TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Tsegaye R Ararssa

18 Mar, 09:32

Open in Telegram Share Report

የተለወጠ የኃይል አሰላለፍ የለም፣ የክፋት ኃይሎች ጥምረት መፈራረስ እንጂ!
==========
በአሁኑ ሰዓት አንዳንድ ሰዎች፣ "የኢትዮጵያ ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ተቀይሯል" ይላሉ። አልተቀየረም።

የሚከተሉትን ምክንያቶች ማንሳት ይቻላል፦

1. የኃይል አሰላለፍ አለ ለማለት በተፋላሚዎች መካከል አዲስ የተፈጠረ የአመለካከት/የመስመር ለውጥ ሲኖርና ከዚህም የተነሳ ከአንደኛው ካምፕ ወደ ሌላኛው ካምፕ የመዝለል ሁኔታ ሲከሰት ነው። እስካሁን ደግሞ፣ አብይና ብልጥግና አቋማቸውን አልቀየሩም፣ ፕሮግራማቸውን አላሻሻሉም፣ ራዕይ፣ መሻትና ህልማቸውን አልለወጡም። ድሮም፣ ኢትዮጵያን ከብሔሮቿ "ለማዳን" እንታገላለን ይላሉ፣ አሁንም ይሄን እያደረጉ ይገኛሉ። የብሔር ፖለቲካን ለማጥፋት ይታገላሉ፣ ክልሎችን ያፈርሳሉ፣ የማንነትና የክልልነት ጥያቄን ያፍናሉ፣ የሕብረብሔራዊ ፌደራል ሥርዓቱን ለማፍረስ፣ ሕገ-መንግሥቱን ለመሻር ይንቀሳቀሳሉ። በዴሞክራሲ አግባብ በነፃና ገለልተኛ ምርጫ አሸንፎ ሕዝብን ከማገልገል ይልቅ፣ በሴራ፣ የኩርፈኞችን ብሶት በመበዝበዝ፣ በአፈናና በጦርነት ኃይል፣ ወዘተ ሥልጣንን ተቀራምተው፣ የሕዝብንና የአገርን ሃብት ይዘርፋሉ፣ ያስዘርፋሉ፣ ያወድማሉ። ሥልጣን ለመቀራመት ሲሉ፣ በከፍተኛ ክህደት ከውጭ ኃይሎች ጋር ተባብረው በአገራቸው ሕዝቦች ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት ያውጃሉ፣ ይፈጽማሉ፣ ያስፈጽማሉ።

2) በዚሁ ጎራ ውስጥ፣ የአብይ ደጋፊ፣ የዘር ማጥፋት አስቻይ፣ ቀስቃሽና አጋዥ የነበሩት ድርጅቶች (አብን፣ ኢዜማ፣ እናት፣ አንድነት፣ ወዘተ)፣ ከአማራ ክልል መንግሥትና ከኤርትራ ጋር በመተባበር የክፋት ኃይሎች ጥምረት (coalition of evil) በመመስረት ሲንቀሳቀሱ ነበር፣ አሁንም ቀጥለውበታል።

በዚህ ስብስብ ውስጥ ያሉት ኃይሎች፣ በጋራም ሆነ በነጠላ አቋማቸውን አልቀየሩም፣ ፕሮግራማቸውን አላሻሻሉም፣ ራዕይ፣ ፕሮግራም፣ ህልምና መሻታቸውን አልለወጡም።

እንደ አብይና ብልጥግና ሁሉ የብሔሮችን መብት በመሻር፣ ከእነሱ ውጭ ያሉ ብሔሮችን ያጥላላሉ፣ ክልሎችን ለማፍረስ ይፈልጋሉ፣ የፌደራል ሥርዓቱን ማፍረስ ይሻሉ። ሕገመንግሥቱን በመሻር ምን እንደሆነ እንኳን የማያውቁትን "መዋቅራዊ" ለውጥ እናመጣለን ብለው ይንቀሳቀሳሉ። ትናንትም፣ ዛሬም፣ ዴሞክራሲን ይፈራሉ፣ ይጠላሉ። ምርጫን በማስቀረት፣ በሴራና በጉልበት ሥልጣንን መቀራመት፣ በተቀራመቱት ሥልጣን ደግሞ በኢትዮጵያ ሥም በሕዝቦቿ ላይ ጦርነት ያውጃሉ።

