ታምሪን ሚዲያ(Tamrin Media)✍✍✍✍✍


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Introducing daily news and information all over the world including our country ethiopia
ለፈጣን እና ተዓማኒ መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ። 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ቻናላችንን በመቀለቀል ወቅታዊ መረጃዎቸችን በፍጥነት ያግኙ👇👇👇
https://t.me/Tamrinmedia
✉️inbox 👉 @tamrin_bot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


"እኔ ስታርሊንክን ባጠፋው የዩክሬይን የጦር ግንባር ይፈርሳል" ሲል ኤሎን መስክ ተናገረ፡፡

አሜሪካዊው ቢሊየነር አሎን መስክ ዛሬ ባሰፈረው መልእክት የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት መስጫ የሆነውን ስታር ሊንክ ለዩክሬይን ጦርነት ወሳኝ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የዩክሬይን ማናቸውም ወታደራዊ ግንኙነቶች የሚከናወኑት በእሱ ባለቤትነት በሚተዳደረው በዚሁ ስታር ሊንክ አማካኝነት እንደሆነም ገልጿል፡፡ መስክ በኤክስ ገፁ ላይ ‹‹እኔ ፑቲንን ከዩክሬይን ጋር በሚደረገው ጦርነት ፈትኜዋለሁ፡፡ እናም የእኔ ስታር ሊንክ ሲስተም ለዩክሬይን የጀርባ አጥንት ነው›› ካለ በኋላ ስታር ሊንኩን ቢያጠፋው የዩክሬይን የጦር ግንባር ሙሉ በሙሉ እንደሚፈራርስ አስረድቷል፡፡

ለአመታት በተደረገው በዚህ ጦርነት ዩክሬን ላታሸንፍ ነገር ይህንን በማድረጉና ሰዎች በመሞታቸው እንደሚፀፅተውም አስረድቷል፡፡ ጨምሮም ‹‹አሁን ሁሉም የሚመለከተው ሁሉ ይህ ሰው እየበላ ያለው ጦርነት እንዲቆም ማድረግ አለበት፡፡ አሁን ሰላም ያስፈልጋል›› ብሏል፡፡

ኤሎን መስክ ይህንን መልእክት ያሰፈው የዩክሬይኑን ፕሬዝደንት ዘለንስኪን ከሩሲያ ጋር የማያልቅ ጦርነት ማድረግ እንደሚፈልጉ ገልፆ ‹‹ጨካኝ›› ካላቸው ከቀናት በኋላ ነው፡፡ ሩሲያና ዩክሬይን ጦርነቱን ከጀመሩ ሶስት አመታት የሞላቸው ሲሆን በሁለቱም በኩል ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡


የኬኒያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለJesus Winner Ministry ለተሰኘ እምነት ተቋም የሰጠው 20 ሚሊዮን ሽልግ በናይሮቢ ተቋሞ አስነሳ።
https://t.me/Tamrinmedia


መረጃ ‼️

የኤርትራ ጦር ከሰሜን ምእራብ የነበረዉን ግዙፍ ሃይል ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል እያሰፈረ  መሆኑን የኤርትራ ሚዲያዎች ዘገቡ

በኤርትራ ከባለፈው ወር ጀምሮ ከፍተኛ የተባለ ወታደራዊ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ሜከናይዝድ ጦሩም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ፡፡

በሀገሪቱ በተላለፈዉ ወታደራዊ ትእዛዝ መሰረት ከብሄራዊ ጦር ተለይተዉ የነበሩ ተጠባባቂ ወታደሮች በፍጥነት ጦሩን እንዲቀላቀሉ መደረጉ ይታወሳል ፡፡

ወታደራዊ እንቅስቃሴዉ ሃገሪቱ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ጋር የቃላት ምልልስ እያደረጉ እንዳለ ይታወቃል ።
እውን ሁለቱ ሀገሮች ወደ ጦርነት ያመሩ ይሆን?ፈጣሪ በቃ ይበለን🙏🙏🙏🙏
https://t.me/Tamrinmedia


🖋የጊዜያዊ ወታደራዊ ደርግ መንግስት ስልጣን በያዘበት ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ላሉ ዋና ዋና
⏭️ የህዝብ መሰረተ ልማቶች (መንገድ፣ ድልድይ፣ አውሮፕላን ማረፊያ)፣
⏭️ የህዝብ ቦታዎች (አደባባይ፣ ጎዳና፣ ስታዲየም)፣ እና
⏭️ የህዝብ የጤና እና የትምህርት ተቋማት (ክሊኒክ፣ ሆስፒታል፣ ወታደራዊ ሆስፒታል፣ ዩኒቨርሲቲ፣ ወታደራዊ አካዳሚ)
ስያሜ ላይ የተደረጉ ለውጦች፤

