YøÑi SªT { ዮኒ ሳት } የመረጃ ቻናል


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


♨️ ስለ ዲሽ ሪሲቨር እንዲሁም የኤሌክትሮኒስ መረጃዎችን ያገኛሉ።
♨️ የሪሲቨር የስልክና የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን @software365
♨️ የመወያያ ግሩፕ @Yonisat2
♨️3 ቪዲዮዎች በሳምንት በአማርኛ በHD ጥራት ለመመልከት ቤተሠብ ይሁኑ
https://www.youtube.com/YonsatTech
CREATOR YONAS GEREMEW
🔥Inbox @YONSAT


Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Digital Satellite Finder

FINDSAT 8600 ምንም ያልተነካካ ጥቂት ያገለገለ ከዋስትና ጋር ከሙሉ አክሠሠሪ ጋር

ትክክለኛ ገዢ የሆናችሁ ብቻ አናግሩኝ ከሙሉ ዋስትና ጋር ትወስዳላችሁ

+251930756350 ዮኒ ሳት


ጠቅላላ የሪሲቨር ጥገና ስልጠና ለመከታተል የተላከ ደረሰኝ ነው።እናመሠግናለን🙏🙏🙏

✔ጠቅላላ የቲቪ ጥገና ስልጠና 1500 ብር ብቻ ሲሆን CRT +LED LCD እና ጠቅላላ የኤሌክትሮኒስ ትምህርት ጨምሮ
✔ጠቅላላ የሪሲቨር ስልጠና Software + Hardware ከጠቅላላ የኤሌክትሮኒስ ትምህርት ጋር 500 ብር ብቻ
ለመሠልጠን ያሠባችሁ @YONSAT1 /@YONSAT2
+251930756350
+251964644627 ይደውሉ


ፋይንደር የምትፈልጉ እጄ ላይ ምርጥ እቃ ከዋስትና ጋር አለ
FINDSAT 8600 ከቻርጀር ጋር ትክክለኛ ፈላጊ አ.አ ከሆናችሁ
+251930756350 ደውሉ
የመጨረሻ ዋጋ 3500 ብር ብቻ


ማንኛውንም አይነት የስልጠና ጥያቄ ያላችሁ በሙሉ ሙሉ መልስ የምታገኙበት ቻናል
@Electronicstraining


ዛሬ የተላከ ደረሰኝ
ጠቅላላ የቲቪ ጥገና ስልጠና በሁለት ዙር 750 ብር
እናመሠግናለን


Satellite Receiver & Tv repair Training

ጠቅላላ የቲቪ ጥገና ስልጠና ከኤሌክትሮኒስ ትምህርት ጀምሮ Crt { ቦርጫሙ} ቲቪ እንዲሁም ፍላት {LED
/LCD}  በቀላሉ በቤትዎ

🌟 ጠቅላላ የሪሲቨር ጥገና ስልጠና { Software + Hardware }  ከኤሌክትሮኒስ ትምህርት ጀምሮ በቀላሉ በቤትዎ ሆነው ለመከታተል 
🌟 ስልጠናውን ከመጀመርያው ዙር ጀምሮ 109 ሠልጣኞችን እያሠለጠንን ሲሆን አሁንም መሠልጠን የምትፈልጉ ምዝገባ ላይ ስለሆንን ከታች በሚገኙት የባንክ አካውንቶች ገቢ ስታደርጉ በቀጥታ የምትጀምሩ ሲሆን በMobile Banking የምታስገቡ Screenshot  በመላክ መመዝገብና መጀመር ትችላላችሁ።
1000139090822
   Cbe
01320263863800 Awash
5052913428001   Dashen
  ዮናስ ገረመው ወ /ማርያም 


🔥 ስለ ስልጠናው እንዲሁም የትምህርቶቹ ቪዲዮ ምን እንደሚመስሉ ከስልጠናው የተወሠዱ ቪዲዮዎችንና PDFዎችን ለመመልከት
@Electronicstraining