የዚህ ጎራ አባላት፣ በጋራ ሆነው የዘር ማጥፋት ጦርነትን (በኦሮሞ፣ በቅማንት፣ በአገው፣ በትግራይ፣ በወሎ ኦሮሞ፣ በመተከል፣ በጉሙዝ፣ በበርታ፣ በሲዳማ፣ በወላይታ፣ በከረዩ፣ በኮንሶ፣ በደራሼ፣ በከምባታ፣ በሃዲያ፣ ወዘተ) ላይ አውጀዋል፣ የዘር ማጥፋት ጦርነቶችንም ተዋግተዋል፣ አዋግተዋል፣ ደግፈዋል፣ ቀስቅሰዋል፣ አስችለዋል። በተለይ ኦሮሞንና ተጋሩን ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት እስካሁን ድረስ የሚችሉትን ሁሉ አድርገው በተጨባጭ በሜዳ ላይ ተሸንፈዋል።

አሁንም በትግራይና በብልጥግና መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተገን በማድረግ፣ አገግመው በመነሳት፣ እነዚህን ጠላት ያሏቸውን ሕዝቦች ለማጥፋት የጦርነት ጥሪ እያደረጉ ነው። እየተዘጋጁ ነው።

በኦሮሚያ ላይ ደጋግመው የሞከሩት ወረራ ቢከሽፍም፣ አሁን በተለያየ የሽብር ተግባር ላይ በመሠማራት ጭምር ሕዝቦችን ለመፍጀት በስፋት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

3) የአብይ ብልጥግናና የእነዚህ ኃይሎች ጥምረት (the coalition of evil)፣ የሃሳብም የግብርም ልዩነት የላቸውም። ልዩነታቸው፣ አብይ በሥልጣን የመቆየቱን ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥቶታል፤ እነሱ ደግሞ ትግራይንና ኦሮሚያን ማጥፋትን ቅድሚያ ሰጥተውታል።

አብይ ቅድሚያ ለወንበሩ ስለሚጨነቅ: ለወንበሩ (እና ለህልውናው) ወቅታዊ ሥጋት የሆኑትን የትግራይና የኦሮሞ ኃይሎች (TDF እና OLA) በውጊያ ስላልቻላቸው፣ በተኩስ አቁም "ድርድር" ማባበል፣ ከተቻለም ማታለል ይፈልጋል።

እነርሱ ደግሞ፣ የትግራይና የኦሮሚያ አለመፍረስ ለእነርሱ የህልውና ስጋት ስለሆነ፣ ለዚህ ተግባር ቅድሚያ ይሰጣሉ። መፍትሔውም ጦርነት ነው ብለው ያምናሉ። የአብይ ተኩስ አቁም ስምምነት/ድርድር ክህደት ("እኛን መክዳት ነው") ብለው ያምናሉ።

የሰላም ሂደቱ ወደፊት መራመዱን ከቀጠለ፣ ወልቃይትን ያስመልስብናል/ ያሳጣናል ብለው ይፈራሉ። ኦሮሞን እንዳንወርና ኦሮሚያን እንዳናፈርስ ይጋርደናል ብለው ይሰጋሉ። በመሆኑም አብይን በኦነግነት ፈርጀው በማጥላላት በጩኸትም፣ በሽብርም፣ በጦርነትም በልምምጥም ስልጣኑን መንጠቅ ይፈልጋሉ።

