ሕግ አገልግሎት/ Legal Services


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Law


እንኳን በደህና መጡ 🙏
ሳሙኤል ግርማ Lawyer
የሕግ አማካሪና ጠበቃ
☎️ +251-911-190-299
🌐 https://samuelgirma.com
@SAMUELGIRMA
@tebeka
@ethiopian_law
አድራሻችን 👇
https://maps.app.goo.gl/NGqgq9A7qD41QBLS8
#ህግ #ጠበቃ #legalservice #ሳሙኤልግርማ #samuelgirma #lawyer #ውል #ውክልና

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Law
Statistics
Posts filter


Forward from: Lawyer 🇪🇹 (ልዩ)
1002-2024.pdf
404.1Kb
☄️ #NGO

ስለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ክትትል፣ ቁጥጥር እና ምርመራ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1002/2016

Directive on monitoring, control, and investigation of civil society organization No.1002/2024



ሳሙኤል ግርማ የሕግ አማካሪና ጠበቃ
☎️ +251-911-190-299

Join 👉 @tebekaSamuel

#Ethiopia 🇪🇹

👉 t.me/+7pFEj9nvtxNjNmM0
👉 t.me/+7pFEj9nvtxNjNmM0

Join us on 🔽

👉 @ethiopian_law
                                        
👉 @tebeka

#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #law #civilsociety


211694 (1).pdf
915.5Kb
የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሕግ.pdf
1.5Mb
ባንኮች በመያዣ የተያዘን ንብረት በራሳቸው የመሸጥ መብት የተሰጣቸው ሲሆን መብቱ ግን  ገደብ የሌለው (absolute right) አይደለም ሰ/መ/ቁ. 211694


‼️ውልና ማስረጃ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን ለመወሰን በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 543/2016 መሰረት የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ከሰኞ ሚያዚያ 7ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ተግባራዊ ያደርጋል።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት

ሳሙኤል ግርማ የሕግ አማካሪና ጠበቃ
☎️ +251-911-190-299

Join 👉 @tebekaSamuel

#Ethiopia 🇪🇹

👉 t.me/+7pFEj9nvtxNjNmM0
👉 t.me/+7pFEj9nvtxNjNmM0

Join us on 🔽

👉 @ethiopian_law
                                        
👉 @tebeka

#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #law #construction

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

31.3k 2 221 1 144

የግንባታ_ሥራዎች_ይፋዊ_ቀጥተኛ_ዋጋ_ተመን.pdf
21.0Mb
‼️በ2016 ዓ.ም የ 3ኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (3rd Quarter Construction Works of Direct Cost)

✔️በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

✔️በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።

#Ethiopia 🇪🇹

👉 t.me/+7pFEj9nvtxNjNmM0
👉 t.me/+7pFEj9nvtxNjNmM0

Join us on 🔽

👉 @ethiopian_law
                                        
👉 @tebeka

#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #law #construction

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ




Directive to Regulate Foreign Investors.pdf
720.9Kb
Directive to Regulate Foreign Investors




አዲሱ_የቤት_ሽያጭ_ዋጋ_ተመን_አሰራር_እና_ታክስ_አገልግሎት_ክፍያ_ማንዋል_ቁ_01_2016_watermark.pdf
1.2Mb
🆕 አዲሱ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን አሰራር እና ታክስ አገልግሎት ክፍያ ማንዋል ቁጥር 01/2016

በአዲስ አበባ ከተማ ለአፓርትመንት ቤቶች እና ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

በተሻሻለው  የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦

➡️ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣

➡️ በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣

➡️ የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣

➡️ G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡

የቦታው መገኛ ዋጋ ('location value') ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል።

የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከ ከመጋቢት17 ቀን 2016 ዓ/ም  ጀምሮ እንዲከፈልም ታዟል።

ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።

ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ያሳወቃል።

#Ethiopia 🇪🇹

Contact: @SamuelGirma

☎️ 0911-190-299


👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn

Join us on 👇

👉 @ethiopian_law
                                        
👉 @tebeka

#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #ጠበቃ #law

📊📊




ከማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ የመንደር ውል ህጋዊ የሚሆንባቸው 5/አምስት/ ሁኔታዎች (Abraham Yohanes)