🌟 ለተጨማሪ መረጃ
+251930756350 / +251964644627
🌟Telegram
@Yonisat1 ወይም @Yonisat2 
🌟Inbox @YONISAT / @YONISAT2


FINDSAT VF 8620 FINDER
ይህ ፋይንደር የFindsat ሌላው ፋይንደር ሲሆን በአንዳንድ ነገሮቹ ተሻሽሎ የቀረበ የቅርብ ጊዜ ምርት ነው።
✔BATTERY /CAPACITY
ይህ ፋይንደር በባትሪው ጥሩ የሚባል ሲሆን እንደስራው አይነት ከ 3-5 ቀናትን ያለ ምንም ቻርጅ መጠቀም ያስችለናል። የሚጠቀመውም 7.4V 1500mah capacity ያለው ባትሪ ሲሆን የቻርጀሩ ደግሞ 12v1A ነው።
✔Signal Speed
ይህ ፋይንደር ኳሊቲ ሲያመጣ ጥሩ የሚባል ሲሆን Real S2 እውነተኛ አይደለም። አንዳንዴ ስንቀርብ DVBS2 እያለ የሚነግረን ቢሆንም በጣም አስተማማኝ አይደለም። ነገር ግን Switch /Port የሚያነብ ሲሆን በተጨማሪም Screen Brightness ፀሀይ ላይ በደንብ ማየት እንችላለን።
✔SHORT CIRCUIT PROTECTION
በገመድ እንዲሁም በLnb short ምክንያት ችግር ቢፈጠር Protection ያለው ሲሆን እንደ FINDSAT 8600 Indicator መብራትም አለው Short ሲፈጠር የሚነግረን
☀ CONCLUSION / በአጠቃላይ
Battery 9/10
Build Quality 9/10
Speed 7/10
Protection 10/10 = 35/40 ሠጥተነዋል


Xcruiser Xs 5500D FINDER
ይህ ፋይንደር በአብዛኛው የሀገራችን የዲሽ ባለሙያ የሚገኝ ሲሆን በጣም ምርጥ የሆነ ፈጣን ፋይንደር ነው።
✔BATTERY /CAPACITY
ፋይንደሩ የሚጠቀመው አሁንም 7.4v 1700mah Capacity ያለው ባትሪ ሲሆን ይህም ጥሩ የሚባል ቆይታ ያለው ነው። በቀን በአማካይ 4 ስራዎችን ብንሠራ 3-4 ቀናት ያለምንም ቻርጅ መጠቀም እንችላለን። የዚህ ፋይንደር Screen Brightness በፀሀይ ላይ የሚያስቸግር ሲሆን ከ FINDSAT አንፃር በጣም የደበዘዘ ነው።
✔SIGNAL SPEED /S2
ይህ ፋይንደር ኳሊቲ ስናገኝ በጣም ምርጥ ሲሆን ትክክለኛ የሆነም S2 አለው። በዚህም ኳሊቲ ሳናገኝ ወደ ሳተላይት እንደቀረብን መረዳት እንችላለን።
✔SHORT CIRCUIT PROTECTION
ይህ ፋይንደር በአብዛኛው Protection ላይ አናሳ ሲሆን ሌላው ቻርጀር ላይ እያለ ካልተነቀለ Charger Ic የመቃጠል እንዲሁም Signal Tunner የመቃጠልም ባህሪ አለበት በእቃነት አንፃር ብዙ Icዎቹ የመቃጠል እድል አላቸው።
☀CONCLUSION / ማጠቃለያ
Battery 7/10
Signal Speed 10/10
Build Quality 8/10
Protection 8/10 =33/40 ሠጥተነዋል


