የ69 ዓመት አዛውንቱ የጅማ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪ ሆኑ
ግንቦት 5/2014 (ዋልታ) የ11 ልጆች አባት እና የ69 ዓመቱ አዛውንት ታደሰ ጊችሌ የጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተቀበላቸው ካሉ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መካከል አንዱ ሆነዋል።
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 502 የመግቢያ ነጥብ ያመጡት እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡት ተማሪ ታደሰ ጊችሌ ከምዕራብ ወለጋ ገንጅ ወረዳ መነሻቸውን አድርገው ለትምህርት ጅማ ዩኒቨርሲቲ በዕድሜ ከልጆቻቸው በትምህርት ደግሞ ከእኩዮቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
እንደ እኩዮቻቸው ፊደል ቆጥረው ሳይንሱን አርቅቀው የሚፈልጉበት የልጅነት ራዕያቸው ላይ ለመድረስ በቤተሰብ ኃላፊነትና በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ቢፈተኑም ካሰቡበት ለመድረስ ባላቸው ጠንካራ የመማር ፍላጎት ዩኒቨርሲቲ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አዲስ ገቢ የሆኑት ተማሪ ታደሰ "አንዳንዶች በዚህ እድሜህ ትምህርቱን አቋርጠህ ለምን ወደ እርሻህ አትመለስም ይሉኛል፤ እኔ ግን የልጅነት ህልሜን ማሳካት ስላለብኝ ከትምህርቴ ጎን ለጎን የእርሻና የቡና ችግኝ እያስፋፋሁ ቆይቻለሁ" ብለዋል።
ከጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው ተማሪ ታደሰ ጊችሌ ወደ ፊት በዩኒቨርሲቲ ቆይታ በጤና ዶክትሬት ማጥናት እና በሕክምናው ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን በማስተካከል ወገኔን ማገልገል እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW