ይገኛል።

ሰደድ እሳቱ ከ2.02 ሄክታር መሬት በላይ ያቃጠለ ሲሆን፤ እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው።
Via:- CGTN (አዩ ዘ ሀበሻ)
=======================

💎 @Sewsinor


ሌላ ሴት ልታገባ ያልክ ቀን እንኳ ብደውልልህ  እሷን ትተህ እኔ ጋር ነው አይደል የምትመጣው? እለዋለሁ ሁሌ …. ፈገግ ብሎ ያየኝና “ደፋር ኮ ነሽ….ይለኛል።

ካለሁ ነገር ሁሉ እኔን አስበልጦ እንደሚወደኝ አውቃለሁ ሲሳሳልኝ ከራሱ ሲያስቀድመኝ ሲጨነቅልኝ ለኔ ሲኖር አይቻለሁ በእርግጥ እንዲ ማለት ከባድ ይመስላል።

እኔ ግን አይኑን ሳያርገበግብ ይሄን ልጅ ግን ምን አስነክታው ነው እስኪባል የሚያውቁን ሁሉ  እስኪገረሙ ድረስ ….ሳናድደዉ ሳበሳጨው ችሎ በክፉ ቀናቶቼ ላይ ለደስታዬ ሲፈጋ አብሮነታችንን ለማቆም ብዙ ሲለፋ አውቅ ነበር።

ይመስለኛል የበዛ መውደዱ የትም አይሄድም ብዬ እንዳስብ ለኛ እንዳልጨነቅና በተወዳጅነት ተኮፍሼ ለሚሰጠኝ መውደድና ክብር ትንሽ እንኳ አፀፌታን መስጠት የማልችል ሴት አደረገኝ።

ከዛ በአንዱ ቀን በትንሽ ነገር ተጋጨንና ….ሂድልኝ አልኩት...ለመነኝ አስለመነኝ….ከቀልቤ መሆን ያልቻልኩት እኔ  ግን ግድ አልሰጠኝምና ምንም እንደጎደለብኝ አልተሰማኝም መሄዱ እንደሚያም እንዴት እንደሚናፍቀኝ ለመረዳት ብዙ ረፈደብኝ።

ሄደ ከዛ አልተመለሰም ልመልሰዉ ሞከርኩ….መሄድ አለማምጄው ኖሮ መመለስ አቃተኝ።

እናማ አሁን የገፋሁት እኔ ወዶኛል አይጠላኝም ያልኩት እኔ በተራዬ እጅግ እየናፈቀኝ:እያመመኝ እያስመሰልኩ አብሮነታችን ማክበር ያልቻልኩት እኔ … ሲያቅፈኝ ህይወት እንደሚቀለኝ ችግሮቼን ችሎ ማሸነፍ ብቻን ያለማመደኝ እሱ እንደነበር በጣም እንደሚናፍቀኝ በጣም እንደማመሰግነው ያልነገርኩት እኔ የሄደበትን ቀን ሻማ እያበራሁ አከብራለሁ።

በስመአብ ጊዜው እንዴት ይሮጣል? አትመጣም በቃ?🙄🙄🙄🙄

✍ By MaHi
------------------------------------------------
ግድ የላችሁም በኔ ይሁንባችሁ ...ዝም ብላችሁ ቤተሰብ ሁኑ
👇👇

🗣
@Sewsinor


ፈይሳ ሌሊሳ......ከእውቀት ሽሽት ነበር ለካ ሲሮጥ የነበረው😁😁😁😁
-----_-----------------------------------------------------

"መኪና ገዘቶ ስለ ነዳጁ መወደድ የሚጨነቅ ሰዉ ይኖራል ብዬ አላስብም: ካለም መኪናዉን ሽጦ ፈረስ ገዝቶ አቢቹ በሰራለት የኮሪደር ልማት ላይ መጋለብ ይችላል::" 😯

🗣የቀድሞ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ

ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ሃሳቡን ገልጿል ።  ይህን የቀድሞውን አትሌት ሃሳብ የተመለከቱም  "  አላዋቂ ሳሚ..." ሲሉ ትችታቸውን ሰንዝረዋል ።