FINDSAT VF 8600 FINDER
ይህ ፋይንደር በአሁኑ ሠአት ገበያ ላይ የማይገኝ ሲሆን ይህ ፋይንደር ሁለት አይነት ሞዴሎች ያሉት ሲሆን VF 8600 እና VF 8600D ሲሆን ሁለቱም ተመሣሣይ ቦርድ የሚጠቀሙ ሲሆን ልዩነታቸው ኳሊቲ የማጋነን አይነት ነው። ተመራጭ የሚሆነው ከሁለቱ VF 8600 ነው።
✔BATTERY
ይህ ፋይንደር 7.4v 1700mah capacity ያለው ባትሪ የሚጠቀም ሲሆን ባትሪ ቆይታውም ምርጥ የሚባል ሲሆን በቀን 5 ስራዎችን ብትሠሩ ከ 3-4 ቀናት በደንብ ያስጠቅመናል። ሲቀጥል ቻርጀሩ 12V 1a ሲሆን ሙሉ ቻርጅ ለማድረግ 3 ሠአታትን የሚወስድ ሲሆን የባትሪው ቆይታ በአጠቃላይ ምርጥ ነው።
SIGNAL SPEED /S2
ይህ ፋይንደር ኳሊቲ ሲያመጣልን በጣም ምርጥ ሲሆን በተጨማሪም ትክክለኛ የሆነ S2 አለው። ይህም እንደ Yahsat /Nss የመሣሠሉ ሳተላይቶች ላይ የሚገኙትን 11785 / 11105 Transponderዎችን ስንፈልግ ኳሊቲ ሳናመጣም ወደ ሳተላይቱ ስንቀርብ S2 የሚል ምልክት ይሠጠናል። ስለሆነም ወደ ሳተላይቱ መቅረባችንን የሚነግረን ሲሆን በዛ ላይ LNB SKIW ተሣስተንም ቢሆን S2 ያሳየናል። በዚህ ፋይንደር ኳሊቲ 70-80% የሚመጣልን ሲሆን Varzish ላይ ደግሞ 38-47% እያሳየ Lock ያደርግልናል። ስለሆነም Lock ካለን ቀጥታ Receiver ላይ በመሠካት 62-75% ኳሊቲ እናገኛለን። በተጨማሪም የኳሊቲ ግነትም አንዳንድ ጊዜ ያሳየናል በተለይ 8600D ሞዴል 99% እያለ የማጋነን ባህሪ አለው ይህንንም በSoftware ማስተካከል እንችላለን።
✔SHORT CIRCUIT PROTECTED
በስራ ላይ በአጋጣሚ በገመድ ወይንምጨበ LNB ምክንያት Short ቢፈጠር Warning ስለሚያሳየን አስተካክለን መልሰን መስራት እንችላለን።
☀ CONCLUSION / ማጠቃለያ
Battery 9/10
Signal Speed 10/10
Build Quality 10/10
Protection 10/10 = 39/40 ሠጥተነዋል


V Made { Trimax } TM 8511
ይህ ዲጅታል ፋይንደር በባትሪው ቆይታ ከሁሉም ፋይንደሮች የተሻለ ሲሆን ፋይንደሩን በአሁን ሠአት ገበያ ላይ የማይገኝ ሲሆን ስለ ፋይንደሩ አንዳንድ ነገሮችን እንመልከት