✅ የማንይቀሳቀስ ንብረትን ለማስተላለፍ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል በ ፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ካልተደረገ ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን ከተወሰኑ የሰበር ችሎት ውሳኔዎች በመነሳት የመንደር ውል ህጋዊ ተብለው የሚቆጠሩበት ሁኔታዎች አሉ። እነዚህ 5 ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው።

❶ኛ የሽያጭ ውል መኖሩ ከታመነ ወይም ካልተካደ

✅ ገዢ ውል እንዲፈፀምለት ክስ አቅርቦ ከሳሽ መከላከያ መልሱ ላይ በመካከላቸው ውል መኖሩን ካመነ ወይም ካልካደና በሌሎች ነጥቦች ላይ መልስ ከሰጠ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ውሉ በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት አልተደረገም ብሎ ውድቅ ሊያደርገው አይችልም።

❷ኛ በማህበር በመደራጀት የተሰራ ቤት በሽያጭ ማስተላለፍ (ሰ/መ/ቁጥር 36294 ቅፅ 8)

✅ በማህበር በመደራጀት እየተሰራ ያለ ቤት ቤቱ ተጠናቆ ካርታ እስኪወጣለት ድረስ የማህበሩ አባል የሆነ ሰው ይህን ቤት ቢያስተላልፍ ቤት የመስራት መብቱን ወይም እጣውን እንዳስተላለፈ እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረትን እንዳስተላለፈ አይቆጠርም። የማህበሩ አባል በስሙ ካርታና የባለቤትነት ማስረጃ እስካልተሰጠው ድረስ ቤቱ ወይም እየተሰራ ያለው ቤት በማህበሩ አጠቃላይ ይዞታ ስር የሚገኝ በመሆኑ የማህበሩ አባል ለ 3ኛ ወገን ሊያስተላልፍ የሚችለው እጣውን ወይም ጥቅሙን እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት አይደለም። እንዲህ አይነት ውሎች የግድ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ሊረጋገጡ አይገባም።

❸ኛ ያልነበረን ቤት ሰርቶ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል (ሰ/መ/ቁጥር 32222 ቅፅ 7)

✅ ብዙን ግዜ እንዲህ አይነት ውል ከ Real Estate ቤቶች ግንባታ ጋር የተያያ ነው። ምንም እንኳን ውላቸው ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ቢሉም ዉሉ በሚደረግበት ግዜ ቤቱ ያልነበረ በመሆኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ከአንዱ ወደ ሌላው ተላልፏል ሊባል አይችልም። ያልነበረን ቤት ሰርቶ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል የግንባታ ውል እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ሊባል የሚችል ባለመሆኑ ውሉ በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መረጋገጥ አይኖርበትም።

❹ኛ አዋዋይ ፊት ቀርቦ ነገር ግን አስተዳደራዊ ወይም የፕሮቶኮል ጉዳዮች ለተወሰነ ግዜ ሳይፈፀምበት የቆየ የመንደር ውል (የሰ/መ/ቁጥር 36740 ቅጽ 8)

✅ ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ በሰጠው ውሳኔ መሠረት በግራ ቀኙ መሀከል የተደረገው የመንደር ውል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ ነገር ግን አስተዳደራዊ ወይም የፕሮቶኮል ጉዳዮች የተሟሉት የተወሰነ ግዜ ከቆየ በኋላ ቢሆንም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰው አካል ፊት ያልተደረገ ነው በሚል ውድቅ ሊደረግ አይገባም የሚል ነው።

✅ ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ እንዳለው ቤቱን የሚመለከቱ እዳና እገዳ ለማጣራትና ክፍያ ለመፈፀም የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በውል ላይ ማህተም ሣያሣርፍበትና የፕሮቶኮል ቁጥር ሰጥቶ ሣያረጋግጥበት የተወሰነ ጊዜ ያለፈ ቢሆንም እነዚህ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እስኪከናወኑ ድረስ በውል ላይ ማህተም ሣያርፍበት መቆየቱ ወይም የፕሮቶኮል ቁጥር ሣይሰጠው መዘግየቱ ውል እንዳልተደረገ የሚያስቆጥረው ነው ለማለት አያስችልም፡፡

