The Ethiopian Economist View


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Economics


Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Economics
Statistics
Posts filter


ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ....

ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ መከተሌን እቀጥላለሁ ሲል ዛሬ ገልጿል..... IMF የገንዘብ ፖሊሲችሁ መጥበቅ አለበት ብሎ በቅርቡ መክሯል።

ለመሆኑ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ (Tight Monetary Policy) ምን ማለት ነው? የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እየተከተለ ያለው ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ መገለጫምች ምንድን ናቸው? የገንዘብ ፖሊሲው ጥብቅ የመሆኑ እድል እና ስጋት ምንድን ነው?

እነዚህን እና የመሳሰሉትን መሰረታዊ ነጥቦች ተከታተሉ...https://youtu.be/PaPaufDSgf0


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሪ አድርጓል። (ልክ ሳየው ከገረመኝ የታሪፍ ጭማሪዎች መካከል ነው!)....

ጊዜያዊ ዕውቅና ክፍያ ከ100ብር ወደ 15,000 ብር፤

የሙሉ ዕውቅና ክፍያ ከ200ብር ወደ 30,000 ብር፤

የሰነድ ማሻሻያ ክፍያ ከ30ብር ወደ 5,000 ብር ገብቷል።


#ደመወዝ : የደመወዝ ጭማሪ ተፈቅዶና በጀቱም ጸድቆ ክፍያው ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም.  ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዛሬ አሳውቋል።

ከገንዘብ ሚኒስቴር የተፈቀደው በጀት፣ የአፈጻጸም መመሪያውንና የክፍያ ትዕዛዙን ለ12ቱ ክልሎች፣ ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችና ለፌደራል ተቋማት ዛሬ መተላለፉም ተገልጿል።

(ከጥቅምት ወር 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው ይፋዊ (Gross Salary) የደመወዝ ስኬል ከላይ ተያይዟል)!

የተጣራ ደሞዝ ለማወቅ
👇
https://youtu.be/1LEjbMptwms


IMF ለኢትዮጵያ የተራዘመ ብድር ለመልቀቅ ሲያደርግ የቆየውን ግምገማ ማጠናቀቁንና አገሪቱ የክፍያ ሚዛን ጉድለቷን ማስተካከል እንድትችል ባፋጣኝ 340.7 ሚሊዮን ዶላር ብድር እንዲለቀቅላት ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚ ቦርዱ መወሰኑን ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።


IMF የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም አንቀሳቃሽ በመሆኑ የሚያወጣቸው መግለጫዎች በሀገር ውስጥ የሚተገበሩ በመሆናቸው በትኩረት መከታተል በጣም ጠቃሚ በመሆኑ..


በመሆኑም ከግምገማው በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣይ መከናወን አለባቸው በሚል ያቀረባቸውን 5 Statements በዝርዝር እንመለከታለን....https://youtu.be/q6Lpd_OwJrg


#ለመረጃ

ጅቡቲ ላይ የተከማቹ የነዳጅ ተሸከርካሪዎች እንዲገቡ ተፈቀደ!


የገንዘብ ሚኒስቴር ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር፣ በጅቡቲና ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ላይ ተከማችተው የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱ ተሰምቷል፡፡


አዲሱ መመሪያ፤ ከዚህ ቀደም እንዳይገቡ ታግደው የቆዩ ተሸከርካሪዎችን ጉዳይ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል፡፡


መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ከተለያዩ ኤጀንሲዎችና ከጉምሩክ ኮሚሽን ተውጣጥቶ የተቋቋመ ኮሚቴ፣ ዝርዝር ግምገማ  ማድረጉን ተከትሎ፣ በጥያቄ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች በተገዙበት ቀንና የጉምሩክ ምዝገባ መሰረት እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡


መንግሥት በተለይም ከየካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የተገዙና በጉምሩክ ተገቢው ምዝገባ የተደረገላቸው ተሽከርካሪዎች፣ ወደ ድሬዳዋ ተጓጉዘው መንግሥት ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚሰጥ ይጠበቃል ተብሏል (@አዲስ አድማስ)፡፡


የጥቅምት ወር ደመወዝ ክፍያ በአዲሱ የተሻሻለው ስኬል መሆን ይጀምራል...