✔ BATTERY/Capacity
ይህ ፋይንደር በባትሪ ቆይታው የማይታማ ሲሆን Orginal Trimax የሚያመርተው ምርጥ ፋይንደር ነው። በባትሪው በአንድ ጊዜ ቻርጅ በቀን በአማካይ 4 ስራዎችን ብትሠሩበት እስከ 5 ቀናት ያለምንም ሀሳብ የሚያስጠቅም ሲሆን ባትሪው የሚጠቀመው 7.4V 1700mah Capacity ያለው 12v 1A ቻርጀር የሚጠቀም ምርጥ ባትሪ ቆይታ ያለው ፋይንደር ነው።
✔Short Circuit Protection
ይህን ፋይንደር እየተጠቀማችሁ በድንገት በገመድ ምክንያት Short ቢሆን ወይንም የራሱ Protection ስላለው ምንም አይሆንም። ሲቀጥል ፋይንደሩ ደማቅ በፀሀይ ላይ የሚታይ ምርጥ Screen አለው።
✔ Signal Quality
በዚህ ፋይንደር ተጠቅሞ የሚያውቅ ካለ ኳሊቲ የመቀነስ ባህሪ አለው። ይህም በ 40% Lock የሚያደርግ ሲሆን በሪሲቨር ስትመለከቱ ግን ኳሊቲው ምርጥ ላይ ነው። ስለሆነም በዚህ ፋይንደር 70-80 ኳሊቲ አንመለከትም።
✔Signal Indicator S2
ይህ ፋይንደር ትክክለኛ የሆነ S2 የለውም በዚህም ምክንያት ከዚህ ፋይንደር Dis Advantage ይህ ነው።
Conclusion / ማጠቃለያ
Battery 10/10
Build Quality 10/10
Signal Speed 5/10
Protection 10/10 = 35/40 ሠጥተነዋል


ሁላችሁንም ስለተሳተፋችሁ ያላችሁን አስተያየት ስለሠጣችሁን ከልብ እናመሠግናለን።

    ☀BEST FINDER EVER FOR 2022

ሠላም ለናንተ ይሁን በዛሬው እለት በጥልቀት ስለ DIGITAL FINDER እንመለከታለን።

አንድ ፋይንደር ምርጥ ለማለት የምንመለከታቸው የተለያዩ መስፈርቶችን እንመለከታለን።

☀BOARD QUALITY :- አንድ ፋይንደር ጥራት አለው ለማለት የመጀመርያው ነገር የሚጠቀመው የCircuit System ሲሆን ይህም ካምፓኒው ራሱ የሚያመርታቸው Orginal Quality Pcb የሚጠቀሙ ናቸው በዚህም
1- FINDSAT 8600

ይህ ፋይንደር ከሁለት አመታት በፊት በብዛት የሚገኝ ሲሆን ይህ ፋይንደር ሁለት አይነት ሞዴሎች ያሉት ሲሆን 8600 እና 8600D የሚባሉ ናቸው። ነገር ግን ቦርዳቸው ተመሣሣይ ሲሆን ጥራታቸውም በጣም ምርጥ ነው።
✔Battery capacity
ምርጥ የሆነ የባትሪ ቆይታ ያለው ሲሆን በቀን 4 ስራዎችን ብንሠራ በአማካይ ከ5 ቀናት በላይ ይቆያል። የሚጠቀመው 12V 1A አዳፕተር ቻርጀር ሲሆን ቻርጅ አድርጎ ለመሙላት ደግሞ 3 ሠአታትን ይፈጃል።
✔ Real S2 Indicator
ይህ ፋይንደር በጣም የምንወድለት ነገሩ ሌላው ደግሞ Real S2 አለው። አንዳንድ ፋይንደሮች ማለትም የውሸት S2 የሚል ያላቸው ሲሆን ይህ ፋይንደር ግን ትክክለኛ ነው። ይህም Yahsat /Ethiosat ስትሠሩ ማለትም በ 11785 እና 11105 ኢትዮ ሳት ስትሠሩ ወደ ሳተላይቱ ስንቀርብ s2 እያለ ምልክት ያሳየናል። ይህም የLNB SKIW በትክክል እንኳን ሳናደርግ እና ምንም ኳሊቲ ሳናገኝ S2 እያለ ይነግረናል። ስለሆነም እዛ አካባቢ መሆኑን ስለምንረዳ በቀላሉ መስራት እንችላለን።
✔ Short Circuit Protection
ይህ ፋይንደር በስህተት የLNB ገመድ መሠክያው ላይ በኮኔክተር ስናገናኝ Short ቢፈጠር ቢጫ መብራት Blink እያደረገ Short መኖሩን ይነግረናል። ስለሆነም ወዲያው ፋይንደሩን አጥፍተን ገመዱን አስተካክለን መልሰን መስራት እንችላለን።
✔Price & Quality Rate
በመጀመርያ ይህ ፋይንደር ሀገራችን ሲገባ በ 2400 ብር ሲሸጥ የነበረ ሲሆን እነኚህን ከላይ ያነሳናቸውን መስፈርቶች ገምተን 10/10 ሠጥተነዋል።


