ፍራንኮ ቫሉታ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ተባለበፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ አማካኝነት እንዲገቡ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ፍራንኮ ቫሉታ መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የምርት እጥረት እንዳይከሰት የተወሰነ እገዛ ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡
ነገር ግን ፍራንኮ ቫሉታ ባልተገባ መንገድ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራው በመደበኛውና በትይዩ ገበያው መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ተቀራራቢ በማድረጉ የፍራንኮ ቫሉታ እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
አክለውም መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉን እና በሂደት ላይ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረግም አመላክተዋል፡፡
በተጨማሪም የንግድ ባንኮች ለመረሰታዊ ሸቀጦች የሚሆን በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዳላቸው ጠቅሰው በውሳኔው መሰረትም ከውጭ የሚመጡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ ብቻ እንዲገቡ መወሰኑንና ይህም ወደ ተግባር መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡
መንግስት በመሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ ለግል ባለሀብቶች ፍራንኮ ቫሉታ መፍቀዱ የሚታወስ ነው፡፡
@Addis_News@Addis_News