ከመስከረም ወር ጀምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ሲጠብቅ የነበረው የመንግስት ሰራተኞች አዲሱ ደሞዝ ከጥቅምት ወር እንደሚጀምር የገንዘብ ሚኒስቴር (አቶ አህመድ ሽዴ) አሳውቋል።

አዲሱ የጭማሪ መጠን፤ ከሰራተኛው የሚቆረጥ የግብር መጠን እና የጡረታ መዋጮ ተቀንሶ በእጁ የሚቀበለው የተጣራ ደሞዝ መጠን ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡https://youtu.be/1LEjbMptwms




ኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር (Ethio Telecom S.c) 10% በመቶ ድርሻውን መሸጥ የሚያስችለውን ሥርዓት (Mini App) በቴሌብር ሱፐር አፕ መተግበሪያው ላይ አካቷል።

ዜጎች ይህንን ሼር ከመግዛታቸው አስቀድሞ ስለ አጠቃላይ የሼር ሽያጭ የቀረበ ዝርዝር መረጃ (prospectus) አንብበው መስማማታቸውን መግለጽ ይኖርባቸዋል።

ይህ ዶክመንት ምን ይላል ?

ዶክመንቱ ፥ የሼር መጠን ፤ መግዛት ስለሚቻለው የሼር ብዛት፤ ስለ አክሲዮን ማኅበሩ ዳራ፤ የሂሳብ ሪፖርት መረጃዎችን፤ ቀነ ገደቦችን፤ ስጋቶችን፤ ለማመልከት የሚያስፈልጉ ዝርዝር ሂደቶችን፤ የሼር አከፋፈል ሥርዓቶችን በዝርዝር ያስቀመጠ ነው።

ሂደቶቹ ምን ይመስላሉ ?

ዜጎች በ prospectus ዶክመንቱ እንዲሁም ውል እና ሁኔታዎች (Terms and conditions) ከተስማሙ በኃላ መግዛት የሚፈልጉትን የሼር መጠን በመምረጥ ያመለክታሉ።

የመኖሪያ አድራሻ ፣ መታወቂያ ፣ ፎቶ ፣ ስልክ ቁጥር ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎችን ከተሞላ በኋላ ሼር ለመግዛት ማመልከት ይቻላል። እነዚህን መረጃዎች ለማስተካከል እና ክፍያ ለመፈጸም 48 ሰዓት ተሰጥቷል።

ሼር ለመግዛት ካመለከቱ በኋላ ኢትዮ ቴሌኮም የክፍያ ሂደቱን እንዲሁም ያስገቡት ዝርዝር መረጃ የማጣራት ሂደት የሚያካሂድ ሲሆን ሂደቱን ካለፉ የተሳካ ማመልከቻ ዝርዝር ውስጥ ይካተታሉ። ሂደቱን ካላለፉ መሰረዞን የሚገልጽ መልዕክት ይደርሶታል።

(የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት መታወቂያ እንዲሁም ፎቶ ሲያነሱት በሚታይ መልኩ እንዲሆን ይመከራል)

ኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር ካቀረበው በላይ ግዢ ከተፈጸመ ምን ይደረጋል ?

መሸጥ ከሚታሰበው በታች ሼር ከተሸጠ ሼር ለመግዛት ያመለከቱ በሙሉ የጠየቁትን የሼር መጠን የሚያገኙ ይሆናል።

ሆኖም የሼር ግዢ ጥያቄው ከተቀመጠው በላይ ከሆነ በprospectus ዶክመንቱ መሰረት የአክሲዮን ድልድል (Allotment of Shares) ይካሄዳል።

ይህም ሼር መሸጥ ከሚያበቃበት ታኅሣሥ 25 ጀምሮ የሚደረግ ይሆናል።

ይህ ድልድል በተመጣጣኝ ድርሻ ስሌት (Pro-rata Algorithm) የሚካሄድ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል የሚከናወን ነው። ይህም እያንዳንዱ አመልካች ተመጣጣኝ ድርሻ እንዲደርሰው የሚያስችል ነው።

ለምሳሌ ፦  አንድ ሰው 100 ሼር ግዢ ለመፈጸም ጥያቄ አቀረበ። የተመጣጣኝ ድርሻ ስሌቱ (Pro-rata Algorithm) ሁሉም 70% እንዲደርሳቸው ቢወስን 100 ሼር ለመግዛት ጥያቄ ያቀረበው ሰው የሚደርሰው 70 ሼር ይሆናል ማለት ነው።

በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ድልድሉ ጥር 23/2017 ዓ.ም በይፋ ለህዝብ በይፋ ይገለጻል።

ተመላሽ ክፍያ በተመለከተ ?

