አስገራሚ ዜና!
በአሜሪካ ለሚገነባው ገዳም ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት በላይ ፈረደ አንድ ሚሊዮን ዶላር ሰጡ።
ትዕግስት በላይ ፈረደ ትውልዷና እድገቷ በውባ ባሕር ዳር ከተማ ሲሆን በሎስ አንጀለስ ለሚገነባው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳም ማስገንቢያ በግላቸው አንድ ሚሊዮን ዶላር አበርክተዋል።
በኮመዲያን እሸቱ በአንድ ምሽት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የተሰበሰበለት የገዳሙ ምስረታ አጀማምር በትዕግት በላይ ፈረደ አንድ ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ ተደርጓል።
ትዕግስ በሎሳን ጀለስ በግል ንግድ ስራ ድርጅት ከፍታ የምትሰራ ሲሆን ቤተሰቦቿና እድገቷ ባሕርዳር ሲሆን እጅግ በጣም ተወዳጅና በረከትን አብዝተው የሚኖሩ የተመሰገኑ ቤተሰቦች ያሳደጓት በመሆኗ አሁንም ይህንን ከቤተሰቧ የወረሰችውን ለወገንና ለሀገር የማበርከት በጎ ተግባር ቀጥላበት አንድ ሚሊዮን ዶላር ለገዳም ግንባታው አበርክታለች።
ትዕግስት ከዚህ በፊትም ለጣና እምቦጭ ማስወገጃ ማሽን ግዥ የሚሆን ከፍተኛ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን ፤ በጣና ታሪካዊው ክብራን ገብርኤል ገዳም ህንጻ አስገንብታ ለአባቶች አስረክባለች።
እንዲሁም በሻሸመኔ ሚስቱና ቤተሰቦቹን በወጣቶች አመፅ ላጣው ግለሰብ ግማሽ ሚሊዮን ብር ሰጥታለች። በተጨማሪም ከዚህ በፊት ለኮሮ ጊዜ ልዩ ድጋ ከማድረጓ ባለፈ 50 አረግዊያንን በቋሚነት ትረዳለች። በወንድሙ ፓስፖርት ገብቶ በአሜሪካ ታሰሮ የነበረውና ወንድሙ በዩንቨርሲቲ የተገደለበትን አንድ ወጣት በፍርድ ቤት ጠበቃ በመቅጠር ህጋዊ ኗሪ እስከመሆን አድርሳለች።
ትዕግስት በላይ ፈረደ እጅግ ትጉህ ሰራተኛ ከመሆኗ በላይ ደግ፣ ሩህሩህና አዛኝ ፤ ወገኗን የምትደግፍና ለኢትዮጵያ ቀናኢ መንፈስ ያላት እህታችን ናት።
አሁንም አንድ ሚሊዮን ዶላር ለገዳሙ የግንባታ በመክፈሏ ፈጣሪ ረጅም እድሜና ሞገስ እንዲሰጣት እንለምናለን። እናመሠግናለን!