🔥🔥🔥 በአዲስ መልክ 🔥🔥🔥

ሠላም ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እንደሚታወቀው ጠቅላላ የቲቪና የሪሲቨር ጥገና ስልጠና በ Online Telegram እንዲሁም በFlash መስጠት ከጀመርን አመታት የሞላን ሲሆን በአሁኑ ሠአት ደግሞ የስልጠናውን ማስታወቂያ በፁፍ ብቻ ትተን አዲስ ቻናል ከፍተናል
✔ ስለ ስልጠናው በቂ መረጃዎችን የምንለቅበት
✔ ከስልጠናው ላይ የተወሠኑ ቪዲዮዎችንና PDF ዎችን ጨምረን ስለ ስልጠናው በቂ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ በማለት ከ 15 በላይ ከስልጠናው የተወሠዱ ቪዲዮዎችን የምንለቅበት አዲስ ቻናል ከፍተናል። ስለሆነም ስለ ስልጠናው ለሚነሱ ማንኛውም አይነት ጥያቄዎችንና በምን መልኩ እንደሆነ ለመመልከት Link ከታች አስቀምጠን በነፃ Join አድርጋችሁ ሙሉ የስልጠናችንን ፕሮግራም ምን እንደሚመስል መመልከት ትችላላችሁ ።
✔ ጠቅላላ ኤሌክትሮኒስ
✔ጠቅላላ የቲቪ ጥገና ስልጠና
✔ጠቅላላ የሳተላይት ሪሲቨስ ጥገና ስልጠና

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉናል።


T.me/Electronicstraining


ባለፉት ቀናቶች የተላኩ ደረሰኞች ናቸው።
ጠቅላላ የቲቪና የሪሲቨር ጥገና ስልጠና

ስለተማመኑብን እናመሠግናለን።

🔥 ጠቅላላ የቲቪ ጥገና ስልጠና
Electronics ትምህርት + Crt { ቦርጫሙ }
LED/LCD { የፍላት } ቲቪ ጥገና ስልጠና በጠቅላላው 1500.00ብር ብቻ ሲሆን በሁለት ጊዜ ክፍያ ለመከታተል 750ብር በማስገባት የስልጠናው Private ቻናልና 109 ባለሙያዎች የሚገኙበትን Private Group መቀላቀል ይችላሉ።
🔥ጠቅላላ የሪሲቨር ጥገና ስልጠና
ኤሌክትሮኒስ ከመጀመርያው ጀምሮ + Software ችግሮችንና +Hardware ችግሮችን እንዴት ማስተካከል እንደምንችል ሲሆን የስልጠናው ሙሉ ክፍያ 500 ብርብቻ ነው።
ስልጠናውን ለመከታተል
⛽ +251930756350
+251964644627
@YONSAT /@YONSAT2 አናግሩኝ


አንድ ፋይንደር ምርጥ የሚባልበት መስፈርቶች የምትሉትን እስቲ Comment አድርጉ። በዛ ላይ እናንተ Recommend የምታደርጉትንና ምክንያቱን እንወያይ