አመልካቾች ድልድል ከተደረገ በኋላ የደረሳቸው የሼር መጠን ያክል ክፍያ ተቆርጦለት ቀሪው ገንዘብ ከአገልግሎት ክፍያው ጋር ተደምሮ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።

ገንዘቡ ድልድሉ ይፋ በሆነ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል። ዜጎች ሼር ለመግዛት ካመለከቱ እና ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ድልድሉን አለመቀበል አይችሉም።

የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር 10% ድርሻ ለኢትዮጵያውያን ብቻ የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሽያጭ የሚደረግበት ይሆናል። በተጨማሪም ዜጎች ለራሳቸው እና ህጋዊ ውክልና ላላቸው ዜጋ ግዢውን መፈጸም ይችላሉ።

ከዚህ የሼር ሽያጭ ኢትዮ ቴሌኮም 30 ቢሊዮን ብር ገቢ የሚያገኝ ሲሆን። ከአገልግሎት ክፍያ ደግሞ 450 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ገቢ ያገኛል። መንግሥት ሙሉ ለሙሉ የቀረበው ሼር ተሸጦ ካለቀ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ብቻ 67.5 ሚሊዮን ብር ያገኛል።

አክሲዮን ማኅበሩ፥ በኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ገበያ ዝርዝር ውስጥ ለመካተት (Listing) የሚያስችለውን ዝግጅት የሼር ሽያጩ ካበቃ በ12 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን በዶክመንቱ ተገልጿል።
@tikvahethiopia




Ethio Prospectus.pdf
14.5Mb
#ለመረጃ

የኢትዮ ቴሌኮም ዝርዝር ጥናት (Prospectus) ማንበብ ለምትፈልጉ። አክሲዮን ለመግዛት ለምትፈልጉ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።


ኢትዮ ቴሌኮም 30 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ 100 ሚሊየን አክሲዮኖችን ለሽያጭ አቀረበ! ዝቅተኛ እና ከፍተኛ አክሲዮኖች...የክፍያ ሁኔታ...የቆይታ ጊዜ...


በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮ ቴሌኮም የ10% ድርሻ ታውቋል! የአንድ አክሲዮን ዋጋ፤ ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የአክሲዮን ጣሪያ፤ ሽያጭ የሚደረግበት ሂደት እና የአክሲዮን የሽያጭ ቆይታ በዝርዝር ቀርቧል https://youtu.be/Rrp2JceCQuA


#ለመረጃ (Expected)

ከዛሬ ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ሚኒ-ባሶች፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶች ላይ የአገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡ 


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከ2 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳስቧል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሁለት ውስጥ የመመሪያ ለውጥ ማድረጉ ምንን ያሳያል? በመጀመሪያው መመሪያ የተፈጠረው ችግር በሁለተኛው መመሪያ ይቀረፋል? ይህ መመሪያ የውጪ ምንዛሬ ፍላጎትን ማስተካከል ይችላል? የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት እና ፍላጎትን በተመለከተ መሰረታዊ መስተካከል ያለበት ጉዳይ ምንድን ነው?https://youtu.be/4Jc7Olob1Wo


የዶላር መሸጫ ከ8 ብር በላይ ቀነሰ (በአንድ ቀን)!
#ትክክለኛ_እርምጃ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 282 ሚሊየን ዶላር ደልድሎ ደንበኞች የወሰዱት 28% (79 ሚሊየን ዶላር ብቻ) ነው። ለዚህ ምክንያት ከሆኑት መካከል የውጪ ምንዛሬ መዋዠቅ ጉዳይ ነው፡፡ አስመጪዎች ዛሬ የሚገዙት ዶላር በመጨረሻ ክፍያ ወቅት ሊኖረው የሚችለው ልዩነት ተገማች አለመሆን ወይም ከፍተኛ መሆን (Spot Exchange Rate) ትልቅ ተጽኖ አለው፡፡

ለምሳሌ፡- አንድ ዶላር በ125 ብር ያስፈቀደ ነጋዴ እቃው ከውጪ ተጭኖ ሲመጣ (ሂደቱ የወራት እድሜ ሊኖረው ስለሚችል) አንድ ዶላር 135ብር ቢደርስ ልዩነቱን በአንድ ዶላር 10 ብር የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡

ስለሆነም ከመነሻው ዶላር የመግዣውን ዋጋ በመቀነስ ወደፊት ልዩነት እንኳን ቢፈጠር ያልተጋነነ የማድረግ እድል ስለሚኖረው ዶላር የመሸጫ ዋጋን መቀነስ (ከ123 ብር ወደ 115 ብር) የተከማቸን የውጪ ምንዛሬ ለመልቀቅ እና ኢኮኖሚው ካለበት የውጪ ምንዛሬ ፍላጎት የመቀነስ አንዱን ችግር የመቅረፍ እድል አለው፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 282 ሚሊየን ዶላር አዘጋጅቼ 28% ብቻ ነው የተወሰደው! የውጪ ምንዛሬ ፍላጎት የቀነሰው ለምንድን ነው?

