ትምህርት ሚኒስቴር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @Students_Guidbot
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
https://t.me/+FNqquONwo4FmZGQ0


Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


❤️‍🩹የብዙ ሰዋች የትዳር (የፍቅር) መፍረስ የሆነው የስንፈተ ወሲብ ችግር ዘላቂ መፍትሄ በሀገራችን አስመጥተናል።

👨‍⚕ዶ/ር ዮናስ አጠቃላይ የስንፈተ ወሲብ አማካሪ🩺✅

🔬ፍቱን የተመሰከረላቸው ኦርጅናል የስንፈተ ወሲብ መድሀኒቶችን ከኛጋ ያገኛሉ።🩺

🔬በሰዎች ላይ ተሞክረው ፈጣን ና ዘላቂ መፍትሄ ያመጡ ኦርጂናል የስንፈተ ወሲብ መድሀኒቶችን በክሬም ና በታብሌት አማራጭ በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸጥ ላይ እንገኛለን።

ይደውሉ +251903970404

💈በወሲብ ወቅት ቶሎ የመጨረስ ችግር በዘላቂነት የሚቀርፍ።

💈የብልት መጠን ማነስ ችግር በዘላቂነት መጠንን የሚጨምር።

💈በወሲብ ወቅት የብልት አለመቆም (ጥንካሬ) የማጣጥ ችግርን በዘላቂነት የሚቀርፉ ።

🩸ዋና ማከፋፋያችን አ.አ በተለያዩ ክልል ከተሞች ሰዋች አዘጋጅተናል ይዘዙን ባሉበት ቦታ ሆነው ያገኛሉ።

ተጨማሪ ይመልከቱ👇👇
https://t.me/TY_ShopCenter


ትምህርት ሚኒስቴር የመቁረጫ ነጥብ በሟሟላት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ ከግንቦት 8-10 ባሉት ቀናት ብቻ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር በአካል በመገኘት እንዲመዘገቡ እና ትምህርት እንዲጀምሩ አስታውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ምዝገባ አድርገው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መልዕክት አስተላልፏል
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


#የ8ኛ_ክፍል_ፈተና

በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል (የሚኒስትሪ) ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል ተብሏል።

ከተማ አቀፍ የሆነው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከ71ሺ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 2014 ዓ.ም ለመፈተን መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ ሰባ አንድ ሺ ስድስት መቶ ስልሳ አንድ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለማስፈተን ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን በትምህርት ቢሮ ፈተና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ተናግረዋል።

የፈተና ዝግጅቱ ተጠናቆ የህትመት ስራዉ የተዘጋጀ ሲሆን በእለቱ የማሰራጨት ስራ ብቻ እንደሚቀርም ገልጸዋል፡፡

የፈተናዉን ምዝገባ በተመለከተ የተማሪዎች የአድሚሽ ካርድ በሚቀጥለው ሳምንት በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚላክ እና ለተማሪዎቹም እንደሚተላለፍ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስምንተኛ ክፍል ፈተና 211 የመፈተኛ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ሲሆን ጣቢያዎቹን ምቹ ናቸው የሚለውን ምልከታ እየተደረገ መሆኑን በማንሳት ቁጥሩ ከፍ አልያም ዝቅ ሊደረግ እንደሚችል አቶ ዲናኦል አብራርተዋል።

ፈተናው በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚሰጥ መታወቁን ብስራት ኤም ሬድዮ ዘግቧል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


📱💻በየቀኑ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናሉን ይቀላቀሉ


#የዩኒቨርሲቲ_መግቢያ_ቀናት

የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን እና ሪፖርት የሚያደርጉበትን ቀን እያሳወቁ ይገኛሉ።

እስካሁን ባለው የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ያሳወቁ ተቋማት እና የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መግቢያ/ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ፦

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2015 ዓ/ም ፤ በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ/ም ድረስ

2. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ/ም ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 ዓ/ም

3. ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም

4. ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 ዓ/ም

5. ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014 ዓ/ም

6. መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ/ም

7. ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014 ዓ/ም

8. ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም

9. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ/ም

10. ASTU / AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በቅጣት ግንቦት 1 /2014 ዓ/ም

11. ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ፤ ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11

12. መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014 ዓ/ም

13. ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14

ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎች ጥሪ ሲያቀርቡ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


#ScholarshipTip

የህንድ መንግስት በ2022/23 ለ55 ኢትዮጵያዊያን ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።

በህንድ ባህላዊ ግንኙነት ም/ቤት (ICCR) የቀረበው ነፃ የትምህርት ዕድሉ፤ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ድህረ ዶክትሬት የትምህርት ፕሮግራሞች የተካተቱበት ነው።

በህንድ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት የሚሰጠው ዕድሉ፤ ከክፍያ ነፃ የትምህርት አገልግሎቶች እና ነፃ የአየር በረራ ትኬት ለአሸናፊዎች ያቀርባል።

ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ዕድሚያቸው ከ18 እስከ 30 ሊሆን ይገባል።

አመልካቾች እስከ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት ማልከት እንደሚችሉም ተገልጿል።

የማመልከቻ ጊዜው ግንቦት 23/2014 ዓ.ም ያበቃል።

ለማመልከት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦
https://a2ascholarships.iccr.gov.in

@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


የምስራች ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኢድ አልፈጥር በአል ምክንያት በማድረግ ለ500 ሰዎች ልዩ የሆነ የበአል ስጦታ አዘጋጅቷል። ወደ ግሩፑ ከ100 ሰው በላይ ያስገቡና ይሸለሙ።

አባላትን Add ለማድረግ የዚህን ግሩፕ ሊንክ ይጠቀሙ 👇 @Safaricom_Official_Group
@Safaricom_Official_Group

Add ያድርጉ በየቀኑ ይሸለሙ
©Safaricom_Ethiopia™
@safaricom_official_Channel


በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ
አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሚያዚያ 28 እስከ 30/2014 ዓ.ም ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

የማመልከቻ ካምፓሶች፦

👉 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዘንዘልማ ካምፓስ፣
👉 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በይባብ ካምፓስ፣ 👉 የተፈጥሮ እና ማኅበራዊ ሳይንስ በመምህርነት
ተማሪዎች በሰላም ካምፓስ

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መጠቀም ይቻላል።

ለምዝገባ ወደ ተቋሙ ስትሄዱ መያዝ የሚገባችሁ፦

• የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ውጤት ዋናውና ኮፒ
• ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

በሌላ በኩል በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ ተብሏል።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


የአበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ጥሪ ፦

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014  የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሚያዚያ 24 ቀን እና ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ የሚያስፈልጋችሁ ነገሮች ከላይ ተዘርዝረዋል አንብቧቸው።

ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ https://portal.aau.edu.et ማግኘት ትችላላችሁ።

በሌሌላ በኩንል ፤ ተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከሚያዚያ 27 እና 28 2014 ዓ.ም እንዲያመለክቱ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አቅርቧል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት ዕቅድ ክንውን ሪፖርት ቀርቦ ከአስተዳደር ካውንስል አባላት ጋር ውይይት ተደካሄደ።

በመድረኩ በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የተመደቡ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የቅበላ ዝግጅት እና የአካዳሚክ ካላንደር ሰነድ ቀርቦ ንግግር ተደርጎበታል።

ዩኒቨርሲቲው የ2014 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎን ለመቀበል እየተደረገ ያለውን ቅድመ ዝግጅት እና የቅበላ ጊዜን በተመለከተ «የተማሪዎች አቀባበልና አካዳሚክ ካላንደር» የተመለከተ ሰነድ በዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ልዩ አማካሪ በሆኑት መምህር ደሳለኝ ደርጋሶ ቀርቧል።

በቀረበው ሰነድ መነሻ፤ ዩኒቨርሲቲው በ2014 ዓ.ም 5000 የ1ኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል በየዘርፉ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲከናወን መቆየቱን በቀረበው ሪፖርት ተብራርቷል።

በቀረበው አካዳሚክ ካላንደር መሰረት ፦

👉 በ2014 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሚያዝያ 27-28/2014 ዓ.ም ድረስ መሆኑ፤

👉 በህገ ደንብ እና ተማሪዎች መከተል ስለሚገባቸው የስነ ምግባር ደንብ ገለጻ (Orientation) ሚያዝያ 29/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ፤

👉 የመጀመሪያ ቀን፥ የመጀመሪያ ቀን ክፍለ ግዜ (DOCO) ግንቦት 01/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር፤

👉 የመጀመሪያ ሴሚስተር አጋማሽ ፈተና ከሰኔ 20-28/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ እንዲሁም

👉 የመጀመሪያ ሴሚስቴር የሚያበቃው እና ተማሪዎች ግቢ የሚለቁት ሰኔ 29 መሆኑን አስተዳደር ካውንስሉ የቀረበውን ሪፖርት ገምግሞ #አጽድቋል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


በ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚጠብቁ ተማሪዎች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በ 2014 ዓ.ም አዲስ የተማሪዎች ቅበላን ለማከናወን መጋቢት 07/2014 ዓ.ም ፈተና መፈተናቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ምደባውን ለመግለፅ እንዳልተቻለ እና መጋቢት 17/2014 ምደባው የተለቀቀ መሆኑ ተገልጿል።

በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ኦፊሲያል ድህረ-ገጽ ላይ አድሚሽን ቁጥር በማስገባት ተማሪዎች መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

www.aastu.edu.et / http://www.astu.edu.et

በሌላ በኩል የ2014 ዓ.ም አዲስ ገቢ አንደኛ አመት ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች፣ ምዝገባ ሚያዝያ 28 እና 29/2014 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመርበት ቀን እና በቅጣት የመመዝገቢያ ቀን ግንቦት 01/09/2014 ዓ.ም መሆኑ ተገልጻል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


AdditionalAmharaStudent.pdf
3.7Mb
#AmharaRegion

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ በሁሉም ዞኖች በጦርነቱ ምክንያት ተጨማሪ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ የተወሰነላቸው ተማሪዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

የተማሪዎቹ ዝርዝር ከላይ በPDF የተያያዘው ነው።

ምንጭ፦ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
@TIMIHIRT_MINISTER


እርስ በእርስ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ መቀያየር እንደማይቻል የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል

የትምህርት ሚኒስቴር በትናንት እለት የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ማደረጉ ይታወቃል።

መደባውን ተከትሎ ከዚህ ቀደም እንደነበሩ ጊዜያት ሁሉ አንዳንድ አካላት " ተማሪዎችን እና ወላጆችን ገንዘብ ክፈሉ ምደባ እናስተካክላለን ፣ ወደ ፈለጋችሁበት እንድትመደቡ እናደርጋለን " በሚል የማጭበርበር እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።

በሌላ በኩል አንዳንድ ተማሪዎች እና ወላጆች የዩኒቨርሲቲ እርስ በእርስ መቀያየር ይቻል እንደሆነ ጥያቄ አቅርበዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳሳወቀው ተማሪዎች ምደባን ተከትሎ ከማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ላይ ከተሰማሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ ፤ ምደባ እንቀይራችኃለን የሚሉትም ሀሰተኞች መሆናቸው እንዲሁም እርስ በእርስ ምደባ መቀያየር የሚባል ነገር እንደሌለ አስገንዝቧል።

በዚሁ አጋጣሚ ዩኒቨርሲቲዎች በአጭር ጊዜ ተማሪዎችን እንዲጠሩ አቅጣጫ በመቀመጡ ተማሪዎች እና ወላጆች አስፈላጊውን ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


የዩኒቨርሲቲዎችን ትክክለኛ ገፅ ብቻ በመከተል ከሀሰተኛ የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎች እራሳችሁን ጠብቁ ፦

👉 ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/DDUniv/

👉 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Hawassa.University/

👉 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Addis-Ababa-University-496255483792611/