መጨረሻ ላይ ምርጥ የሚባሉትን 3 ፋይንደሮች ስለ ቦርድ እቃነት እንዲሁም ቆይታ ያላቸውን ፖስት አደርግላችዋለው


ሠላም ለናንተ ይሁን ውድ የዮናስ ዲሽና ኤሌክትሮኒስ ጥገና ቤተሠቦች በዛሬው እለት በSoftware ምክንያት የተበላሹ በአብዛኛው ኢትዮፅያዊ ቤት የሚገኙትን ሪሲቨሮች በቀላሉ እንዴት በፍላሽ /USB / ብቻ በመጠቀም እንደምናስተካክል እንመለከታለን
----------------------------------------------------------
☀ በቅድምያ አንድን ሪሲቨር የSoftware ችግር እንደሆነ ለመረዳት እነኚህን ነገሮች መመልከት ያስፈልጋል ።ይህም ሪሲቨሩ Display ላይ Boot - On - Start - Load ብሎ ያለምንም መጥፋት መብራት መፃፍ አለበት ።
☀ የተለያዩ ሪሲቨሮች በሚጠቀሙት የMain board processor አንፃር የተለያዩ ሲሆኑ በቀላሉ ለመረዳት ሪሲቨራችንን ፈተን Main board ላይ የሚገኘውን ትልቁን Ic Model እና ቁጥር መመልከት አለብን።
☀ ሪሲቨሮቹ በፍላሽ የሚስተካከሉ ሲሆኑ ወደ Memory card
/TF Card በማድረግ በReader መጠቀም በአብዛኛው ሪሲቨር ላይ ስለማይሠራ ስትጠቀሙ ወይንም ለማስነሳት ስትፈልጉ የግድ ጥሩ የሆነ ፍላሽ መጠቀም አለብን።
☀በፍላሽ ሪሲቨራችንን ለማስነሳት ስንጠቀም የምንጠቀመው ፍላሽ ብዙ የተለያዩ ፋይሎች ባይኖሩት ይመረጣል። ይህም ሪሲቨሩ ወድያው ፍላሻችንን እንዲያነብ ይረዳናል።
🚫 በአብዛኛው የሪሲቨር ችግር የሚከሠተው በፍላሽ ሙዚቃ ወይንም የተለያዩ ቪዲዮዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ ሪሲቨራችን የመበላሸት እድሉ ከፍተኛ ስለሆነ በተቻለ መጠን ሪሲቨር ላይ ፍላሽ ለSoftware እንጂ ለ Entertainment መጠቀም አያስፈልግም !

        Ali processor  ለሚጠቀሙ ሪሲቨሮች
       ------------------------------------------------------
☀ ይህንን Chipset የሚጠቀሙ ሪሲቨሮች በSoftware ምክንያት Boot ብለው ሲቀሩ ለማስተካከል ከታች በሚገኘው መንገድ መጠቀም ትችላላችሁ
1- የሪሲቨሩን ትክክለኛ Software ማውረድ በመቀጠል ስሙን ወደ AliUpdate.bin መቀየር  የሪሲቨሮቹ ፋይል Bin ስለሆነ በቀጥታ AliUpdate ማድረግ ከዛን ከFolder ውጪ ወደ ፍላሽ መላክና ፍላሹን መሠካት በመቀጠል የሪሲቨሩን Stand by Button ማለትም ከዋላው ከሚገኘው Power Switch ውጪ ያለውን ተጭነን ሪሲቨሩን አጥፍተን እናበራዋለን ከዛን Update Software ብሎ መቁጠር ሲጀምር Standby Button ኑን እንለቃለን ከዛን ራሱ መቁጠር ጀምሮ ሲጨርስ ይስተካከላል።
2- በዚህ መንገድ መስተካከል የሚችሉ ሪሲቨሮች
Supermax 2425Hd
SM 9700 CA HD
SM 2560 Brilliant
Lifestar 9090
LS 8080
LS 6060
LS 1000
LS 2000
LS 3000
LS 4000
LS 9200
LS 9300 ባለ አንድ ፍላሾች
Tiger T8 እና ሁሉም Starsat Extreme ሞዴሎች በሙሉ በዚህ መንገድ በቀላሉ ያለምንም Rs cable እና ኮምፒውተር መስተካከል ይችላሉ።
         
