የከተማ መሬቶች በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሊዝ የመሬት ስርዓት ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ተጠቆመ
ኅዳር 20/2017 (አዲስ ዋልታ) በኢትዮጵያ ከተሞች ያሉ መሬቶች በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሊዝ የመሬት ስርዓት ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ተሻሻሎ በቀረበው የከተማ መሬትን በሊዝ ለመያዝ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተጠቆመ።
በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረት ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ለመመዝገብ እና የከተማ መሬትን በሊዝ ለመያዝ ተሻሽሎ የቀረቡ ረቂቅ አዋጆች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ይገኛል።
በተሻሻለው አዋጅ ውስጥም የከተማ መሬት ሊዝን በተመለከተ ከኅዳር 18/2004 በኋላ ያለፈቃድ የተያዙም ሆነ ፈቃድ ባላገኙ መሬት ላይ ያሉ ግንባታዎችን ጭምር በማፍረስ መንግስት የመሬት ይዞታዎቹን እንደሚረከብ ተመላክቷል።
እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ከተሞች በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሊዝ የመሬት ስርዓት ውስጥ መካተት እንዳለባቸው በተሻሻለው በረቂቅ አዋጅ ላይ መካተቱን ለሚመለከታቸው አካላት ተብራርቷል።