በርግጥም  ሃሳቡ በሰው ቁስል እንጨት እንደመስደድ ነውና የነዳጅ ዋጋ መጨመር የመኪና ባለቤቶች ችግር ብቻ አይደለም ።

የነዳጅ ዋጋ መጨመር ከከተሜው እስክ አርሶ አደሩ ጓዳ  የሚሻገር ተጽእኖ ይኖረዋል ። 

አሁን ካለው የኑሮ ውድነት አለመረጋጋት ጋር ሲደመር ደግሞ ከባድ ችግር ይፈጥራል ።

ሀገራዊ ተጽእኖውን አንተ እንዳልከው  "....ፈረስ ገዝቶ አቢቹ በሰራለት የኮሪደር ልማት ጋልቦ " ማምለጥ የሚቻል አይደለም ።   እናም  ጀግናው ፈዬ ሆይ ' ዝምታ ወርቅ ነው' ነገሮችን አጢኖ መናገር ቢቻል መልካም ይሆናል ።

      ብትችል ያስቀየምከውን የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቅ 🙏🙏 ወንድማዊ ምክሬ ነው

🗣
@Tesh5050 🤝 @CheramlakT


መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ፤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡


በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፤

በምሉእ ፍቅሩ ሰውን ከባርነት ወደ ነጻነት ለመመለስ በሥጋ ሰብእ የተወለደው ጌታችን  ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዘሠምሮ ለሰብእ፤ ክብር በሰማያት ለእግዚአብሔር ይሁን›› በምድርም እጅግ ለወደደው የሰው ልጅ ሰላም ይሁን” (ሉቃ ፪÷፲፬)
ይህ ቃለ ሰላም በጌታችን ዕለተ ልደት የተነገረ ነው፣ ቃሉ የተነገረው እንዲሁ እንደ ተራ ነገር ሳይሆን በቃለ መዝሙር እየተደጋገመ ነው፡፡ የተዘመረውም በምድራውያን ደራሲዎች ሳይሆን በሰማያውያን መላእክተ እግዚአብሔር ነው፣ የያዘው መልእክትም ሰማያውያንና ምድራውያንን ሁሉ ያካለለ ነው፡፡ የመልእክቱ ገዢ ሓሳብም አምላክ ከሰውነታችን ጋር ባለመለያየት፣ ባለመጠፋፋት፣ ባለመቀላቀል፣ ባለመዋዋጥ፣ ባለመለዋወጥና ያለባዕድና አንድ አካል፣ አንድ ክዋኔ፣ አንድ ጠባይ ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጾኣልና እግዚአብሔር ይክብር ይመስገን፡፡ የተዋሕዶውም ምስጢር ሰላምን ያሰፍናልና እግዚአብሔር ሰውን በእጅጉ መውደዱ ከዚህ ተዋሕዶ ዓውቀናል የሚል ነው፡፡