🖋Changes to the names of major
⏭️ PUBLIC INFRASTRUCTURE (Road, Bridge, Airport)
⏭️ PUBLIC SPACES (Square, Avenue, Stadium), AND
⏭️ PUBLIC Healthcare & Educational FACILITIES (Clinic, Hospital, and Military Hospital, and University, Military Academy)
in Addis Ababa made by the Provisional Military Dergue Government when it came to power;

"ከዛሬ የካቲት 10 ቀን 1967 ዓ.ም ጀምሮ ስያሜአቸው የተቀየሩ ተቋማት ስያሜ። / Institutions whose names were changed starting from February 10, 1975 (Ethiopian Calendar)."

"የቀደሞ ስያሜ" "አዲሱ ስያሜ" / "FORMER NAME" "New Name":

1️⃣ አስፋወሰን ጎዳና / ASFA WOSSEN AVENUE
➡️ እንጦጦ ጎዳና / Entoto Avenue

2️⃣ እቴጌ መነን ጎዳና / ETEGE MENEN AVENUE
➡️ እድገት በህብረት ጎዳና / Idget Behibret Avenue

3️⃣ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ጎዳና / HAILE SELASSIE I AVENUE
➡️ አድዋ ጎዳና / Adwa Avenue

4️⃣ ልዕልት ፀሐይ ኃ/ሥላሴ ጎዳና / PRINCESS TSEHAI HAILE SELASSIE AVENUE
➡️ ባልቻ አባ ነፍሶ ጎዳና / Balcha Aba Nefso Avenue

5️⃣ ልዕልት ተናኘወርቅ መንገድ / PRINCESS TENAGNEWORK ROAD
➡️ ቢሃንኬ መንገድ / Bihanke Road

6️⃣ መስፍን ሐረር መንገድ / MESFIN HARAR ROAD
➡️ በላይ ዘለቀ መንገድ / Belay Zeleke Road

7️⃣ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ሆስፒታል / HAILE SELASSIE I HOSPITAL
➡️ የካቲት 12 ሆስፒታል / Yekatit 12 Hospital

8️⃣ መኮንን ሆስፒታል / MEKONNEN HOSPITAL
➡️ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል / Black Lion Hospital

9️⃣ ዘነበወርቅ ሆስፒታል / ZENEBOWERK HOSPITAL
➡️ ሥጋ ደዌ ሆስፒታል / Leprosy Hospital

🔟 ልዕለት ፀሐይ ሆስፒታል / PRINCESS TSEHAI HOSPITAL
➡️ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል / Armed Forces Hospital

1️⃣1️⃣ ልዕልት የሻሽወርቅ ክሊኒክ / PRINCESS YESHASHWORK CLINIC
➡️ መሐል ከተማ ክሊኒክ / Mehal Ketema Clinic

1️⃣2️⃣ ልዕልት ፀሐይ አደባባይ / PRINCESS TSEHAI SQUARE
➡️ ካሌብ አደባባይ / Kaleb Square

1️⃣3️⃣ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ አደባባይ / HAILE SELASSIE I SQUARE
➡️ እድገት አደባባይ / Idget Square

1️⃣4️⃣ ሚያዝያ 27 አደባባይ / MIYAZYA 27 SQUARE
➡️ መጋቢት 28 አደባባይ / Megabit 28 Square

1️⃣5️⃣ ኦሜድላ አደባባይ / OMEDLA SQUARE
➡️ አርበኞች መንገድ / Arbegnoch Road

1️⃣6️⃣ ልዑል መኮንን ድልድይ / PRINCE MEKONNEN BRIDGE
➡️ አርበኞች ድልድይ / Arbegnoch Bridge

1️⃣7️⃣ ልዕልት ዘነበወርቅ ድልድይ / PRINCESS ZENEBOWERK BRIDGE
➡️ ኮልፌ ድልድይ / Kolfe Bridge

1️⃣8️⃣ እቴጌ ድልድይ / ETEGE BRIDGE
➡️ አዲስ አበባ ቄራ ድልድይ / Addis Ababa Qera Bridge

1️⃣9️⃣ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ / HAILE SELASSIE I UNIVERSITY
➡️ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ / Addis Ababa University