              ይቀጥላል ....


satellite Receiver Repair Training
500 birr
Tnx


የተለያዩ ሪሲቨሮች የሚጠቀሙት Control(Switching Ic ) ቁጥሮች ከታች የሚገኙትን መጠቀም ትችላላችሁ

1_ Mewe Decoder Power Ic
Sl 2128c = 6830 ይተካዋል

2_ Star sat Satellite Receiver
6834 = DP 2360 መጠቀም ይቻላል

3_ Oscar Hd Satellite Receiver
D2606A =6830 መተካት ይቻላል

4_ Coronet
/Salvador /Mewe
👉DK 1203 በ Eurostar FSL 206 መጠቀም ይቻላል።

5_Mewe Satellite Receiver
2604A ይህ Fake ስለሆነ በ SD6830 በመቀየር መጠቀም ይቻላል

6_ LEG Satellite Receiver
Sl0380 ይህ Ic ነው። እናንተ ጋር Icው ጨሶ ቢመጣ ቁጥሩን ይህ ነው

7_EUROLINE 3030 ሪሲቨር Power Ic Dk1203 ነው።

8_ Lifestar All Gold እና Smart ማለትም
9200-9300-1000-2000-3000-LS 4000 HD GOLD በሙሉ የሚጠቀሙት Power Supply Switching Ic 6834 ነው።

🌟 DK1203 ይህንን የሚጠቀሙ የሪሲቨር ቦርዶች ማለትም የአሁኖቹ Salvador -Coronet የመሣሠሉት በተደጋጋሚ Icያቸው ስለሚቃጠል አዲስ የምትገዙ ይህንን ቦርድ የሚጠቀሙ ሪሲቨሮችን ባትገዙ ይመረጣል።

