#🚩በውጪ ሀገር የሥራ ስምሪት #በነርስ_ሙያ ተጠቃሚ መሆን ለምትፈልጉ በሙሉ
በውጪ ሀገር የሥራ ስምሪት በነርስ ሙያ (all categories) ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (
lmis.gov.et) በመመዝገብ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በሚደረግ የምልመላ ሂደት የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ለአገልግሎቱ ምንም አይነት ክፍያ የማይጠየቅ መሆኑን አውቃችሁ ከአጭበርባሪዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ ለማሳሰብ እንወዳለን።
#ማሳሰቢያ፡-
በዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የሚከተሉትን ደረጃዎች መጠበቅ ይርባቹሀል
📌 1ኛ
lmis.gov.et ላይ መመዝገብ እና
📌 2ኛ አቅሪያቢያችሁ በሚገኝ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት የባዮሜትሪክስ መረጃ መሥጠትና የሠራተኛነት መለያ ቁጥር ማገኘት፣
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ነሃሴ 16/2016 ዓ.ም