በመሆኑም፣ ለጊዜውም ቢሆን፣ ሰይፋቸው ከኦሮሚያና ከትግራይ ተመልሶ አቅጣጫውን ወደ አብይ አዙሯል።

በብልጥግና ታዝለው ትናንሽ የሥልጣን ፍርፋሪ ሲለቅሙ የቆዩት እነ ኢዜማ፣ አብን፣ እናት፣ ወዘተም በመግለጫ፣ አዛይ-ጌታቸውን (PPን) መወረፍ ጀምረዋል። የብልጥግና ታላላቅ ቁምቡርሶችም (አብይ እራሱ፣ ሽመልስም፣ አዳነችም) ከያሉበት ሆነው በታዛዮቹ ላይ ማንባረቅ ጀማምረዋል። እናም ትልቁ የጥፋት ኃይሎች ጥምረት (the Grand Coalition of Evil) ተፍረክርኮ እርስ በእርሱ መራኮት ጀምሮአል ማለት ነው።

ይሄ የሥልጣን ቅርምት ጠብ፣ "ለምን የተጀመረው የዘር ማጥፋት ጦርነት በድል ሳይቋጭ ተቋረጠ ለምን ክልሎች አልፈረሱም? ለምን ትግራይና ኦሮሚያ አልጠፉም? ለምንስ የፌደራል ሥርዓቱ አልቀረም? ለምንስ ሕገመንግሥቱ አልተሻረም?" ወዘተ ከሚል ቁጭት የተነሳ ነው እንጂ፣ ከፖለቲካ አቋም ማስተካከል የመነጨ አይደለም።

የተቀየረ መስመር የለም። የተለወጠ ፕሮግራም የለም። የተሻሻለ አሠራርም የለም። የተቀየረ ፕሮጀክትም ሆነ ፖሊሲ የለም። እራሱን የቀየረ ድርጅትም የለም።
ይልቅ የክፋት ኅይሎች ጥምረት ከመፍረክረኩ የተነሳ፣ ታዛዮች ከብልጥግና ሌላ፣ የተሻለ የሚሉትን አዛይ (ኤርትራን) ይዘው፣ አብይን መውጋት ይፈልጋሉ። አብይም ብቻዬን ከምገጥማቸው ከትግራይ ጋር አብሬም ቢሆን እከላከላለሁ ብሎ አስቦ ሊሆን ይችላል።

የሆነ ሁኖ ግን፣ የተከሰተው ሁኔታ፣ የክፋት ኃይሎች ጥምረት ፈርሶ እርስ በእርስ መባላት መጀመሩን ያሳያል እንጂ የኃይል አሰላለፍ ለውጥ መኖሩን ፈጽሞ አያሳይም።

እስካሁን እንደምናውቀው፣ በሌላኛው ጎራ ያሉት የትግራይ TDFም ሆነ የኦሮሚያ OLA፣ ዓላማቸውንም፣ ስልፊታቸውንም፣ ፕሮግራማቸውንም አልቀየሩም።

እርግጥ ነው፣ በጽናት መራራ ትግልን ታግለው (በተለይ TDF)፣ ብልጥግናና የክፋት ጥምረቱን እልህ አስጨራሽ ጦርነት መክተው፣ ጥምረቱ እርስ በርስ እንዲባላና የውስጥ ጦርነት (internal fight) እንዲጀምር አስገድደውታል። ይሄ ደግሞ የእነሱን ድል አድራጊነት ያሳያል እንጂ የኃይል አሰላለፍ ለውጥ አያሳይም። በሁለቱ ጎራዎች (ማለትም በክፋት ኃይሎች ጥምረት እና በTDF-OLA) መካከል አዲስ የተፈጠረ የመስመርና የአደረጃጀት ለውጥ የለም። ትግራይና ብልጥግናም የተስማሙት ስምምነት የተኩስ አቁም እንጂ የትብብርና የመረዳዳት (አዲስ የፖለቲካ መግባባት ወይም new political pact) አይደለም።

ለውጥ አለ ከተባለም፣ በዘር-አጥፊዎችና ከሃዲዎች ጥምረት (The Coalition of Genocidaires and Traitors) ውስጥ የተፈጠረ፣ የስልጣን ሽኩቻን የወለደ፣ በጨካኝና በበጣም ጨካኝ መካከል የሚታይ ሽኩቻ ብቻ ነው።

9.4k 2 21
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Blog Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot