Super Boost-up


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Sport


የማስታወቂያ አቅምዎንና በአረጀ በአፈጀ የማስተዋወቅ ብልሃት በከንቱ አያባከኑ ፤ እኛ ዘመኑን በሚመጥንና በተጠና የዲጂታል ማስታወቂያ ጥበብ ደንበኞቾ ጋር በእንርግጠኝነት እናደርሶታልን !! contact- 0908 222223  / 0914 949494

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Sport
Statistics
Posts filter


የጊዜ ፈተና!

ሰዎችን ጊዜ እንዲፈትናቸው ፍቀዱ!


አንድ የስነ-ልቦና አዋቂ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- “ማንኛውም ሰው ያልሆነውን መስሎ በመኖር ወይም በአስመሳይነት ከሶስትና ከአራት ወራት በላይ የመቆየት አቅም የለውም፡፡ ሰዎች በዚህ ጊዜ ውስጥ እውነተኛ ቀለማቸውንና እናንተን የቀረቡበትን እውነተኛ የመነሻ ሃሳብ አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት መግለጣቸው አይቀርም”፡፡

ሰዎችን ጊዜ እንዲፈትናቸውና እውነተኛ ቀለማቸውን እንዲያወጣው የመፍቀዳችን እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ የእኛ የቤት ስራ ግን መዘንጋት የለብንም፡፡ አንዳንድ ሰዎች እኮ “ጊዜ” የተሰኘው እውነተኛ ፈታኝ የቤት ስራውን በመስራት ሰዎችን ማንነት ቀስ በቀስ ቢገልጥላቸውም እነሱ ግን ያንን ለማየት የሚያስችል ንቃቱም የላቸወም፡፡ ጊዜ እውነቱን ሲያወጣልን ያንን ለማየት የተከፈተና የነቃ አይን ከሌለን ምንም ትርጉም የለውም፡፡

ከሰዎች ጋር ያገናኛችሁ ሁኔታ የፍቅር፣ የንግድም ሆነ ሌላ የአጋርነት ሂደት፣ ምንም ነገር ውስጥ በፍጹም በችኮላ አትግቡ፡፡ ሰዎቹ ላይ ላዩን የተቀቡት አርቴፊሻል ቀለም እየፈዘዘ ሄዶ እውነተኛው ቀለማቸው እስከሚወጣ ድረስ ልባችሁን ጠብቁ፡፡  

የጊዜን እውነተኛ ፈታኝነት ለመጠቀም የሚከተሉትን መርሆች አትዘንጉ . . .     

1. የሰዎቹን ንግግርና ተግባር በሚገባ ተከታተሉ፡፡


ለሰዎች ጊዜን ስትሰጡ ንግግራቸውና ተግባራቸው በሚገባ አጢኑ፡፡ ዛሬ የተናገሩትን ነገ ያለመድገማቸውን፣ ታሪካቸው የመለዋወጡንና ተግባራቸው አንድ ወጥ የመሆኑንና ያለመሆኑን በሚገባ ብትመለከቱ ምልክቶችን ማየታችሁ አይቀርም፡፡

2. ካለማቋረጥ ውስጣችሁን አድምጡ፡፡

ከሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት ውስጣችሁ የሚከለከላችሁንና የሆነ የተዛባ ነገር እንዳለ የሚሰማችሁን ነገር በፍጹም አልፋችሁ አትሂዱ፤ በሚገባ አስቡበት፡፡

3. ወጥመድን ለዩ፡፡

በዚህ አውድ መሰረት “ወጥመድ” ማለት አንድ ነገር ትክክል እንዳልሆነ እያወቃችሁት ነገር ግን ሰውየው ከሚያሳያችሁ የሚጠቅም የሚመስል ሁኔታ የተነሳ አልፋችሁ ስትሄዱና በጓጓችሁለት ነገር ምክንያት ስህተቱን ከማየት ስትጋረዱ ነው፡፡

4. የውሳኔ ሰዎች ሁኑ፡፡

አንድ ግንኙነት ወይም መንገድ እንዳማያዛልቃችሁ አውቃችሁ ሳለ ነገር ግን ከተለያዩ ጥቅሞች ወይም ዋጋ የሚያስከፍል ሁኔታ የተነሳ ከውሳኔ እንዳትገቱ መጠንከር አስፈላጊ ነው፡፡ ምን ያህል ብልሆች ብንሆንም የውሳኔ ሰዎች ካልሆንን ከመሳት አናመልጥም፡፡

የጥበብ ዘመን ይሁንላችሁ!

☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup




አትጨነቁ!

አንድን ምርጫ እና ውሳኔ ያደረጋችሁበትን የመነሻ ሃሳባችሁን በሚገባ ሳይገነዘቡ የግድየለሽነት ሃሳብ ስለሚሰነዝሩ ሰዎች አትጨነቁ፡፡

በእርማት አልፋችሁ የመጣችሁትንና ትምህርት ያገኛችሁበትን ያለፈው ስህተታችሁን አሁንም ስለሚያወሩ ሰዎች አትጨነቁ፡፡

ስለጤናማነቱና ስለትክክለኛነቱ በእርግጠኝነት አስባችሁበትና አቅዳችሁ የምትከተሉትን ዓላማችሁን ስለሚቃወሙ ሰዎች አትጨነቁ፡፡

በምን አይነት ሁኔታ አልፋችሁ አሁን የደረሳችሁበት የስኬት ደረጃ እንደደረሳችሁ የማያውቁ ሰዎች በእናንተ ላይ ስላላቸው አመለካከት አትጨነቁ፡፡

በአጭሩ፣ ስለሚያስበውና ስለሚያወራው አትጨነቁ!!!
መልካም የስራ ሳምንት🙏

☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup


የእውቀት፣ የክህሎት እና የጥበብ ቅንጅት!

1.  እውቀት ማለት፣ ምን እንደሚደረግ ማወቅ ማለት ነው፡፡


አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ ምን እንደሚደረግ ያውቃል ማለት ስኬታማ ነው ማለት አይደለም፡፡ ብዙ ሃሳብ መሰንዘር የሚወዱና ተግባር ላይ ግን ብዙም የሌሉበት ሰዎች እዚህ ክፍል ውስጥ ይመደባሉ፡፡

እንደዚህ አይነት ሰዎች ምን እንደሚደረግ የማወቃቸውን የመረጃ እውቀት ወደ “እንዴት ይደረግ” ደረጃ ሊያሳድጉት ይገባቸዋል፡፡  

2.  ክህሎት ማለት፣ አንድ ነገር እንዴት እንደሚደረግ ማወቅ ማለት ነው፡፡

አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ ምን እንደሚደረግ ከማወቅ የጽንሰ ሐሳብ እና የመረጃ እውቀት አልፎ፣ እንዴት እንደሚደረግ ተግባራዊ እውቀት ሲኖረው እዚህ ይመደባል፡፡

ሆኖም፣ ምንም እንኳን እንዴት እንደሚደረግ የማወቅ ብቃቱና ልምዱ ቢኖረውም እሱ ብቻውን ረጅም ርቀት ላይሄድ ስለሚችል መቼ እና በምን መልኩ ሊያረግ እንደሚገባው ወደማወቅ ደረጃ ማደግ ያስፈልጋል፡፡

3.  ጥበብ ማለት፣ አንድ ነገር መቼ እንደሚደረግ ማወቅ ማለት ነው፡፡

በመረጃ መልክ ወደ ማወቅ ያመጣነውን እና ከዚያም አልፈን እንዴት መደረግ እንዳለበት ክህሎቱን ያዳበርንበትን ነገር በወቅቱ መደረግ ይኑርበት እና አይኑበት የመለየት ብልሃት ጥበብ ይባላል፡፡ ምንም አይነት የመረጃም ሆነ ተግባራዊ ክህሎት የመጨረሻ ስኬታማነቱ ያለው በጥበብ ሲያዝ ነው፡፡

መረጃ-ተኮር ከሆነው እውቀት፣ ተግባር-ተኮር ወደሆነው ክህሎት፣ ከክህሎት ደግሞ ብልሃት-ተኮር ወደሆነው ጥበብ ስናድግ ከአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ቀደም ብለን እንገኛለን!

☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup


Telegram




ለምንድን ነው?

