Posts filter












በኢትዮጵያ ውስጥ የኮንስትራክሽን እቃዎች እና መኪናዎችን ያስገባችሁ የዕለቱን ዜናችንን እንድትመለከቱ እንጠቁማለን።




Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ከፍተኛ ረሀብ ተከስቷል::




በመንግሥትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ትኩረት የተነፈገው የሽርካ ኦርቶዶክሳውያን ግድያ እንደቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኅሣሥ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም የወረዳ ቤተ ክህነቱን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ 20 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ግድያና እገታ እንደተፈጸመባቸው ነዋሪዎቹ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል፡፡

ከታገቱት ውስጥም የወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ሌሎች 8 ኦርቶዶክሳውያን ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ግድያ እንደተፈጸመባቸው እንዲሁም ያሉበት እንደማይታወቅ አክለዋል፡፡ በዚህ ዕለት ብቻ ከ80 በላይ የኦርቶዶክሳውያን ከብቶች በታጣቂዎች ተወስደዋልም ተብሏል፡፡

ሀገረ ስብከቱ በየዓመቱ በሚካሄደው በ43ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በ2016 ዓ.ም 271 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡

በተጨማሪም ከ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ 91 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል በጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤው ሪፖርቱ መጥቀሱ አይዘነጋም፡፡

በጀጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ 150 ምእመናን በጉሬ ደቢኖ ቅ/እግዚአብሔር አብና አርጆ ቅ/ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምእመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን 499 አባወራና እማወራ ለስደት መዳረጋቸውም ተገልጿል፡፡

በጠቅላይ ቤተ ክህነትም ሆነ በመንግሥት ትኩረት የተነፈገው የኦርቶዶክሳውያን ግድያ ተባብሶ ኅዳር 19 እና 20 ቀን 2017 ዓ.ም የ13 ዓመት ታዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያው ላይ ተወስደው መገደላቸውንና 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ያለማንም ከልካይ በተገኙበት ሁሉ በሚገደሉበት በዚያ ሀገረ ስብከት የ45 ቀን አራስ ሕጻንን ጨምሮ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና አብያተ ክርስቲያናት ላይም ጥቃት እየተፈጸመ መቆየቱ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘገብ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም የኦርቶዶክሳውያን ግድያና ስደት እንዲሁም የሀብት ዝርፊያ ሰሚ ያጣና በወረዳው ተጠናክሮ የቀጠለ በመሆኑ የአካባቢው ምእመናን በትልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ መሆናቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል፡፡

“የማይጠቅሙና ፋይዳ የሌላቸው ጉዳዮችን ሲዘግቡ የሚስተዋሉ ሚዲያዎች የእኛ ሞት እንደምን ቀለላቸው?” ያሉት ኦርቶዶክሳውያን ነዋሪዎች ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በወረዳችን እየተፈጸመ ያለው ግፍ ትኩረት አለመሰጠቱ እጅጉን አሳዝኖናል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሰብዓዊነት የሚሰማችሁ ግለሰቦችና የግፍ ግድያውን የምትቃወሙ ሚዲያዎች ሀብት ንብረት ባፈራንበት ወልደን ከብደን በተቀመጥንበት ሀገራችን እንዳውሬ እየታደንን ስንገደል ድምጽ ትሆኑን ዘንድ እንማጸናችዋለን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አስተያየት ሰጭዎች አክለውም መንግሥት የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት በመገንዘብ ሞታችንን ሊያስቆምና መፍትሔ ሊያመጣ ይገባዋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

@ማህበረ ቅዱሳን






እነማንን ያውቃሉ?















20 last posts shown.