ሰዋስው/@zsewasw


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Linguistics


ሰዋስው

# ሰዋስው ማለት መሰላል ነው።
መሰላል የማይደርሱበት ነገር ተጠቅመው እንዲቻል እንደሚያደርጉት ሁሉ በዚህም ቻናል ችግር የሚባል ነገርን አስወግዳችሁ ወደ መልካም ነገር የምትወጡበትን ትምህርት ታገኛላችሁ።
እኔን ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ
+251934636523

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Linguistics
Statistics
Posts filter




ወዳጄ ጥበብ


ከአዲስ ንጉሥ የቆየ ወታደር፣ ከአዲስ ባለትዳር የቆየች ሠራተኛ፣ ከአዲስ ሐኪም የቆየ በሽተኛ፣ ከአዲስ ባለጠጋ የቆየ ደላላ፣ ከአዲስ ሰባኪ የቆየ የደብር ዘበኛ፣ ከአዲስ መካሪ የቆየ ጥፋተኛ፣ ከአዲስ ቄስ የቆየች አቃቢት ይበልጣሉ። የከረመ ወይን ዋጋው ትልቅ ነው፣ የበሰለም ሰው ተፈላጊ ነው። አገር የምታብደው እውነተኛ አዋቂዎቿን የናቀች ቀን ነው።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


ወዳጄ ትኩረት


የወደቅህበት ቦታ ላይ ስታለቅስ አትኑር፣ የተንሸራተትህበትን ቦታ መመርመር ከዳግም ውድቀት ያድንሃል። ንግግርህ እውነት ቢሆን እንኳ ፍቅር ከጎደለው ሰባሪ ነው። የማያጸጽት ምርጫ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ዙሪያህን ካየህ ጨለማ ነው፣ ወቅቱን ካዳመጥህ ነፋስ ነው። የጠራህን አምላክ ስታይ የማይቻለው ይቻልሃል፣ እርሱን ስታደምጥ ልብህ በእምነት ይጸናል። ጨለማ እንዲወገድ እውነት፣ እውቀትና ኑሮ ያስፈልጋሉ። ያልተኖረ እውቀት የባከነ ነው። እውነት በሌለበትም እውቀት ሊኖር አይችልም።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw




ወዳጄ መልካም


መልካምነትህ ተዳፍኖ አይቀርም፣ አንድ ቀን ይወጣል። ወዴት እንደምትሄድ ካወቅህ ጉዞ አጭር ነው። ብዙ አስበህ አንዴ ካልወሰንህ፣ አንዴ ወስነህ ብዙ ጊዜ ታስባለህ። እውቀትህ ጥበብ ከሌለው የመጠላትህ ምክንያት ነው። ምክርን ርቀህ አትወርውር ፣ የመከርከውን ሰው ቀርበህ አግዘው። መልካሙን ተግባር ለማቆም ብታመነታም ጨርሰህ ተስፋ አትቁረጥ። ምቹ ልብ የማይመቹ ቀኖችን ይለውጣል። የሚቻለው ያቃተህ ቀን የማይቻለው የተቻለልህ በእግዚአብሔር መሆኑን ተረዳ።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw




ወዳጄ ማህቶት

ሦስት መብራቶች ያዝ፣ እነርሱም እምነት፣  ተስፋ፣ ፍቅር ናቸው። እምነትህ ሲጠፋ በተስፋ ለኩሰው። ተስፋህ ሲጠወልግ በፍቅር አነሣሣው። ፍቅር ሲከስም በእምነት አንድደው። ብዙ ለማወቅ የማታውቀውን አላውቅም ማለት፣ ብዙ ለመኖር ድርሻህን ለይተህ ማወቅ፣ ብዙ ለመሥራት ማልዶ መነሣት ወሳኝ ነው። የያዝከውን ውድ ነገር አያያዝህ እንዳይሰብረው ተጠንቀቅ። ከሌለህ ሳይሆን ካለህ ነገር መቁጠር ጀምር፣ ያን ጊዜ የጎደለህ እንደሌለ ትረዳለህ። የእግዚአብሔር ቡሩክ ነህና ደስ ይበልህ!