ለምንድንነው ሰዎች እንደፈለጉ የሚያደርጉኝ?፤ ለምንድንነው ክልከላ ማድረግ ላለብኝ ነገር እምቢ ማለት የሚያስቸግረኝ?፤ ለምንድን ነው በቀላሉ በሰዎች ቁጥጥርና ጭቆና ስር ወድቄ  ራሴን የማገኘው?፤ ለምንድን ነው ሰዎች ለሚሰማቸው ስሜት እኔ ሃላፊነትን የምወስደው?፤ ለምንድን ነው?  

ምክንያቱም፦

1.  ሁል ጊዜ በሁሉም ሰው መወደድን መፈለግ
በሰዎች መወደድን የሚፈልግ ሰው ማንም ሰው እንዳይቀየመው ስለሚፈልግ ለሁሉም ነገር በመስማማት ሳይወድ በግዱ በሰዎች ቁጥጥር ስር ይኖራል፡፡ ሆኖም፥ ሁል ጊዜ በሁሉም ሰው መወደድ ስማይቻል አንደኛችንን ነጻነታችን ማወጅ ይሻለናል፡፡

2.  የግንዛቤ ጉድለት
የግል የቀይ መስመርን አስመልክቶ የተዛባ አመለካከት ወይም ያልበሰለ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች፡ ያንን ማድረግ ያቅታቸዋል፡፡ ይህ የተዛባ ዝንባሌ፥ ከአስተዳደግ ወይም አንዳንድ የሃይማኖት አስተምህሮቶችን በተሳሳተ መንገድ ከመገንዘብ ሊመጣ ይችላል፡፡ ማንኛውም ግንኙነት የቀይ መስመር፣ ማለትም የሚፈቀደውና የማይፈቀደው ነገር ሊለይ እንደሚገባው ማወቅ ተገቢ ነው፡፡

3.  የዝቅተኛነት ስሜት
የበታችነት ስሜት የሚሰማው ሰው የራሱ የሆነ አመለካከት እና አቋም የመያዝ ችግር ስላለበት ሁል ጊዜ የበላዩ እንደሆኑ በሚያስባቸው ሰዎች ቁጥጥር ስር ራሱን ያገኘዋል፡፡ ከሰዎች ጋር ምናልባት በችሎታ ልንለያይ ብንችልም “በሰውነት” ግን እኩል መሆናችንን መቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ 

4.  አለመግባባትን መፍራት
አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት ነገር እንዲፈጠር ስለማይፈልጉና ስለሚፈሩ፣ ትንሽ ኃይለኛነትን የሚያንጸባርቁ ሰዎች ካጋጠሟቸው ቶሎ ብለው የበታችነቱን ስፍራ በመያዝ ይገዛሉ፡፡ በማንኛውም ግንኙነት ውስጥ አለመግባባት ሊፈጠር እንደሚችል አምኖ በመቀበል ሁኔታውን ለእድገት መጠቀም የግድ ነው፡፡

5.  ሰዎችን ካለልክ ማመን
ሁሉን ሰው እንዲሁ በየዋህነት የማመን ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች ማንም ሰው ይጎዳኛል ብለው ስለማያስቡ በሁሉም ነገር ተስማሚዎች ሆነው ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ሰዎችን ማመን መልካም ሆኖ ሳለ፣ ራሳችንን ከመጠበቅ እና ሁሉን በልክ ከማድረግ ጋር መያዝ ተገቢ ነው፡፡

👉 🙏🏽☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy

☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup

Telegram

Telegram




“እሺ” እና “እምቢ”

ሕይወት ተፈጥሯዊ ሂደቷን እንድትቀጥልና ሁኔታዎች በራሳቸው መስመር እየያዙ እንዲሄዱ መለማመድ የምንችላቸው ሁለት ልምምዶች አሉ፡፡ እነዚህ ልምምዶች ከለመድናቸው እጅግ ቀላል የሆኑ፣ ካላወቅንበት ግን የሚከብዱ ልምምዶች ናቸው፡፡ 

1.  ለተገቢው ነገር “እሺ” ማለት፡- በሕይወታችን መልካም ነገሮች እንዲገቡ በሩን የሚከፍተው ቁልፍ!