2️⃣0️⃣ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ እስታዲየም / HAILE SELASSIE I STADIUM
➡️ አዲስ አበባ እስታዲየም / Addis Ababa Stadium

2️⃣1️⃣ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ አየር ማረፊያ / HAILE SELASSIE I AIRPORT
➡️ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ / Bole International Airport

2️⃣2️⃣ መስቀል አደባባይ / MESKEL SQUARE
➡️ አብዮት አደባባይ / Abiyot Square

2️⃣3️⃣ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ጦር አካዳሚ ት/ቤት / HAILE SELASSIE I MILITARY ACADEMY SCHOOL
➡️ ሐረር ጦር አካዳሚ ት/ቤት / Harar Military Academy School

2️⃣4️⃣ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ጦር ት/ቤት / HAILE SELASSIE I MILITARY SCHOOL
➡️ ገነት ጦር ትምህርት ቤት / Genet Military School

ቀን: 10/6/67 ዓ.ም / Date: 10/6/1975 (Eth.Cal)

PHOTO SHARED Via: ታሪክን ወደኋላ
https://t.me/Tamrinmedia


"የፈጠራ ክስ ቀርቦብኛል"- ኤርትራ‼️
ተመድ እና የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር ገብተው ጥቃት እየፈፀሙ መሆናቸውን ተከትሎ ያቀረበባትን ክስ ኤርትራ አስተባበለች።

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገ/መስቀል በx ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አውሮፓ ህብረት እና ተመድ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ተመሳሳይ እና የፈጠራ ክስ በኤርትራ ላይ መስርቷል ሲሉ ገልፀዋል።

በጄኔቫው ስብሰባ ላይ ኤርትራ በትግራይ ክልል ወረዳዎች ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየፈፀመች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ይሁንና ኤርትራ ክሱን የፈጠራ ክስ ነው ስትል አስተባብላለች።
https://t.me/Tamrinmedia
====================


ካናዳ የአሜሪካ 51ኛዋ ግዛት እንድትሆን የቀረበዉን ሀሳብ በመቃወም ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ነፃነታችንን ማስጠበቅ ቀዳሚ ስራችን ነው አሉ

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከንጉሥ ቻርልስ ጋር ካደረጉት ውይይት አስቀድመዉ እንደተናገሩት ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ነው ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካናዳ 51ኛው የአሜሪካ ግዛት እንድትሆን በቅርቡ ሀሳብ ካቀረቡ በኋላ ነዉ፡፡

ትሩዶ የካናዳ ርዕሰ መስተዳድር ከሆኑት ቻርለስ ጋር ከመገናኘታቸዉ በፊት ለዜጎች “ለሉዓላዊነታችን እና ለነፃነታችን ከመቆም” የበለጠ ጠቃሚ ነገር የለም ብለዋል።ትሩዶ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ከግርማዊነታቸው ጋር ተቀምጦ ለመወያየት በጉጉት እጠብቃለሁ፣ እንደተለመደው ለካናዳ እና ለካናዳውያን አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን፣ ለካናዳውያን ለሉዓላዊነታችን እና እንደ ሀገር ለነፃነታችን ከመቆም የበለጠ ጠቃሚ ነገር እንደሌለ እናገራለሁ” ብለዋል።

ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ባለፈው ወር እንደተናገሩት ትራምፕ ካናዳን ስለመጠቅለል የተናገሩት ንግግር “እውነተኛ ነገር ነው” እናም ከሀገሪቱ የበለፀገ የተፈጥሮ ሀብት ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።ትራምፕ ካናዳ 51ኛው የአሜሪካ ግዛት ለመሆን ከተስማማች የተሻለች ትሆናለች ሲሉ ደጋግመው ጠቁመዋል።

ትሩዶ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ትራም ስላደረጉት ውይይት ተጠይቀዉ ከዘለንስኪ ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል፡፡
https://t.me/Tamrinmedia


የግብፅ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርትራ ይገኛሉ

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት ማምሻውን በግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር በድር አብደላቲ የተመራው የግብፅ ልኡካን ቡድን ተቀብለዉ አነጋግረዋል። 

ሁለቱ ሀገራት ሰፊ ውይይቶችን አድርገዋል ያሉት የኤርትራ የመረጃ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ሲሆኑ በሁለቱ ሀገራት እንዲሁም በአህጉራዊ - የአፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባህር - የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ምክክር አድርገዋል ብለዋል።