ይቀጥላል መልካም ቀን


Tv repair Training 2nd payment and receiver Training payment


[Forwarded from YoN Sat Tech]
4ኛው ዙር ጠቅላላ የቲቪ እንዲሁም የሪሲቨር ጥገና ስልጠና
__
በዚኛው ዙር በአዲስ መልክ ጠቅላላ የቲቪ( Crt + Flat) እንዲሁም የሳተላይት ሪሲቨር ጥገና ስልጠና ለመስጠት ተዘጋጅተናል። በዚህም ስልጠና ላይ ጠቅላላ የቴሌቭዥን ትምህርት ከመጀመርያው እስከ መጨረሻ እንዲሁም የሪሲቨር የSoftware እና Hardware ጥገና ትምህርቶችን ያካትታል።
✔️ ስልጠናው በዚኛው ዙር ምን የተለየ ነገር አለው ?
በዚኛው ዙር ስልጠና ከዚህ በፊት ከተዘጋጁት ቪዲዮዎች በተጨማሪ አዳዲስ ቪዲዮዎችን ያዘጋጀን ሲሆን ስልጠናውም በሁለት አይነት መንገድ መከታተል ይቻላል።
✔️ ስልጠናውን ለመከታተል ጠቅላላ የቲቪ ጥገና ስልጠና 1500.00 ብር ብቻ ሲሆን ይህም Crt እና Lcd Led ቲቪን ያካተተ ነው። የሪሲቨር ስልጠና መከታተል የምትፈልጉ ደግሞ 500ብር ብቻ በመክፈል የስልጠናው አካል መሆን ይቻላል።
✔️ ስልጠናውን በሁለት አይነት መንገድ ያዘጋጀን ሲሆን ይህም Internet መጠቀም የምትችሉ ለሠልጣኞች ብቻ በተከፈተው Private የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል በሳምንት አራት ቀናት የምንለቃቸውን ቪዲዮዎች በቀላሉ በመመልከት መከታተል የምትችሉ ሲሆን እያንዳንዳቸው ቪዲዮዎች 07:00_12:00ደቂቃ ርዝመት ያላቸው Highly compressed የሆኑ ከ 35_45Mb የሚደርሱ ቪዲዮዎች ናቸው።
✔️ ስልጠናውን ለመከታተል Internet አገልግሎት የምትቸገሩ ደግሞ ጠቅላላ የስልጠናውን ቪዲዮ 16Gb ፍላሽ ላይ አድርገን በፖስታ በ3 ቀናት ያላችሁበት ድረስ በመላክ ፍለሹን በመውሰድ በቤታችሁ ቲቪ ላይ :ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ በማገኛኘት በ Full Hd ጥራት መከታተል ትችላላችሁ። በፍላሽ የምትፈልጉ ሠልጣኞች የፍላሽ 300ብር ብቻ በመጨመር መላኪያውን በራሳችን አድርገን የምንልክ ይሆናል።
✔️ስልጠናው ምን ያህል ጊዜ ይቆያል ? የክፍያው ሁኔታስ ?
እንግዲህ ከዚህ በፊት በነበሩን የስልጠና ጊዜያት ስልጠናው 2 ወራት አካባቢ የመጀመርያው ዙር የቆየ ሲሆን በአሁኑ የስልጠና ጊዜ ግን ወደ አንድ ወር የተቀየረ ሲሆን ይህም የሆነው ቪዲዮዎች የሚለቀቁበት ቀናት በሳምንት አራት ቀኖች ስለሆነ ነው። ስለሆነም ስልጠናውን መከታተል የምትፈልጉ በ1 ወራት ውስጥ ብቁ የሆነ የኤሌክትሮኒስ ባለሙያ መሆን ይቻላል።
✔️ የክፍያው ሁኔታ የቲቪ ስልጠና የምትከታተሉ በአንድ ጊዜ ማከናወን ወይም በሁለት ዙር ክፍያችሁን መጨረስ ትችላላችሁ። ጠቅላላ የቲቪ ስልጠና ክፍያ 1500 ብር ብቻ ሲሆን በሁለት ዙር ማጠናቀቅ የምትፈልጉ ደግሞ የመጀመርያ ክፍያ 750ብር በመክፈል ከዛን በስልጠናው ላይ እያላቹ መሀል ላይ ደግሞ ቀሪውን ክፍያ መፈፀም ይቻላል። ነገር ግን ለሪሲቨር ሠልጣኞች ክፍያው አንድ ዙር ብቻ ሲሆን እሱም 500ብር ብቻ ነው።
✔️ በዚህ ስልጠና ለመከታተል ገንዘብ ገቢ ስታደርጉ ደረሰኝ ፎቶ በመላክ ወይም Mobile banking ከሆነ ደግሞ Screenshot በመላክ መመዝገብና ቀጥታ ስልጠናውን መጀመር ትችላላችሁ። ባለፈው ጊዜያት በነበሩት የስልጠና ሠአቶች በጠቅላላ ከ 109 አካባቢ የሚደርሱ ሠልጣኞችን አሠልጥነን የጨረስን ሲሆን አሁንም አዲስ ተመዝጋቢዎችን እየተቀበልን እንገኛለን
✔️ ገንዘብ ገቢ ለማድረግ ከታች በሚገኙት የባንክ አካውንቶች መጠቀም ይችላሉ
1000139090822 - ንግድ ባንክ
01320263863800 - አዋሽ ባንክ
5052913428001 - ዳሸን ባንክ ዮናስ ገረመው ።
✔️ተጨማሪ መረጃዎችን
Youtube - www.youtube.com/YonsatTech
Telegram - @Yonisat1 * @Yonisat2
Phone - +251930756350

በቤትዎ በመሆን የሙያ ባለቤት ይሁኑ !


ጠቅላላ የሪሲቨር Software እና Hardware ጥገና ስልጠና ዛሬ የተላከ ደረሰኝ ነው። እናመሠግናለን

20 last posts shown.