👉 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/TheUniversityofGondar/

👉 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/bduethiopia/?ref=page_internal&mt_nav=0

👉 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/?_se_imp=0ueaW0ZojpEObV9zR

👉 ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/HRMUNIV/

👉 ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/JimmaUniv/

👉 አርሲ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=357578986410375&id=100064748293256

👉 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፦https://m.facebook.com/pages/category/Education-website/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

👉 ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/WachemoUniversity2008/

👉 ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/265529850297666/posts/1845133279003974/?app=fbl

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/141864125910414/posts/4794315817331865/?app=fbl

👉 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/pages/category/Education-website/Wollega-University-Corporate-Communications-2319182621440303/

👉 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/234983083247967/posts/5141798579233035/?app=fbl

👉 ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/2181225212102194/posts/3109977289226977/?app=fbl

👉 ቦረና ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/BoranaUniversityBRU/

👉 ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/pages/category/Education/Kebri-Dehar-University-306587496533329/

👉 ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/pages/category/Education/Jinka-University-178538809733160/

👉 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/547073878695780/posts/5065885566814566/?app=fbl

👉 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/1879460055640998/posts/3057857987801193/?app=fbl

👉 ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/WoldiaUniversity/

👉 ወሎ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/WolloUniversity111/

👉 ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/1301588393256101/posts/5145148712233364/?app=fbl

👉 ኦዳቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/OBUEthiopia/

👉 አምቦ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/AmboUniversityofficial/

👉 ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Mizan-Tepi-University-MTU-362390684253048/

👉 ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/614590095253065/posts/5432186613493365/?app=fbl

👉 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/979926502053136/posts/5129611493751262/?app=fbl

👉 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/336146983089022/posts/5029908297046177/?app=fbl

👉 ኮተቤ ፦ https://www.facebook.com/792405150779154/posts/5397052686981021/?app=fbl

👉 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/100064618752509/posts/386404006856888/?app=fbl

👉 መቱ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/330316734055129/posts/1468350973585027/?app=fbl

👉 መቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Mekdela.Amba.University/

ለሁሉም ተማሪዎች ሼር ያድርጉ
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ‼️

⚡ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።

⚡የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

⚡ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

⚡በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት በድህረገፅ፡-https://result.ethernet.edu.et ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ።

⚡ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድህረገፅ https://complaint.ethernet.edu.et በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

⚡ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ ያቀርባል፡፡©ትምህርት ሚ/ር
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


Forward from: Midroc Investment Group
የምስራች ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የፋሲካን በአል ምክንያት በማድረግ ለ500 ሰዎች ልዩ የሆነ የበአል ስጦታ አዘጋጅቷል። ወደ ግሩፑ ከ100 ሰው በላይ ያስገቡና ይሸለሙ።

አባላትን Add ለማድረግ የዚህን ግሩፕ ሊንክ ይጠቀሙ 👇 @Safaricom_Official_Group
@Safaricom_Official_Group

Add ያድርጉ በየቀኑ ይሸለሙ
©Safaricom_Ethiopia™
@safaricom_official_Channel


Forward from: Midroc Investment Group
🎉አሸናፊዎች በሽልማት ተንበሽብሸዋል። ምን ይጠብቃሉ እርሶም ወደ ግሩፑ ከ100 ሰው በላይ ያስገቡና ይሸለሙ።

የዚህ ሳምንት ውድድር ተጀምሯል። ከ100+ በላይ አባላቶችን ያስገቡና የሽልማቱ ተካፋይ ይሁኑ።

አባላትን Add ለማድረግ የዚህን ግሩፕ ሊንክ ይጠቀሙ 👇 @Safaricom_Official_Group
@Safaricom_Official_Group

Add ያድርጉ በየቀኑ ይሸለሙ
©Safaricom_Ethiopia™
@safaricom_official_Channel


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ጠቃሚ መልዕክት ለኢትዮጽያ ተማሪዎች

የትምህርት ሚኒስቴርሩ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ያስተላለፈው አጠር ያለ ጠቃሚ መልእክት ከላይ በቪዲዮ ተያይዟል። #ሼር
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ፤ ከክልሉ ተጨማሪ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የተወሰነላቸው 4339 ተማሪዎች በምን አግባብና ሂደት እንደሚመረጡ አሳውቋል።