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ "ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአራት ዙር 282,459,436 ዶላር ለበርካታ ደንበኞች ቢደለድልም ካዘጋጀው የውጪ ምንዛሬ ውስጥ ደንበኞቹ የተጠቀሙት በአማካይ 28 በመቶ መሆኑን ገልጿል"፡፡

ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ፍላጎት ባለበት የኢትዮጵያ አሁናዊ ኢኮኖሚ ግዙፊ የንግድ ባንክ ያቀረበውን የውጪ ምንዛሬ የመውሰድ ፍላጎት ለምን ከ28% በላይ አላለፈም?

ለዚህ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ 4 ምክንያቶችን እንመለከታለን....https://youtu.be/QRVg35M9vG8




የሪል_ስቴት_ልማት_እና_የማይንቀሳቀስ_ንብረት_ግብይትና_ግመታ_አዋጅ_2.pdf
1.7Mb
ያልተገነባ ቤት /ግንባታ ከማከናወናቸው በፊት ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካውንት እንዲያስቀምጡ ሊገደዱ ነው ፤ በተጨማሪ ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ሊከለከሉ ነው።

ይህንም የሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ቀርቧል።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?


ሀገራት የBRICS አባል የመሆን ፍላጎታቸው እየጨመረ ነው!


የብሪክስ (BRICS) አባል ሃገራት የመሪዎች ጉባኤ ከቀናት በኋላ በሩሲያ ካዛን ይካሄዳል።
በርካታ ሃገራት ስብስቡን ለመቀላቀል ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን በጉባኤው ውሳኔ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቅበታል።


የብሪክስ አባል እና የአባልነት ጥያቄ ያቀረቡ ሃገራት ጥቅል ሃገራዊ ምርት የሚከተለው ነው።

የብሪክስ አባል ሃገራት ኢኮኖሚ (GDP)....

🇧🇷 Brazil: $2.27 trillion
🇷🇺 Russia: $1.9 trillion
🇮🇳 India: $4.11 trillion
🇨🇳 China: $18.56 trillion
🇿🇦 South Africa: $401 billion
🇪🇬 Egypt: $357 billion
🇪🇹 Ethiopia: $192 billion
🇮🇷 Iran: $386 billion
🇦🇪 UAE: $536 billion


ለብሪክስ አባልነት ጥያቄ ያቀረቡ ሃገራት ዝርዝር እና ኢኮኖሚ....


🇩🇿 Algeria: $239 billion
🇧🇭 Bahrain: $47 billion
🇧🇩 Bangladesh: $455 billion
🇧🇾 Belarus: $66 billion
🇧🇴 Bolivia: $49 billion
🇨🇺 Cuba: no data
🇰🇿 Kazakhstan: $290 billion
🇰🇼 Kuwait: $167 billion
🇳🇬 Nigeria: $394 billion
🇵🇰 Pakistan: no data
🇵🇸 Palestine: no data
🇸🇳 Senegal: $35 billion
🇹🇭 Thailand: $543 billion
🇻🇪 Venezuela: $97 billion
🇻🇳 Vietnam: $469 billion

ከ30 በላይ ሀገራት ጥምሩን የመቀላቀል አዝማሚያ እና እንዳላቸው ታውቋል።

Real Data @World of Statistics 2024


ለኢትዮጵያውያን፤ ለትውልደ ኢትዮጵያን....

ኢትዮጵያ ውስጥ የውጪ ምንዛሬ አካውንት አከፋፈት እና አጠቃቀም ዙሪያ መሰረታዊ መረጃዎች!

የውጪ ምንዛሬ አካውንት መክፈቻ መስፈርት፤ የአካውንት አይነቶች፤ ከአካውንት የውጪ ምንዛሬ አጠቃቀም እና ገደብ፤ የአካውንት ዋስትና ሁኔታ፤ የወለድ እና የምንዛሬ ድርድር ሁኔታ መሰረታዊ መረጃዎችን ተመልከቱ.....https://youtu.be/A2Hj5kRjUKk


#ለመረጃ....የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተደረገ!
ቤንዚን በሊትር 91 ብር!
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

20 last posts shown.