በሚገባና በተረጋጋ መንፈስ አስባችሁበት ትክክለኛ እንደሆነ ላመናችሁበት ነገር “እሺ” ማለት ሌሎች መልካም ነገሮች እየተወለዱ የሚሄዱበትን መስመር ይከፍትላችኋል፡፡

2.  ተገቢ ላልሆነ ነገር “እምቢ” ማለት፡- በሕይወታችን ጤና-ቢስ ነገሮች እንዳይገቡ በሩን የሚዘጋው ቁልፍ! 

በሚገባና በተረጋጋ መንፈስ አስባችሁበት ትክክለኛ እንዳልሆነ ላመናችሁት ነገር “እምቢ” ማለት ደግሞ በሕይወታችሁ መልካም ያልሆኑ ነገሮች እየተበራከቱ እንዳይሄዱ መንገዱን ይዘጋዋል፡፡

እነዚህ ሁለት ልምምዶች ፍርሃትን አልፎ መሄድን ይጠይቃሉ፡፡

በአንድ ጎኑ፣ “እሺ” ለምንለው ነገር ብቁ ባንሆንስ፣ ባይሳካስ፣ በኋላ ብጸጸትስ . . . እና የመሳሰሉትን ፍርሃቶች ማስወገድን ይጠይቃል፡፡

በሌላ ጎኑ ደግሞ “እምቢ” በማለታችን ምክንያት ችግር ቢደርስብንስ፣ እድል ቢያመልጠንስ፣ ሰዎች ቢቀየሙንስ . . . እና የመሳሰሉትን ፍርሃቶች ማስወገድን ይጠይቃል፡፡

👉 🙏🏽☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup

Telegram




ሚዛናዊ ጥቅም

“ሌላውን ቤተሰብ ለመጥቀም የራሳችሁን ቤተሰብ መጉዳት የለባችሁም፤ የራሳችሁን ቤተሰብ ለመጥቀም ደግሞ ሌላውን ቤተሰብ መጉዳት የለባችሁም” (Balanced Life Quotes)

ለሌላው ሰው ጥቅም ስንል ራሳችንን እስከመጉዳት ድረሰ የምንደርስበት ሁኔታ ሊኖር የመቻሉ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከሚዛናዊነት አንጻር ሲታይ ግን ይህ መርህ ሁለገብ እውነትነት አለው!

የሌላውን ነጋዴ ንግድ ለመደገፍ የራሳችሁን ንግድ መጣል የለባችሁም፤ የራሳችሁን ንግድ ለማሳደግ ደግሞ የሌላውን ሰው ንግድ መጣል የለባችሁም፡፡

የራሳችሁን አካባቢ ለመጥቀም የሌላውን ሰው አካባቢ መጉዳት የለባችሁም፤ የሌላውን ሰው አካባቢ ለመጥቀም የራሳችሁን አካባቢ መጉዳት የለባችሁም፡፡

               መልካም ቀን🙏

☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup

Telegram


ወደ አለንበት እንመለስ!
(“ትኩረት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

ፓይለቱ አይሮፕላን ማብረር ከጀመረ ሰንበት ብሏል፡፡ ከአጠገቡ ገና ጀማሪ የሆነ ረዳት ፓይለት ተቀምጧል፡፡ የበረራውን ቅድመ-ዝግጅት ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ተመደበላቸው የከፍታ መጠንና አቅጣጫ ተነሱ፡፡ መብረር ከጀመሩ የተወሰኑ ሰኮንዶች አልፈዋል ሆኖም የዋናው ፓይለት አይኖች ወደታች በማየት ተተክሏል፡፡

የሚያየው አንድን አነስተኛ ሃይቅ ነው፡፡ በዚህ ሃይቅ ዙሪያ የአካባቢው ሰዎች ይርመሰመሳሉ፡፡ ውኃ የሚቀዳው፣ ከብቶቹን የሚያጠጣው፣ የሚዋኘው ሰው ወዲህና ወዲያ ይላል፡፡ የአይሮፕላኑ ከፍታ እየጨመረ ቢሄድም እንኳ የዋናው ፓይለት አይኖች ከዚህ ሃይቅ ላይ አለመነሳቱን አይቶ ረዳቱ፣ “ምነው ፈዝዘህ ቀረህ?” አለው፡፡