ጥልቀት ከተሰጣቸዉ ጉዳዮች ዉስጥም በሶማሊያ የሀገር ግንባታ ላይ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር አካባቢዎች የሰላም እና የደህንነት ፈተናዎች በኤርትራ እና ግብፅ ባለስልጣናት ሰፊ ዉይይት መደረጉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር በድር አብደላቲ ለኤርትራ ዜና አገልግሎት በሰጡት አጭር መግለጫ እንደገለፁት በየወቅቱ የሚደረጉ ምክክሮች በቀጠናዊ ጸጥታና መረጋጋት ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋሞችን ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኤርትራ እና ግብፅ መሪዎች መካከል ከአስመራ ካይሮ የሚደረጉ ጉብኝቶች በርከት ብለዋል። የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደልፋታህ አልሲሲን ጨምሮ በርካታ የግብፅ ባለስልጣናት ወደ ኤርትራ ጉብኝት ሲያደርጉም ተስተዉሏል።

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር በባህር በር ስምምነት ጉዳይ ዉዝግብ ዉስጥ ከገባችበት ጊዜ አንስቶ የግብፅ የምስራቅ አፍሪካ እንቅስቃሴ እየተስተዋለ መጥቷል።
https://t.me/Tamrinmedia




ማስጠንቀቂያ :- 1ሚሊየን ብር ሊቀጡ ይችላሉ

አለማወቅ ከቅጣት አያድንም

👉 በባህሪው አደገኛ የሆነ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ በወንዝ ዳርቻ ያሰወገደ ድርጅት አንድ ሚሊዮን ብር ይቀጣል፣

👉 ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ወንዝ ላይ የጣለ ግለሰብ 500 ሺህ ብር ይቀጣል

👉 ፍቃድ የወሰዱም ሆነ ሳይወስዱ ፍሳሽን ቀጥታ በወንዞች ዳርቻ ሲያስወግዱ ቢገኙ 100 ሺህ ብር ይቀጣሉ፣

👉 በወንዝ ዳርቻና አካባቢ መጸዳዳት ሁለት ሺህ፤

👉 የፈሳሽ ማጣሪያ ሳይኖር በወንዝ ዳርቻና አካባቢ ተሽከርካሪ ማጠብ 400ሺህ ብር፤

👉 እንስሳትን ማሰማራት፣ ማስገባት ከተፈቀደው ውጪ ተሽከርካሪ ማሽከርከር 30 ሺህ ብር

👉 ለመዝናኛ፣ ለመናፈሻና ለፖርክ ከተፈቀደ ውጪ ግንባታ መገንባት 200 ሺህ ብር፤

👉 ከአምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማንኛውም ያልታከመ ቆሻሻ መልቀቅ 300 ሺህ ብር ያስቀጣል፣

👉 ኬሚካል ነክ ቆሻሻዎችን የማከሚያ ዘዴ ሳይጠቀም የለቀቀ ግለሰብ 50 ሺህ፤ ድርጅት 300 ሺህ ብር ይቀጣሉ፣

👉 ማንኛውም በካይ ቆሻሻ ከተፈቀደ የፈሳሽ ማጠራቀሚያ ውጪ ያፈሰስ ግለስብ 50 ሺህ ድረጅት 400 ሺህ ብር፤

👉 የአትክልትና ፍራፍሬ ተረፈ ምርቶችን በወንዝ ዳርቻ ማስወገድ ግለሰብ 20 ሺህ፣ ድርጅት 100 ሺህ፤

👉 ዘይት፣ ጨዋማ ፈሳሽ፣የሞተር ዘይት፣ ነዳጅ ሳሙና ነክ ነገሮችን በወንዝ ዳርቻ ያስወገደ 400 ሺህ ብር ይቀጣል፣

👉 ማንኛውም ያልተጣራ ቆሻሻ ወደ ወንዝ መልቀቅ ግለሰብ 150 ሺህ ድርጀት 300 ሺህ ይቀጣል፣

👉 ፍቃድ ሳይሰጠው ያልታከመ ቆሻሻን ወደ ወንዝ ያስወገደ ግለሰብ 15 ሺህ ብር ድርጅት 40 ሺህ ብር ይቀጣል፣

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
https://t.me/Tamrinmedia


መረጃ :-

በሳውዲ ዛሬ ጨረቃ ሰለታየች የመጀመሪያ
ረመዳን ቀን ነገ ቅዳሜ ይጀምራል ተብሏል::
https://t.me/Tamrinmedia


እነ ዮሃንስ ዳንኤል ( ጆን ዳንኤል) የፍር ቤት ውሎ

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል ( ጆን ዳንኤል) እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ

) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል እንዲከላከሉ ብይን ሰጠ።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ላይ በነሐሴ 16 ቀኔ 2016 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 3፡30 ሰዓት ላይ ከአበባ ከተማ ወደ መቐለ ከተማ ለመጓዝ አውሮፕላኑ ለበረራ ዝግጁ ቢሆንም የአየር ሁኔታ ለበረራ አዳጋች በመሆኑ በረራው ቢደረግ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የሚያደርሰውን ከባድ አደጋ ለመከላከል ጉዞው ተሰርዞ መንገደኞች ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ሲነገራቸው በረራው በግድ መደረግ አለበት፤ አውሮፕላኑ ይከስከስ፤ አንወርድም በማለት ቀሪ ተሳፋሪዎችም እንዳይወርዱ በመክልከል አሳድመዋል በሚል በዝርዝር ጠቅሶ ክስ አቅርቦባቸው ነበር።

በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ 1ኛ ተከሳሽን ጆን ዳንኤል በተባለ ተከሳሽ ላይ በ3ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፍ ቲክቶክ በተባለ ማሀበራዊ ሚዲያ በተንቀሳቃሽ ምስል ቀርጾ በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር።

በዚህ መልኩ ተከሳሾቹ የክስ ዝርዝሩ ከደረሳቸው በኋላ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ከማረሚያ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ተከታትለዋል።

ተከሳሾቹ "የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምንም" በማለት የዕምነት ክህደት ቃላቸውን በመስጠታቸው ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች ቃል አሰምቷል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ዛሬ በዋለው የችሎት ቀጠሮ ሁሉም ተከሳሾች በ1ኛ ክስ ማለትም በወንጀል ህግ አንቀጽ 504 መሰረት እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።

ሁለተኛውን ክስ በሚመለከት ፍሬ ነገሩ በአንደኛ ክስ ተጠቃሎ የተገለጸ በመሆኑ ተከሳሾቹን በሁለተኛ ክስ ነጻ በማለት በአንደኛው ክስ ብቻ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ጆን ዳንኤል የተባለው 1ኛ ተከሳሽን በተደራቢነት በቀረበበት በ3ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፍ በሚለው ክስ እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን የመከላከያ ማስረጃ ለመጠባበቅ ለመጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጥሯል።
https://t.me/Tamrinmedia


መንታ ልጆች አረገዘች ፣

ግራድ ፒ አዲሷ ሚስቱ መንታ እንዳረገዘችለት ይፋ አደረገ!
https://t.me/Tamrinmedia


ካሪም ቤንዜማ ለመቄዶኒያ ድጋፍን ሊያደርግ ነው !
📌 የቤንዜማ የግል አውሮፕላን ረዳት አብራሪው 5ሺህ ዶላር ለግሷል።

በስፔን ላሊጋ የነገሰው እና በሪያል ማድሪድ መለያ የደመቀው በዋንጫ ያቆጠቆጠ ታሪክን ያፃፈው በአሁኑ ሰአትም ለሳውዲው ክለብ አሊትሀድ እየተጫወተ የሚገኘው ፈረንሳዊው አጥቂ ካሪም ቤንዜማ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ህሙማን ማዕከል ልገሳን ሊያደርግ ነው።

የተጫዋቹ የግል አውሮፕላን ረዳት አብራሪ የሆነው ኢትዮጵያዊው አቤል ወይም ጆንሰን ግን በግሉ ለመቄዶንያ የ5 ሺህ ዶላር ድጋፍን ዛሬ አድርጓል።
https://t.me/Tamrinmedia


የመሬት መንቀጥቀጥ‼️
በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 5:29 በአዲስ አበባና በሌሎች የተለያዩ አከባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.75 መመዝገቡን ዘገባዎች ያመላክታሉ።
https://t.me/Tamrinmedia


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ለመኖር የሚያስችል ፈቃድ በ5 ሚሊየን ዶላር ለሽያጭ አቀረቡ።