❺ኛ የሊዝ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል (የሰ/መ/ቁጥር 191095 & 225796)

✅ በሊዝ የተገኘ ይዞታ ላይ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት ወይም ተጀምሮ በግማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የሊዝ መብት ዘመኑ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በቦተው የመጠቀም መብትን ማስተላለፍ ይቻላል። ነገር ግን የሚተላለፈው በቦታው ላይ ግማሽ ግንባታ ከተከናወነ በኋላ ከሆነ በቦታው ላይ የመጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን በቦታው ላይ ከተሰራው ህንፃ ጭምር በመሆኑ የሊዝ መብት ማስተላለፍ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንደ ማስተላለፍ ይቆጠራል። ስለዚህ ሁለት ነገር መታየት ይኖርበታል። የመጀመሪያው አንድ ሰው መሬት በሊዝ ወስዶ ምንም አይነት ግንባታ ካልፈፀመበት ወይም ግንባታ ጀምሮ በግማሽ ከማጠናቀቁ በፊት የሊዝ መብቱን በመንደር ውል ማስተላለፍ ይችላል። ሁለተኛው የግንባታው ደረጃ ግማሽና ከዛ በላይ የደረሰ ከሆነ ግን የሚተላለፈው በቦታው ላይ የመጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን በቦታው ላይ የተገነባውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ጭምር በመሆኑ ውሉ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ መረጋገጥ ይኖርበታል።

39.9k 1 143 1 137

Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደርን በተመለከተ ⚠️

#Ethiopia 🇪🇹

አዲሱ የቤት ኪራይ ሕግ #PDF 👇

👉 @t.me/tebekasamuel/2808
👉 @t.me/tebekasamuel/2808

#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #ጠበቃ
#law #samuelgirma

⚡️



44.8k 1 113 1 109



‼️ በአዲስ አበባ የመሬት አገልግሎት ስለመጀመሩ 🆒

#Ethiopia 🇪🇹

👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn

Contact: @samuelgirma

Join us on 👇

👉 @ethiopian_law
                                        
👉 @tebeka

#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #law #samuelgirma

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


የቤት ኪራይ .pdf
3.4Mb
‼️ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016

#Ethiopia 🇪🇹

Contact : @samuelgirma

☎️ 0911-190-299

👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn

Join us on 👇

👉 @ethiopian_law
                                        
👉 @tebeka

#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #law #samuelgirma

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


ሰ-መ-ቁ 235844.pdf
267.4Kb
ከጋብቻ በፊት የተፈራ ንብረት የተጋቢዉ የግል ሀብት ሲሆን፣ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ሊሆን የሚችለዉ በገዛ ፍቃዳቸዉ በሚያደርጉት የጋብቻ ዉል የጋራቸዉ እንዲሆን የተስማሙ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ በቤተሰብ ህጉ አዋጅ 213/92 አንቀጽ 42፣ 57 እና 85 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡

የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ (የምስክር ወረቀት)፣ አንድ ሰዉ በአንድ ንብረት ላይ ያለዉን መብት ለማረጋገጥ ሲባል በማስረጃነት የሚሰጥ እንጂ በእራሱ መብትን የሚፈጥር አይደለም፣

የማይንቀሳቀስ ንብረት (መኖሪያ ቤት) ስመ ሀብቱ የተመዘገበው በባልና ሚስት ስም ቢሆንም አንደኛው ተጋቢ ንብረቱ የግሉ መሆኑን ማስረዳት ከቻለ ንብረቱ የግል እንጂ የጋራ ሀብት አይደለም።


#Ethiopia 🇪🇹

👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn

Join us on 👇

👉 @ethiopian_law
                                        
👉 @tebeka

#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #ባልናሚስት #Marriage #law #Family #samuelgirma #ቤተሰብ

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

63.2k 1 254 2 282

የንግድ ቤት ኪራይ ውል ስምምነት.docx
14.1Kb
ቤት ኪራይ ዉል .docx
16.2Kb
የብድር ውል..docx
10.8Kb
የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል .pdf
185.1Kb
🔔 የውል ስምምነቶች

👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ጠበቃ #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba ውል ስምምነት #samuelgirma #law

Follow Us On WhatsApp

17 last posts shown.