አንድ ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመጨመር ቢፈልግ የግድ ገድላትን ተአምራትን መቀበል የለበትም ስንል የትኛውን ገድልና ታምር ነው ?
ገድል - የምንለው የሰማዕታትንና የጻድቃንን መጋደል ወይም ሥራቸውን ልፋታቸውን የሚነግር መጽሐፍ።
ታምር - የምንለው ደግሞ ለማመን እራሱ የሚከብድ በእግዚአብሔር ካልሆነ የሰው ልጅ ለማድረግ የሚከብደው ነው የሆነ ነገር የተደረገ ለማመን ግን የሚከብድ ነገር ሲገጥመን ይሄ ታምር ካልሆነ በስተቀር ምን ይባላል እንደምንለው ነው ለምሳሌ በመጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 30)
37፤ ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው።
38፤ የላጣቸውንም በትሮች በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ በበጎቹ ፊት አኖራቸው፤ በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ይጎመጁ ነበር።
39፤ በጎቹም በትሮቹን አይተው ከመጎምጀታቸው የተነሣ ፀነሱ፤ በጎቹም ሽመልመሌ መሳይና ዝንጕርጕር ነቍጣም ያለበቱን ወለዱ።
40፤ ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ሁሉ በላባ በጎች ፊት ለፊት አኖረ፤ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው፥ ወደ ላባም በጎች አልጨመራቸውም።
41፤ እንዲህም ሆነ፤ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፤
💦በያዕቆብ የተደረገው እንደ ሰው አስተሳሰብ ሳይሆን በጣም ያልተለመደ እና ከተፈጥሮአዊ አመክንዮ በላይ ነበር እስኪ ይሄን እንደው ከእግዚአብሔር አንጻር ካላየንው እኔ አሁን ይሄን በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የማላምን ብሆን እንዴት ይሄን ታሪክ እውነት ነው ብዬ እቀበላለሁ ተረት ተረት ከማለት ውጭ እስኪ ንገሩኝ እንዴት ሊሆን ቻለ የተላጠ በትር ዝንጉርጉር በጎች እንድወለዱ እንዴት አደረገ ? ከመቸስ ውድህ ነው እንደዚህ አይነት ነገር ያለው ? ምን አይነት ሰውስ ይሄን ሊያሳምነኝ ይችላል ከእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት እና ኃይል ውጭ ካየንው ?ምንም ነገር ሊኖር አይችልም።
💦በነገራችን ላይ ይሄ ገድላት እና ድርሳናት ላይ ቢሆን ያለው ብላችሁ አስቡ የምር አይደለም ሌላ ቤተ እምነት ያለ ኦርቶዶክስ ነኝ የሚልም ይሄ ልክ አይደለም ይሄ ተረት ነው የሚል ይበዛ ይመስለኛል ደግነቱ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው ያለው ለዚህ እኮ ነው መዝሙረኛው ዳቂት “እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት። ሥራህ ግሩም ነው ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ።ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ፤ ከሰው ልጆች ይልቅ በምክር ግሩም ነው።” ያለው ሰው ኹሉ አንድ የሚያስገርም ነገር ሲአገኘው ተአምር ነው ድንቅ ነው ይላል
ታምር ማለት በምታቀው ነገር የምትረዳው ሳይሆን ከአዕምሮ በላይ የሆነ ነው እንደዚያም ካልሆነ ምኑን ታምር ሆነው እግዚአብሔርስ ከአንተ በላይ መሆኑን በምን ነው የምታውቀው አንተ ልትሠራው የምትችለው ነገር ከሆነመ ምኑን ታምር ሆነ ?