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


ወዳጄ እምነት

አደራ የሚሉህ እጅግ የሚያምኑህ ናቸው፣ አደራህን የሚጠይቅህ ግን የታመነው እግዚአብሔር ነው። ከተከፈቱ በሮች የተከፈተ ልብ አምላክን ይጋብዛል። እግዚአብሔር ወደ አንተ የሚመጣው ያንተን ሽቶ ሳይሆን የራሱን ሊሰጥህ ነው። ቀጥሮ የማይቀር እግዚአብሔር ብቻ ነው። እውነተኛ መንፈሳዊ ጥም እርካታውን ያገኛል። በሌለህበት ዘመን የሚኖር እግዚአብሔር አለ።


#ዘሰዋስው


https://t.me/ZSewasw


⭐️Telgram premium⭐

⭐ 3 Month- 1300 ETB
⭐ 6 Month- 1800 ETB
⭐ 12 Month- 2800 ETB

🌟For personal, Business or Gift☀️
💧Telegram
   
☀️Inbox  @aklil24 or @aklil25

🌟በታማኝነት በፍጥነት👌


​​⭐⭐⭐⭐⭐⭐
አዲስ የኦላይን ስራዎች
⭐⭐⭐⭐⭐⭐
አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች
የሚያገኙበት
⭐⭐⭐⭐⭐
#Website
#application
#airdrop
⭐⭐⭐⭐⭐⭐
በእየለቱ ይለቀቃሉ
⭐⭐⭐⭐⭐
በቪዲዮ በመታገዝ የሚስሩበት ድንቅ ቻናል
⭐⭐⭐⭐⭐⭐⭐




ወዳጄ ደስታ

ስታዝን በእግዚአብሔር ትጽናናለህ፣ እግዚአብሔር ሲያዝንብህ በንስሐ ታስደስተዋለህ። የራበውን ወገንህን ነገ ና አትበለው። ባዶ ቤት ድምፅ ያስተጋባል፣ እውቀት ሲያንስም ጨኸት ይበዛል። ብዙ መናገር መሰልቸት፣ ብዙ መታየት መጥፋት ያመጣል። በወረኞች የከበረ በወረኞች ይዋረዳል። ሁሉን አውቃለሁ የሚል ምንም አያውቅም። እግዚአብሔር የቀባውን የደፈረ ያለ ቅጣት አይተውም።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


ወዳጄ ብርሃን

መፍራት ብርሃንን ነው ቀጥሎ ሊጨልም ይችላል፣ ጨለማ ግን አያስፈራም ቀጣዩ ብርሃን ነውና። ብዙ ሰው ብትሰበስብ አንድ ወዳጅ ይኑርህ። የተሠራውን ካጠፋህ የምትሠራው እንዲጠፋ እያስተማርህ ነው። ነጻነት ያለ እውቀት ከባርነት በላይ ይከብዳል። ለቀላል ሰውም ፍቅር ያመዋል። ችግርን በፈጠረ አስተሳሰብ ችግርን መፍታት አይቻልም። መኖርህን ለሚጠሉ አብዝተህ ኑር። የበታችህ እንዲያከብርህ የበላይህን አክብር። ልጆችህ አንተን እንዲወዱህ አንተ ወላጆችህን ውደድ። ገና ባልኖርህበት ዘመን የሚወድህ አምላክ አለ። እኮ ደስ ይበልህ!!