ከዚህ ቀደም ከሚታወቀው አረንጓዴ ካርድ (የመኖሪያ ፈቃድ) ጋር የሚስተካከለውና 5 ሚሊየን ዶላር የመክፈል አቅም ላላቸው የሚቀርበው ወርቃማው ካርድ በቀጣዮቹ ቀናት ለገዥዎች ክፍት ይሆናል።
ወርቃማው ካርድ በሂደት የአሜሪካ ዜግነትንም ያስገኛል ተብሏል።
የአረንጓዴ ካርድ ዕጣ ፈንታን በተመለከተ ፕሬዝዳንቱ አስተያየት አልሰጡም። ስለጉዳዩ የሚያውቁ ግን ፕሬዝዳንቱ አረንጓዴ ካርድን የመገደብ ፍላጎት አላቸው። አዲሱ ወርቃማ ካርድ ተሽጦ የሚገኘው ገንዘብ የአሜሪካን የበጀት ጉድለት ለሟሟላት ይውላል።
https://t.me/Tamrinmedia


የዲጂታል ስክሪን ማስታወቂያ ባለቤቶች ከነገ ጀምሮ የብልፅግና ፓርቲ ማስታወቂያን በግዴታ እንዲያሳዩ ሊደረጉ መሆኑ ታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የዲጂታል ስክሪን ማስታወቂያ ባለቤቶች እና ህንፃዎቻቸው ላይ የማስታወቂያ ስክሪን የገጠሙ ባለሀብቶች ከነገ ጀምሮ የብልጽግና ፓርቲ መልእክት የሆኑ ምስሎችን እና ጽሁፎችን በአስገዳጅነት እንዲያሰራጩ ጥብቅ ትዕዛዝ እንደተላለፈላቸው ታውቋል።

በራሳቸው ወጪ አውጥተው የሰሩትን የዲጂታል ስክሪን ለፖለቲካ ፓርቲ መልዕክት ማስተላለፊያ መደረጉ በህዝብ ዘንድ ለአንድ ወገን ያደሉ ወይም የፓርቲ አባል እንደሆኑ እንዳይወሰድባቸው የሰጉት ግለሰቦቹ አማራጭ እንዳጡ እና አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ ተናግረዋል።

የብልጽግና ሹሞች ቁጣ በተቀላቀለበት መልዕክት በአስገዳጅነት ማስታወቂያውን ከነገ ጀምሮ ለማሰራጨት እንዳስገደዷቸው ጨምረው ተናግረዋል።

"ከሳምንት በፊት ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ መሪዎች ሲመጡ 'እንኳን ደህና መጣችሁ' የሚልና ስለ አፍሪካ ህብረት ስብሰባ ተመሳሳይ ትዕዛዝ ተላልፎ  ያስተላለፍነው የፖለቲካ ይዘት የሌለው በመሆኑ ነበር" የሚሉት የማስታወቂያ ድርጅቶቹ "አሁን የታዘዝነው የፖለቲካ ፓርቲ  መልእክት ገበያው በተዳከመበት መሀል ከህዝቡ ጋር እንዳያቃቅረን ስጋት አለን" ብለዋል።

በሌላ በኩል በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ወቅት በርካታ የመኪና ኪራይ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ተሽከርካሪዎቻቸውን በነፃ ለስብሰባው አገልግሎት እንዲሰጡ ተገደው እንደነበር ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

"ቢዝነስ በተዳከመበት በዚህ ወቅትም ይሁን ድሮ በአመት አንዴ ጥሩ ስራ የምንሰራው እንደ አፍሪካ ህብረት ያሉ ስብሰባዎች ሲመጡ ነበር" የሚሉት የመኪና አከራዮቹ አሁን ግን እሱንም በግዴታ እንደተነጠቁ እና መኪናዎቻቸው የተመለሱላቸው ስብሰባው ካለቀ በኋላ መሆኑን አስረድተዋል።

via# መሠረትሚዲያ !
https://t.me/Tamrinmedia


ሶማሊላንድ‼️
ከሳምንት በፊት የሶማሊያ ራስ ገዝ የሆነችዉ ፑንትላንድ በርካታ ኢትዮጵያዊያንን በቁጥጥር ስር አውላ ወደ ሀገራቸው መላኳን ማስታወቋ ይታወሳል‼️
ዛሬ እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ የሶማሊላንድ መንግሥት ፖሊስ በሃገሪቱ በተለይም በዋና ከተማዋ ሀርጌሳ የሚኖሩ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የገበያ ማዕከላትን ጨምሮ ከተለያዩ ሥፍራዎች በቂጥጥር ስር በማዋል ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ መጠነሰፊ ዘመቻ መክፈቱ ታውቋል።
https://t.me/Tamrinmedia

17 last posts shown.