በእርግጥም እግዚአብሔር ሰውን ለመውደዱ ከዚህ የበለጠ ማሳያ ወይም ማስረጃ የለም፤ እንከን የለሽ ንጹህ አምላክ የእኛን ኃጢአተኛ ሰውነት አካሉ አድርጎ ተወለደ ሲባል ላስተዋለው ሰው ምንኛ ቢወደን ነው የሚለው ጥልቅ አድናቆትን ያጭራልና ነው፡፡ይህ ብቻም አይደለም በዚህ ነገረ ተዋሕዶ ምክንያት ሰውነታችን አምላክ ሆኖ በመንበረ ጸባኦት እንዲቀመጥ መብቃቱ የድኅነታችንና የክብራችን ከፍታ ምን ያህል አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መንፈሳችን በአንክሮ ይረዳዋል፡፡ድምር ውጤቱም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ፍጹምና አስተማማኝ ሰላም መፈጠሩን ያስረዳናል፤ ሰማያውያኑ መላእክተ እግዚአብሔር በመዝሙራቸው ያበሰሩን ይህንን የምስራች ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር በእጅጉ ይወደናል ስንል እንዲሁ ከሜዳ ተነሥተን ኣይደለም፡፡ በበደላችንና በኃጢአታችን ሳይጸየፈን ሰውነታችንን በረድኤት ወይም በኅድረት ያይደለ በኩነት ተዋሕዶ ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ስላደረገው  ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ፍጹምና ምሉእ ፍቅሩ ሰውነታችንን በመበረ ጸባኦት ኣስቀምጦ መላእክት ሳይቀሩ ፍጥረታትን በሙሉ እንድንገዛ አድርጎናል፤ ምክንያቱም መላእክት በዕለተ ልደት የዘመሩለት በተዋሕዶ አምላክም ሰውም ለሆነ ለቤተ ልሔሙ ሕፃን እንጂ ለመለኮት ብቻ ኣይደለምና ነው፡፡ የዕለተ ልደት መዝሙር ዛሬም በሰማያትም ሆነ በምድር በተዋሕዶ ሰውም ኣምላክም የሆነ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለክበታል፣ ይመሰገንበታል፡፡የሰማዩና የምድሩ ዕርቅ ወደ ኋላ ላይመለስ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ተከናውኖኣል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰውም አዋጭ ምርጫ ይህ ዕርቅ ተጠብቆ እንዲኖር ነው፣ ያለ ዕርቅ ሰላም ሕይወት የለውምና፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ክብርና ሰላም በእጅጉ የተሳሰሩና የተቆራኙ ናቸው፤ እኛ እግዚአብሔርን ካከበርነው፣ ካዳመጥነው፣ ከታዘዝነውና ከተከተልነው ሰላም አለ ማለት ነው፡፡ ለሱ ካልታዘዝንና እሱን ካላከበርን ግን ዘላቂ ሰላምን ማግኘት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፤ ምክንያቱም ሰላምን ጨምሮ መልካም ነገር ሁሉ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነውና፡፡ ዛሬ በሁሉም የዓለማችን ማዕዘን የሚታየው የሰላም መደፍረስ እግዚአብሔርን ካለማክበራችንና ለሱ ካለመታዘዛችን የተነሣ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡ ዓለም ከእግዚአብሔር ቃል ርቃ ለመሄድ በእጅጉ እየኳተነች ነው፤ በዚህ እኩይ ተግባርዋ ደግሞ እግዚአብሔር ለስጋትና ለጉስቁልና አሳልፎ እየሰጣት ነው፡፡ እግዚአብሔር በምስጢረ ሥጋዌው ቢታረቃትም ዕርቁን ማክበር አቅቶአታል፤ ይህንን የእግዚአብሔር ጸጋ ቸል ብላ የምታደርገው ሩጫ የትም ሊያደርሳት እንደማይችል ብታውቅና በንስሓ ብትመለስ እግጅ ተጠቃሚ ትሆናለች፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ቃል “እናንተስ ከማይጠፋ ዘር ተወለዳችሁ” ብሎ ተስፋውን እንደነገረን ምድባችን ከማይጠፋ ዘር እንዲሆን ክርስቲያኖች የሆን ሁላችን በአእምሮ ጐልብተን፣ በሥነ-ምግባር ኣምረን፣ ጤናማ ሕይወትን ልንመራ ይገባናል፡፡

የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ ነገረ ፍቅርን፣ ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል፡፡

ጠቡ ፣ ጥላቻው፣ መለያየቱ፣ መጠፋፋቱ፣ ለወንድሜ  ከማለት ይልቅ ለኔ ለኔ ማለቱ ሲጎዳን እንጂ ሲጠቅመን ኣላየንም፡፡ አሁንም ወደ ልባችን እንመለስና በፍቅር፣ በዕርቅና በእኩልነት፣ በስምምነትና በወንድምነት ወደሚገኝ አንድነት እንምጣ፤ የልደቱ መዝሙር ያስተማረን ይህና ይህ ብቻ ነውና፡፡ በሌሎቹ ክፍለ ዓለማት እንደሆነው ሁሉ በሀገራችን የተከሠተው አላስፈላጊ ግጭት ብዙዎችን አሳጥቶናል፤ ብዙዎችንም ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ ፈሰው የሰቆቃ ኑሮ እንዲገፉ አድርጎብናል፡፡ የሀገር ሀብት እንዲወድም ሆኖአል፤ ልጆቻችን ምናለ ከእንግዲህ ወዲህ ቢበቃንና ምድሪቱን የሰላም አየር እንድትተነፍስ ብንፈቅድላት፤ ይህ የወቅቱ የቤተክርስቲያናችን ዋነኛ መልእክትና ጥሪ ነው፡፡    

