ከአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ!
እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ክፍለጦራችን ብዙ ገድሎች ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል። ከትግሉ ጎንለጎን ብዙ ውስጣዊና ውጫዊ ችግር ቢኖርም እንደክፍለጦር በወንድማማችነትና በተከባበረ ሁኔታ ጠላቶቻችን በአቀዱልን ሳይሆን እኛ በአቀድነው ስራዎቻችንን ስናካሂድ ቆይተናል።
ለሰሚም ለነጋሪም ቸገረው ነውና ነገሩ ከትናንት ወዲያ የሰጠንውን የሀዘን መግለጫ በዘመቻ ሻለቃ ሰይድ አለምየ አውጀን መላው ክፍለጦሩ በቁጭትና በእልህ እየተዋደቅን ሲሆን ትናንት በአማራ ሳይንት ተድባማርያም በሚባል ቦታ ጀግኖቹ የአርበኛ ይታገሱ አራጋው ልጆች ታሪክን በክንዳቸው ጽፈው ለአማራ ህዝብ ታላቅ ጀብድ ፈጸሙ።
ብሬን ማርኪው በመባል የሚታወቀው ፋኖ ደሳለው ስጦትንና ፋኖ አረቡ ታደሠን ጨምሮ የተሰራውን አስደማሚ ታሪክ በደማቸው በመፃፍ ለአማራ ህዝብ በዛሬው ዕለት ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የአገዛዙን በርካታ የጠላት ኃይሕ ድባቅ ከመቱ በኋላ የመጨረሻውን ጽዋ ተጎንጭተዋል።
እንደ አለመታደል ሁኖ ክፍለጦሩ ከተመሠረተ ጀምሮ በወገንም በጠላትም እየተዋከበ ከመሪው ጀምሮ የተለያዪ አመራሮችን እየገበርን እዚህ ደርሰናል።
ወደፊትም እንደ ሻማ እየቀለጥንና እየሞትን የአማራን ህዝብ ክብር እናሥቀጥላለን።
በጭራሽ ወደ ኋላ አንልም በመቀጠልም ጀግኖቹ የአማራ ሳይንት ልጆች ፋኖ ደሳላው ስጦት የአብይን ጥምር ጦር ሰፍሮበት የነበረውን ምሽግ ተቆጣጥረው ከመሬት ደባልቀው ነው መሠዋትነትን የከፈሉት።
በዚህም ሚዲያዎችም ሆነ ከላይ ያለ አመራር ድል ስናደርግ ብቻ ሳይሆን ሲከፋንም ስንሞትም ከጎናችን ሊቆሙ ይገባል ብለን እናምናለን።
የእኛ አመራሮችም ይሁን መሪ ወደፊት ገብተን መዋጋትእጅ ከኋላ ሁኖ የድሃን ልጅ ብቻ እየገበሩ በእነሱ ደም እኛ መቆም ስለማንፈልግ እሰከ መጨረሻዋ ጽዋ ድረስ አብረን እየገደለን እንወድቃለን።
ፋኖ ደሳለው ስጦት ከእዚህ ቀድም አባቱ የቀበሌ ሊቀመንበር ሁኖ አባቱን ፋኖ ገድሎበት አባቴም ቢሆን ባንዳ ከሆነ ባንዳነው በማለት አባቱ ቀብር ላይ እንኳን ያልተገኘ ጽኑና ቆራጥ የአማራ ልጅ ነበር።
በዱር በገደሉ በመንከራተት ከሳይንት እሰከ ሰሜን ሸዋ ሬማ ድረስ በመጓዝ ለአማራ አንድነትና ትግል ሲታገል የነበረ ጀግና ነበር!
እወቀራዋለሁ ጥርሴን በጥይት
ከሸጋ ልጅ ሀገር አማራ ሳይንት
የተባለው ጀግና ደሳለው ስጦት የአማራ ፋኖ በወሎ አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ቀጠናዊ ትስስር እና የታቦር ብርጌድ አዛዥ የነበረ ጀግና ሲሆን ከእዚህ ቀድም በከላላ ወረዳ ብቻውን ብሬን የማረከ ጀግና ነበር፤
ይሄን ጀግንነቱን ደግሞ በቀኝ አዝማች ይታገሱ ዘመቻ መልሶ ብሬን መማረኳ ይታወቃል። ፋኖ አረቡ ታደሰ በበኩሉም የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር የሠው ሀብት አሥተዳደር በመሆን መሠዋት እሰከ ከፈለበት ወቅት ድረስ ለአማራ ህዝብ በጽናት ታግሏል።
ፋኖ ደሳለው ስጦት በዛሬው ዕለትም ለቁጥር የሚሠለች ጠላትን ደምስሶ ከፋኖ አረቡ ታደሠ ጋር በመሆን ለአማራ ህዝብ ሲል በክብር በጀግንነት ተሠውተዋል።
በቀጣይ የሻለቃ ሠይድ አለምየን ዘመቻ ጨምሮ የፋኖ ደሳለኝ ስጦት እና አረቡ ታደሠን ዘመቻ ስለምናካሂድ ሁሉም ዝግጁ እንዲሆን እናሣሥባለን።
መቸም አንረሳህም!!
ታሪክ ሠርተሃል ታሪክ እሠራለን!!
እየጣልን በእየተራ እንወድቃለን!!
ፋኖ ሙሃመድ አሊ(ጭቅየለሽ )
የአማራ በወሎ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር አዛዥ
ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
@Showapress