Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Politics


I didn't bit the land that feeds you!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Politics
Statistics
Posts filter


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የጎጃሟ ሞንጀሪኖ በዚህ ደረጃ ስታለቅስ መስማት አልፈልግም ነበር። ከመጀመሪያውም ያለ አቅሟ በማታውቀው ጉዳይ ነበር የገባችው። ለማንኛውም የአንቺም ሆነ የሌሎቻችሁ መጨረሻ ያማረ እንዲሆን እመኛለሁ። መንግሥትና ሕዝብ ያቀረበላችሁን መልካም ዕድል ተጠቀሙ። ካፈርኩ አይመልሰኝ ብላችሁ አጉል አትድከሙ። አታባክኑት።


የኢሰመጉ መታገድ የዘገየ ውሳኔ ነው። መታገድ የነበረበት ፋኖ ወደጫካ ሊወጣ ሲያሟሙቅ በታየበት ወቅት ነበር። ኢሰመጉ(ኢህአፓ ሰማያዊ መኢአድ ጎዴፓ) ጫካ ገባው ካለው ጃውሳ የሚለየው ክላሽ ታጥቆ በፎቶ ባለመታየቱ ብቻ ነው። በሌላ መልኩ ኢሰመጉ አሁን ላይ ሕልውና ያለው እናት ፓርቲ ማለት ነው። እናት ፓርቲ ኢሰመጉና ፋኖ አንድም ሶስትም ናቸው። ፋኖ ወደ ጫካ ሲወጣ ኢሰመጉና እናት ፓርቲ የከተማውን ግንባር ሸፍነው ጫካ ወጥቶ ለነበረው ጃውሳም በተቀናጀ መንገድ በመግለጫ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ሲያግዙ የቆዩ የፈነኑ አካላት ናቸው። በየጊዜው መረጃ ስንቅና ትጥቅ በማቀበል የሚችሉትን ሁሉ ድጋፍ ሲሰጡ ቆይተዋል። እስካሁን ያልሰጡት ድጋፍ ቢኖር የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ነው። እናም የኢሰመጉ መታገድ ዘገየ እንጅ ትክክል ነው። ደግሞ እሱ ያልታገደ ማንስ ይታገዳል? ለውጡን ተከትሎ የፖለቲካ ድርጅት ብቻ ሳይሆን የለየለት የነውጥ የትጥቅ ድርጅት ነው እኮ የሆነውም።


የሕዝብን ድምጽ የሰማና ያከበረ ይከበራል!!

በአዊ/ብሔ/አስተዳደር የሚገኘው ጀግናው ሕዝባችን አስተዳደር የአማራ ክልል መንግሥት ያለ መሰልቸት ደጋግሞ ላቀረበው የሰላም ጥሪ ጀሮ ሰጥተው ሕዝባቸውን ለመካስ ለተመለሱ ታጣቂዎች የጀግንነትን መንገድ መርጣችኋልና ክብር ይገባችኋል ብሎ በደማቅ አቀባበል ተቀብሎ የእራት ግብዣም አድርጎላቸዋል።
ይገባቸዋል። ምስጋና ለሁሉም ይገባል።

የወጡበትን ሕዝብ ድምፅ መስማት የሰላም መንገድን መምረጥ ጀግንነት ነው። በረሃ የመውጣቱ ምክንያትም ለራስ ጥቅምና ዝና አለመሆኑን ማረጋገጫም ነው።

ሰላም ለሁሉም!!


እንዲህ ነው አባቶችን ማክበር ለሽምግልና ቦታ መሰጠት የወጡበን ማህበረሰብ ለመካስ የሰላም መንገድን መርጦ መመለስ። ትግሌ ለወጣሁበት ማህበረሰብ ጥቅም ነበር ብሎ የሚያስብ ሃይል ያ ሕዝብ የሰላም ጥሪ ሲያቀርብለት የምናየው እንዲህ በአዊ/ብሔ/አስተዳደር ሲንቀሳቀሱ እንደነበሩ የታጠቁ ሃይሎች ምላሽ ይሆናል። ጀግኖች ናቸው!!!

ሰላም ለሕዝባችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!!


በአዊ/ብሔ/አስተዳደር በመንግስቱ ገነት የተባለ ፅንፈኛ ይመራ የነበረው ታጣቂ እስከ ቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ጨምሮ ከ62 ታጣቂ ከባላቱ ጋር የሰላም መንገድን መርጦ ተመልሷል። የሰላም መንገድን ለመረጣችሁ ጀግኖች ምስጋና ይገባችኋል።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ተራው ሰው አይደለም የፖለቲካ ኤሊት ከሚባለው በተለይ ደግሞ በተቃዋሚው ጎራ በአክቲቪዝሙ ከተሰማራው መካከል ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅምና ሐብት የማህበረሰቡን ስሪት ቀርቶ ያላትን ክልል በቅጡ የሚያውቀው ጥቂት ነው። አብዛኛው ወጣሁበት በሚለው ክልል ያሉ ዞኖችን እንኳ አያውቅም። ለዛ ነው ዋ የእኛ ችግር ቅድሚ ካልተሰጠ ወይም ካልተፈታ ወይም ካከረፍን ኢትዮጵያ ያልቅላታል የሚለው። ኢትዮጵያ ለእነሱ የወጡባትና ያች የሚያውቋት መንደር ብቻ ትመስላቸዋለችና።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በኢትዮጵያ ሕልውና እና ልዕልና አደጋ ሆኖ ለሚመጣ የትኛውም ምድራዊ ሃይል የማይንበረከከው ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለታላቅ ተልዕኮ እየተሰማራ ነው።


በሁሉም ክልል ብሔር አካባቢ በወያኔ ይመራ የነበረውን ፌኩን የፌደራሊስት ሃይል 1001% እንደ አደረጃጀት አከርካሪውን ሰብረን ውልቅልቁን አውጥተነዋል። መቼም እንዳይነሳ አድርገን ነው ድል የነሳነው። የሚቀረን በብልጽግና ፓርቲ እና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከዛሬ ነገ ከጥፋታቸው ይታረማሉ የበደሉትን ሕዝብና መንግሥት ይክሳሉ ተብለው ባላየና ባልሰማ ለጊዜው የታለፉና የተንጠባጠቡ (ዕድል ያገኙ) ተላላኪዎች ናቸው።እነሱም ቢሆን ለጊዜው መታለፉን እንደ አለማወቅ ወይም እንደ ድክመት የሚቆጥሩና በጥፋት መንገድ ለመረማመድ የሚሞክሩ፣ እውነተኛ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መቃብር ጠባቂዎች ሆነው ለመታየት የሚሞክሩና ይህን ወርቃማ ዕድል የማይጠቀሙበት ከሆነ በሚገባቸው ቋንቋ የሚዳኙ ይሆናል። ያኔ ሁሉም ነገር ግልጽ ሆኖ ይገባቸዋል።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ደባርቅ አልተቻለም!

ሰላም ለሕዝባችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!


በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ እና ደባርቅ ወረዳ ሲያሰለጥኗቸው የነበሩ የሚሊሻ አባላትን አስመርቀዋል።

ሰላም ለሕዝባችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!



11 last posts shown.