ባንኩ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
ሐምሌ 29/2014 (ዋልታ) አዋሽ ባንክ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ ጸጋዬ ማሞ እንደገለጹት ክልሉ ሰፊ ጸጋ ያለበትና ሊለማ የሚችል አካባቢ ነው። ክልሉ መንግስታ ተልዕኮዎችን ለማስፈጸም የአጋሮችን ድጋፍ በመጠየቅ ሃብት የማሰባሰብ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል ።
ባንኩ ላደረገው ድጋፍ በክልሉ መንግስት ስም በማመስገን በክልሉ ባንኩ ለሚሰራቸው ስራዎች የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የአዋሽ ባንክ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ዋና ዳይሬክተር ይርጋ ይገዙ የአዋሽ ባንክ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ክልላዊና ሀገራዊ ጥሪዎችን በመቀበል ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ለመነሻ የሚሆን የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።
በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።በርክክቡ ስነስርዓት ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የአዋሽ ባንክ ቦንጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ መገኘታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።