የዋናው ፓይለት ትካዜ የሞላበት መልስ፣ “አይ አንዳንድ ነገሮች ትዝ ብለውኝ ነው፡፡ ይህ አሁን አይተነው ያለፍነው ሃይቅ እኔ ያደኩበት አካባቢ ነው፡፡ ያን ጊዜ በዚያ ሃይቅ ዙሪያ ሆነን አሳ እናጠምድ ነበር፡፡ ታዲያ በዚያን ጊዜ አይሮፕላኖች ከላያችን ሲያልፉ ቀና በማለት፣ “መቼ ይሆን ከዚህ የሕይወት ሁኔታ ወጥቼ በአይሮፕላን የምበረው እያልኩ እመኝ ነበር፡፡ አሁን ይህ ምኞቴ ደርሶ በአይሮፕላን መብረር ብቻ ሳይሆን ማብረርም ከጀመርኩ ሰንብቻለሁ፡፡ አሁን ግን ሃይቁን ወደታች እያየሁ፣ መቼ ይሆን አሁን ካለሁበት የስራ አዙሪት ወጥቼ አሳ የማጠምደው እያልኩ ነው”፡፡

ያተኮረን የሕይወት ዘይቤ የተለማመዱ ሰዎች ዋናው አላማቸው አሁን ያሉበትን ስፍራና አሁን በእጃቸው የገባውን ነገር ተጠቅመውና በእለቱ ሁኔታ ደስተኛ በመሆን መድረስ የሚችሉበት ደረጃ ለመድረስ መጣጣራቸው ላይ ነው፡፡ ነገ መሆን የሚፈልጉትና ለማድረግ የሚያቅዱት ነገር ቢኖራቸውም አሁን ግን ባሉበት ሆነው የወቅቱን ሁኔታ ማሻሻልና በእጃቸው ባለው ነገር መደሰት እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡

ይህንን አትዘንጉ፡- “ወሳኙና ትኩረታችንን ልንጥልበት የሚገባው ነገር በእጃችን የሌለን ነገርና ያልተገኘንበት ስፍራ ላይ ሳይሆን በእጃችን ባለው ነገርና አሁን ባለንበት ስፍራ ላይ ሊሆን ይገባዋል”

በሉ እንግዲህ ወደ አለንበት እንመለስ!


👉 🙏🏽☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup




ዛሬ የሕይወታችሁ የመጀመሪያው ቀን ቢሆን!

“ዛሬ የሕይወታችሁ የመጀመሪያው ቀን ነው!” ብትባሉ . . . 

•  ምን በማድረግ ቀኑን ትጀምራላችሁ?

•  ምንስ በማቆም ቀናችሁን ትጀምራላችሁ?

•  የትኛውን ነገር በመርሳትና ወደኋላ በመተው ሕይወታችሁን ትጀምራላችሁ?

•  ከየትኛው መርዛማ ግንኙነት በመለየት ወደፊት ለመሄድ ውሳኔን ታስተላልፋላችሁ?

•  ለወደፊቱስ ምን አይነት እቅድ ታወጣላችሁ?

•  እስካሁን ተጨንቃችሁ ምንም ለውጥ ያላመጣችሁትን የትኛውን ጭንቀት ለመተው ትወስናላችሁ?

በሉ እንግዲያው፣ “ዛሬ ለተቀረው ዘመናችሁ የመጀመሪያው ቀን ነው”!

“Today Is The First Day Of The Rest Of Your Life” - Charles Dederich

መልካም የአዲስ ጅማሬ ቀን ይሁንላችሁ!

🙏🏽☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup


🌻🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼🌻

🌼 እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2017 በሰላም አደረሳቹአደረሰን !!!

አዲሱ ዓመት የሰላም፣የፍቅርና የጤና የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ድምጻችሁ ይስተካከል!

ዛሬ . . .

•  የስሜታዊነታችሁን ድምጽ ቀንሱ፣ የምክንያታዊነታችሁን ድምጽ ጨምሩ . . .።

•  ሰዎች ስለእናንተ የሚያወሩትን ድምጽ መስማት ቀንሱ፣ እናንተው ስለራሳችሁ የምታውቁትን የእውነታ ድምጽ ጨምሩ . . .።

•  ያልሆነውንና ያልተሳካውን ነገር ድምጽ ቀንሱ፣ የተሳካውንና መስመር የያዘውን ሁኔታ ድምጽ ጨምሩ . . .።

•  ግራ የገባችሁንና እርግጠኛ ያልሆናችሁበትን ሁኔታ ድምጽ ቀንሱ፣ እርግጠኛ የሆናችሁበትን ሁኔታ ድምጽ ጨምሩ . . .።

•  የማይቀበሏችሁንና የማይወዷችሁን ሰዎች የመከተል ድምጽ ቀንሱ፣ የሚወዷችሁንና የሚናፍቋችሁን ሰዎች ድምጽ ጨመር አድርጉ።

ብልህ ሁኑ፤ በክፉው አትገኙ፤ አመዛዝኑ፤ የምታስቡትንና የምታምኑትን ለዩ!

🙏🏽☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup


የግብ እውነታዎች
“""""""""""""""""""‟

በሕይወታችሁ ልትሰሩት ከምችሏቸው ቀንደኛ ስህተቶች መካከል ከግብ ውጪ የመኖር ሁኔታ ተጠቃሽ ነው፡፡ የግብ መኖር ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ሁሉ የግብ አለመኖርም ብዙ ጉዳቶች አሉት፡፡

የግብ ጥቅሞች

1.  ትኩረት፡-
ግብ ያለው ሰው የሚያስበውንም ሆነ የሚያደርገውን ነገር ከግቡ አንጻር ስለሚቃኘው የየእለት ኑሮውን በከፍተኛ ትኩረት የሚኖር ሰው የሚሆነው፡፡

2.  አዎንታዊ ስሜትና አመለካከት፡- ግብ ያለው ሰው በየእለቱ አዎንታዊ ስሜት፣ አዎንታዊ አመለካከትና አዎንታዊ ጉልበት ያለው ሰው ነው፡፡ ማታ ሲተኛ የቀኑን የግብ ጉዞ ገምግሞ የመተኛት፣ ጠዋት ሲነሳ ደግሞ የእለቱን ግብ አስቦ የመውጣት ልምምዱ ከፍተኛ አዎንታዊነትን ይሰጠዋል፡፡

3.  በራስ መተማመን፡- ግብ ያለው ሰው መቼ ከየት ተነስቶ አሁን የት እንደደረሳና መቼ የቱ ጋር እንደሚደርስ በሚገባ ስለሚውቅ ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ያለው ሰው ነው፡፡

4.  ቆጣቢነት፡- ግብ ያለው ሰው የለውን የጊዜ፣ የገንዘብ፣ የስሜትና የመሳሰሉትን ሃብቶቹን ሳያባክን በሚገባ የሚጠቀም ሰው ነው፡፡

5.  ተፈላጊነት፡- ግብ ያለውን ሰው ያለውን የከበረና ዓላማ-መር ሕይወት ብዙዎች ሊጠቀሙበት ስሚፈልጉ ተፈላጊነቱን ይጨምረዋል፡፡

አምስቱ “በፍጹሞች”!

1.  በፍጹም ከግብ ውጪ አትኑሩ! -
የሕይወታችሁን ዓላማ እወቁና ከዚያ አንጻር ግልጽ የሆነን ግብ አውጡ፡፡

2.  በፍጹም “ቅንጥብጣቢ” ግቦችን ስትከተሉ አትኑሩ! - ከሕይወታችሁን ዋና ዓላማ ጋር የማይዛመዱ ጥቃቅንና የተበጫጨቁ ግቦችን ከመከተል ተጠበቁ፡፡

3.  በፍጹም ሰውን የማስደሰት ግብ አታውጡ፡- የግችሁን መሳካት ሰዎችን (ቤተሰብ፣ የትዳር አጋር፣ ፍቅረኛ . . . ) ከማስደሰት ጋር ካነካካችሁት ከተደሰቱ ግባችሁን እንደመታችሁ፣ ካልተደሰቱ ደግሞ ግባችሁን እንዳልመታችሁ ይመስላችሁ በከንቱ ትደክማላችሁ፡፡

4.  በፍጹም ቀን ገደብ ያልተቀመጠለት ግብ አታውጡ! - የቀን ገደብ የሌለው ግብ መነሳሳት የማይሰጥ ከመሆኑም በላይ መሳካቱና አለመሳካቱን መመዘኛ ነጥብ የሌለው ግብ ነው፡፡

5.  በፍጹም ከግባችሁ አትመለሱ! - ግብ ካለ እንቅስቃሴ አለ፤ እንቅስቃሴ ካለ ደግሞ ሁል ጊዜ እንቅፋት አለ፡፡ ወደግባችሁ ስትሄዱ እንቅፋት ሲያጋጥማችሁና ስትወድቁ እንደገና ተነሱና ቀጥሉ፡፡

👉በየቀኑ ጠቃሚ መልእክቶችን፣ መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ በነፃ የምታገኟቸው አሪፍ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች፣ የቢዝነስ ሃሳቦች እና የገንዘብና የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።

☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup




የታያችሁን ያህል ተንቀሳቀሱ!