በመጨረሻም፡-

በዓለ ልደት የእግዚአብሔር በዓል ነውና፣ እግዚአብሔር በምድራችን ሰላምን ያወርድ ዘንድ ካለን ከፍለን ለተፈናቃዮች፣ ለነዳያን እና ለአካል ጉዳተኞች በመለገስ በዓሉን በመንፈሳዊ ደስታና በሰላም እንድናከብር አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር  አሜን!

      አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ
ተክለሃይማኖት
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

https://t.me/sewsinor


የቴሌውን የገና ጨዋታ እንዴት አገኛችሁት 😁 ገና አልገኝ ብሏል ፤ ከ ገና ፊደል ውጪ ሌላው ደብል ደብል አለኝ 😎 ገና ፊደል ያለው በሌላ ፊደል እንቀያየር 😁

Inbox @CheramlakT


#ታላቅ_የሚያደርግህ_የጦር_መሳሪያ_እንካ!

👉 ጸልይ
👉 ክብደት አንሳ
👉 ሱስህን ተው
👉 ከቤትህ ውጣ
👉 ተፈጥሯዊ ነገር ተመገብ
👉 የጥበብ መጻሕፍትን አንብብ
👉 ለቤተሰቦችህ ጊዜ ይኑርህ
👉 ፈገግ በል
👉 በሁሉ አመስግን

እነዚህን መሳሪያዎች ታጥቆ የተሸነፈ የለምና አትፍራ!

#ታላቅነትህን_አትጠራጠር መጽሐፍ
#YOU_ARE_A_BADA** (በእንግሊዝኛ)

@Sewsinor


Here’s a strategic plan and roadmap for Wakanda token, Wakanda, focusing on its African roots and potential to empower communities:

Wakanda Token Vision

Empower Africa's digital future by creating a token that fosters innovation, inclusivity, and economic growth, inspired by the resilience and unity of African communities.

Key Goals

1. Economic Empowerment: Enable financial inclusion by providing accessible financial tools and services to unbanked communities.


2. Support for African Entrepreneurs: Foster innovation and entrepreneurship by funding projects and startups in Africa.


3. Cultural Preservation and Promotion: Support initiatives that celebrate and preserve African heritage and culture.


4. Community Engagement: Build a strong, participatory community that benefits from the token's growth.


Roadmap

Phase 1: Foundation (0-3 Months)

Token Launch: Complete the distribution via Blum Airdrop and list Wakanda on decentralized exchanges (DEXs).

Community Building: Host AMAs, set up social media platforms, and engage the African diaspora to support Wakanda.

Partnerships: Collaborate with African blockchain developers, financial institutions, and cultural organizations.


Phase 2: Utility Development (3-6 Months)

Payment Solutions: Integrate Wakanda as a payment option for local businesses, starting with pilot programs in Ethiopia and other African countries.

Governance System: Launch a decentralized governance platform, allowing token holders to vote on future developments.

Awareness Campaigns: Promote blockchain adoption in Africa through education programs and partnerships with universities.


Phase 3: Ecosystem Expansion (6-12 Months)

DeFi Integration: Introduce staking, lending, and borrowing opportunities to grow the token's utility.

NFT Marketplace: Create a platform to showcase and trade African art and cultural artifacts as NFTs.

Cross-border Transactions: Develop solutions for seamless and affordable remittances across African countries.


Phase 4: Long-term Growth (12+ Months)

Token Adoption: Expand partnerships to include NGOs, governments, and major businesses in Africa.

Sustainability Initiatives: Allocate a percentage of token revenue to environmental and social development projects in Africa.

Global Reach: Promote Wakanda as a symbol of African innovation, targeting global markets and investors.


Call to Action

Encourage community members to contribute ideas, participate in governance, and spread the word about Wakanda. This collective effort will strengthen its position as a token of unity and progress for Africa.

https://t.me/blum/app?startapp=ref_D1lmsLt6rM



20 last posts shown.