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንድህ የሚሉ ቃላቶች አሉ፦
‘መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፣ ሩጫውን ጨርሻለሁ፣ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ’ ። — 2 ጢሞቴዎስ 4:7
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፣ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ።” — 1 ጢሞቴዎስ 6: 7–12
1ኛ ተሰሎንቄ
2: ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።
ስለዚህ ከላይ ባያናቸው ጥቅሶች ገድል ማለት ሃይማኖትን ወይም እምነትን መጠብቅ ፣ለእግዚአብሔር ወንጌል መከራን መቀብል፣ እና ማንኛውም አይነት እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኝ የሚችል መልካም ተጋድሎ እና የዘላለም ህይወትን መያዝ የመሳሰሉት ናቸው ታድያ ይሄን የመሰለውን መልካም ገድል ነው ግዴታ መቀበል የለብህም የምንለው ?
እንደዚያ ከሆነማ ምኑን ኦርቶዶክስ ሆነው ሲጀመር ምክንያቱም ኦርቶዶክስ ሲሆን እምነቱን መጠበቅ ፣ ለእግዚአብሔር ወንጌን መከራን መቀበል ፣ማንኛውም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኝ የሚችል መልካም ተጋድሎ ማድረግ አለበት ስለዚህ ቅዱሳን ያደረጉት ይሄን ስለሆነ የቅዱሳን መልካም ገድል ካልተቀበል እምነታቸውን አልተቀበለም ማለት ነው ምክኛቱም ቅዱሳን የተጋደሉት ስለእምነታቸው እንጅ ስለሌላ አይደለም እምነት ደግሞ ዶግማ ነው ዶግማን አለመቀበል ደግሞ ምንፍቅና ነው ።
ታምራትም ስንል ከእግዚአብሔር ግብረ ባሕርይ አንጻር የሚቃረን ካልሆነ በስተቀር ታምሩን መቃወም በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት አለማመን ነው። ስለዚህ እንደው ብድግ ብሎ ለእኔ አዕምሮ የከበደኝን ሁሉ እየተነሳው ይሄ ልክ አይደለም ማለት አልችልም ምክንያቱም ታምሩ እውነትም ተፈጽሞ ከሆነ እግዚአብሔርን ነው እየተቃወምን ያለንው።
ታድያ እንድህ ስንል በገድል ስም ትክክለኛ ገድል ያልሆኑ ትክክለኛ ታምር ያልሆኑትን ማለትም ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር የማይሄዱትን የመቀበል ግዴታ የለበትም ብቻ ሳይሆን መቃወም አለበት እንጅ እንደውም የመቀበል ግደታ የለበትም የሚለው አማርኛ ትክክል አይደለም ሰው ሲጀመር ትክክለኛ ያልሆነ ገድል እና ታምራትን ሲጀመር መቀበል የለበትም ። ምክንያቱም ሀሰተኛ ክርስቶስ እንደሚመጣ ሁሉ ሀሰተኛ ታምር እና ገድልም ሊኖር ይችላል። በትክክለኛ ገድል ውስጥ የቅደሱ ገድል ያልሆነ በሰርጎ ገብ የገባ ሊኖር ይችላል የሚበረዙ ገድላት እና ታምራት ይኖራሉ አይደለም ገድላት እና ድርሳናት መጽሐፍ ቅዱስ እራሱ ይበረዛል። ስለዚህ የተበረዘ መጽሐፍ ቅዱስ የመቀበል ግደታ ሳይሆን መቀበልም የለብኝም ። መጽሐፍ ቅዱስ አይሳሳትም ስንል በሐሰት የተዘጋጀውን መጸሐፍ አይደለም በእውነተኛ የተዘጋጀውን እንጂ መጽሕፍ ቅዱስም የማይበረዝ ሁኖ አይደለም ።
ስለዚህ ስለ እውነተኛ ገድላት እና ታምራት ከሆነ የምናወራው ገድላትና ድርሳናትም አይሳሳቱም ስለተበረዙት ከሆነ የምናወራው አይደለም እነሱ መጽሐፍ ቅዱስም ይበረዛል ።ግን ቤተ ክርስቲያን የምትመራው በመጽሐፍ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ነው ።
@felgehaggnew