Temari Podcast - ተማሪ ፖድካስት


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Education


የዩቲዩብ ቻናላችን መቀላቀል አትርሱ 👇👇👇
https://youtube.com/@temari_podcast?si=--vADFvenliwbocx

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Education
Statistics
Posts filter


የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT)

የ2017 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ዓመት ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ከጥር 7-9/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

👉For Registration: https://ngat.ethernet.edu.et/login

@Temari_podcast


#Wolaita_Sodo_University

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፡-

በ2017 የትምህርት ዘመን ከኢ. ፌ. ዴ. ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች የ2017 የትምህርት ዘመን መግቢያ ቀን ታህሳስ 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን እናስታዉቃለን፡፡

👉 ማሳሰቢያ 1

1.ምዝገባ (በአካል ቀርበው) ታህሳስ 21 እና 22 ቀን 2017 ዓ.ም
2.አጠቃላይ ገለፃ (orientation) ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
3.ትምህርት የሚጀመረው ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

👉 ማሳሰቢያ 2

ሁሉም ተማሪዎች ሲመጡ፡-
1.የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት (ዋናው እና ኮፒው)
2.ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ
3.አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

👉 ማሳሰቢያ 3
ከA አልፋበት አስከ Z ድረስ የስማችሁን የመጀመሪያ ፊደል በማየት በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ የተመደባችሁበትን ካምፓስ ከምስሉ በመለየት እንድትመዘገቡ፣ ገለፃ ላይ እንድትሳተፉ እና ትምህርት እንድትጀምሩ ዩኒቨርሲው ያሳስባል፡፡

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

👉 የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

@Temari_podcast
@Temari_podcast


በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

📘 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ ቀናት  ጥር 01 እና 02/2017 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል። የምዝገባ ቦታለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ መሆኑንም ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳውቋል።

📘 ቦረና ዩኒቨርሲቲ - በ2017 ዓ.ም ወደ ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 22 23/2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ብቻ በመሆነ· በተባለዉ ቀን ቦረና ዩኒቨርሲቲ ግቢ ዉስጥ በመገኘት ምዝገባ እንድታካሄዱ ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

📘 ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ - በ2017 ዓ.ም ወደ ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም ሲሆን የማመልከቻ ቀን ጥር 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡


#BorenaUniversity

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም ወደ ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 22 23/2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ብቻ በመሆነ· በተባለዉ ቀን ቦረና ዩኒቨርሲቲ ግቢ ዉስጥ በመገኘት ምዝገባ እንድታካሄዱ ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

https://t.me/Temari_podcast
https://t.me/Temari_podcast


#DiredawaUniversity

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም ወደ ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም ሲሆን የማመልከቻ ቀን ጥር 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

https://t.me/Temari_podcast
https://t.me/Temari_podcast


#UniversityofGonder

በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ ቀናት 👉 ጥር 01 እና 02/2017 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል።


የምዝገባ ቦታ፡- ለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ መሆኑንም ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳውቋል።

https://t.me/Temari_podcast
https://t.me/Temari_podcast






#BahirDarUniversity

በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ ከጥር 5-7/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግሽ አባይ ግቢ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@Temari_podcast
@Temari_podcast


የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና

የኦሮሚያ ት/ት ቢሮ ላይ ከ4 ቀን በፊት እንደጻፈው በሰማያዊ ከለር የተከበበት
"የዘንድሮ ፈተና
🔹 Grade 9 & 10: old curriculum
🔹 Grade 11 & 12: new curriculum
እንደሆነ እና ተማሪዎች ለእዚህ እንዲያዘጋጁ" ተናግሯል

@Temari_podcast
@Temari_podcast


Upcoming video ቻናላችን ሰብስክራይብ አድርጋችሁ ጠብቁ 👇👇

https://youtube.com/@freshman_tricks?si=S-CjNc7qdA_UMxv4


#HaramayaUniversity #Remedial

በ2017 ዓ.ም. በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ በ2017 ዓ.ም. ትምህርት ዘመን በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች በጥር 02፣ 03 እና 04፣ 2017 ዓ.ም. ሀረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ግቢ በአካል ተተኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው ገልጿል።

#ማሳሰቢያ
1ኛ. የህብረተሰብ ሳይንስ ተማሪዎች በቨተርነሪ (Veterinary) ካምፓስ እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ (Technology) ካምፓስ ሪፖርት የምታደርጉ መሆኑን እናሳውቃለን።

2ኛ. ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ትምህርት ያጠናቀቃቸሁበትን ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ከፍል ሰርትፍኬት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ 4 ፓስፖርት መጠን ያላቸው ጉርድ ፎቶ እንዲሁም በማስታወቂያው የተጠቀሱ የግል መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን ይዛቹህ እንድትሄዱ ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳስቧል።