4,339 ተማሪዎች 50 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ ካመጡ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች መካከል በውጤታቸው ቅደም ተከተል ይመረጣሉ ብሏል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሌሎች 50 ፐርሰንት እና በላይ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባት ያልቻሉት ደግሞ በክልሉ መምህራን ኮሌጆቾ በመደበኛው የዲግሪ ኘሮግራም የመምህርነት ስልጠና እንዲጀምሩ ሰፋ ያለ ቁጥር ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ቢሮው አሳውቋል።

ሌላው መግቢያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች በመደበኛ ተማሪነት በድጋሜ ፈተና ይወስዳሉ የተባለው ሁሉንም የክልሉን ተማሪዎችን የሚያካትት ሲሆን ይህም በልዩ ሁኔታ ለአማራ ክልል ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ወደ ዩኒቨርስቲዎች ሆነ ወደ መምህራን ኮሌጆቾ መግባት ያልቻሉት ተማሪዎች በቂ ዝግጅት አድርገው መፈተን እንዲችሉ የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል የፈተና ጊዜ እንዲራዘም ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

ትምህርት ሚኒስቴርም ቢሮው ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ከመስከረም 2015 ዓ/ም በፊት ፈተናው እንደማይሰጥ ትላንት መወሰኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልሉ ተማሪዎች የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 20 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ጊዚያት ሊሰጥ እንደሚችል አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ቢሮው አሳስቧል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER


" ከ4 ክልሎች ተጨማሪ 8,080 ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ "

የትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ይፋ ካደረገው ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ ካላቸው 152,014 ተማሪዎች በተጨማሪ 8 ሺህ 80 የሚሆኑ ተማሪዎችን ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደሚመድብ አሳውቋል።

ምንም እንኳን ጦርነት ሁሉንም ክልሎች በተወሰነ ደረጃ ተፅእኖ ቢያሳድርባቸውም ነገር ግን በተለየ ሁኔታ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የነበረው ሁኔታ በልዩነት እንዲታይ ተደርጓል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተጠቀሱት አራቱ ክልሎች ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያቸው ፥ " የጦርነት ስሜት የፈጠረው ነገር ተማሪዎችን ጎድቷቸው እንደሆነ አስተያየት የሚደረግበት መንገድ እንፈልግ በሚል የክልል ትምህርት ቢሮዎች ተስማምተው ለትምህርት ሚኒስቴር የሰጡት ስራ አስተያየት የሚደረግበት ሁኔታ ካለ እንዲፈለግ " የሚል እንደነበር አስረድተዋል።

በዚህም ፥ በፊት ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ከተቆረጠው ቁጥር 152 ሺ ተጨማሪ የሚገኝ ቁጥር ካለ ታይቷል ሲሉ ገልፀዋል።

በተለይም ፥ ከትግራይ ክልል መጥተው አራተኛ ዓመት ጨርሰው የሚወጡ ተማሪዎች ስለሚኖሩ የቅበላ ቦታዎችን ማግኘት ይቻላል በሚል ስራ ላይ ያሉት 43 ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን አቅም አሟጠው ወደ 8,080 ተማሪዎች የቅበላ ቦታ እንዳሳወቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የተገኘውን የተማሪ ቅበላ አቅም በፍትሃዊነት ለ4ቱ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት በተጎዱ ተፈታኞች መጠን እንዲከፋፈል መወሰኑንም አሳውቀዋል።

ምንም እንኳን የተገኘው የቅበላ ቦታ ለ4ቱ ክልሎች ይከፋፈላል ቢባልም በምን አግባብ እና መንገድ ተማሪዎቹ እንደሚለዩ እስካሁን በግልፅ የተብራራ ሆነ የታወቀ ነገር የለም።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER

20 last posts shown.