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


ይህ አዲሱ የቴሌግራም ቻናላችን ነው
ስለ ቴክኖሎጂ,የኦንላይን ስራዎችን,ስለ airdrop እንማማራለን እንሰራለን።
ሁላችሁም የቻናላችን ቤተሰዎች Join share , አድርጉልን
🙏🙏🙏🙏🙏

https://t.me/sewaswTech


ወዳጄ ማስተዋል

አንድ ንጉሥ ካልመራህ ብዙ ሺህ ነገሥታት ይመሩሃል። አንዱን እግዚአብሔር ካልፈራህ የሚያስፈራሩ ብዙ ነገሮች ይገጥሙሃል። ትላንት የነበርህበት፣ ነገ የምትኖርበት ቢሆንም ዛሬ ግን ያለህበት ነው። ልብህን ካላስፈቀድኸው የፍቅር ሰው መሆን አትችልም። ትዕግሥትም ነገ የምትመነዝረው ሀብትህ ናት። አባቶችህ በአደባባይ የተሰየፉ ሰማዕታት ናቸውና የአደባባይ ክብርን አትሻ። ያልተፈቀደልህ የማይጠቅምህ ነውና ደስ ይበልህ። አበጀዋለሁ ብለህ ቢበላሽብህ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ነህና ደስ ይበልህ። አይነጋም ብለህ አልተኛህምና አይለወጥም ብለህ ተስፋን አትጣል።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw




ወዳጄ ተስፋ


ወንጌል የምሥራች ሁኖ የተላከው ከውስጣችንና ከዓለሙ የምንሰማው የሞት ድምፅ ስለሆነ ነው። እግዚአብሔርን ባወቅኸው መጠን ቅዱስ ፍርሃትህ ካልጨመረ በትክክል አላወቅኸውም ማለት ነው። እግዚአብሔር ያለ መንገዱ አይገኝም። በፈለግኸው ጊዜም አይታጣም። አለማመን ውስጥህን ሲያናውጠው የሰጠህን ተስፋና ያደረገልህን አስበው።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw




ወዳጄ ትኩረት

ጥያቄ በውስጥህ ሲፈጠር መልስ ደግሞ ከሰማይ ተዘጋጅቷል። ጥያቄህን እንደ መልስ ይዘህ መኖር በማይበርድ ወጀብ ውስጥ ማለፍ ነው። ያጋጠሙህ ነገሮች ለአንተ ድንገተኛ ለአምላክ ግን ቀድመው የታዩ ናቸው። ያየኸው ሲሰወርብህ ያየልህ ሊገለጽ ነው። መጽሐፍ ካልገለጥከው እንደማይታወቅ ነገም ዛሬ ላይ አይታወቅም። የመጽሐፍ ሙሉ አሳብ ሲጠናቀቅ እንደሚገባህ ሕይወትንም ዛሬ በሙሉነት ልታውቃት አትችልም። የአስተሳሰብ እኩያህን ለጓደኝነት፣ ታናሽህን ለተማሪነት፣ የአስተሳሰብ ታላቅህን ለመምህርነት ምረጥ። የትላንት አሳብህ ዛሬ የለምና በሰዎች አስተሳሰብ አትዘን።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


ወዳጄ ሰላም

በማግኘትህ ውስጥ ማጣት አለ፣ በማጣትህ ውስጥም ያለውን ማግኘት ቁጠረው። ጌጠኛ ቤት ያላቸው ጥቁር ኑሮ ውስጥ ያልፋሉና ሰውን በላይ ኑሮው ብቻ አትለካው። ሚዛን በወደቀበት ዘመን ኃጢአት ጽድቅ፣ ክፉም ደግ ይባላል። ማርጀት የተፈጥሮ ሂደት ነው፣ ከዘመን ጋር መራመድ ብልህነት ነው። ለየት ያለ ኑሮ ስትመርጥ ለየት ያለ መከራ ጠብቅ። ያለህበት ሁነህ ከመጣራት ያሉበት ሄደህ አንሣቸው። ባዶ ሰው የለምና ዓለም በሙሉ አስተማሪህ መሆኑን እወቅ። የተሻለ ቀን ጠብቅ።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw

20 last posts shown.