የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል ቃል አቀባይ ቬንዳት ፓቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሁለት ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ጥያቄዎች ተነስተውላቸው ነበር፡፡ እነዚህም በኬንያና በፈረንሳይ የሚደረገውን ተቃውሞና የፀጥታ ሀይሎችን የሀይል እርምጃ የሚመለከቱ ናቸው፡፡
ፓቴል ለኬንያው ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹በኬንያ ለጠፋው ህይወትና ለወደመው ንብረት አሜሪካ ጥልቅ ሀዘኗን ትገልፃለች፡፡ በእኛ በኩል ሁሉም የፖለቲካ አመራሮች፣ ተቃዋሚዎችና ሁሉም አካላት ከአመፅና አመፅን ከሚቀሰቅስ ድርጊት እንዲታቀቡ እናበረታታለን፡፡ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎችም የህዝብን ደህንነትና ንብረት ለመጠበቅ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ይህም ሆኖ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅና የመሰብሰብ እንዲሁም ሰላማዊ ተቃውሞ የማድረግ መብትን መጠበቅ የዲሞክራሲ መሰረት መሆኑን ለመናገር እንወዳለን›› ብለዋል፡፡
ምክትል ቃል አቀባዩ ስለፈረንሳይ ጉዳይ ሲመልሱ ደግሞ ‹‹በመጀመሪያ ደረጃ ጉዳዩን ሰፋ አድርገን ካየነው የማንኛውም ሰው በሰላማዊ መንገድ የመቃወምና በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን የመግለፅ መብት ሊከበር የሚገባ ቢሆንም ይህ በአመፅ መሆን የለበትም፡፡ እኔ ማለት የምችለው ግን ይህ የፈረንሳይ ውስጣዊ ጉዳይ በመሆኑ እዛ ውስጥ ጣልቃ እንደማንገባ ነው፡፡ ከፈረንሳይ ጋር ረጅም እድሜ ያስቆጠረና ወሳኝ ወዳጅነት ያለን በመሆኑ ለዚህ ትልቅ ዋጋ እንሰጣለን›› ብለዋል፡፡