ተማሪዎች የዶርም ምደባችሁን ከዩንቨርሲቲው ዌብሳይት (www.haramaya.edu.et) ላይ በመግባት መለያ ቁጥራችሁን ተጠቅማቹህ መመልከት ትችላላቹህ።

@Temari_podcast


የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጀኔራል ዋቁ ጉቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።
----------------------//--------------

(ታህሳስ 03 / 2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የሚገኘውን ጀኔራል ዋቆ ጉቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት የሚፈልገው ጥረት መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ተማሪዎች ጠንክረው መማርና ማጥናት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በትምህርት ሥርዓቱ የፈተና አስተዳደር ስርዓቱን ማስተካከል ያስፈለገው የትምህርት ጥራት እንዲሻሻልና ሀገር የሚረከቡ እውነተኛ ዜጎችን ለማፍራት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።

ኩረጃ ለጊዜው የሚጠቅም ሊመስል ይችላል ነገር ግን ሄዶ ሄዶ ራስንም ሀገርንም ይጎዳል ያሉት ሚኒስትሩ ኩረጃን የሚጸየፉ በራሳቸው የሚሰሩና የሚተማመኑ ተማሪዎች መሆን እንዳለበቸውም አሳስበዋል።

የትምህርት ጥራት እንዲሻሻልና ትውልዱ ይህችን ሀገር የመገንባት የወደፊት ሀላፊነቱን በታማኝነት እንዲወጣ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት በትምህርት ሴክተሩ እየተከናወኑ መሆኑንም አብራርዋል ።

አክለውም ነገ ብቁ ሀገር ተረካቢ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ተማሪዎች ትምህርታቸው ላይ ብቻ አተኩረው እንዲማሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


https://t.me/Temari_podcast
https://t.me/Temari_podcast


#Ad
ሽልማቱ ዛሬ ድረስ እንደቀጠለ ነው ።
ዘወትር ምሽት 03:00 የ 50 ብር ካርድ የሚለቀቅበት ቻናል 👇👇👇

@Habesha_Gebeya1
@Habesha_Gebeya1




Upcoming video stay tuned on our you tube channel 👇👇

https://youtube.com/@temari_podcast?si=zwnt4Q7vAHCNOTHv


የተማሪዎች የምግብ ሜኑ‼️
ከዘንድሮው አመት ጀምሮ በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎች የሚቀርበው የምግብ ሜኑ ይፋ ተደርጓል።
ዝርዝር መረጃ ከላይ ከተቀመጠው ምስል ይውሰዱ።

https://t.me/Temari_podcast
https://t.me/Temari_podcast




#ትምህርት_ሚኒስቴር

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ በድጋሜ እገዳ ተጣለባቸው፡፡

ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ከጥቅምት 4/2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውንና በትግበራ ወቅት ክፍተት የታየበት "የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ" በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

በዚህም ማሻሻያው ተጠናቆ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከሚላክ ድረስ በሁሉም ተቋማት የፕሮፌሰርነት ዕድገት አሰጣጥ ለጊዜው መታገዱን ሚኒስቴሩ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ለተቋማቱ በጻፈው ደብዳቤ ገልጾ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ "አንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክልከላውን በመጣስ፣ መመሪያውን ባልተከተለ፣ ግልጽነት በጎደለው፣ ወጥነት በሌለው እና ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ሪፎርሞች ጋር በሚጣረስ መልኩ የፕሮፌሰርነት ዕድገት መስጠት መቀጠላቸውን ለመረዳት ችለናል" ብሏል በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ተፈርሞ ለተቋማቱ የተላከ ደብዳቤ።

ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው የገለፀው ትምህርት ሚኒስቴር፤ የተቋማቱ ከፍተኛ አመራር አካላት እና የሥራ አመራር ቦርድ የተሻሻለው መመሪያ ተጠናቅቆ እስኪደርሳችሁ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

@Temari_podcast


ፌስቡክ የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው አስታወቀ
***************

ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የፌስቡክ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ተጠቃሚዎች ችግር እንዳጋጠማቸው በተለያየ ሁኔታ ሲገልፁ ተስተውሏል።

በሜታ ኩባንያ ስር የሚንቀሳቀሰው የፌስቡክ መተግበሪያም የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው በራሱ ገፅ ላይ ለተጠቃሚዎቹ ይፋ አድርጓል።

ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር በአፋጣኝ ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለፀው ተቋሙ፤ ለተፈጠረው ችግር ተጠቃሚዎቹን ይቅርታም ጠይቋል።

https://t.me/Temari_podcast
https://t.me/Temari_podcast

20 last posts shown.