አንድ ምሽት ላይ አባት ልጁን ወደ ሲኒማ ቤት ሊወስደው ውጪ መንገድ ላይ መኪና ውስጥ እየጠበቀው ነው፡፡ ልጅ ከቤት እንደወጣ በጣም ስለጨለመበት ስልኩን አውጥቶ አባቱ ጋር ደወለ፡፡

• ልጅ፡- “አባዬ እንዴት ልምጣ? ጨለማ ስለሆነ አይታይም”፡፡

• አባት፡- “ምን ያህል ይታይሃል?”

• ልጅ፡- “አምስት እርምጃ ያህል ብቻ ነው የሚታየኝ”

• አባት፡- “አምስት እርምጃ ተራመድ”

• ልጅ፡- “እሺ” (አምስት እርምጃ ተራመደ)

• አባት፡- “አሁንስ ምን ያህል ይታይሃል?”

• ልጅ፡- “አሁንም ሌላ አምስት እርምጃ ያህል ርቀት ይታየኛል”

• አባት፡- “በፊትህ የሚታይህን አምስት አምስት እርምጃ እያልክ ከመጣህ እኔ ጋ ትደርሳለህና የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ”

ልጅ ብዙም ሳይቆይ አባቱ ጋር ደረሰ፡፡

ሁሉም ነገር ጥጉ ድረስ እስኪታያችሁ አትጠብቁ፡፡ በሚታያችሁ መጠን ተራመዱ፡፡ የሚታያችሁን ያህል ስትራመዱ፣ ከመራመዳችሁ በፊት ያልታያችሁን ማየት ትጀምራላችሁ፡፡

ሁሉንም ነገር እስከምታውቁ አትጠብቁ፡፡ በምታውቁት ልክ ስራን ጀምሩ፡፡ በምታውቁት እውቀት መጠን ስራን ስትጀምሩ፣ ያንን ከመጀመራችሁ በፊት ያልነበራችሁ ልምድና እውቀት ወደ እናንተ ይመጣሉ፡፡

ሁሉም ሰው እስኪቀበላችሁ አትጠብቁ፡፡ የሚቀበሏችሁ ላይ በማተኮር ተሰማሩ፡፡ በሚቀበሏችሁ ላይ ስታተኩሩና ደስተኛ ስትሆኑ፣ ቀድሞ የማይቀበሏችሁ ሁሉ እናንተን ከመቀበል ውጪ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡

የጠየቃችሁት ነገር ሙሉ በሙሉ እስኪሰጣችሁ አትጠብቁ፡፡ የተሰጣችሁን ተቀበሉና በዚያ በመጀመር የምትችሉትን አድርጉ፡፡ በተሰጣችሁ በጥቂቱ የምታደርጉት ጥረትና የምታከናውኑት ነገር የቀረው እንዲለቀቅላችሁ መንገድ መክፈቱ አይቀርም፡፡

አትቀመጡ! የታያችሁን ያህል ተንቀሳቀሱ!

👉በየቀኑ ጠቃሚ መልእክቶችን፣ መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ በነፃ የምታገኟቸው አሪፍ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች፣ የቢዝነስ ሃሳቦች እና የገንዘብና የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።

☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup

Telegram
Super Boost-up
የማስታወቂያ አቅምዎንና በአረጀ በአፈጀ የማስተዋወቅ ብልሃት በከንቱ አያባከኑ ፤ እኛ ዘመኑን በሚመጥንና በተጠና የዲጂታል ማስታወቂያ ጥበብ ደንበኞቾ ጋር በእንርግጠኝነት እናደርሶታልን !! contact- 0908 222223  / 0914 949494



20 last posts shown.